TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" መጥታችሁ የጤና ምርመራ አድርጉ ፤ ምንም ክፍያ አትከፍሉም " - ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት " በጎነት ለጤናችን " በሚል ከነሐሴ 11 ጀምሮ ነፃ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ይኸው አገልግሎት ነገ ያበቃል ብሏል።

" የጤና ምርመራ ማድረግዎ ለእርስዎ በእጅጉ ይጠቅምዎታል፡፡ " ያለው ሆስፒታሉ " የጤናዎን ሁኔታ ለማወቅ እኛ ጋር ብቅ ይበሉ፦
- የዓይን ፥
- የውስጥ ደዌ፥
- የደም ግፊት ፥
- ከአንገት በላይ ፥
- የስኳር ህመም
- የጡት እና የማህጸን  ካንሰር  እና ሌሎች ምርመራዎች ከላቦራቶሪና ከአልትራ ሳውንድ ምርመራ ጋር ያገኛሉ፡፡ " ብሏል።

ሆስፒታሉ ለሚሰጠው አገልግሎት ፤ " ምንም ክፍያ የለውም " ሲል ገልጿል። ነፃ የህክምና አገልግሎቱ እየተሰጠ የሚገኘው በራስ ኃይሉ ስፖርት ማዘውተሪ መሆኑንም አሳውቆናል።

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

ዛሬ በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ልጆች የሚካፈሉባቸው የፍፃሜ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ዛሬ የሚደረጉት ውድድሮች የ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ እና የ3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ናቸው።

ውድድሮቹ ምሽት 4:30 እና ምሽት 4:42 ላይ ነው የሚደረጉት።

ሀገራችን የሚወክሉ አትሌቶች እነማን ናቸው ?

- በ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ (አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ሀየሎም)

- የ3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ (አትሌት ጌትነት ዋለ እና ለሜቻ ግርማ)

በ1500ሜ ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለኔዘርላንድ ከምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ጋር ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport 
TIKVAH-ETHIOPIA
ጾመ ፍልሰታ እና የቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት ! በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ " የጾመ ፍልሰታ " መልዕክት አስተለልፈዋል። ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦ " . . . እንደ እግዚአብሔር ቃልም እንደ አባቶቻችን ትውፊትም የጾመ…
#EOTC

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያኖች ከመጠላላት ርቀው #በፍቅር እንዲኖሩ እና #ሰላማውያን እንዲሆኑ አሳሰቡ።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህንን ያሳስቡት ዛሬ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የጾመ ማርያም ሱባኤ ማጠናቀቂያ በዓል ላይ ነው።

ቤተክርስቲያንኗ ፤ " በኢኦተቤ በዐዋጅ ከተደነገጉት አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገተ ሥጋ አስመልክተው ሐዋርያት የጾሙት ጾመ ማርያም በየዓመቱ በወርሓ ነሐሴ ከመባቻው አንስቶ ባሉት 16 ቀናት ካህናት እና ምእመናን ሌሊት በሰዓታት ጸሎት፤ ቀን በሥርዓተ ቅዳሴ በመሳተፍ በሕብረት ያሳልፉታል " ብላለች።

" በዚህ በጾመ ማርያም ወይም በተለምዶ የፍልሰታ ጾም ተብሎ በሚታወቀው ወቅት በርካታ ምእመናን እንዲሁም ሕጻናት በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ሥርዓተ ቅዳሴውን ይከታተላሉ፤ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን ይቀበላሉ " ስትል ገልጻለች።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትም በዚህ ሕጻን ዐዋቂው፤ ወንድ ሴቱ የክረምት ብርድ እና ዝናብ ሳይበግረው በሕብረት በሚጸልበት የሱባኤ ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመገኘት ሥርዓተ ቅዳሴውን በመምራት እና ምእመናንን በመባረክ ማሳለፋቸውን ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው በዛሬው ዕለት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር  በገዳሙ ተገኝተው በዓሉን ያከበሩ ሲሆን በቅዳሴው መካከል ባስተላለፉት ትምህርትና ቃለ ቡራኬ " የሰላም ባለቤት የሆነው ልዑል እግዚአብሔርን ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያኖች ከመጠላላት ርቀው በፍቅር እንዲኖሩ እና ሰላማውያን እንዲሆኑ አሳስባለሁ " ብለዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ በሱባኤው ወቅት የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው፡፡ 

መረጃ እና ፎቶ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ/ጽ/ቤት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
የባንክ አካውንት ለመክፈት ወደባንክ ቅርንጫፍ መምጣት ቀረ! ባሉበት ሆነው የአፖሎ ዲጂታል ባንክ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ!

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ። 
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo 
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
እንኳን ለአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉን በማስመልከት እስከ 20% በሚደርስ ቅናሽ በቴሌብር ሱፐርአፕ እና ማይ ኢትዮቴል እንዲሁም በ*999# የቀረቡትን የሞባይል ጥቅሎች ለራስዎ ይግዙ፤ በስጦታ ያበርክቱ!

መልካም በዓል!
ስለ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል ምን ያህል ያውቃሉ ?

የሻዳይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በአማራ ክልል የሚከበር በዓል ነው።

በዋግ ሹሞች መዲና ሰቆጣና አካባቢዋ ሻደይ፣ በቆቦ አካባቢ ሶለል እና በላስታ እና በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አሸንድዬ በሚል የሚከበረ የልጅ አገረዶች ጨዋታ በዓል ነው።

በዓላቱ አማራ ክልል ባለብዙ ዘርፍ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብት ባለቤት መሆኑን ፣ የተለያዩ ቋንቋዎች እና ባሕላዊ ትውፊቶች ያሉት፣ ሕዝቦች በመተሳሰብ በመፈቃቀር እና በአንድነት የሚኖሩበት መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።

የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል በዓል የአዲስ አመት መምጣቱን ተከትሎ የሚከበር ብስራት ነው።

ልጃገረዶች ከክረምት መግባት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ውጣ ውረዶችን አልፈው ብሩህ ዘመን እየመጣ መሆኑን የሚያበስሩበት፣ እጮኛ የሚያጩበት፣ ከአቻዎቻቸው ጋር የሚጨፍሩበት እና የሚጫወቱበት ባሕላዊ ጨዋታ ነው።

በተጨማሪ እናቶች እና ህጻናት ያለ ልዩነት ሚሳተፉበትም ነው።

በዓላቱ በህዝባዊ አንድነት የሚያከብሩ፣ የመተሳሰብ፣ የፍቅር እና አብሮ የመኖር እሴትን ለትውልድ ማስተላለፊያ ጠንካራ ገመድ ናቸው።

ለውጭ ሀገራት ብርቅ በመሆኑም የገቢ ምንጭም ነው።

እነዚህ በዓላት በተለይም ባለፉት አመታት በአማራ ክልል በነበረው ጦርነት እና አለመረጋጋት እንዲሁም በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 ምክንያት በሚፈለገው ልክ በተሟላ ሁኔታ አልተከበሩም።

ዘንድሮም በዓሉ በተቃረበበት ወቅት በክልሉ ሰላም ደፍርሶ ፣ ንፁሃን ተገድለው፣ በርካቶች ተጎድተው አጠቃላይ ቀውስ በመፈጠሩ እንዲሁም ክልሉ ባአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በመውደቁ ድባቡ እንደከዚህ ቀደሙ የደመቀ አይደለም።

በነዚህ በዓላት በተለይ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት በርካታ ቱርስቶች ወደ ክልሉ ይጎርፉ የነበረ ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት እንቅስቃሴ ሁሉ ተዳክሞ ነበር ፤ ከወራት በፊት በተገኘው አንፃራዊ ሰላም የቱሪስት እንቅስቃሴ ትንሽ የመነቃቃት ነገር ቢፈጠርም ዳግም በፀጥታ ችግር እና ጦርነት ወደ ክልሉ የሚደረግ የቱሪስት እንቅስቃሴ እጅግ ተዳክሟል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia