TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት #ለጥንቃቄ

" በካፒታል ገበያ አዋጅ መሰረት የቀረበ የአክስዮን ሽያጭ " በሚል የሚቀርቡ ማስታወቂያዎች እውቅና  የላቸውም ተብሏል።

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፤ አንዳንድ ኩባንያዎች " በካፒታል ገበያ አዋጅ መሰረት የቀረበ የአክስዮን ሽያጭ " በሚል የሚያስነግሩት ማስታወቅያ እውቅና የሌለው ነው ሲል አሳውቋል።

አንዳንድ ኩባንያዎች " በካፒታል ገበያ አዋጅ መሰረት የቀረበ የአስክሲዮን ሽያጭ " በሚል ማስታወቂያ እያስነገሩ አክሲዮን እየሸጡ እንደሆነ ደርሼባቸዋለሁ ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መክሯል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአክስዮን ሽያጮችን መመዝገብና ማጽደቅ እንዳልጀመረ ገልጾ አሁን ላይ የአክስዮን ምዝገባ የሚያደርግበትንና የደንበኛ ሳቢ መግለጫ የሚያጸድቅበትን የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ አስገንዝቧል።

አክስዮን ሻጭ ኩባንያዎችም የአክስዮን ሽያጭ ሂደቱ በባለስልጣኑ ታይቶ ባልጸደቀበትና ባልተመዘገገበበት ሁኔታ ሽያጩ በካፒታል ገበያ አዋጅ መሰረት የተዘጋጀ እንደሆነ በማስታወቅያ ማስነገር ህብረተሰቡን የሚያሳስት ነው ብሏል።

የዚህ አይነት አሳሳች የሆኑ የአክስዮን ሽያጭ ማስታወቅያዎችን በማንኛውም መንገድ በሚያስነግሩ ኩባንያዎች ላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ በካፒታል ገበያ አዋጅ አንቀጽ 106 በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አስጠንቅቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።)

Via @TikvahethMagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሥራ መደቦች ሰልጣኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ✓ ሰልጣኝ አብራሪ/ፓይለት (Trainee Pilot) ✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ቴክኒሽያን (Trainee Aircraft Maintenance Technician) ✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ሜካኒክ (Trainee Aircraft Mechanic) ✓ ሰልጣኝ የበረራ አስተናጋጅ (Trainee Cabin Cors) …
#ማስታወሻ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሥራ መደቦች ሰልጣኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ምዝገባው ዛሬ ይጀምራል።

የስልጠና መጠሪያዎች ፦
✓ ሰልጣኝ አብራሪ/ፓይለት (Trainee Pilot)
✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ቴክኒሽያን
(Trainee Aircraft Maintenance Technician)
✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ሜካኒክ (Trainee Aircraft Mechanic)
✓ ሰልጣኝ የበረራ አስተናጋጅ (Trainee Cabin Cors)
✓ ሰልጣኝ የመንገደኛ አገልግሎት ኢጀንት (Trainee Customer Service Agent) ናቸው።

አመልካቾች ለምዝገባ ፤ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውንና ኮፒው፣ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ፣ የልደት ካርድ፣ የታደሰ የቀበሌ የነዋሪነት ማረጋገጫ ካርድ እና አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ ማሟላት አለባቸው።

አመልካቾች ከተዘረዘሩት የሥራ መደቦች ውስጥ ማመልከት የሚችሉት በአንዱ ብቻ ነው።

ምዝገባእ ከነሐሴ 15 ጀምሮ እስከ 19/2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው የሚቆየው።

የምዝገባ ቦታ፡-
- አዲስ አበባ በኦንላይን (አዲስ አበባ)
- አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ (አምቦ)
- አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ (አርባምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ (አሶሳ)
- ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ (ባህርዳር)
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ (ደ/ብርሃን)
- ደብረ ማርቆስኦኒቨርሲቲ፣ (ደ/ማርቆስ)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ (ድሬዳዋ)
- ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣ (ፍቼ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ (ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ (ጎንደር)
- ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሀረር ካምፓስ ሀረር)
- ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ (ነቀምቴ)
- ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሚዛን ቴፒ)
- ሮቤ ቲቺንግ ኮሌጅ፣ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ)

ዕድሜ ፣ ቁመት ፣ ክብደትና ሌሎች መረጀዎችን ከላይ በተያያዘው የተቋሙ ይፋዊ ማስታወቂያ ይመልከቱ።

More ፦ https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies?fbclid=IwAR1ZLHg_fw9VhghmXo-oOL9ykrsCmq3vcUISCzYl8QtRPPg5fnW4VW_Yfig

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
ቴሌግራም ላይ በኮፕ ቻፓግራም https://t.iss.one/ChapagramBot ገንዘብ መላላክ ተቻለ!
የታሰሩት የምክር ቤት አባላት የት ናቸው ?

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተያዙ የም/ቤት አባላት ታስረውበት ከነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የማቆያ ቦታ እንደሌሉ እና ያሉበትን ቦታ ማወቅ እንዳልቻሉ ከጠበቆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዲሁም በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ ተሻገር ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ለቤተሰቦቻቸው ቢገለጽም፣ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

በተጨማሪ እስካሁን ድረስ ቤተሰቦቻቸውም ይሁን ጠበቆቻቸው ሁለቱ ታሳሪዎች ያሉበትን ቦታ እንዳላወቁ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ተናግረዋል።

ጠበቃ ሔኖክ ምን አሉ ?

" ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚያቀርቧቸው ከቤተሰቦቻቸው ሰምተን ፍርድ ቤት ተገኝተን ነበር፤ አልቀረቡም።

በኋላ ላይ ስናጣራ ይገኙበት በነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ እንደሌሉ እና ለጊዜው ያላረገገጥነው ቦታ እንደተወሰዱ ሰምተናል።

ቤተሰቦቻቸውም ወደ እስር ቤቱ አስገብተውላቸው የነበሩ ንብረቶችን መውሰድ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። በሐዘን እና በከፍተኛ የስሜት መሰበር ላይ ይገኛሉ።

አንዳንድ ቤተሰቦቻቸውም ሌላ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል በሚል የመረበሽ ስሜት ውስጥ ናቸው።

11፡00 ሰዓት ላይ ሊነጋጋ ሲል ነው የወጡት'፣ 'ወደ አዋሽ ተወስደዋል'  ከሚል ያልተረጋገጠ ወሬ በስተቀር የት እንዳሉ አናውቅም።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተጠርጥረው በእስር ላይ ከነበሩ ሌሎች ግለሰቦች መካከል ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ነበሩ ፤ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የተነገራቸው በፖሊስ ነው።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አሳሪው አካል ተጠርጣሪዎችን ፍርድ ቤት የማቅረብ ግዴታ የለበትም።

ሆኖም ፍርድ ቤት ቢያቀርባቸውም፣ ባያቀርባቸውም በእስር ላይ እስካሉ ድረስ በጠበቃ እንዲሁም በቤተሰባቸው የመጎብኘት መብት አላቸው።

ፍርድ ቤት የሚያቀርቧቸው ከሆነም በጠበቆች ተወክለው የሕግ ድጋፍ የማግኘት መብት ስላላቸው ያሰራቸው አካል ለጠበቆች የማሳወቅ ግዴታ አለበት።

እስካሁን ድረስ ከጠበቆቻቸው እንዳይገናኙ ተከልክለዋል። ያሉበትን ቦታ እና ሁኔታም ቤተሰቦቻቸውም ሆኑ ጠበቆቻቸው አናውቅም።

በሕግ ጥላ ሥር ያሉ ሰዎችን ያለምንም እውቅና ወደ ሌላ ቦታ ማዛወር ሕገ ወጥ ነው። በሕግ አግባብ ይዣቸዋለሁ የሚለው የመንግሥት ተቋም ያሉበትን ሁኔታ የማሳወቅ ግዴታውን እየተወጣ አይደለም።

የምክር ቤት አባላቱ ያለ መከሰስ መብታቸው ሳይነሳ መታሰራቸው ሕጋዊ አይደለም በማለት አካልን ነጻ የማውጣት ክስ መሥርተው ጉዳዩን እየተከታተሉ ነው። በቀጣይ እነዚህ ግለሰቦች የት እንዳሉ የማሳወቅ ግዴታ ያለበትን መርማሪ ቦርዱን እንጠይቃለን።

አንድን ሰው አስገድዶ መሰወርም ሆነ ያለበትን አለማሳወቅ ዓለም አቀፍ ወንጀልም ነው፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ቢሆን የተከለከለ ተግባር ነው። ቤተሰቦቻቸውም ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ የማወቅ መብት አላቸው። "

Via BBC AMAHRIC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሲዳማ

የሲዳማ ክልል መንግሥት ፤ " የተሰጣቸውን የመንግስትና የህዝብ አደራ ወደ ጎን በመተው በሙስናና ብልሹ አሰራር ላይ ተሳትፈዋል " ባላቸው አመራሮች ላይ የፖለቲካ ውሳኔ መተለለፉን አሳወቀ።

ክልሉ እኚሁ አመራሮች እንደየሥራቸው ከህግ ተጠያቂነት አያመልጡም ብሏል።

የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት  አቶ ደስታ ሌዳሞ በሰጡት መግለጫ ፤ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ያልተወጡና በብልሹ አሰራር ላይ የተሳተፉ አመራሮችን በክልሉ ማዕከል ሀዋሳ ከተማ ሲደረግ በቆየው አካላዊ ግምገማ የፖለቲካ ውሳነ መተላለፉን ገልጸዋል።

" ማንም ባጠፋው ጥፋት ልክ ከህግ አግባብ እንዲጠየቅም ይደረጋል " ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ባለፉት ለ10 ቀናት ሲካሄድ ከርሟል ባሉት የሲዳማ ክልል የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ ላይ በአፈፃፀም ላይ ዝቅተኛ ዉጤት ያስመዘገቡ ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ግምገማ መደረጉን ገልጸዋል።

በብልሹ አሰራር ላይ የተሳተፉ አካላት ላይ ፖለትካዊ እርምጃ የተወሰደ መሆኑና የህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አመልክተዋል።

አቶ ደስታ ፤ በሀዋሳ ከተማ ላይ ከፍተኛ ሌብነትና ብልሹ አሰራር በመታየቱ ያለውን ሁነታ በመሸሽ ስብሰባ ረግጠው ወጥቶ የሄዱ አመራሮች መኖራቸውን አንስተው በዚህ ብቻ የምተወው አይደለም ተጠያቂነት ይቀጥላል ብለዋል።

የትኞቹ አመራሮች ስብሰባ ረግጠው እንደወጡ በስም ጠቅሰው አልተናገሩም።

በተደረገ ማጣራት 97 ሰዎች በተለይ በመዳበሪያ ግብዓት ጋር ተያይዘው ከአራት ወረዳ ፦
- ከቀበሌ ልቀመምበር ጀምሮ፣
- ስራ አስኪያጅዎች፣
- የልማት ሰራተኞች፣
- የመጋዘን ጠባቂዎችና ሀላፊዎች ሁለት ወረዳ አስተዳደር ጨምሮ ለህዝብ የሚደርሰውን በማስተጎያጉል በዝርፊያ ጉዳይ ተሳታፊ መሆናቸው ተለይቶ ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርገናል ብለዋል።

የክልሉ ፕሬዜዳንት የሁለት ወረዳ አስተዳደሮችን ጨምሮ ተይዘዋል ያሏቸውን 97 ሰዎች በስም አልገለፁም።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " በግምገማ መድረኩ 25 ግለሰቦች በብልሹ አሰራር በህግ ቁጥጥር ስር ሆነዋል " ያሉ ሲሆን በተጨማሪም 10  አመራሮች ከሀላፊነት እንድነሱ ተደርገዋል ሲሉ አሳውቀዋል።

እነዚህ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉት አመራሮች ስም በይፋ አልተገለፀም ፤ በተጨማሪ ከኃላፊነት ተነሱ የተባሉትንም አመራሮች በግልፅ ስማቸውን አልተናገሩም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰሞኑን ከክልሉ ግምገማ ጋር በተያያዘ የሀዋሳ ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰት ፀጋዬ ቱኬ ከኃላፊነት መነሳታቸውንና በህግ እንዲጠየቁም ውሳኔ መተላለፉን ሌሎች በርካታ አመራሮች ላይ መሰል እርምጃ እንደሚወሰድ የክልሉን ብልፅግና ፓርቲ ዋቢ በማድረግ መዘገቡ አይዘነጋም።

የክልሉ ነዋሪዎችም በክልሉ ያለው እጅግ ህዝብን የሚያማርር ብልሹ አሰራር፣ ሙስናና ዘረፋ ስር የሰደደ መሆኑን በመግለፅ እያንዳንዱ አመራር ከታች እስከ ላይ እንዲጣራ መጠየቃቸውም ይታወሳል።

የሲዳማ ክልል በሙስና እና በብልሹ አሰራር በቁጥጥር ስር ዋሉ፣ ከኃላፊነታቸውም እንዲነሱ ተደረጉ ስላላቸው አመራሮች ይፋዊ ዝርዝር የሚያወጣ ከሆበ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#ኣሸንዳ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የ #ኣሸንዳ በዓል ሲከበር እና ሲዘከር የተጀመረውን ሰላምን በማጠናከር እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።

ይህን ጥሪ ያቀረበው ዛሬ የኣሸንዳ በዓል ምክንያት በማድረግ በሰጠው መግለጫ ነው።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ " ኣሸንዳ ፣ ማርያ ፣ ዓይኒ ዋሪ የነፃነት የእኩልነት ተምሳሌት ፤ የሴቶች የአብሮነትና የአንድነት ምልክት በመሆን ፤ የትግራይ ክብርና እሴቶች በቅብብሎሽ የትውልዶች ማስተሳሰርያ ገመድ እንዲሆኑ የራሱ አስተዋፅኦ አድርገዋል እያደረገም ይገኛል " ብሏል።

ባለፉት አመታት በነበረው ጦርነት ምክንያት የትግራይ ሴቶች እንደ አሸንዳ የመሰሉ የአደባባይ በአላት በደስታና ፌስታ ሊያከብሩት ይቅርና ፀሃይ ወጥታ ሳለች ጨልሞባቸው ደግሞ ለመተረትክ የሚከብድ ግፍ እንደደረሰባቸው ገልጿል።

" ይሁን እንጂ ግፉ እንዲቆም በፅናት በመታገላችሁ እና በማታገላችሁ ቢያንስ አሁን ለተደረሰው ደረጃ ለመድረስ መተኪያ የሌለው ተግባር ፈፅማቹሃል " ያለው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፤ " አስተዳደሩና ህዝቡ በናንተ ኩራት ይሰማዋል " ብሏል።

በዓሉ ሲከበር እና ሲዘከር የተጀመረው ሰላም በማጠናከር ፣ የህዝብ ጥያቄዎች እና ፍላጎቶች ፣ በሰላማዊና ፓለቲካዊ ትግል ለመመለስ በሚደረገው ትግል አሁንም እንደትናንት በፅናት እንደምትታገሉ በመታመመን ነው ብሏል።

" ያለው ሁኔታ ከባድ ነው " የሚለው አስተዳደሩ " ተፈናቃይ ወገኖች አጅግ በከፋ የኑሮ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት ፣ በአማራና ኤርትራ ታጣቂ ሃይሎች ስር የሚገኝ ህዝባችን ማለቅያ የሌላቸው ግፎች እየተፈፀሙበት ነው ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጥር ህዝባችን በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ ይገኛል " ብሏል።

የትግራይ ሴቶች ይህን የመሰለ ከባድ ሁኔታ ተቋቁማችሁ የአሸንዳ ፣ ማሪያ ፣ ዓይኒ ዋሪ በዓል ለማክበር መቻላችሁ መንፈሳዊ ጥንካሬአችሁ ብርቱና ከፍተኛ መሆኑ ማሳያና ማረጋገጫ ነው ሲል ገልጿል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ጥያቄዎች በሰላማዊና ፓለቲካዊ ትግል እንዲመለሱ እጅግ እልህ አስጨራሽ ትግል እያካሄደ መሆኑን ገልጾ " አሁንም ተፈናቃይ ወገኖች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ፣ በትግራይ መሬት የሚገኙ የአማራና የኤርትራ ታጣቂዎች ለቀው እንዲወጡ ፣ የተቋረጠው ሰብአዊ አርዳታ እንዲጀምር ፣ ወንጀለኞች በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያላሰለሰ ትግል አካሂዳለሁ " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ የኣሸንዳ በዓል መቼ ይከበራል ? የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፤ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2015 ዓ.ም የአሸንዳ በአል አከባበር መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት፤ በዓሉን #ነሃሴ_28 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለማክበር እቅድ መያዙ ገልጿል። የሚደረግ የጊዜ ለውጥ ካለ አስቀድሞ የሚገለፅ መሆኑንም አስተዳደሩ አሳውቋል። የበዓሉ መርሀግብር ምን ይመስላል ? - ነሃሴ 13…
ፎቶ ፦ ዛሬ ነሃሴ 15 ቀን 2015 ዓ/ም የ #ኣሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመቐለ ከተማ የጎደና የካርኒቫል ትርኢትና ሰማእታት የሚያስታውስ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።

#ማስታወሻ ፦ ከ " ኣሸንዳ " አከባበር ጋር በተያያዘ በክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የወጣው መርሀ ግብር ከላይ ተያይዟል። በቢሮው ከተገለፀው ውጭ የሚካሄደ የአሸንዳ በዓል ዝግጅት እውቅና እንደሌለው ተነግሯል።

Photo Credit : Demtsi Weyane

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ። የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። " ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን…
#ሶማሊያ

ሶማሊያ ቲክቶክ እና ቴሌግራም እንዲሁም 1ኤክስቤት (1XBet) የተባለውን የስፖርት ውርርድ ገጽን እንዲዘጉ አዘዘች።

" ቲክቶክ " እና " ቴሌግራም " የአሸባሪዎች መረጃ ማስተላለፊያ ሆነዋል ብሏል የሶማሊያ መንግሥት።

መተግበሪያዎቹ " አሸባሪ ድርጅቶች እና ቡድኖች አሰቃቂ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲሁም ፎቶግራፎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ጥቅም ላይ ውለዋል " ሲል ገልጿል።

የሀገሪቱ መንግሥት የኢንተርኔት አግልግሎት አቅራቢዎች እስከ ሐሙስ ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም. ድረስ  " እንዲዘጉ " የሚለውን ትዕዛዝ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ፤ የማያደርጉ ከሆነ ግን ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቋል።

ይህ ውሳኔ የተሰማው የሶማሊያ መንግሥት አልሸባብን ለማጥፋት ዘመቻ ከጀመረ በኃላ ነው።

በቅርቡ በሞቃዲሹ ኢንተርኔት እና ማኅበራዊ ሚዲያን በተመለከተ በተካሄደ ኮንፈረንስ ላይ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እና ኢንተርኔት በአጠቃላይ በተለይ በወጣቱ ላይ " ሕይወት እስከ ማሳጣት " የሚደርስ ጉዳት እያደረሰ ነው የሚል ሃሳብ በስፋት ተንጸባርቆ ነበር ተብሏል።

በኬንያም እንዲሁ በተለይም በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያለውን " ቲክቶክ "ን ለማገድ የሚያስችል ሃሳብ ለምክር ቤት ከሰሞኑም መቅረቡ ይታወሳል።

ቲክቶክ እንዲታገድ የተጠየቀው ፤ ኬንያ ቲክቶክን ለመቆጣጠር የሚያስችል ጠንካራ ሕግ ስለሌላት ጉዳት የሚያስከትሉ እና ተገቢ ያልሆኑ ይዘቶች በመድረኩ ላይ በስፋት እንዲቀርቡ ምክንያት ሆኗል በሚል ነው።

የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ሞሰስ ዊታንጉላ ፤ " ቲክቶክ በኬንያውያን በወጣቶች ዘንድ ተዘውታሪ በመሆኑ ፦
- ግጭቶችን በማባባስ፣
- ልቅ ወሲብን በማስፋፋት፣
- የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት፣
- የብልግና ቃላትን በማስፋፋት፣
- አደገኛ ባሕሪያትን በማስፋፋት ለአገሪቱ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጠንቅ እየሆነ ነው " ብለዋል።

ቲክቶክ እንዲታገድ ጥያቄ ያቀረቡት ግለሰብ ምክር ቤቱ ቲክቶክን የሚያግደው ከሆነ፣ በወጣቶች ዘንድ እየተስፋፋ ያለውን ሱሰኝነት እና የአእምሮ ጤና ችግርን ለመከላከል ይቻላል ብለዋል።

የቲክቶክ መተግበሪያ በሕገወጥ መንገድ የኬንያውያንን ግላዊ መረጃ በመሰብሰብ እና በማጋራት ተጠያቂ ነውም ብለዋል።

የቀረበውን ሃሳብ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት የደገፉት ሲሆን ሌሎች ደግሞ እገዳው ኬንያውያንን ከቴክኖሎጂ የሚያርቅ እና በቲክቶክ ላይ ይዘቶችን በማቅረብ ገቢ የሚያገኙ ወጣቶችን የሚጎዳ ነው በማለት ተቃውመውታል።

ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸውን የምክር ቤቱ አባላትን ጨምሮ አንዳንድ እንደራሴዎች ደግሞ ተክቶክን ሙሉ ለሙሉ ከማገድ ይልቅ በይዘቶቹ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ደንብ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

#BBC

@tikvahethiopia
" መጥታችሁ የጤና ምርመራ አድርጉ ፤ ምንም ክፍያ አትከፍሉም " - ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት " በጎነት ለጤናችን " በሚል ከነሐሴ 11 ጀምሮ ነፃ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ይኸው አገልግሎት ነገ ያበቃል ብሏል።

" የጤና ምርመራ ማድረግዎ ለእርስዎ በእጅጉ ይጠቅምዎታል፡፡ " ያለው ሆስፒታሉ " የጤናዎን ሁኔታ ለማወቅ እኛ ጋር ብቅ ይበሉ፦
- የዓይን ፥
- የውስጥ ደዌ፥
- የደም ግፊት ፥
- ከአንገት በላይ ፥
- የስኳር ህመም
- የጡት እና የማህጸን  ካንሰር  እና ሌሎች ምርመራዎች ከላቦራቶሪና ከአልትራ ሳውንድ ምርመራ ጋር ያገኛሉ፡፡ " ብሏል።

ሆስፒታሉ ለሚሰጠው አገልግሎት ፤ " ምንም ክፍያ የለውም " ሲል ገልጿል። ነፃ የህክምና አገልግሎቱ እየተሰጠ የሚገኘው በራስ ኃይሉ ስፖርት ማዘውተሪ መሆኑንም አሳውቆናል።

@tikvahethiopia