TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Facebook

ፌስቡክ ታሊባንን እንደ አሸባሪ ቡድን እንደሚመለከተውና ከቡድኑ ጋር የተያያዙ መልዕክቶችን እንደሚያቅብ አስታወቀ።

ፌስቡክ ታሊባንን የሚያደንቁ ይዘቶችን፣ የቡድኑን መልዕክቶችን አግዳለሁ ብሏል።

ይህን ሳንሱር እንዲሠሩለት አንድ ልዩ የአፍጋኒስታን ባለሙያዎች ቡድን ማዋቀሩን እና በእነዚህ ባለሙያዎች እየታገዘ የታሊባን ይዘቶችን ወዲያውኑ ከፌስቡክ ሰሌዳዎች ላይ እንደሚያጠፋ ፌስቡክ ዝቷል።

ታሊባን ለዓመታት መልዕክቶቹን በመላው ዓለም ለማድረስ ፌስቡክን እንደ አንድ መገናኛ ብዙኃን ሲጠቀምበት ቆይቷል።

ታሊባን አሁን የመንግሥትን መዋቅር መቆጣጠሩ ማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ቡድኑን እንዴት ማስተናገድ እንዳለባቸው በድጋሚ እንዲያጤኑ እያደረጋቸው ነው።

የፌስ ቡክ ቃል አቀባይ ፥ "በአሜሪካ ሕግ ታሊባን አሸባሪ ቡድን ነው። ይህ ሕግ እኛም በዚያው ሁኔታ እንድናያቸው የሚያደርገን ነው። በመሆኑም ከታሊባን ጋር የሚያያዙ ማናቸውንም መልዕክቶች እናቅባለን" ብለዋል።

ፌስቡክ ዋንኛ የአፍጋኒስታን ቋንቋ የሆኑትን ዳሪ እና ፓሽቶን የሚናገሩ አፍጋኒስታዊያን ተወላጆችን ለዚሁ ተግባር ሲል መልምሎ፣ ቀጥሮ እያሠራ እንደሆነ ተናግሯል።

የፌስቡክ ኩባንያ እቀባውን ተግባራዊ የሚያደርገው በእህት ኩባንያዎቹ በኢንስታግራምና በዋትስአፕ የትስስር መድረኮች ጭምር ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#Facebook

ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም መተግበሪያዎች መስራት አቁመዋል።

በፌስቡክ ስር የሚገኙት እኚህ መተግበሪያዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት ሙሉ ለሙሉ መስራት አቁመዋል።

እዚሁ ሀገራችን ላይም ከ25 ደቂቃዎች በፊት አገልግሎታቸው ተቋርጧል።

እስካሁን መተግበሪያዎቹ መስራት ያቆሙበት ምክንያት አልታወቀም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Facebook ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም መተግበሪያዎች መስራት አቁመዋል። በፌስቡክ ስር የሚገኙት እኚህ መተግበሪያዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት ሙሉ ለሙሉ መስራት አቁመዋል። እዚሁ ሀገራችን ላይም ከ25 ደቂቃዎች በፊት አገልግሎታቸው ተቋርጧል። እስካሁን መተግበሪያዎቹ መስራት ያቆሙበት ምክንያት አልታወቀም። @tikvahethiopia
#Facebook

ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር በአሁኑ ወቅት በበርካታ አገሮች ውስጥ አገልግሎታቸው መቋረጡን ኔትብሎክስ አሳውቋል።

ክስተቱ በአገር ደረጃ ካለ የኢንተርኔት ግንኙነት ጋር ያልተገናኘ መሆኑንም ጠቁሟል።

እስካሁን በፌስቡክ በኩል ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከ6 ሰዓታት በላይ ተቋርጠው የቆዩት ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እንዲሁም ሜሴንጀር ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል። ፌስቡክ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ከመጠየቅ ውጭ እስካሁን ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ማብራሪያ አልሰጠም። እንደብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ በፌስቡክ መቋረጥ በ5 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የማርክ ዙከርበርግ የግል ሃብት በ7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዝቅ ብሏል። @tikvahethiopia
#Facebook

ፌስቡክ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ከ6 ሰዓታት በላይ አገልግሎቶቹ የተቋረጡበት ምክንያት ከተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል።

የተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ መከሰቱን ተከትሎ በአጠቃላይ የኩባንያውን ውስጣዊ መሳሪያዎች እና ስርዓቶች ላይ ተፅእኖ በማሳደሩ ችግሩን ለመፍታት አዳጋች አድርጎታልም ሲል ገልጿል።

መግለጫው አክሎም "ተቋርጠው በነበሩበት ሰዓታት የተጠቃሚዎች ግላዊ መረጃ ተጥሷል የሚል ማስረጃ የለም" ብሏል።

የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ አገልግሎቶቹ በመቋረጣቸው ምክንያት ለተጎዱ ሰዎች ይቅርታ መጠየቃቸውን #BBC / ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Facebook

የቀድሞው የፌስቡክ ሠራተኛ ፍራንሲስ ሐውገን የፌስቡክን ሚስጥር አጋልጠዋል።

ፌስቡክ ኢትዮጵያን🇪🇹ጨምሮ በሌሎችም አገራት ሐሰተኛ መረጃና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን እንዳላስቆመ በይፋ ተናግረዋል።

የአሜሪካ ኮንግረስ ፊት ቀርበው ቃላቸውን የሰጡት ፍራንሲስ ሐውገን ፌስቡክ በኢትዮጵያና በምያንማር ግጭት ቀስቃሽ እና ሐሰተኛ መረጃዎችን ሳያስቆም ቀርቷል ብለዋል።

"እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ አሁን ላይ የምናያቸው ጽንፈኛ ድርጊቶች እየተባባሱ ይሄዳሉ ብዬ እፈራለሁ። በኢትዮጵያና በምያንማር ያየናቸው ነገሮች ወደባሰ ደረጃ የሚደርሱ፣ የአስፈሪ ታሪክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ናቸው" ብለዋል።

ፌስቡክ ሐሰተኛ መረጃዎችን፣ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን እንዲሁም የጥላቻ ንግግሮችን ከመሰራጨት ማስቆም እንዳልቻለ ተናግረዋል።

የ37 ዓመቷ የቀድሞው የፌስቡክ ፕሮዳክት ማናጀር በአሜሪካ ምክር ቤት ተገኝተው ቃላቸውን ሲሰጡ ድርጅቱን በጽኑ ወቅሰዋል።

ፌስቡክ ለሚለጠፉት መልዕክቶች ኃላፊነት እንዲወስድ መደረግ እንዳለበት ለኮሚቴው ባደረጉት ንግግር ጠቁመዋል።

ፌስቡክን ተጠያቂ ማድረግ የሐሰተኛ መረጃ ስርጨትን እንደሚገታ አልፎም ግጭት እንዳይነሳ እንደሚከላከል ተናግረዋል።

ፌስቡክ በአምባገነን እና የሽብር ድርጅት መሪዎች ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሆነ በንግግራቸው አጋልጠዋል። እነዚህ አካሎች እየተጠቀሙበት እንደሆነ ፌስቡክ መረጃው እንዳለውም አክለዋል።

የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይክና ሼር እንዲያደርጉ እንዲሁም አስተያየት እንዲሰጡ የሚያነሳሱ ጽሑፎች በገጹ ወደላይ እንደሚገፉ ተናግረዋል።

"እነዚህ መልዕክቶች እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በብሔር ክፍፍል የሚናጡ አገሮች ውስጥ ግጭት እያስነሱ ነው" ሲሉ አብራርተዋል።

ፌስቡክ ክሱን ውድቅ አድርጓል።

ያንብቡ : telegra.ph/BBC-10-06

@tikvahethiopi
TIKVAH-ETHIOPIA
#Facebook ፌስቡክ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ከ6 ሰዓታት በላይ አገልግሎቶቹ የተቋረጡበት ምክንያት ከተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው ብሏል። የተሳሳተ የአወቃቀር ለውጥ መከሰቱን ተከትሎ በአጠቃላይ የኩባንያውን ውስጣዊ መሳሪያዎች እና ስርዓቶች ላይ ተፅእኖ በማሳደሩ ችግሩን ለመፍታት አዳጋች አድርጎታልም ሲል ገልጿል። መግለጫው አክሎም "ተቋርጠው በነበሩበት ሰዓታት የተጠቃሚዎች ግላዊ…
#Facebook

ፌስቡክ ፣ ኢንስታግራም እንዲሁም ሜሴንጀር መተግበሪያዎች ዳግም የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟቸው እንደነበር ድርጅቱ ገለፀ።

ድርጅቱም በድጋሚ ይቅርታ ጠይቋል።

ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ ባለፈው ሰኞ መስከረም 24/2014 ዓ.ም ከ6 ሰዓታት በላይ ከተቋረጡ በኋላ በድጋሚ ትላንት ፌስቡክ እና ኢንስታግራም መስተጓጎል ገጥሟቸዋል።

ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ ላይ የአሠራር ለውጥ በሚደረግበት ወቅት መስተጓጎሉ እንደተፈጠረ ድርጅቱ ገልጿል።

ይህ የአሠራር ለውጥ በመላው ዓለም ያሉ ተጠቃሚዎቹ ላይ ለፈጠረው የአገልግሎት መቆራረጥ ፌስቡክ ይቅርታ ጠይቋል።

ሰኞ የተፈጠረው የአገልግሎት መቋረጥ እና የትላንቱ ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው ድርጅቱ ተናግሯል።

ለሁለት ሰዓታት ገደማ አገልግሎታቸው የተቋረጠው ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ሜሴንጀር እና ወርክፕሌስ ናቸው።

"ላለፉት ሁለት ሰዓታት አገልግሎታችንን ማግኘት ባለመቻላችሁ ይቅርታ እንጠይቃለን። የእኛን አገልግሎቶች ተጠቅማችሁ እርስ በእርስ መረጃ እንደምትለዋወጡ እናውቃለን። አሁን ላይ ችግሩን ቀርፈነዋል። በዚህ ሳምንት ላሳያችሁን ታጋሽነት እናመሰግናለን" ሲል ፌስቡክ በይፋዊ ትዊተር ገፁ መግለጫ አውጥቷል።

Credit : BBC

@tikvahethiopia
#Facebook

ፌስቡክ ኩባንያ የኢትዮጵያ መንግስት ሽብርተኛ ብሎ የፈረጀውን "ሸኔ" ፤ እራሱን ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ የሚጠራውን ቡድን ከፌስቡክ ማገዱን አስታውቋል።

ፌስቡክ ቡድኑን ያገደው 'አደገኛ ድርጅቶች' በሚለው መመሪያው መሠረት ነው።

የኩባንያው ቃል አቀባይ ለቢቢሲ በላኩል የኤሜል መልዕክት ፥ "የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከፌስቡክ የታገደው አደገኛ ድርጅቶች በተለይ ደግሞ መንግሥታዊ ያልሆኑ ሁከት ፈጣሪ አካላት በሚለው ፖሊሲ ሥር ነው" ብለዋል።

ፌስቡክ ቡድኑን ከፌስቡክ ማገዱን ተከትሎ "በኦሮሞ ነጻነት ጦር" ወይም ጦሩን ወክለው የሚከፈቱ /የተከፈቱ የፌስቡክ አካውንቶች እንዲኖሩ አይፈቀድም።

ለዚህ ቡድን ድጋፍ የሚሰጥ ወይም ቡድኑ የሚፈጥረውን ሁከት የሚያወድስ ይዘት ከፌስቡክ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረክ ላይም ይጠፋል።

የፌስቡክ ቃል አቀባይ ኩባንያው ድርጅቶችን በተለያየ ጎራ ከመፈረጁ በፊት ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች ጋር ዝርዝር ሥርዓቶችን እንደሚከተል አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ውስጥ ከፌስቡክ መመሪያ በተቃራኒ የተለያዩ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ሌሎች በርካታ ቡድኖችና ግለሰቦች መንግሥታዊ ባልሆኑ ሁከት ፈጣሪ አካላት ወይም በሌሎች ዘርፎች ውስጥ ተካተው እገዳ እንደተጣለባቸው የፌስቡክ ኩባንያ ገልጿል።

Credit : BBC

@tikvahethiopia
#Facebook

CNN ለአሜሪካ ህግ መምሪያ ምክር ቤት የቀረበ አንድ ሚስጥራዊ የፌስቡክ ኩባንያ ሰነድ መመልከቱን አሳውቋል።

ይኸው ሚስጥራዊ ሰነድ ፌስቡክ በኢትዮጵያ ግጭትን እያባባሰ እንደሆነ እያወቀ አንደችም ርምጃ እንዳልወሰደ የሚገልፅ ነው።

የፌስቡክ ኩባንያ ኢትዮጵያን "ለግጭት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራት" በሚለው ምድብ ያስቀመጣት ሀገር ናት።

የኩባንያው ሰራተኞች ፌስቡክ በኢትዮጵያ ግጭትን ለማባባስ እየዋለ መሆኑን ላቀረቧቸው ጥቆማዎች ኩባንያው ምላሽ እንዳልሰጠ ከሚስጥራዊው ሰነድ መመልከቱን CNN ዘግቧል።

ይኸው ሚስጥራዊ ነው የተባለው የፌስቡክ ሰነድ የውጭ መንግስታት እንዲሁም ድርጅቶች በኢትዮጵያ #የጥላቻ_ንግግር እና ግጭትን ለመስበክና ለማሰራጨት ፌስቡክን እንደተጠቀሙበት ያሳያል ሲል CNN ባወጣው ዘገባ ጠቅሷል።

ሙሉ የCNN ሪፖርት በዚህ ተያያዟል : https://edition.cnn.com/2021/10/25/business/ethiopia-violence-facebook-papers-cmd-intl/index.html?utm_content=2021-10-25T11%3A51%3A04&utm_term=link&utm_medium=social&utm_source=twCNN

Credit : CNN/WAZEMA

@tikvahethiopia
#TikvahFamily

ስለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ፦

• ቲክቫህ/ተስፋ ኢትዮጵያ ሰውነትን ያስቀደሙ ሁሉንም የሰው ፍጡር፣ ህዝብን እና ሀገርን የሚያከብሩ ፣ በማንኛውም ጉዳይ ሚዛናዊ አመለካከት ያዳበሩ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ ቤት ነው።

• የቤተሰቡ አባላት መረጃ ማካፈል፣ አንዱ ያልሰማውን ሌላው እንዲሰማው መጠቆም ፣ በሚዲያ ላይ የሚከታተሉትን ሌላው የቤተሰቡ አባል እንዲያውቀው ማድረግ ይችላሉ። በአጭሩ የቤተሰብ አባላቱ እርስ በእርስ መረጃ ልውውጥ የሚያደርጉበት ነው። (ምንጭ በመጥቀስ)

• በቤተሰቡ / አባላት በማንኛውም ጉዳይ ላይ ሀሳብን በነፃነት መግለፅ የሚቻል ሲሆን አንዲት ቃል ስድብ ሆነ የሰዎችን ክብር ፣ ሃይማኖት፣ ብሄር ማንነትን የሚነካ መልዕክት መላክ ከቤተሰቡ ወዲያው በቀጥታ ያስቀንሳል።

• ቲክቫህ ኢትዮ. ከተመሰረተ አንስቶ ከማንም ወገን ፣ ከየትኛውም አካል (የመንግስት ሆነ ተቃዋሚ፣ አልያም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት) ጋር ግንኙነት የሌለው ሲሆን በየትኛውም አካል አይደግፍም፤ አይታግዘም። ለስራ በሚል ከቤተሰቡ ገንዘብ አይጠይቅም አያሰባስብም።

ተቋርጠው የነበሩ የቤተሰቡን ስራዎች ስለማስቀጠል ፦

- ባለፉት ሁለት ክረምቶች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በጦርነት ሳቢያ ዓመታዊ ለገጠር ት/ቤቶች የሚደረገው የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እና የፀረ ጥላቻ ንግግር ዘመቻ ተቋርጦ ቆይቷል። በዚህ አመት ለማስቀጠል ዝግጅት ተደርጓል።

- ሲቆራረጥ የነበረው ለግለሰቦች የሚደረግ የህክምና ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻም በዚህ ዓመት የሚጀምር ሲሆን ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ስራው ይሰራ የሚለውን ሃሳብ ያላችሁ የቤተሰባችን አባላት ማሳወቅ ትችላላችሁ።

- ከዚህ ቀደም በቤተሰቡ አባላት የሚተላለፉ አጭር የቅሬታ ፣ የጥቆማ፣ የፀጥታ ችግር ማሳወቂያ ፣ ትችት፣ ጥያቄ በስፋት መላክ ይቻላል። እንደከዚህ ቀደሙ መልዕክት ሲላክ አጭር ከጥላቻ ሃሳብ የፀዳ እና የመፍትሄ ሃሳብንም የሚጠቁም ሊሆን ይገባል።

- ለጀማሪ ወጣቶች ላለፉት ዓመታት ክፍት የተደረገው የነፃ ማስታወቂያ ስራም በዚህ ዓመት ይቀጥላል። በግል ሆነ ተደራጅተው እራስን ሆነ ሀገርን ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ወጣት የቤተሰቡ አባላት ስራቸውን ሆነ አገልግሎታቸው በነፃ ያለምንም ክፍያ ለሌሎች የቤተሰቡ አባላት ማስተዋወቅ ይችላሉ መብታቸውም ጭምር ነው። ነገር ግን በሚሰሩት ስራ ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል።

- በጋዜጠኝነት ሞያ ውስጥ ያሉ የቤተሰባችን አባላት እንዲሁም ደራስያን መፅሀፍቶቻቸውን በነፃ ለቤተሰባችን እንዲያስተዋውቁ የተጀመረው ስራ በዚህ ዓመት የሚቀጥል ይሆናል።

#ማሳወቂያ፦ የ "ዕርቅ ሀሳብ አለኝ" በሚል በቲክቫህ አስተባባሪነት የተካሄደው ሀገር አቀፍ በሀገር በቀል ባህላዊ የዕርቅ ስነስርዓት ላይ ባተኮረው ውድድር ላይ የቀረቡ ፅሁፎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደቤተሰቡ ይላካል።

#ማሳሰቢያ ፦ ማስታወቂያን በተመለከተ በቀን እጅግ ውስን ማስታወቂያ ለቤተሰቡ ይላካል ፤ የሚላከው ማስታወቂያ ጠቃሚ እና ህጋዊ ሲሆን ብቻ ነው። ማስታወቂያውን የሚያስነግሩትም የቤተሰቡ አባላት በመሆናቸው የእርስ በእርስ ተውውቅን ያጎለብታል። በዚህ መሃል ችግር ቢፈጠር በማስታወቂያ ስም ማጭበርበር ቢሰራ ድርጅቱን ከነስሙ የምናጋልጥ ይሆናል። የቤተሰቡ አባላትን ገንዘባቸው እንዲመለስ ይደረጋል። ድርጅቱም ከቤተሰቡ ይቀነሳል።

#ከአጭበርባሪዎች_ተጠንቀቁ ፦ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት
- " Tikvah Mart "
- " Tikvah Market "
- " Tikvah Business " በሚሉ አድራሻዎች/ቦታዎች አይሰባሰቡም። በእነዚህ ገፆች የሚተላለፉ ሁሉ ሀሰተኛ መልዕክቶች ናቸው። በማስታወቂያ ስም ገንዘብም እንደሚቀበሉ ደርሰንበታል ፤ ከዚህ በፊትም እንዳልነው ተጠንቅቋቸው። ቻናሎቹንና ግሩፖቹን ለቴሌግራም ሪፖርት አድርጉ ፤ ይህን ስራ ለመስራት የሚጠቀሙበትን የስልክ ቁጥር ካላቸውም ላኩልን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ ምንም አይነት የ #Youtube#TikTok#Facebook አካውንት የለም።

መልዕክት ማስቀመጫ ፦ @tikvahethiopiaBOT

@tikvahethiopia
#Facebook

• " ፌስቡክ በገፁ የዘር ግጭትን የማስፋፋት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን #ሆን_ብሎ የማሰራጨት አደጋ አለ " - ግሎባል ዊትነስ

• " የተወሰኑ የጥላቻ ንግግሮች ተላልፈዋል። ችግሩ የተፈጠረው የምንጠቀማቸው ማሽኖች እና ሰዎች በሰሩት ስህተት ነው " - ፌስቡክ

በጎረቤት ኬንያ በነሐሴ ወር ከሚካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፌስቡክ የጥላቻ ንግግርን ከገፁ ላይ እንዲያጠፋ የኬንያ ባለስልጣናት ጠይቀዋል።

ፌስቡክ ማስተካከያ ካላደረገ እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።

ግሎባል ዊትነስ የተባለ የመብት ቡድን ባወጣው ሪፖርት ፌስቡክ የዘር ግጭት የሚቀሰቅሱ የጥላቻ ንግግሮች ያሉባቸው ማስታወቂያዎችን ማፅደቁን ይፋ አድርጓል።

ግሎባል ዊትነስ በጥናቱ ሂደቱ 10 በእንግሊዘኛ እና 10 በስዋሂሊ ቋንቋ የተሰሩ የጥላቻ ንግግር ያዘሉ ማስታወቂያዎችን ለፌስቡክ ያስተላለፈ ሲሆን ሁሉም ማስታወቂያዎች መፅደቃቸውን የተቋሙ ዋና አማካሪ ጆን ሎይድ ተናግረዋል።

በኬንያ ፌስቡክ #ከ10_ሚሊየን_በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በነሐሴ ወር የሚካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በማህበራዊ ድህረገፁ የዘር ግጭትን የማስፋፋት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን #ሆን_ብሎ የማሰራጨት አደጋ መኖሩን ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።

ሪፖርቱን ተከትሎ ፌስቡክ ትላንት ባወጣው መግለጫ የተወሰኑ የጥላቻ ንግግሮች በገፁ መተላለፉን አምኖ ችግሩ የተፈጠረው ድህረገፁ የሚጠቀማቸው ማሽኖች እና ሰዎች በሰሩት ስህተት ነው ብሏል።

አክሎም፣ በተለይ የስዋሂሊ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና ቴክኖሎጂዎች ጎጂ መረጃዎችን በማስወገድ እንዲያግዙት እና ምርጫው ሰላማዊ እና ስጋት የሌለበት እንዲሆን በሰዎች ላይ እና ቴክኖሎጂዎች ላይ እንዲሰራ መጠየቁን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ቀጣይ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ቅዳሜ ጥቅምት 30 ከረፋዱ 4:30 በፌስቡክ ፔጃችን ላይ ይደረጋል፡፡ በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ!
ዛሬውኑ የፌስቡክ ፔጃችን በመቀላቀል እና ቀላል ጥያቄዎችን በመመለስ ይሸለሙ!

የፌስቡክ ሊንክ፡ https://www.facebook.com/BoAeth

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Facebook #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ