TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰላም

" እርቅ ይውረድ ! የሰው ደም መፍሰስ ይብቃ ! ሰላም ይታወጅ ! ምድሪቱንም እናሳርፋት ! " - ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ አባታዊ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው ካስተለለፉት መልዕክት የተወሰደ ፦

" ከአካላዊ ጦርነት እስከ ቃላት ውርወራ ብዙ ጥላሸት የመቀባባት ሰለባ ሆነው የወደቁት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆቻችን ትምህርት ሆነውን ልባችን ዘንበል ባለማለቱ ለወደፊት ሊመጣ የሚችለው ሲታሰብ እጅግ ያስፈራልና በዐራቱም ማዕዘን ነፍጥ አንሥታችሁ ያላችሁ በሙሉ ያነገባችሁትን ገዳይ መሣርያ አውርዳችሁ ለሰላምና ለዕርቅ ቅድሚያ በመስጠት ለአንዲት አገራችሁ ሕልውና ተገዢዎች እንድትሆኑ፤ መንግሥትም ልበ ሰፊ ሁኖ ሁሉንም ለውይይት እንዲሰበስብ በጽኑ እንለምናለን።

በኢትዮጵያ ምድር ላይ ያላችሁ ሽማግሌዎች ሽምግልናችሁ ለዚህ ቀን ካልሆነ ለመቼም አይሆንምና በአገሩም ሽማግሌ የለም ወይ? መባሉ በሰማይ በምድር ያስወቅሳልና ልጆቻችሁን እንድትመክሩና እንድታስታርቁ ከዛሬ ጀምሮም ለሰላም ጠበቆች ሁናችሁ እንድትቆሙ አበክረን እንጠይቃለን።

በውጭ አገር የምትኖሩም #እናንተ_በሰላም_አገር_እየኖራችሁ ዘመዶቻችሁ በእሳት ሲጠበሱ ዝም ብሎ ማየት ስለማይገባ እስከአሁን ስታደርጉት እንደቆያችሁት ሁሉ አሁንም ለሰላሙ ብርቱ ጥረት እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

በተጨማሪም ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ግጭት ባለባቸው አከባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን ጥረትና እገዛ እንዲያደርጉ፣ ቤተ ክርስቲያንን የምንመራ ውሉደ ክህነትም መፍትሔ መሆን ሲገባን የችግሩ አካል ሆነዋል እየተባልን ነውና ውስጣችንን አጥርተን ለወገኖቻችን በአስታራቂነት ለመድረስ ጊዜው አሁን ስለሆነ ዛሬ እንድንነሣሣ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን። "

ቅዱስነታቸው ዛሬ ባወጡት አባታዊ የሰላም ጥሪ ፤ " አሁን ያለው ችግር ወደ ቀጣይ አመት እንዳይሻገር ገትተነው ቀጣዩን አዲስ ዓመት በሰላም ለመቀበል እንችል ዘንድ ከጉልበት ሳይሆን ከልብ ሽብረክ በማለት እርቅ ይውረድ ! የሰው ደም መፍሰስ ይብቃ ! ሰላም ይታወጅ ! ምድሪቱንም እናሳርፋት ! " በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #UAE

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ / UAE ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ተሰምቷል።

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል ተብሏል።

በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከተለያዩ የመንግስት የስራ ኃፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው፤ ከዚህ ቀደም የአቡዳቢ አልጋ ወራሽ በነበሩትበት ወቅት በ2018 በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው ነበር።

መረጃው አልአይን ኒውስ ነው።
Photo : PM Office Ethiopia

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ፖሊስ ከቡሄ በዓል ጋር በተያያዘ ርችት መተኮስ ክልክል ነው አለ።
  
የቡሄ በዓልን ምክንያት በማድረግ በየአካባቢው በሚከናወነው የችቦ ማብራት ስነ ስርዓት ወቅት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ፖሊስ ፤ የፀጥታ ስራውን በአግባቡ ለመምራት እና ለመቆጣጠር  እንዲሁም  አጋጣሚውን በመጠቀም ሊፈፀሙ የሚችሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ሲባል ርችት መተኮስ መከልከሉን አመልክቷል።

@tikvahethiopia
በአቢሲንያ ባንክ ደሞዝ ለሚከፈላቸው ሰራተኞች ደሞዝ ባይደርስም ደሞዛቸውን ቀድመው መበደር የሚችሉበት አስደሳች ዕድል ከአቢሲንያ ባንክ! የአፖሎ የሞባይል መተግበርያን አሁኑኑ ያውርዱ!

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalbank
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
መጣና ባመቱ፥
ኧረ እንደምን ሰነበቱ

ክረምቱ አልፎ ወደ ብርሃን መሻገራችንን በሚያበስረው፤ በህጻናት ውብ ዜማ እና የጅራፍ ድምጽ የሚደምቀው ቡሄ ሌላ ድምቀት የሆነውን ቡሄ የሞባይል ጥቅል በ20% ቅናሽ እንዲሁም በቴሌብር ከ10% ስጦታ ጋር ለራስዎ ይግዙ፤ በስጦታ ያበርክቱ!

እንዲሁ እንዳለን አይለየን!
ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን!

መልካም ቡሄ!

(ኢትዮ ቴሌኮም)
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA 🤝 #UAE

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) በፋይናንስና ኢንቨስትመንት ጨምሮ በሌሎች 17 ዘርፎች ስምምነት ተፈራርመዋል።

የስምምነቱ  ፊርማ ከመከናወኑ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ልኡካን ቡድኖቻቸውን በመያዝ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በኢትዮጵያ በኩል ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የስራ ኃላፊዎች ጋር ስምምነቱን የተፈራረሙት ፦

- የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ
- የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ
- የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ
- የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምፀሀይ ጳውሎስ
- የግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ
- የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል
- የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ
- የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆንዲንግስ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ መለከት ሳህሉ
- የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ
- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አረጋ
- የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ ናቸው።

ፎቶ፦ PMOEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ህገ-መንግስት በጉባኤው አባላት በአብላጫ ድምጽ መፅደቁ ተነግሯል።

ዛሬ ጠዋት በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ በጀመረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ-መንግስት አጽዳቂ ኮሚሽን ጉባኤ የቀረበው ረቂቅ ህገ-መንግስት በ10 ተቃውሞ በ2 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ መፅደቁ ተነግሯል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል  ረቂቅ ህገ-መንግስቱ 11 ምዕራፎች፣ 141 ዋና ዋና አንቀጾች እና በርካታ ንዑሳን አንቀፆች አሉት ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ ፥ 32 ብሔሮችና ብሔረሰቦች ይኖሩበታል የተባለው ይኸው ክልል የመወከልበት ሰንደቅዓላማ ለጉባኤው አባላት ቀርቦ ተዋውቋል።

በሌላ በኩል ፤ የደቡብ ብሔር-ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል ህገ-መንግስትን በማሻሻል በአዲስ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ለሚደራጀው ክልል የተዘጋጀው ረቂቅ የህገመንግስት ሰነድ በወልቂጤው ጉባዔ ላይ ፀድቋል።

የህገመንግስት ሰነዱ በ5 ተቃውሞ፣ በ3 ድምፅ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ መጽደቁን ነው ለማወቅ የተቻለው።

@tikvahethiopia