TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HamaqPLC
Car Hand Break And Gear Shift Lock -ለመኪናዎ የሚያገለግል አስተማማኝ መቆለፊያ  
-በአሁኑ ጊዜ እየተበራከተ ለመጣው የመኪና ስርቆት ሁነኛ መፍትሄ
-በኮንዶሚኒየም፣አፓርታማና በጋራ መኪና ማሳደሪያ ለሚጠቀሙ ተመራጭ
-የእጅ ፍሬንን ከማርሽ ጋር የሚቆልፍ    

ዋጋ =3000 ብር  ☎️ 0912917632 ከየማይቀረፅ ቁልፎች ጋር ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን::👉Free delivery

አድራሻ:- አቢሲኒያ ፕላዛ
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) በረራ ነገ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን አሳውቋል።

መንገደኞች የአየር መንገዱን ድረ-ገጽ (www.ethiopianairlines.com) ወይም የሞባይል መተግበሪያውን (https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app) በመጠቀም ለጉዟቸው የሚያስፈልጉ ተግባራትን ካሉበት መከወን ይችላሉ ተብሏል።

ተጨማሪ ዕገዛ የሚሹ መንገደኞች በአቅራቢያቸው የሚገኙትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከሉ (6787) በመደወል መስተናገድ እንደሚችሉ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል ! ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች። ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ። ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ…
" ኢፍትሃዊ እና ግብዝነት የተሞላበት ነው " - ኡጋንዳ

የዓለም ባንክ ለኡጋንዳ አዲስ ብድር አልሰጥም ብሏል።

ይህን ያለው ለምን የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ህግን አውጥተሽ ተግባራዊ አደረግሽ በሚል ነው።

የዓለም ባንክ ኡጋንዳ ያወጣችው ሕግ " መሰረታዊ ከሆኑ እሴቶቼ ጋር ይቃረናል " ብሏል።

ተቋሙ ለሁሉም ኡጋንዳውያን ያለምንም ልዩነት " ከድህነት እንዲወጡ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እና ሕይወታቸውን እንዲያሻሽሉ ለመርዳት " ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

በኡጋንዳ ከዚህ ቀደምም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነቶች ሕገ ወጥ የነበሩ ሲሆን ግንቦት ላይ በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሰረት ደግሞ የዕድሜ ልክ እስራትን ጨምሮ #ሞት ያስቀጣል።

በኡጋንዳ ተግባራዊ በተደረገው የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ሕግ ፤ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ ሰው ጋር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የፈጸመና የኤችአይቪ ቫይረስ በደሙ ከሚገኝበት ሰው ጋር ግኝኑነት የፈጸመ ሰው እስከወዲያኛው ይሸኛል / የሞት ቅጣት ይፈረድበታል።

ዓለም ባንክ ይህ ሕግ ተግባራዊ ከተደረገ በኃላ አንድ ቡድን ወደ ኡጋንዳ አሰማርቶ የነበረ ሲሆን ሕጉ " በመሰረታዊነት የዓለም ባንክ ቡድን እሴቶችን ይቃረናል " ብሏል።

ራዕያችን " ዘር፣ ጾታ ወይንም ተመሳሳይ አፍቃሪነትን ሳይለይ ሁሉንም ያካተተ ነው " ሲል ገልጿል።

በሕጉ ውስጥ የተካተቱ አዳዲስ እርምጃዎች እስኪገመገሙ ድረስ " ለኡጋንዳ አዲስ ብድር እንዲጸድቅ ለሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አይቀርብም " የሚል ውሳኔ አሳልፏል።

ኡጋንዳ ምን አለች ?

የዓለም ባንክ የወሰደው እርምጃ ኢፍትሃዊ እና ግብዝነት ነው ብላለች።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኡጋንዳ አምባሳደር አምባሳደር አዶኒያ አየባሬ ፥ " የገንዘብ ተቋሙን እርምጃ በጣም የከፋ ነው። የዓለም ባንክ የአሰራር ዘዴ እና የቦርዱን ውሳኔ እንደገና የማጤን ጊዜው አሁን ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታ ኦኬሎ በበኩላቸው ፤ እርምጃው ከሌሎች አገራት ጋር ሲወዳደር ወጥነት የለውም ብለዋል።

" የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የማይታገሱ በርካታ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት አሉ። ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችንም የሚቀጡት በመስቀልና በመግደል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" በአሜሪካ ውስጥ በርካታ ግዛቶች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚቃወሙ ወይንም የሚገድቡ ሕጎችን አውጥተዋል። ታዲያ ለምን ኡጋንዳ ላይ አነጣጠራችሁ ? "ሲሉም ጠይቀዋል።

ከዓለም ባንክ በተጨማሪ አሜሪካ በጸረ ተመሳሳይ አፍቃሪ ሕግ ምክንያት በኡጋንዳ ላይ ማዕቀብ ጥላለች። (ሮይተርስ/ቢቢሲ)

ኡጋንዳ ፤ ሕጉን ከማፅደቋ በፊት ከምዕራባውያን ሀገራት እና ተቋማት ብዙ ማስጠንቀቂያዎች ቢደርሳትም ሕጉ ለሀገሬ አስፈላጊ ነው በማለቷ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፈርመውት አፅድቀውታል፤ ተግባራዊም ሆኗል።

ከዚህ ቀደም የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፤ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ #በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ  " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉ ነበር የገለፁት።

ስለ ኡጋንዳ አዲሱ ሕግ ለማወቅ ፡ https://t.iss.one/tikvahethiopia/78787

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፅሙ የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው " - ፖሊስ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ወግ እና ባህል ያፈነገጡ ድርጊቶችን አስመልክተው መግለጫ አውጥተዋል። " ሀገራችን በህብረ ብሄራዊነቷ የምትታወቅና የተለያዩ ባህሎችና ወጎች ያሏት ሀገር ነች፡ " ያሉ ሲሆን ፤ " ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከማህበረሰቡ ወግና ባህል ያፈነገጡ…
#Update

በአዲስ አባባ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚፈጸምባቸው ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰድ እንደተጀመረ ተገለፀ።

እርምጃውን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመተባበር እየወሰዱ ነው ተብሏል።

እርምጃ እየተወሰደባቸው ያሉት ሆቴሎች፣ ባሮችና ሬስቶራንቶች መሆናቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ፤ ከነባሩ የሀገሪቷ ባህል፣ ወግ፣ የአኗኗር ስርዓት እና ኃይማኖቶች ባፈነገጠ መልኩ የግብረ-ሰዶም ተግባር በሚያስፈጽሙ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ፔንሲዮኖችና መሰል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከህብረተሰቡ በሚደርስ ጥቆማ መሰረት አስተማሪ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብሏል።

ቢሮው ፤ የግብረ-ሰዶም ተግባር መፈጸምና ማስፈጸም በኢትዮጵያ በሥራ ላይ ባሉ ሕጎች የተከለከለ መሆኑ ገልጾ " ይህንን አስጸያፊ በሰውም በአምላክም ዘንድ የተጠላ ደርጊት በሚፈጽሙና በሚያስፈጽሙ የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቆማት ላይ ካለ አንዳች ርህራሄ ከህብረተሰቡ በሚደርሰን ጥቆማ መሰረት ከፖሊስ ጋር በመተባበር እርምጃ መውሰዳችንን አጠናክረን እንቀጥላልን " ሲል አሳውቋል።

በዚህም ፤ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ውስጥ በሚገኝ " አበባ ገስት ሐውስ " በሚባል የመዝናኛ አገልግሎት መስጫ ተቋም ላይ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት እርምጃ እንደተወሰደበት አሳውቋል።

የተቋሙ ኃላፊም በከተማው ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ምርመራ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል።

ከግብረሰዶም ፀያፍ ተግባር ጋር የተገናኘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት ይችላል።

@tikvahethiopia
ካርድ በመሙላት ብቻ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም በነፃ ያለገደብ ቀኑን ሙሉ ወይም ሳምንቱን ሙሉ ማውራት እንችላለን። አሁኑኑ አየር ሰዓት ገዝተን እደልብ እናውጋ።

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
#CBE

ባሻዎት ጊዜና ቦታ ይላኩ!
EthioDirect
===========
በኢትዮ-ዳይሬክት ከውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ የማስተር ወይም የቪዛ ካርድዎን ተጠቅመው በማንኛውም ጊዜና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ መላክ ይችላሉ፡፡

#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
=============
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም App Store በማውረድ አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
TIKVAH-ETHIOPIA
" ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል " አስራ ሁለተኛ ክልል በመሆን ፌዴሬሽኑን የተቀላቀለው አዲሱ የ " ደቡብ ኢትዮጵያ " ክልል፤ ከነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ስልጣን ተረከበ። ነባሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ ክልል ስልጣኑን ያስረከበው፤ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 29፤ 2015 ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ነው። አዲሱን ክልል በህዝበ ውሳኔ የመሰረቱት ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች…
" የተቋማት ሽንሸናው ኢፍትሐዊ ነው " - የዱራሜ ነዋሪ

ከሰሞኑን የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግሥት አዲስ ለተደራጀው " የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል " በይፋ ስልጣኑን አስረክቧል።

ክልሉ ከዚህ ቀደም ሪፈረንደም ተደርጎባቸው እንደ አዲስ ለተዋቀሩት " ሲዳማ ክልል " እና " የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ " ክልል ስልጣን ማስረከቡ ይታወሳል።

ከሰሞኑን ስልጣን ሲያስረክብ 3ኛው ሲሆን ይኸው ሰሞነኛው የስልጣን ርክክብ ክልሉ ቅርፁን ይዞ የተጓዘበት ምዕራፍ የተጠናቁናበትና መዋቅሩ ፣ ስያሜው እና ህገ መንግስቱን እንዲቀይር የሚያደርግ ነው።

በዚህም መሰረት 5ቱ ዞኖች (ሀድያ ፣ ሀላባ ፣ ከምባታ ጠንባሮ ፣ ጉራጌ  ፣ ስልጤ) እና 1 ልዩ ወረዳ (የም ልዩ ወረዳ) " የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " በሚል ስያሜ አብረው ይቀጥላሉ።

' ነባሩን ክልል ' በተመለከተ ዛሬን ጨምሮ ሰሞኑን በመዋቅሩ ውስጥ ያሉት ዞኖች ረቂቅ ሕገመንግቱን፣ የሕግ ማዕቀፎች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለተ እየተወያዩ ይገኛሉ።

ከዚህ ከነባሩ ክልል / ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከቢሮዎች መቀመጫ ጋር በተያያዘ የፍትሃዊነት ጥያቄዎች ስለመነሳታቸውን ካደረግነው ዳሰሳ እና ከተላኩልን መልዕክቶች ለማወቅ ችለናል።

በተለይ የፍትሐዊነት ጥያቄዎች ከነዋሪዎች ዘንድ ሲነሱ የተመለከትነው ከከምባታ ጠምባሮ በኩል ነው።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን መቀመጫ የሆነችው " ዱራሜ ከተማ " በአዲሱ አደረጃጀት " የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር ማዕከል " እንደተደረገች ከዞኑ ይፋ በተደረገ መረጃ ለማየት ተችሏል።

በዚህ ክላስተር ፦ የግብርና ቢሮ፣ ደን ልማት እና አከባቢ ጥበቃ ቢሮ፣ ህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ፣ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ ግብርና ግብዓቶች ቁጥጥር እና ኳረንታይን ባለስልጣን፣ ምርጥ ዘር ድርጅት፣ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ፣ የመስኖ ልማትና ተቋማት አስተዳደር ፣ የአከባቢ ጥበቃ ቁጥጥር ባለስልጣን ተቋማት መቀመጫ እንደሆነች ተነግሯል።

ይህ በነባሩ ክልል የተደረገው ሽንሸና " ፍፁም ፍትሃዊ አይደለም " በሚል በዞኑ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ያለ መሆኑን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጻዋል።

ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች እንዳሉት ከሆነ ሽንሸናው የአካባቢውን እድገት ወደኃላ የሚያስቀር ፣ ከሌሎች አንፃር ሲታይም ፍፁም ፍትሐዊ ያልሆነ በመሆኑ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ከሰሞኑን ከዚህ የቢሮዎች ኢፍትሃዊ አደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በዱራሜ የንግድና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ተዘግተው የነበረ ሲሆን ነዋሪዎችም በተለያየ መልኩ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ነበር።

ከቀናት በፊት ዱራሜ ላይ አመራሩ ከህረተሰቡ ጋር ባካሄደው ስብሰባ ህብረተሰቡ የተሰጠው " ግብርናና ተጠሪ ተቋም " ለዞኑ ማህበረሰብ በቂ አለመሆኑና ተጨማሪ ቢሮዎች ተካተው ሊሰጡ ይገባል ሲል ጠይቋል።

በዚሁ መድረክ ላይ የከተማው ሆነ የመላው ዞኑ ህዝብ ማንኛውም ጥያቄ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ፣ከሁከት እና ከብጥብጥ በፀዳ መልኩ ማቅረብ ይችላል ተብሏል።

ከተደረገው የተቋማት ምደባ ጋር በተያያዘ " በቂ አይደለም ይጨመርልን " የሚለው ጥያቄ ከክልል እስከ ታች ያለው የዞኑ አመራር ጥያቄ መሆኑ በመድረኩ ላይ ተመላክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ የነዋሪዎችን አስተያየት እንዲሁም በዞኑና በአዲሱ አደረጃጀት ላይ የሚወጡ መረጃዎች እየተከታተለ ያቀርባል።

ፎቶ፦ ሰሞኑን ከነበሩ ተቃውሞዎች የተወሰደ

@tikvahethiopia
#ኣሸንዳ

የዘንድሮው የኣሸንዳ በዓል " ለሰላም ፣ ለመዳንና ለመልሶ ግንባታ " በሚል በትግራይ እንዲሁም ከትግራይ ውጭ ባሉ አካባቢዎች ላይ ይከበራል።

ከትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተገኘው መረጃ በዓሉ በቅድሚያ የሚከበረው በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ስር በሚገኙ ነፃ በሆኑ አካባቢዎች ሲሆን በመቀጠል አዲስ አበባ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ይከበራል።

ነሐሴ 16 በአዲስ አበባ ከተማ በዓሉ እንዲከበር እንቅስቃሴ ሲደረጉ የነበሩ ሌሎች አካላት እንደነበሩ የጠቆመው ቢሮው በመናበብ ችግር የተፈጠረ መሆኑ መግባባት ላይ በመደረሱ በዓሉ ነሐሴ 16 አዲስ አበባ ላይ እንደማይከበር አሳውቋል።

የዘንድሩው በዓል የሚከበረው የትግራይን አሁናዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ትውፊት እና ክብሩን በጠበቀ መልኩ ሲሆን ትግራይ ላይ ከተከበረ በኃላ በአዲስ አበባ እንደሚከበር ተገልጿል።

አዲስ አበባ ላይ ለሚከበረው በዓል አቅጣጫ ተቅምጦ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንና ከከተማው አስተዳደር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እየተደረገ ስለመሆኑ የትግራይ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አሳውቋል።

ባለፉት ዓመታት አስከፊው ጦርነት ምክንያት በዓሉ በሚፈለገው ልክ ሳይከበር ቀርቷል።

ዘንድሮ ያለውን ሰላም ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ እና የዓለም ክፍሎች ለዚሁ በዓል ትግራይ ይገኛሉ ፤ በክልሉ የተዳከመው የቱሪስት እንቅስቃሴም መነቃቃት ያሳያል ተብሎ ይጠበቃል።

የኣሸንዳ በዓል ፍቅር ፣ ይቅር ባይነትና መልካም ተግባቦት በተግባር የሚንጸባረቅበት በዓል ሲሆን የበዓሉ ይዘት በዋናነት ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ መልካም ተግባቦቶች፣ ፍቅርንና ይቅር ባይነት ላይ ያነጣጠረ ነው።

በዓሉ የሌሎች ሃሳቦች፣ ጭፈራዎችና ትእይንቶች እንዲታዩ የሚጋብዝ ከመሆኑ ባለፈ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት አይንፀባረቅበትም።

በዚህ በዓል ላይ ህብረትን የሚሰብኩ ፣ መድልዎን የሚጠየፉ እና ለሰው ክብርን የሚያጎናጽፉ መልዕክቶች ይተላለፉበታል።

@tikvahethiopia