TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

" ግለሰቡ ህፃናቱን በተለያዩ ቀናት ከረሜላ እየገዛ በማታለል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ አስገብቶ ወንጀሉን ፈፅሞባቸዋል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሶስት ህፃናት ላይ የ ' ግብረሰዶም ወንጀል ' የፈፀመ ግለሰብ  በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ እንደተላለፈበት ተገለፀ።

የ43 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሽ ወንጀሉን የፈፀመው በክ/ከተማው ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ማር ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።

ግለሰቡ የጎረቤቱ ልጆች የሆኑ የ5 ፣ የ6 እና የ10 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃናትን በተለያዩ ቀናት ከረሜላ እየገዛ በማታለል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ አስገብቶ ወንጀሉን ፈፅሞባቸዋል።

ወንጀሉ ከተፈፀመባቸው ህፃናት መካከል የ6 ዓመቱ ህፃን ስለሁኔታው ለወላጅ እናቱ በመናገሩ ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

ይህንን ተከትሎ ሌሎቹ 2 ህፃናትም ተመሳሳይ ድርጊት እንደፈፀመባቸው በመግለፃቸው በ3 የምርመራ መዝገቦች ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል፡፡

መዝገቡን ሲመረምር የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የተከሳሹን ጥፋተኝነት በሰው እና በህክምና ማስረጃ በማረጋገጡ በ19 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡

ህብረተሰቡ ከህግ እና ከማህበራዊ እሴቶች ያፈነገጡ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲያጋጥሙ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

#ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፁም የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ  መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት ይችላል ሲል ፖሊስ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
(ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ) " የስራ ሀላፊነትን በፈቃድ ስለመልቀቅ ! በ2011 ዓ.ም ታህሳስ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በመሆን ስራዬን ስጀመር ተቋማችንን ተአማኒ እና ራሱን ችሎ ምርጫን ማከናወን የሚችል ተቋም ለማድረግ በማለም ነበር። ባለፉት አራት አመት ከስድስት ወራት ሶስት ህዝበ ውሳኔዎችን እና አገራዊ ምርጫን በማካሄድ እና ፓለቲካ ፓርቲዎችን በማስተዳደር የተሰጡኝን ሃላፊነቶች…
ወ/ሪት ብርቱካን ሽኝት ተደረገላቸው።

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ያሳወቁት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሽኝት ተደረገላቸው።

ወ/ሪት ብርቱካን ፤ ጤናቸውን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ከነሀሴ 1/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ለተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ማሳወቃቸው አይዘነጋም።

ፎቶ፦ NEBE

@tikvahethiopia
Audio
#Gondar

የጎንደር ግጭት ከተማዋን አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደጣላት አንድ በጎንደር ሆስፒታል የሚሰራ የቲክቫህ የቤተሰብ አባል የሆነ የሕክምና ዶክተር አሳውቆናል።

የጎንደር ሁኔታ #እጅግ_አስከፊ እንደነበር የገለፀልን የህክምና ዶክተሩ " በግጭቱ ምክንያት የመጨረሻ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሟል ፤ ሰላማዊ ዜጎች እዚህም እዚያም ተገድለዋል " ሲል አስረድቷል።

በሆስፒታሉ ውሃ ፣ ኦክስጂን ፣ እንዲሁም ደግሞ መድሃኒት ቤት ከመድሃኒት ውጭ እየሆኑ መሆኑን ገልጿል።

" የከባባድ መሳሪያ ድምጾች ከሆስፒታሉ ውስጥ ሆነን ይሰማን ነበር " ያለው ዶክተሩ ላለፉት ቀናት ከተማዋ በተኩስ ስትናጥ መቆየቷን አመልክቷል።

እስከ ትላንት ሰኞ ከሰዓት ድረስ በግጭቱ ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል የሚያመላልስ እና አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ አንድ አምቡላንስ ብቻ እንደነበር እሱም በሚያስዝን ሁኔታ ዒላማ መደረጉን የጎንደር ሆስፒታል ዶ/ር የሆነው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል አሳውቆናል።

የንፁሃን ነዋሪዎች ጉዳይ ትኩረት የሚሻው መሆኑን አስገንዝቧል።

(ድምፅ ዛሬ ጥዋት ላይ የተቀዳ)

@tikvahethiopia
"  ምግብ ካገኘን ሦስት ቀን አልፎናል " - ጎንደር የሚገኙ መምህር

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ለመስጠት አማራ ክልል ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የሄዱ መምህራን በክልሉ በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት ወደየመጡበት አካባቢ ለመመለስ እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

እንጃባራ ዩኒቨርሲቲ ፈታኝ የነበሩ አንድ መምህር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፤ በክልሉ " የሰላም ሁኔታው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው ፤ ለመፈተን ሄደን በማናውቀው ሁኔታ ውስጥ ገብተናል " ብለዋል። " መንገዱ ዝግ ነው ነገሩ የደፈረሰ ነው ፤ ያለው ሁኔታ ያስፈራል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት በመጣልን መልዕክት ' እዛው ባላችሁበት ፔንስዮን ቆዩ፣ አልጋ ይከፈላል ' የሚል ሲሆን እኛ ደግሞ ችግራችን የአልጋ አይደለም ፤ ችግር ውስጥ ነው ያለነው ፤ የየራሳችን ፕሬዜዳንቶችም እየደወሉ አይዟቹ እዛው ሁኑ ነው የሚሉን ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተነጋገርን ነው ኮማንድ ፖስቱ ያለውን ነገር እስኪያሳውቅ ጠብቁ ነው ያሉን ፤ ያለው ሁኔታ ግን ያስፈራል " ሲሉ ገልጸዋል።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ መምህር ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ፤ በከተማው ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት መሃል ከተማ ከሚገኘው የሆቴል ክፍላቸው ከወጡ ሦስት ቀናት መቆጠራቸውን ገልፀዋል።

" በከተማዋ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም " ያሉት መምህሩ " የሆቴሉ ሠራተኞችም ወደ ሥራ እየገቡ ስላልሆነ ምግብ ማግኘት እጅግ ከባድ ሆኗል " ብለዋል።

" ምግብ ካገኘን ሦስት ቀን አልፎናል። ባለፈው ሳምንት የገዛነውን ቆሎ ነው እየቆጠብን እየበላን ያለነው። ከሆቴሉ እያገኘን ያለነው ውሃ ብቻ ነው " ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

ቃላቸውን ለቢቢሲ የሰጡ በደብረ ማርቆስ የሚገኙ መምህር ደግሞ በከተማው ግጭት ባይኖርም የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና የንግድ ተቋማት ዝግ መሆናቸውን ተናግረዋል።

" ከተማው ከሞላ ጎደል ሰላም ነው። የደረሰብን ጉዳት የለም። ዋናው ችግራችን ወደ መጣንበት ለመመለስ አለመቻላችን ነው " ብለዋል።

አሁን ላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በከተማዋ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የሚገልጹት መምህሩ ፤ በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከዚህ በላይ ተባብሶ የበለጠ ችግር ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክት ያደረሱ የተለያዩ ተቋማት መምህራን ከግጭት ቀጠና የሚወጡበት መንገድ በፍጥነት እንዲመቻችና ወደቤተሰቦቻቸው የሚመለሱበት መንገድ እንዲፋጠን ጠይቀዋል።

በአማራ ክልል ያሉ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሆኑ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Amahra

" የባልደረባችንን አስክሬን ማምጣት አልቻልንም ፤ እዛው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ነው ያለው " -ዶ/ር ፋሪስ ደሊል

ተቋማት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን ወደ አማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የሄዱ እና በክልሉ ባለው ግጭት ምክንያት  መመለስ ያልቻሉ መምህራንን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን አሳውቀዋል።

በርከታ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመፈተን ወደ አማራ ክልል በሄዱበት በተባባሰው ግጭት ምክንያት ከክልሉ መውጣት ባለመቻላቸው ችግር ላይ መሆናቸውን እየገለፁ ናቸው።

መምህራኖቹ አማራ ክልል ከሚገኙ ተቋማት አንዱ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ፤ መምህራኑን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፤ ባለፈው ሳምንት በጎንደር የተገደለው መምህር የተቋማቸው ባልደረባ መሆኑን ገልጸው እስካሁን እስክሬኑ ከከተማው እንዳልወጣ ጠቁመዋል።

ሌሎችም መምህራን ጎንደር እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ዶ/ር ፋሪስ ፤ " ለመፈተን ከሄዱ መምህራን አንዱ መምህር ታደሰ አበበ አስክሬኑን ማምጣት አልቻልንም እዛው ነው ያለው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ " ያሉ ሲሆን " ሌሎች ለመፈተን የሄዱ መምህራንም አሉ እነሱን በስልክ እያገኘናቸው ነው መመልስ አልቻሉም " ብለዋል።

ካሉበት ወጥተው ለመምጣት ደህንነት የለም ያሉት ፕሬዜዳንቱ " የጥይት ድምፅ በተለያየ ቦታ ይሰማል ዩኒቨርሲቲው ባላችሁበት ቆዩ ነው ያላቸው። " ሲሉ ገልጸዋል።

ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመምህራኑ ጉዳይ እየተነጋገርን ነው ያሉት ዶ/ር ፋሪስ " መንገዱ ሰላም ሆኖ መውጣት የሚችሉበት ሰዓት ደርሶ እስኪመጡ በትግዕስት መጠበቅ እንዳለብን ነው የምንነጋገረው ፤ እዛው ከለው የዩኒቨርሲቲ አመራር ፣ ፕሬዜዳንቱም ጋር እየተደዋወልን ነው በትዕግስት ጠብቀን መንቀሳቀስ ሲችሉ መምህራኖቻችን እና የባልደረባችንን አስክሬን እንደምናገኝ ነው የምንነጋገርው " ብለዋል

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ፤ 53 መምህራን በጎንደር ፣ ደባርቅ እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች እንደተመደቡና ሁኔታቸውን በቅርበት እየተከታተልን ነው ብለዋል።

ደህንነታቸው ተጠብቆ በሚወጡበት ሁኔታ ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጋር እየተነጋገርን ነው ሲሉ አሳውቀዋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፤ ፈታኝ መምህራንን ቀደሞ ወደመጡበት መሸኘቱን ተፈታኝ ተማሪዎች ግን በመንገድ መዘጋት ምክንያት ከግቢ መውጣት አልቻሉም ብሏል። ተቋሙ ባህር ዳር ነዋሪ የሆኑትን እና ቤተሰብ ያላቸውን የሸኘ ሲሆን ወደ ወረዳ እና ዞን መመለስ የነበረባቸውን በመንገድ መዘጋት መሄድ ስላልቻሉ ግቢ ውስጥ እንዲቆዩ መደረጉን ለሬድዮ ጣቢያው (ቪኦኤ) ገልጿል።

የአውሮፕላን በረራ በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የፈተና አስፈጻሚዎች / መምህራን " ያለው ሁኔታ እስከሚረጋጋ ድረስ ትንሽ ቀን " መጠበቅ እንደሚኖርባቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ባለፈው አርብ በሰጡት መግለጫ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

@tikvahethiopia
Visa Everywhere Initiative (VEI) ልዩ የኢትዮጵያ ውድድር: ቢዝነሳችሁን ወደ ላቀ ደረጃ ለመውሰድ ዝግጁ ናችሁ?

ለVisa Everywhere Initiative 2015/16 በመመዝገብ እውቅና ማግኘት፣ የቬንቸር ካፒታሊስቶችን ዐይን መሳብ ፣ ኢንቬስትመንት እና አጋሮችን ማግኘት ይቻላል።

የVEI ልዩ የኢትዮጵያ ውድድር ምዝገባ እስከ ነሐሴ 14 ድረስ ክፍት ነው። https://africa.visa.com/visa-everywhere/everywhere-initiative/initiative.html

#EverywhereInitiative8
#ሰከላ_ስኩል_ሲስተም

የግልና የመንግስት የትምህርት ተቋማትን ሁለንተናዊ ክንውን የሚያዘምነውን የሰከላ ሲስተምን (SIMS) በአዲሱ የት/ት ዘመን ይተግብሩ!

ክፍያዎችን በኦንላይን ለመፈፀም፣ መረጃ አያያዝና አስተዳደርን ዲጂታል ለማድርግ ሁሉን በአንድ የያዘ አስተማማኝ መተግበርያ!

ይህንን https://sekela.app ወይንም https://sekela.app/school-registration ሊንክ በመከተልና በመመዝገብ ያለምንም ኢንስታሌሽንና ቅድመ ክፍያ ካሉበት ይጠቀሙ
እስራኤል ዜጎቿን ከአማራ ክልል ወደ #ትግራይ ክልል ማስወጣቷን " ጄሩሳሌም ፖስት " ዘግቧል።

እስራኤል በአማራ ክልል ውስጥ ያለውን ግጭትና የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቅርበት እየተከታተለችው መሆኑ ተነግሯል።

ባለፈው ሰኞ ከአካባቢው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመሆን ተጓዥ ዜጎቿን ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ እንዲወጡ ማድረጓ ተገልጿል።

ዘገባው ተካሂዷል ባለው የእስራኤል ዜጎችን ከግጭት ቀጠና የማስወጣት ኦፕሬሽን 13 ተጓዥ እስራኤላውያን እና ሌሎች 7 ሌሎች የውጭ ሀገር ዜጎች ከደባርቅ ወደ ትግራይ ሽረ ከተማ እንዲወጡ ተደርጓል።

ከሽረ ከተማም በአውሮፕላን በረራ ወደ አዲስ አበባ እንደሚጓዙ ተነግሯል።

በሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች እስራኤላውያን መኖራቸው የተመላከተ ሲሆን ሀገሪቱ ክትትል እያደረገችና ከግጭት ቀጠና ደህንነታቸው ተጠብቆ ለማስወጣት በሚቻልበት ሁኔታ መንገድ እየተፈለገ መሆኑ ተነግሯል።

በአማራ ክልል በተለይም በጎንደር ከተማ ፤ ወደ እስራኤል ለመሄድ የሚጠባበቁ አባላት በርከታ ቤተእስራኤላውያን ማህበረሰብ አባላት አሉ።

#ጄሩሳሌም_ፖስት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በአዲስ አበባ ሞተር ብስክሌት እስከ ረቡዕ ድረስ ታገደ። የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ፤ በከተማው ለሚገኙ የሞተር ብስክሌተኞች በሙሉ ባስተላለፈው መልዕክት ከነገ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ እሮብ ነሀሴ 3/2015 ዓ.ም እስከ ምሽት 12:00 ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍፁም የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል። ቢሮው ፤ ክልከላው በምን ምክንያት እንደተጣለ…
እገዳው ተራዘመ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከርን እስከ እሮብ ነሐሴ 3/2015 ዓ.ም ማገዱ ይታወቃል።

ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት እግዱ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል።

ክልከላው የፀጥታና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን ፤ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እግዱ እሰኪነሳ በትዕግስት እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ቢሮው አስጠንቅቋል።

በከተማዋ ሞተር ለምን እንደታገደ በቢሮው በኩል የተሰጠ ማብራሪያም ይሁን ገለፃ የለም።

በርካታ ወጣቶች በሞተር በመንቀሳሰቅ በሚሰራ የስራ ዘርፍ / እቃ በማድረስ ተሰማርተው ገቢ እንደሚያገኙ ይታወቃል።

እገዳውን በተመለከተ ቃላቸውን የሰጡን ሞተረኞች " ሰርተን ቤተሰብ ከላስተዳደርን እንዴት እንኖራለን ፤ ችግሮች ካሉም ማስተካከያ ማድረግ ይቻለል ፤ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ጊዜ እየታገድን ነበር ፤ አሁንም ታግዷል ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ አይደለም ፤ አስተዳደሩ ስለኛም ህይወት ያስብልን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gondar የጎንደር ግጭት ከተማዋን አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደጣላት አንድ በጎንደር ሆስፒታል የሚሰራ የቲክቫህ የቤተሰብ አባል የሆነ የሕክምና ዶክተር አሳውቆናል። የጎንደር ሁኔታ #እጅግ_አስከፊ እንደነበር የገለፀልን የህክምና ዶክተሩ " በግጭቱ ምክንያት የመጨረሻ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሟል ፤ ሰላማዊ ዜጎች እዚህም እዚያም ተገድለዋል " ሲል አስረድቷል። በሆስፒታሉ ውሃ ፣ ኦክስጂን ፣ እንዲሁም ደግሞ…
#GONDAR

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የህክምና ዶክተር የሆነው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በከተማው ስላለው ሁኔታ መረጃዎችን አጋርቶናል።

- ታማሚዎች በኦክስጂን እና ደም እጥረት እየሞቱ መሆኑን ገልጿል።

- ለአምቡላንስ ጨምር ምንምአይነት የትራንስፖርት አማራጭ እንደሌለ ፤ ታማሚዎች በሰው ኃይል በሸክም ወደ ሆስፒታሉ እየመጡ መሆኑን አስረድቷል።

- ወደ 20 (ሰላማዊ ሰዎች) ወደ ሆስፒታሉ ከደረሱ በኃላ እንደሞቱ እንዲሁም ከ200 በላይ ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል እንደሚጡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸውን ገልጿል።

- በርከታ ሰዎች በቤታቸው ሞተው፣ ቀብራቸውም በአካባቢያቸው በተለይም በቀበሌ 4 ፣ 12 ፣ 11 እና 18 መፈፀሙን አመልክቷል።

- ባለፈው ሰኞ በነበረ ግጭት ከሆስፒታሉ የተወሰኑ ህፃዎች በመሳሪያ ቢመቱትም የተጎዳ ሰው ግን እንዳልነበር ገልጿል።

- ሆስፒታሉ ምግብ እንዲሁም መድሃኒት እያለቀበት መሆኑን አመልክቷል።

ዛሬ ጎንደር እንዴት ናት ?

አሁን ላይ በጎንደር ከተማ ከየትኛውም አቅጣጫ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ አይደለም። ጥዋት ላይ ለጥቂት ሰከንድ ፒያሳ እና ቀበሌ 18 አካባቢ ተኩስ ተሰምቶ ነበር።

ከትላንት ማታ አንስቶ ዛሬም ጥዋት በከተማው አብዛኛው ክፍል ላይ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለ ሲሆን ሰራዊቱ በሆስፒታሉ አካባቢም መኖሩን ይኸው ዶክተር ገልጿል።

የህክምና ዶክተሩ ከምንም በላይ በሆስፒታል ያለው የኦክስጅን ፣ የደም እጥረት እንዲሁም የአምቡላንስ ትራንስፖርት ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።

ጥንታዊቷ እና ታሪካዊቷ #ጎንደር ባለፉት ቀናት ከፍተኛ የሆነ ግጭት ካስተናገዱ የአማራ ክልል ከተሞች መካከል አንዷ ናት።

@tikvahethiopia