#ቅዱስ_ሲኖዶስ
• የግጭት ተሳታፊዎች ካለፈው የጦርነት ውጤት ተማሩ።
• የተፈጠረውን ችግር #በጥበብና #በማስተዋል ፤ በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ ተወያይታችሁ ፍቱ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ስብሰባ በማድረግ ወቅታዊ ሀገራዊ ሰላምን በተመለከተ አጀንዳ በመቅረጽ በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም መደፍረስና የእርስ በርስ ግጭቶች ምክንያት የበርካታ ወገኖቻችን ውድ ሕይወት እያለፈ እና በርካታ የሀገርና የሕዝብ ሀብትና ንብረት እየወደመ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ትገልጻለች " ብሏል።
" ሰላም ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ፍጡራን መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ " ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ " ሰላም ከሌለ ቀድሶ ማቁረብ፣ ነግዶ ማትረፍ፣ አርሶ ማምረት፣ ተምሮ ማስተማር ወልዶ ማሳደግ፣ ወጥቶ መግባት፣ አገር መምራትና ማስተዳደር አይቻልም ። በጥቅሉ ሰላም ሲጠፋ አብረው የሚጠፉ መልካም እሴቶቻችን ብዙ ናቸው፡፡ " ሲል አስገንዝቧል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በቅርብ ጊዜ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ጦርነት የበርካታ ወገኖቻችንን ሕይወት የቀጠፈ ከመሆኑም በላይ ከሞት የተረፉት ወገኖቻችንም ለስደትና ለረሀብ የዳረገ ፣ ለአካልና ለእእምሮ ስብራት ያጋለጠ ከመሆኑም በተጨማሪ በርካታ አድባራትና ገዳማትን እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትን ያፈረሰ እና መተኪያ የሌላቸውን ውድ ቅርሶቻችንን ያወደመ እጅግ በጣም አስከፊ ተግባር መሆኑን አስታውሷል።
በመሆኑም ፡-
በሀገራችን በኢትዮጵያ የተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነትና ግጭት ተወግዶ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ልንማጸን ይገባል ብሏል።
በሀገራችን በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሰላም እጦትና የእርስ በርስ ግጭት ወደፊት ሊያስከትል የሚችለው ችግር ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለአገራዊ ሰላም የበኩላቸውን ጥረት እንዱያደርጉ መልእክቱን አስተላልፏል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል እየተደረጉ ባሉ ግጭቶች ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች ካለፈው የጦርነት ውጤት በመማር የተፈጠረውን ችግር በጥበብና በማስተዋል እንዲሁም በሰለጠነ አካሄድና በሰላማዊ መንገድ ተወያይተው እንዲፈቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ከአደራ ጋር ታስተላልፋለች ብሏል።
@tikvahethiopia

የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግን መጠቀም የተለያዩ የክፍያ አገልግሎቶችን በአንድ ላይ እንዲያገኙ ያስችላል፣ ከነዚህም አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ የወርሃዊ የዲኤስቲቪ ክፍያዎን መክፈል የሚያስችለው ሲሆን የዲኤስቲቪ አገልግሎትዎ ሳይቋረጥ ካሉበት ሆነው ሳይጉላሉ ክፍያዎን መፈፀም ይችላሉ።
የሞባይል መተግበሪያውን ከ Play Store ወይም App Store ያውርዱ፡፡
ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://shorturl.at/beiJT
ለአፕል ስልኮች፡ https://shorturl.at/opP48
#BankofAbyssinia #remittance #Banking #BankingService #Digital #DigitalEthiopia #DigitalPayment #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

ጥምረት የፊልም ፌስቲቫል በአዳማ እና በአዲስ አበባ በሚኖሩን መርኃግብሮች ፍጻሜውን ያገኛል።
ዛሬ በመጨረሻው ቀን፦
#በአዲስአበባ "ለዘር ጥያቄ ግሩም ምላሽ የሰጠኝ አርሶ አደር" እና "ሙስሊምና ክርስትያን ድንቅ ተዓምር ሰሩ" የተሰኙ ዶክመንተሪዎች ለዕይታ ይቀርባሉ።
📍በጣሊያን ባህል ማዕከል🕒 ከ 11፡ 00 ሰዓት ጀምሮ መታየት ይጀምራሉ።
#በአዳማ "Zeyse" የተሰኘው ዶክመንተሪ ይቀርባል።
📍በኦሊያድ ሲኒማ🕒 ከ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ መታየት ይጀምራል።
በፊልም ፌስቲቫሉ ለሚገኙ ተሳታፊዎች በሰርተፊኬት አዘጋጅተናል።
📣 መግቢያው #በነጻ ነው።
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉 https://t.iss.one/TimretEth
ዛሬ በመጨረሻው ቀን፦
#በአዲስአበባ "ለዘር ጥያቄ ግሩም ምላሽ የሰጠኝ አርሶ አደር" እና "ሙስሊምና ክርስትያን ድንቅ ተዓምር ሰሩ" የተሰኙ ዶክመንተሪዎች ለዕይታ ይቀርባሉ።
📍በጣሊያን ባህል ማዕከል
#በአዳማ "Zeyse" የተሰኘው ዶክመንተሪ ይቀርባል።
📍በኦሊያድ ሲኒማ
በፊልም ፌስቲቫሉ ለሚገኙ ተሳታፊዎች በሰርተፊኬት አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉 https://t.iss.one/TimretEth
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
" በመደበኛ የሕግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ ተገኝቷል " - የአማራ ክልል መንግሥት በቀን 27/11/2015 ዓ/ም በአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ተፈርሞ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በተላከ ደብዳቤ ፤ አሁን ላይ በአማራ ክልል ያለውን የፀጥታ ችግር በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቋም የማይቻልበት ሁኔታ እንደተፈጠረ ይገልጻል። የፀጥታ መደፍረሱ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ…
#NewsAlert
በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ።
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት 23ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።
በዚህም ስብሰባ ፤ " የሕዝብን ሠላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ " በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ መመምከሩ ተነግሯል።
ምክር ቤቱ ፤ " በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ፤ ይህ እንቅስቃሴ የክልሉን ነዋሪ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያወከ እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ፤ የሕዝብን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም ህግ እና ስርዓት ለማስከበር የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ እንቅስቃሴው በሃገር ደህንነት እና በህዝብ ሰላም ላይ የደቀነው አደጋ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል፡፡ " ብሏል።
" መንግስት ትጥቅ አንስተው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሁሉ የሰላም እና ህጋዊ መንገድን እንዲከተሉ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ " ያለው ምክር ቤቱ " የታጠቁ ፅንፈኛ ቡድኖች እየፈፀሙ ባለዉ ጥቃት ምክንያት የክልሉ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡ " ሲል ገልጿል።
የክልሉ መንግስትም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያጋጠመው የፀጥታ መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ፣ ሁኔታውን በመደበኛው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ፣ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት እንዲደነግግ እና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ አቅርቧል ሲል አመልክቷል።
" በመደበኛ የህግ ስርዓትን መሰረት አድርጎ ይህን ፈር የለቀቀ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ በመፈጠሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ " ሲል ምክር ቤቱ አሳውቋል።
በዚህም ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

#Update
በሀገር አቀፍ ደረጃ ላለፉት አራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተጠናቋል፡፡
የፈተናው መጠናቀቅን ተከትሎ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደየመጡበት መመለስ ጀምረዋል።
በሌላ በኩል፥ ትላንት ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ቀኑን ሙሉ በከባድ ተኩስ ስትናጥ እንደዋለች አንድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህር ገልፀውልናል።
ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ የነበረው በከተማ አቅራቢያ ላይ እንደነበር ጠቁመዋል።
እሳቸው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሚገኝ የመምህራን መኖርያ ወስጥ እንደሚኖሩ አመልክተው በነበረው ግጭት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ብሔራዊ ፈተና የወሰዱት በጠዋቱ ፈረቃ ብቻ እንደነበር ገልጸዋል።
ለፈተናው ከተቀመጡት ግማሾቹም ቢሆኑ ጥለው በመውጣታቸው እንዳልተፈተኑ አመልክተዋል።
በትላንቱ የጎንደር ሁኔታ ከፍተኛ የሰው ጉዳቶችን እንደተመለከቱ የገለፁት መምህሩ ፤ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችም በከተማው በነበረው ሁኔታ ችግር ላይ ወድቀው እንደነበር ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በአማራ ክልል ካለው የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ምን ይመስል እንደነበር ? ተማሪዎች እና መምህራን ላይ ስለደረሱ ጉዳቶች ከትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።
ፎቶ፦ ወላይታ ሶዶ፣ ወልድያ፣ ጅማ ፣ ዋቸሞ፣ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲዎች

#AAU
አንጋፋው የ " #አዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ " በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆነ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ወስኗል።
ውሳኔው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ መፈጸም እንደሚያስችላቸው የታመነበት በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።
በዚሁ መሰረትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ሆኖ አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ነፃነቱ ተጠብቆ መንቀሳቅስ እንዲችል፣ በትምህርት ዘርፍ ለተጀመረው የሪፎርም እንቅስቃሴ ፈር ቀዳጅ ሆኖ እንዲወጣ እድል ይፈጥርለታል ተብሏል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ስርዓትን በቀዳሚነት ተግባራዊ እንደሚያደርግና ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተምሳሌት እንደሚሆን ይጠበቃል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ እና ጎንደር የሚደረጉ በረራዎች መሰረዛቸውን እንደገለፀለት አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ዘግቧል። የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ አሸናፊ ዘርዓይ " ወደ ጎንደር እና ላሊበላ የሚደረጉ በረራዎች ተቋርጠዋል " ሲሉ እንደነገሩት የዜና ወኪሉ ፅፏል። በረራዎች የተሰረዙበትን ምክንያት ግን እንደማያውቁ ተናግረዋል። ወደ ላሊበላ የሚደረገው በረራ ማክሰኞ ከሰዓት በኃላ መሰረዙን…
#Update
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደሴ ፣ ጎንደር እና ላሊበላ የሚያደርገው የቅዳሜ እና እሁድ በረራዎች የተሰረዙ መሆኑን አሳውቋል።
ወደተጠቀሱት አካባቢዎች ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ ደንበኞቹ በረራዎቹ እንደተመለሱ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

በሳምንታዊ የዳታ ጥቅሎቻችን በአነስተኛ ዋጋ ብዙ ይጠቀሙ!
ለወዳጆችዎ በስጦታ ያበርክቱ!
ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ሲገዙ 10% ስጦታ ያገኛሉ
ለወዳጆችዎ በስጦታ ያበርክቱ!
ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ሲገዙ 10% ስጦታ ያገኛሉ
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE
ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነገ መግለጫ ሰጥተዋል።
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?
- ፈተናው ከኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል።
- ፈተናውን ለመፈተን በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ ከነዚህም ውስጥ 840 ሺህ 859 ፈተናውን ውስደዋል።
- በማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና የተወሰነ የሥነ-ምግባር ችግር ጨምሮ አንዳንድ ችግሮች ተስተውለው ነበር።
- በጉዞ ሂደት ያጋጠመ የትራፊክ አደጋ፣ በሕመም ፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ እና ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶችን ወደ ፈተና ጣቢያ ይዞ መግባት በመሞከር እና የሥነ ምግባር ችግሮች አጋጥመዋል።
- በፈተና ሂደቱ የጎላ ችግር አልገጠመም።
- በጎንደር ዩኒቨርሲቲ 3 ካምፓሶች ላይ (ማራኪ ፣ ፋሲል ፣ ቴዎድሮስ) ትናንት ባጋጠመ ችግር 16 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን ሳይፈተኑ ቀርተዋል። በቀጣይ በሚመቻች መርሐ-ግብር ይፈተናሉ።
- በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ኢመደበኛ ኃይሎች መከላከያው ላይ በከፈቱት ተኩስና ከዛ በኃላ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲሰጥ የነበረ አንድ ግለሰብ እና ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባሎች ተገድለዋል። አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ቆስሏል።
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የገቡ 16 ሺህ ተማሪዎች፤ ትላንት ከሰዓትና ዛሬ ጠዋት የተሰጡትን ፈተናዎች አልወሰዱም።
- በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ካጋጠመው ችግር ውጪ በአማራ ክልል በሚገኙ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የተሰጠው ፈተና በሰላም ነው የተጠናቀቀው።
- በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይም የአውሮፕላን በረራ በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ያሉ የፈተና አስፈጻሚዎች ሁኔታው እስከሚረጋጋ ድረስ ትንሽ ቀን መጠበቅ አለባቸው።
- ጋምቤላ ላይ የተወሰኑ ተማሪዎች ባጋጠማቸው ሕመም 38 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም።
- ከአዲስ አበባ ለፈተና ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የገቡ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻቸው ተቧድነው ጸብ ፈጥረው ነበር። በዚህም በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
- በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ እና ልደታ ካምፓሶች የቡድን ጸብ ነበር ከሁሉም የከፋ የነበረው በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ነው። በዚህ ግቢ ተማሪዎች በቡድን ሆነው ተማሪዎችን ከማስፈራራት እና ከመስረቅ ባሻገር የተማሪዎችን የመኝታ ቤት በር እና መስታወት እንዲሁም የተማሪ ሎከር ሰብረዋል።
- በአዲስ አበባ ከነበሩ ተቋማት 87 ተማሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። 49 ያህሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ካምፓስ ከተፈጸመው ድርጊት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው።
- በአንጻራዊነት ሲታይ ከባለፈው ዓመት አንጻር ሲታይ የፈተና አሰጣጡ ስኬታማ ነበር።

#MoE ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነገ መግለጫ ሰጥተዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? - ፈተናው ከኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል። - ፈተናውን ለመፈተን በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ ከነዚህም ውስጥ 840 ሺህ 859 ፈተናውን…
#ጎንደር
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለፈተና የገቡ 16 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትላንት ሰዓት እና የዛሬውን ፈተና እንዳልወሰዱ የትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።
ሚኒስቴሩ ፤ በማራኪ ፣ ቴዎድሮስ ፣ ፋሲል ግቢ ለፈተና የገቡ ተማሪዎች በአካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ፈተናቸውን ሳይወስዱ እንደቀሩ አመልክቷል።
በዕለቱ በነበረ የተኩስ ልውውጥም 1 ፈታኝ / የፈተና አስፈፃሚ እና 2 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሲገደሉ ፤ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ደግሞ ቆስሏል።
በአጠቃላይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ፈተናቸውን መፈተን ያልቻሉ 16 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ በሚመቻችላቸው መርሐ ግብር ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ጎንደር ካጋጠመው ችግር ውጭ በሌሎች የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉም ፈተና ተሰጥቶ መጠናቀቁን አሳውቋል።

#Tigray
ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በትግራይ ክልል በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አጠናቀው በተፈጠረው ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች የማጠናከሪያ እና የማካካሻ ትምህርት ከተሰጣቸው በኃላ ከመስከረም 29 - ጥቅምት 2 ቀን 2016 ድረስ ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።
በትግራይ ለተማሪዎች የማካካሻ እና ማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጠው በክልሉ ውስጥ በሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች ነው።
የራያ እና የኣክሱም ዩኒቨርሲቲዎች የማካካሻ እና የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጧቸውን ተማሪዎች ባለፉት ቀናት የተቀበሉ ሲሆን ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ እና ነገ ይቀበላል።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የሚቀበልበትን ቀን በቅርብ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ፎቶ፦ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ