TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ መግለጫው ምን አለ ? በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት…
" በተጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል " - የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

ሁሉም ብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 /2015 ዓ/ም ለተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በድጋሜ ጥሪውን አስተላለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት ፤ በትግራይ ክልል በአክሱም  ርእሰ አድባራት ወገዳማት ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16/2015 ዓ/ም ኢቀኖናዊና ሕገወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደተፈፀመ በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለመምከር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ/ም መጠራቱ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያኗ የገጠማት ፈተና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ምክክር እንዲደረግበት የተጠራ አስቸኳይ  ምልዓተ ጉባኤ መኖሩ ቢታወቅም አንዳንድ ብፁዓን አባቶች ግን ከወዲሁ በተለያየ ምክንያት #እንደማይካፈሉ እየገለጹ ይገኛሉ ተብሏል።

ከአቅም በላይ ያጋጠመ ችግር ቢኖርም እንኳ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ጉዳይ የሚበልጥ ባለመኖሩና የቤተ ክርስቲያን ቀኖናና አንድነት በከፍተኛ ደረጃ ሲፈተን እያዩ በጉባኤው አለመገኘት የተጠሩለት የቤተ ክርስቲያን እውነትን የመጠበቅ ተልእኮ እንደመግፋት ስለሚያስመስል በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በተጠራው ቀን በጉባኤው እንዲገኙ በድጋሜ ጥሪ ተለልፏል።

በተጠራው ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ  አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳስቧል።

መረጃው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት / EOTC TV ነው።

@tikvahethiopia
@coopbankoromia
ግብይትዎን በኮፔይ ኢብር ያቅልሉ!
Download https://bit.ly/45f71CP
#ጥምረት . . የፊልም ፌስቲቫል . . ለሁሉም

ዩኤስኤይድ ከፕሮሎግ ማርኬቲንግ ጋር በመተባበር  ጥምረት የተሰኘ የፊልም ፌስቲቫል ከሐምሌ 25 እስከ 28 ድረስ ለዕይታ ያቀርባል።

📽 በአዲስ አበባ፦  የጣሊያን ባህል ማዕከል፣
📽 በአዳማ፦ ኦሊያድ ሲኒማ
📽 በባህር ዳር፦ ሙሏዓለም አዳራሽ ያካሂዳል።

ይኽ የፊልም ፌስቲቫል ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን የሚያንሸራሽሩበት መድረክ ጭምር በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል።

📣 መግቢያው #በነጻ ነው።

ቀድመው ይመዝገቡ ፦  https://forms.gle/wjNi3Dk5ssNpsZ9s7

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉  https://t.iss.one/TimretEth
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#የፀጥታ_ችግር

ዘላቂ ሰላም ያልተገኘለት እና ዛሬም ድረስ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው ቀጠና መፍትሄው ምንድነው ?

• ከ2010 ዓ/ም አንስቶ የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ንብረት ወድሟል። እርቅ ለመፈፀም ተሞክሮ ዘላቂ ሰላም አልመጣም።

• ከሰሞኑ በተፈፀሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ንብረት ወድሟል ፤ እርቅ ለመፈፀም ጥረት እየተደረገ ነው።

• ዛሬ ወደ ገበያ በሚያቀኑ ሰዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ ተጎድተዋል።

በደቡብ ክልል መን፤ በጉራጌ ዞን በመስቃን እና ማረቆ መካከል በተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግሮች እየተከሰቱ የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣ ንብረት ሲወድም ፣ ተማሪዎች ከትምህርት ሲስተጓጎሉ ፣ የመንግሥት ስራም ሲበደል በአጠቃላይ በቀጠናው ከፍተኛ ተፅእኖ ሲደርስ ቆይቷል።

በአካባቢው ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከዚህ ቀደም የዕርቅ ጥረቶች ተደርገውም ያውቃሉ።

ከሰሞኑን ደግሞ በዚሁ አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ጉዳትም ደርሷል።

አንድ ስለ ጉዳዩ አውቃለሁ ያሉ የቤተሰባችን አባል ፤ " መስቃን እና ማረቆ ባንተ ወረዳ ይሄን ያክል ቀበሌ አለኝ አንተ የለህም የኔነዉ ያለኝ ባንተ ወረዳ እየተባባሉ ግጭት ከተጀመረ ከ2010 ዓ.ም አንስቶ እስከ ዛሬዉ ቀን ሰዉ ከመሞትና ቤት ንብረት ከመቃጠልና ከመዘረፍ አልቆመም " ብለዋል።

እኚሁ የቤተሰባችን አባል ፤ በዞኑ እንዲሁም በክልሉ ያሉ አመራሮች ለችግሩ ምንም አይነት ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጡ እንዳልቻሉ ፤ ካቅማችን በላይ ነዉ ብለዉም ለከፍተኛ አካል ለፌደራል መንግስት የሰጡት / ያስረከቡት ነገር እንደሌለ አስረድተዋል።

ከሰሞኑንም በዚሁ ቀጠና ላይ የሰዎች ህይወት መቀጠፉን ንብረት መውደሙን አመልክተዋል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-29

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" ኢንፎኔት ኮሌጅ " ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞችን ሙሉ የትምህርት ማስረጃ እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንዲያስረክብ የአዲስ አበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሳሰበ።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ " ኢንፎኔት ኮሌጅ " በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በቴ/ሙ ዘርፍ እውቅና ፍቃድ በማግኘት ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ነገር ግን ኮሌጁ በባለስልጣኑ የእውቅና ፍቃድና እድሳት መመሪያ መሰረት ህጋዊ የቤት ኪራይ ውል ማቅረብ ባለመቻሉ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ #ፍቃድ_የሌለውና ፍቃዱም በባለስልጣን መ/ቤቱ #መሰረዙን ሚያዝያ 12/2014ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ እንዳሳወቀው አመልክቷል።

" ኮሌጁ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ስልጠና እየሰጠ አለመሆኑን " በቀን 11/11/2015 ዓ.ም በተፃፈው ደብዳቤ ቁጥር ኢንፎ/2910/15 ገልፀውልናል " ያለው መ/ቤቱ  ኮሌጁ ቀደም ሲል እውቅና ፍቃድ በነበረው ወቅት ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞችን ሙሉ የትምህርት ማስረጃ እስከ ነሐሴ 17 / 2015 ዓ.ም ድረስ እንዲያስረክብ ቀነ ገደበ አስቀምጠናል ብሏል።

ኮሌጁ በተቀመጠው ጊዜ ይህን መፈፀም ካልቻለ በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርገውም ባለስልጣን መ/ቤቱ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#ExitExam

ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚተገበረው አስገዳጅ መመሪያ ምን ይላል ?

(የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን)

" ከቀጣዩ ዓመት 2016 ዓ/ም ጀምሮ እያንዳንዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመውጫ ፈተና ከሚያስቀምጣቸው ተማሪዎች በየትምህርት መስኩ ቢያንስ 25 በመቶዎቹ ማለፍ ይጠበቅባቸዋል።

የግል ተቋማቱ 25 በመቶ ተፈታኞቻቸውን ማሳለፍ ካልቻሉ የትምህርት ፕሮግራሙ #ይሰረዛል

በተጨማሪም የትምህርት ተቋማቱ ለማስተማር የሚመዘግቧቸውን ተማሪዎች የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው። "

NB. ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ 72 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ውጤት ያመጡት 12,422 ወይም 17.2 በመቶ ብቻ ናቸው።

Credit : #FBC

@tikvahethiopia
#CBE

ኢትዮ-ዳይሬክት (EthioDirect)

• በሞባይል ስልክዎ
• የቪዛ እና ማስተር ካርድዎን በመጠቀም
• ያለምንም ክፍያ
• ከውጭ ሀገራት 
• ወደ ሀገር ውስጥ 
• ቀጥታ ወደተቀባዩ ሂሳብ 
• ገንዘብ የሚልኩበት የሞባይል መተግበሪያ!

#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ 
=============
የEthioDirect  መተግበሪያን ከPlay Store ወይም ከApp Store በማውረድ የአግልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ!

•  ለአንድሮይድ ስልኮች፡- https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
•  ለአይፎን ስልኮች፡- https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
#ሳፋሪኮም_ኢትዮጵያ

በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡትን የሳፋሪኮም ቲክቶክ ጥቅሎችን በመጠቀም አዳዲስ ቪዲዮዎችን እየሰራን ለምንወዳቸው ሰዎች እንላክ፣ ዘና ፈታ እንበል!
አሁኑኑ ወደ *777# በመደወል ጥቅላችንን እንግዛ!

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፊ አውደርዕይ

ከሐምሌ 24-ነሃሴ 24 'የዘወትሯ ኢትዮጵያ' በሚል ርዕስ ሀገራዊ የፎቶግራፍ አውደርዕይ ተዘጋጅቷል፡፡ የኢትዮጵያን አንድነትና የጋራ የአኗኗር ዘይቤዎች የሚያሳዩ የፎቶግራፍ ስብስቦችን ያዋቀረው ይህ የፎቶ ኤግዚቢሽን በአራት የተለያዩ ከተሞች የሚደረግ ይሆናል፡፡

በመጪው ሰኞ  ሐምሌ 24/2015 በባህር ዳር ከተማ በድምቀት የሚከፈተው ይህ የፎቶ ኤግዚቢሽን ለአምስት ተከትታይ ቀናት እስከ ሐምሌ 28/2015 አርብ ድረስ የሚዘልቅ ይሆናል፡፡

በቀጣይ ከነሃሴ 3-7/2015 - ድሬዳዋ ላይ ከዚያም ሐዋሳ ላይ ከነሃሴ 12-16/2015 መዳረሻውን አድርጎ ከነሃሴ 20 -24/2015 ደግሞ አዲስ አበባ ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

በተዘረሩት ቀናት ላይ በፎቶ አውደርዕዩ ላይ በመገኘት የዘወትሯን ኢትዮጵያ አብረውን ይቃኙ! ኑ! ግሩም ተሰጥኦ ባላቸው የፎቶ ባለሙያዎች የተቀነጨቡትን የማህበረሰባችንን ገጽታዎች በጋራ እንመልከት፣ በጋራ እናድንቅ!

#የዘወትሯኢትዮጵያ #ተጓዥየፎቶግራፍአውደርዕይ
ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ በኣካል ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ አደረገ።

ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ምከንያት ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል ሲያደርገው የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ፦

- ሶስተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የነበሩ መደበኛ (Regular) የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች፣ ሁሉም የሕክምና ትምህርት ክፍል (Medicine department) ተማሪዎች እና ሁሉም መደበኛ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ነሐሴ 2 እና 3 ቀን 2015 ዓ/ም ፤

- ሁሉም የክረምት(summer) ቅድመ-ምረቃና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ነሐሴ 4 እና 5 ቀን 2015 ዓ/ም፤

- ሁሉም የኤክስቴንሽን (Extension) ቅድመ-ምረቃና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ነሐሴ 6 እና 7 ቀን 2015 ዓ/ም ፤

- 1ኛና 2ኛ ዓመት የነበሩ መደበኛ (Regular) የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች መስከረም 10 እና 11 ቀን 2016 ዓ/ም፤

- በትግራይ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውጪ ተመድበው የመሄድ ዕድል ያላገኙ ወይም ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ኣስፈላጊ የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን በመያዝ ከላይ ከላይ በተገለፀው መሰረት በየተመደቡበት ግቢ በአካል በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎች ሪፖርት የሚያደርጉት የት ግቢ ነው ?

• ከሕብረተሰብ ሳይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ ተማሪዎች በስተቀር ሁሉም የዋና ግቢ ተማሪዎችና የዓድዋ ግቢ ተማሪዎች በኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ

• የጤና ሳይንስ ግቢ ተማሪዎችና ሁሉም መደበኛና ክረምት የሕብረተሰብ ሳይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ ተማሪዎች በኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ግቢ

• የኣከሱም ዩኒቨርሲቲ ሽረ ግቢ ተማሪዎች በሽረ ግቢ

@tikvahethiopia
መምህራኑ ወደ ተቋማቸው እንዲመለሱ ጥሪ ተደረገ።

በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ተመድበው የነበሩ የኣክሱም እንዲሁም የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህራን ወደ ተቋማቸው እንዲመለሱ ጥሪ ተደርጓል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ተቋርጦ የቆየውን ትምህርት ለመጀመር የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁን ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

በመሆኑም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ተመድበው የነበሩ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህራን የአገልግሎት ጊዜና የተከፈላቸውን ደመወዝ የሚገልጽ ክሊራንስ በመያዝ ከነሐሴ 10/2015 ዓ.ም በፊት ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በመመለስ ሪፖርት እንዲያደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

በተመሳሳይ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህራን ወደ ተቋማቸእ እንዲመለሱ ጥሪ ተደርጓል።

ዩኒቨርሲቲው ተቋርጦ የቆየውን ትምህርት ለመጀመር የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁን ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴርም ፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ተመድበው የነበሩ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህራን የአገልግሎት ጊዜና የተከፈላቸውን ደመወዝ የሚገልጽ ክሊራንስ በመያዝ ከነሐሴ 05/2015 ዓ.ም በፊት ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በመመለስ ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@tikvahuniversity
በጥምረት የፊልም ፌስቲቫል ምን ይቀርባል?

ከሐምሌ 25 እስከ 28 ድረስ የተዘጋጀው #ጥምረት የፊልም ፌስቲቫል በሀገራችን የሚገኙ የተለያዩ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ለማሳየት የተዘጋጀ ነው። በፌስቲቫሉ ላይ፥ ዘጋቢ ፊልሞች ይታያሉ፤ የፓናል ውይይቶችም ይካሄዳሉ።

በዚህ ዝግጅት ለሚሳትፉ #ሰርተፊኬት ይሰጣል። የሚመቾትን ቀን መርጠው በፊልም ፌስቲቫሉ ይሳተፉ፤ ሀሳቦትንም ያካፍሉ!

📽 በአዲስ አበባ ለምትገኙ በጣሊያን ባህል ማዕከል፤
📽 በአዳማ ለምትገኙ በኦሊያድ ሲኒማ፤
📽 በባህር ዳር ለምትገኙ ሙሉዓለም አዳራሽ በሮች ከ10 ሰዓት ጀምሮ ክፍት ይሆናሉ።

📣 መግቢያው #በነጻ ነው።

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉  https://t.iss.one/TimretEth

ቀድመው ይመዝገቡ ፦  https://forms.gle/wjNi3Dk5ssNpsZ9s7
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ሕገወጥ " እንደሆነ ገልጻ እንዲቆም ያሳሰበችው የትግራይ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተፈፀመ። " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " ዛሬ ሃምሌ 15 / 2015 ዓ.ም  በአክሱም ከተማ የኤጲስ ቆጶሳት በአለ ሲመት አከናውኗል። በዚህም ፦ 1. ንቡረ ዕድ መሓሪ - አቡነ ሊባኖስ 2. ቆሞስ…
በትግራይ የኤጲስ ቆጶሳት ሲመት ዛሬም ቀጥሎ ተከናወነ።

የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት የሚያከናውነው የጳጳሳት በዓለ ሲመት መቀጠሉ ተነግሯል።

ሃምሌ 9 /2015 ዓ.ም በኤጲስ ቆጶስነት የተሸሙት ሶስት አባቶች ሃምሌ 23 /2015 ዓ.ም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን የጳጳስነት መአርግ አግኝተዋል። 

በዚሁ መሰረት ፦

1. መልአከ ገነት አባ ዘርአዳዊት ብርሃነ  የነበሩት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ - ሊቀ ጳጳስ ዘሚኒሶታ ወዘኲሎን አድያሚሃ

2. መልአከ ፀሓይ አባ ዮሃንስ ከበደ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም -  ሊቀ ጳጳስ ዘአውሮፓ

3. መልአከ ፀሓይ አባ የማነብርሃን ወልደሳሙኤል የነበሩት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በመባል - ሊቀ ጳጳስ ዘዳላስ ቴክሳስ ወዘኲሎን አድያሚሃ በመባል ተሹመዋል። 

ሃምሌ 15 እና 16  / 2015 ዓ.ም  በአክሱም ከተማ በተካሄደው የኤጲስ ቆጶሳት በአለ ሲመት በክልሉ የሚያገለግሉ 6 ጳጳሳት መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የሃምሌ 23 /2015 ዓ.ም ጨምሮ የተሸሙት ጳጳሳት ቁጥር 9 ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት ፤ በትግራይ ክልል በአክሱም  ርእሰ አድባራት ወገዳማት ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16/2015 ዓ/ም ኢቀኖናዊና ሕገወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደተፈፀመ በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለመምከርና ለመወሰን አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ/ም መጠራቱ የሚታወስ ነው።

መረጃ በመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተሰናዳ ነው።

@tikvahethiopia