TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወይራ የወጣቶች መድረክ ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የተሰባሰቡ ወጣቶች ያሳተፈና በአገራዊ ሠላምና መግባባት ላይ ያላቸውን አስተዋጾ  እንዲገልጹ የተዘጋጀ መድረክ ነው። መድረኩ ሐምሌ 13– 14 በአዲስ አበባ ተካሂዶ ነበር። 

የፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ USAID ሚሽን ተጠባባቂ ምክትል ዳይሬክተር ቶማስ ሳል ስለ ፕሮግራሙ ንግግር ካደረጉ በኋላ የወይራ የወጣቶች መድረክ ተሳታፊዎች ለሀገራቸው ሰላም ያላቸውን ራዕይ የያዘውን ካንቫስ ሰላም ሚኒስቴር  ተረክቧል።

ያለፉት 2 ቀናት የወይራ ወጣቶች መድረክ የወጣቶችን ድምጽ በሰላምና በብሄራዊ መግባባት ግንባታ ሂደት ውስጥ ማካተት ያለውን ጠቀሜታ አጉልቶ አሳይቷል!

#ወይራ
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም
=========
ለትምህርት ቤቶች፣ ለመምህራን፣ ለተማሪዎች እንዲሁም ለወላጆች የጊዜው ውድ ስጦታ! በአዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም ስራዎን ያዘምኑ!

👉ትክክለኛውን የአዋሽ ባንክ ኢ-ስኩል ድረ-ግፅ ለማግኘት ይህንን ማስፈንጠሪያ (Link) https://eschool.awashbank.com/ ብቻ በመጠቀም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ!

አዋሽ ባንክ!
#Tigray

በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል የ " ቶጎጋ ሲሚንቶ ፋብሪካ አ/ማ " እና የ " ትግራይ ኢንቨስትመንት ትስስር መድረክ " ተካሂዶ ነበር።

በዚሁ መድረክ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተው ነበር።

አቶ ጌታቸው ፤ ጦርነት ያወደማትን ትግራይን መልሶ ለመገንባት የቶጎጋ ሲሚንቶ ፋብሪካ አ/ማ የትግራይን ህዝብ ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ፤ በመልሶ ግንባታ ስራ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ኡሁንም ድረስ በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት ከቄያቸው ተፈናቅለው ወደ ቄያቸው ያልተመለሱ በርካታ ዜጎችን በመደገፍ " ከጎናችን ሁኑ " ሲሉ በአስተዳደራቸው ስም ጥሪ አስተላልፈዋል።

በትግራይ በተካሄዳው ጦርነት ተፈናቅለው ፀሀይ እና ብርድ የሚፈራረቅባቸውን ወገኖች ለማገዝ በሚደረገው እንቅስቃሴ የድርሻውን ይወጣል ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

አሁን ላይ የሚታየው የሰላም ጭላንጭል ሙሉ በሙሉ በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች መስፈን የሚችልበት ስራ አሁንም እንደሚቀር ገልጸው ይህን ለማድረግ እንደሚሰራ አመልክተዋል።

የ " ተጎጋ ሲሚንቶ ፋብሪካ አ/ማ " ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል  በትግራይ በሲሚንቶ ምርት ለመሰማራት በቅርቡ የተቋቋመ አክሲዮን ማህበር መሆኑን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EOTC

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በክልል ትግራይ ጉዳይ ከተናገሩት ፦

" የኢፌዴሪ መንግሥት  ትናንት ተፈጥሮ በነበረው የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ችግር (ኦሮሚያ ላይ) በውይይትና በምክክር  በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲፈታ ማድረጉን ይታወሳል።

አሁንም በትግራይ  ክልል ባሉ የአህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት እየተከተሉት ያለውን መፍትሔ የማይሆነውን ችግር  በማስቆምና ሰላማዊ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ እምነታችን ነው።

ይህ ካልሆነ ግን በታሪክ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትን ማን ከፋፈለ ሲባል የፌደራልና የክልሉ መንግሥት የሚል የታሪክ ተወቃሽ ሆኖ በታሪክ የሚመዘገብ ይሆናል።

ስለሆነም ይህን በትግራይ ክልል ይፈጸማል የሚባለውን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገወጥ የሆነ ሹመት እንዲቆም ብሎም ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ በማመቻቸት ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች። "

(ብፅዕ አቡነ አብርሃም የሰጡት ቃል ከላይ ተያይዟል)

በትግራይ ያሉ ብፁአን አባቶች በትግራይ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከማዕከል ተነጥለው " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል።

በቅርቡ በኣክሱም በተካሄደው ስነስርዓት ለዛው ለትግራይ የሚመደቡ 5 እንዲሁም ለውጭ ሀገር 5 በድምሩ 10 የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ አካሂደው የነበረ ሲሆን በቀጣይ ሹመት ይሰጣሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስ በኣክሱም የተካሄደው ምርጫ አሁን እየተደረገው ያለው የሹመት እንቅስቃሴ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና ሕገወጥ ድርጊት መሆኑን በመግለፅ #እንዲቆም እያሳሰበ ነው።

የፌዴራል መንግሥት እና የትግራይ አስተዳደር የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዘንድሮ በመደበኛው 667 ሺህ 483 ፤ በግል፣ በማታ እና በርቀት 200 ሺህ 691 ተፈታኞች ፈተና ይወስዳሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ባለፈው ዓመት የተስተዋሉ የተለያዩ እንከኖች በዚህኛው ዓመት መስተካከላቸውን የትምሕርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። ምዝገባው በማንዋል በመሆኑ ተፈጥሮ የነበረውን የተፈታኞች መረጃ…
" ተፈታኞች በአካልም ይሁን በስነልቦና እራሳችሁን ዝግጁ አድርጉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሃ ግብርን ይፋ አድርጓል።

በዚህም ፥ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ 16 እና 17/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ይገባሉ።

ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም ገልጻ ይሰጣቸዋል።

ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ። ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ተማሪዎች ወደመጡበት ይመለሳሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች  ደግሞ ሐምሌ 22 እና 23/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ይገባሉ።

ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም ገለጻ ይሰጣቸዋል።

ከሐምሌ 25 እስከ 28/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።  ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ተማሪዎች ወደመጡበት ይመለሳሉ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን በሚውስዱበት ጊዜ የፈተናውን ህግና ስርዓት እንዲያከብሩ በጥብቅ አሳስቧል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ግልጋሎት ከሚሰጡ የፅህፈት መሳሪያዎች እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ እና ስክቢቶ ውጭ ወደ ፈተና ክፍል ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን እንዲያውቁት ብሏል።

ተማሪዎቹ ከቤታቸው ሲወጡ፦
- መታወቂያ ፣
- አድሚሽን ካርድ
- የት/ቤት ዩኒፎርም መያዛቸውን እንዳይረሱ ፤ ወላጆችም ይህንን እንዲያስታውሷቸው ጥሪ ቀርቧል።

ወደ መፈተኛ ተቋማት ቆሎ፣ ጭኮ፣ በሶ የመሳሰሉ ደረቅ ምግቦችን ይዞ መግባት የሚፈቀድ ሲሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ አይፓድ፣ ላፕቶፕ የመሳሰሉ እንዲሁም ማንኛውም ጌጣጌጥ ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተፈታኞች በአካልም ይሁን በስነልቦና እራሳቸውን ዝግጁ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን ይፋ መደረጉ አይዘነጋም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
ጊዜዎ ምን ያህል ውድ እንደሆነ በትክክል እንረዳለን። ፈጣን እና ምቹ በሆነው በኮፔይ ኢብር ነዳጅ በመሙላት ጉዞዎን ይቀጥሉ!
@coopbankoromia
#GashunaCoffee ☕️

Taste the beauty of nature
Our product is offered in various options ✔️ 1 kg ✔️ in 500 grams ✔️ in 250 grams ✔️ in 50 grams

Phone : +251-9-79-18-15-56| +251-9-03-91-92-93| +251-9-03-18-18-68| +251-9-88-80-82-02

Our products are available in supermarkets, mini markets and shops in our city. Take and enjoy the coffee
GASHUNA COFFEE
TASTE THE BEAUTY OF NATURE

www.gashunacoffee.com
Facebook: https://www.facebook.com/gashunacoffee
Join and share our pages
Thank You!!
#ምረቃ

በዛሬው ዕለት የተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ።

- ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
- ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
- ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
- አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ
- መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
- አርሲ ዩኒቨርሲቲ በየተለያዩ የትምህርት መስኮችና መርሀ ግብሮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው።

@tikvahethiopia
በአሜሪካን ሀገር ሚኖሳታ የሚገኘው  " ኢስላሚክ ዩንቨርስቲ " ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ሸይህ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ እና ለአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይህ ሱልጧን ሐጅ አማን የክብር ዶክትሬት አበረክቶላቸዋል።

የክብር ዶክትሬት ዲግሪውን ያጎናጸፉት የኢስላሚክ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር  ወሊድ እድሪስ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የደረሰን መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ፤ የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በወሰነው ውሳኔ ዛሬ ለሁለት ኢትዮጵያውያን የክብር ዶክትሬት ያበረክታል። የክብር ዶክትሬት የሚበረከትላቸው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሸይህ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ እንዲሁም አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ መሆኑን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia