TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ወይዘሮ_እህተ_በቀለ #ዮርዳኖስ_ወሮታው👏

" አራት ዓመት ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ በማዕረግ አስመርቄያለሁ " - ወይዘሮ እህተ በቀለ

ወይዘሮ እህተ በቀለ ይባላሉ። ልጃቸው ዮርዳኖስ ወሮታው አካሏን በራሷ ማንቀሳቀስ የማያስችል ጉዳት አለባት።

ዮርዳኖስ በእናቷ ድጋፍ ዛሬ ትምህርቷን አጠናቃ ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ከሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል #በማዕረግ ተመርቃለች፡፡

እናት አህተ ፤ " አራት ዓመት ሙሉ ልጄን በዊልቸር እያመላለስኩ አስተምሬ አጠናቅቄያለሁ። አራት ዓመት ለእኔ እንደ አራት ቀን ነው። ምንም አልተሰማኝም ደስ ብሎኝ አልፏል" ብለዋል።

በአራት ዓመት የትምህርት ቆይታዋ የሚሰጣትን ትምህርት ክፍል ውስጥ አብረዋት ቁጭ ብለው እየጻፉላት እንዳስተማሯት እናት ለኢፕድ ተናግረዋል።

" ዮርዳኖስ የማንበብ ችሎታዋን እወድላታለሁ። ያነበበችውን አለመርሳቷንና አስተዋይነቷን እወድላታለሁ፤ ልጄ ትጉህ ናት " ሲሉ ገልጸዋል።

ዮርዳኖስ እስከ 12ኛ ክፍል በሞግዚት ድጋፍ የተማረች መሆኑን ጠቅሰው እንደምትችል መታየት አለበት ብዬ አራት ዓመት በዩኒቨርሲቲ አብሬያት ዘልቀናል ብለዋል፡፡

አትችልም የተባለች ልጅ ለዚህ በመብቃቷ ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቅሰው፤ የእርስዋ ብርታት እንደ ልጃቸው ቤት ለተዘጋባቸው ልጆች አርአያ የሚሆን መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

መኖሪያ ቤታቸው ከዮኒቨርሲቲው ራቅ ያለ በመሆኑ ጠዋት 12 ሰዓት ተነስተው ለአራት ዓመታት ልጃቸውን ወደ ትምህር ገበታዋ በዊልቸር በማመላለስ ለምረቃ ያበቁት እናት ዛሬ ደስታቸው እጥፍ ድርብ ሆኖ ታይተዋል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶንያ መስራች አቶ ቢንያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ( #ጂጂ ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል። አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ ላከናወኗቸው በጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል። በሰሩት ስራ በሰው ልጆች…
#AAU #DrBinyamBelete😢

ዛሬ ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው የሜቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ በመድረኩ ላይ ንግግር አድርገው ነበር።

ያደረጉት ንግግር እጅግ ስሜትን የሚነካ ስለነበር ተመራቂዎች እና ታዳሚያንን #እያለቀሱ ሲያዳምጡ ነበር።

አቶ ቢንያም በለጠ ምን አሉ ?

" ...ለእኔ ብዙ ትልቅ ቦታ አትስጡኝ ፤ እኔ የማልረባ ሰው ነኝ ፤ ቅድም ስለእኔ ስትገልፁ ከብዶኛል።

እውነቴን ነው እግዚአብሔር ይሰራል እሱን አልክድም ሜቄዶንያ ላይ ፤ ምክንያቱም ካለምንም እርዳታ ይሄን ሁሉ ሺህ ሰው በሀገር ውስጥ በየቀኑ አንድ ሚሊዮን የእግዚአብሔርን ስራ መሆኑ ግልፅ ነው በጣም።

እኔኮ በሽተኛ ነኝ ሲጀምር ብዙ ጊዜ ተኝቼ ነው የምውለው ፤ ስራ ያቆምኩ ሰው ነኝ እኔ እንደውም የህብረተሰብ ሸክም መሆን ያለብኝ ሰው ነኝ እውነት ለመናገር።

እንደ እኔ አይነት ሰው ዝም ብላችሁ ብታስቡት እንኳን እንደዚህ ለማድረግ ይቅርና እራሴንም ለመቻል ወይ አግብቶ ወልዶ ለመኖር ሰው ለመርዳት ቀርቶ ለመለመን እንኳን አንድ ሰው ጤነኛ መሆን አለበት ፤ ለመለመን ወጣ ብሎ አንድ ቦታ መቀመጥ አለበት እኔ መቀመጥም አልችልም።

ለመኖር እራሱ የማይገባኝ ሰው ነኝ ፤ በእግዚአብሔር ኃይል ነው ያለሁት ፤ እውነቴን ነው የምነግራችሁ ቀልዴን አይደለም። አንድ ሰው ለመለመን መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ ሰው መጠየቅ አለበት አይደል እንደዛ እንኳን የምችል ሰው አይደለሁም። ስለዚህ እግዚአብሔር ነው የሚሰራው።

አንድ የህብረተሰብ ሸክም የሆነ ሰው ፤ እግዚአብሔር ምን ያህል ሃጥያተኛ ሰዎችን በመንፈስም በስጋም ደካማ የሆኑ ሰዎችን እንዴት መርዳት እንደሚችል አንዳንድ ሰዎች በቤተሰብ፣  በትዳር፣ ወይ ሰው አስቀይሟችሁ እንደው እግዚአብሔርን የለም ብላችሁ/ እግዚአብሔር ረሳኝ ብላችሁ ከሆነ እግዚአብሔር እንደዚህ ይሰራል። በማይረቡ ሰዎች፣ በተራ በጣም በወንጀለኛ ሰዎች መስራቱን ስታዩ ሁሉንም ሰው እግዚአብሔር እንደሚረዳ የሚያሳይ ነገር ነው።

ክብር ዶክትሬት ተብሏል ፤ እኔ ትንሽ ከብዶኛል በጣም ምክንያቱም እናተ ሸልማችሁኛል ፤ የእግዚአብሔር ፍርድ ደግሞ ከባድ ነው እውነት የእግዚአብሔር ፍርድ በጣም አስፈሪ ነውና ከሲኦል እንድድን እግዚአብሔር ከዚያ እንዲያወጣኝ ፀሎት አድርጉልኝ የእውነት። ይሄ በጣም ከባድ ነገር ስለሆነ ነው። ቀልድ አይደለም እግዚአብሔር ዝም ብለን ሃጥያት ስንሰራ ዝም የሚለን አምላክ አይደለም። የእግዚአብሔር ፍርድ ከባድ ነውና እኔ የምፈራው እሱን ነው እንኳን ልሸለም ለፍርድ እንዲቀልልኝ የማስብ ሰው ነኝ።

ሜቄዶንያ ላይ ብዙ ሰው አስተዋጽኦ ያደርጋል። እኔ የተለየ አስተዋጽኦ የለኝም ከዛ ያነሰ ነው የእኔ አስተዋፅኦ። በሽተኛ ስለሆንኩኝ ስራም ስለሌለኝ አንደኛው ተደጓሚ ነኝ እራሴ በመቄዶንያ ነገር ግን መቄዶንያ ባልፉት ዓመታት እዚህ ለመድረስ ብዙ አስተዋፅኦ ያደረጋችሁ ሰዎች አላችሁ ምስጋናም ክብርም የሚገባው ለእናተ ነው።

ተማሪዎች፣ ወጣቶች ፣በጎፍቃደኞች፣ የመንግሥት ኃላፊዎች፤ የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ፣ ሚኒስትሮች ፣ ኮሚሽነሮች፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ሁሉም ሜቄዶንያን አግዘዋል በየቢሮው ያስተናግዱናል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የክልል መስተዳደሮች በሙሉ፣ ለሜቄዶንያ እዚህ መድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። "

(የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶንያ መስራች አቶ ቢንያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ( #ጂጂ ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል። አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ ላከናወኗቸው በጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል። በሰሩት ስራ በሰው ልጆች…
" ይሄ ለእኔ የሚገባኝ አይደለም። ግን ስላከበራችሁኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ " - እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)

እጅግ ተወዳጇ አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተበረከተላትን የክብር ዶክትሬት በተመለከተ መልዕክት አስተላልፋለች።

ምን አለች ?

እጅጋየሁ ሽባባው ፦

" እምዬ ሀገሬ ፤ ውድ ሀገሬ ኢትዮጵያ እንዲሁም በጣም የምወዳችሁ የማከብራችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሰላም ሰላም ሰላም ብያለሁ።

በአክብሮት የሰጣችሁኝን የአክብሮት ዶክትሬት በጣም በትልቅ ደስታ ነው የተቀበልኩት ፤ በጣም አመሰግናለሁ፤ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

እኔ በጣም በጣም ነው የገረመኝ ታጭቼ ብገኝ እንኳን የሚያስደንቀኝ ነበር ተመርጬ ስለተነገረኝ በጣም ነው የማመሰግነው፤ እግዚአብሔር ያክብርልኝ።

ፍቅራችሁ እንዲሁ አክብሮታችሁ ስለሆነ በእኔና በወገኖቼ ስም እንዲሁም በዚህ ሁሉ ደስ በሚላቸው ኢትዮጵያውያን ስም ከልቤ በጣም በጣም አመሰግናለሁ።

እግዚአብሔር ህይወታችሁን ይባርከው ፣ የኢትዮጵያ ዛሬ ያሉትን #ተማሪዎች እንዲሁም የወደፊቱን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክ፣ ሀገራችንን መንፈስቅዱስ ይጠብቅልን።

ያስቸግራል ለመግለፅ ደስታዬን ፤ በጣም አመሰግናለሁ፣ ፍቅራችሁና ክብራችሁ ከልክ ያለፈ ነው ፤ ለእኔ የሚገባኝ አይደለም። ግን ይሄን ሁሉ ስላከበራችሁኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

የኢትዮጵያን ህዝብ እግዚአብሔር ይጠብቅልን ፤ ምስጋናዬ በጣም ከፍ ያለ ነው፤ በአካል ተገኝቼ አንድ ቀን እዛ መጥቼ አያችኃለሁ ፤ በሰላም ቆዩኝ ይሄንን አጭር መልዕክቴን ይቅር በሉኝ ፤ በደንብ አድርጌ ሌላ ቀን አመሰግናችኃለሁ ፤ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

እጅጋየሁ ነኝ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው። በዛሬው ዕለት በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ። ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦ - ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ) - ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ) - አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ዋናው ግቢ) - ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ - ጂንካ ዩኒቨርሲቲ - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ…
ምን ያህል ተማሪዎች ተመረቁ ?

ዛሬ ብቻ ከ53,582 በላይ ተማሪዎች ተመርቀዋል።

ዛሬ ከ28 የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) ብቻ ከ53,582 በላይ ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች፣ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተመርቀዋል።

- አዲስ አበባ ፦ 8,642 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 5,121 ፣ በ2ኛ ዲግሪ 3,221 ፣ በ3ኛ ዲግሪ 300)

- ሀዋሳ ፦ 7,571 ተማሪዎች (ቅድመ እና ድህረ ምረቃ)

- አምቦ ፦ 4,036 ተማሪዎች (ቅድመ ምረቃ 2,829 ፣ 1207 ድህረ ምረቃ ፣ 3 Phd ፣ 21 የህክምና ዶክተር)

- መደ ወላቡ ፦ 4,017 ተማሪዎች (በቅድመ እና ድህረ ምረቃ)

- ዋቸሞ ፦ 2,276 ተማሪዎች (በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በከፍተኛ ዲፕሎማ)

- ደብረ ብርሃን ፦ 2,147 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 1692 ፣ 2ኛ ዲግሪ 448 ፣ Phd 3 ፤ PGDT 4)

- ጅማ ፦ 2,124 ተማሪዎች (1,835 የቅድመ ምረቃ ፣ 282 ድህረ ምረቃ 7 ፒ.ኤች.ዲ)

- ደብረ ማርቆስ ፦ ከ2 ሺህ በላይ (በመጀመሪያ ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ)

- ዲላ ፦ 1,829 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 1,590 ፣ ሁለተኛ ዲግሪ 100 ፣ ሶስተኛ ዲግሪ 2 ፣ HDP 137)

- አርባ ምንጭ ፦ 1,457 (በቅድመ ምረቃ 859 ፣ በ2ኛ ዲግሪ 586 ፣ በ3ኛ ዲግሪ 12)

- ወልድያ ፦ 1,376 ተማሪዎች (በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ)

- ወለጋ ፦ 1,347 ተማሪዎች (976 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 350 በሁለተኛ ዲግሪ፣ 21 በሶስተኛ ዲግሪ)

- ሰመራ ፦ 1,309 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 1,104 ፣ በሁለተኛ ዲግሪ 190)

- ቡሌ ሆራ ፦ 1,299 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 907 ፣ 2ኛ ዲግሪ 392)

- አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፦ 1,236 ተማሪዎች (በመጀመሪያና በ2ኛ ዲግሪ ፣ በPhd)

- ደብረ ታቦር ፦ 1,202 ተማሪዎች (በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ)

- ሚዛን ቴፒ ፦ 1,285 ተማሪዎች

- ወልቂጤ ፦ 1,195 ተማሪዎች (በቅድመ ምረቃ 1,112 ፣ በድህረ ምረቃ 83)

- ወላይታ ሶደ ፦ 1129 ተማሪዎች (ባችለር ዲግሪ 374፣ ማስተርስ 743 ፣ ስፔሻሊቲ 11 ፣ ዶክትሬት 1)

- ጅግጅጋ ፦ 1,090 ተማሪዎች (808 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 282 ሁለተኛ ዲግሪ፣ 34 የእስሳት ህክምና ዶክተሮች)

- ቀብሪ ድሃር ፦ 885 ተማሪዎች (በመደበኛ 818 ፣ በ2ኛ ዲግሪ 67)

- ሰላሌ ፦ 855 ተማሪዎች (የመጀመሪያ ዲግሪ 617 ፣ 238 ሁለተኛ ዲግሪ)

- እጅባራ ፦ 750 ተማሪዎች (በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በከፍተኛ ዲፕሎማ)

- ወራቤ ፦ 720 ተማሪዎች (በመጀመሪያ ዲግሪ 632 ፣ በ2ኛ ዲግሪ 88)

- መቱ ፦ 647 ተማሪዎች (በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ)

- ጂንካ ፦ 501 ተማሪዎች

- ደባርቅ ፦ 374 ተማሪዎች

- ኦዳ ቡልቱም ፦ 283 ተማሪዎች (በአንደኛ እና ሁለተኛ ዲግሪ)

በድምሩ የዘረዘርናቸው የመንግሥት ተቋማት ዛሬ ያስመረቁት ከ53,582 በላይ ተማሪዎችን ነው።

ተቋማቱ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እና በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቁት።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia @tikvahuniversity