TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.35K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ ያሉ በትግራይ የሚገኙ አባቶች ለሃምሌ 9/11/2015 ዓ.ም በርእሰ አድባራት ወ ገዳማት ቅድስት ከተማ አክሱም  ፅዮን ለሚያካሂደው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከየሃገረስብከቱ 12  ፤ ከካሳቴ ብርሃን መንበረ ሰላማ መንፈሳዊ…
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ ብፁዓን አባቶች የሚፈፀም የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ በመሆኑ እንዲቆም ውሳኔ ቢያሳልፍም የኤጲስ ቆጶሳቱ ምርጫ ግን ዛሬ ተካሂዷል።

በትግራይ ያሉ ብፁዓን አባቶች ፤ በትግራይ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከማዕከል ተነጥለው " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል።

ዛሬ በኣክሱም በተካሄደው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ በተሰጠው ድምፅ ለምርጫ ከቀረቡ ብፁአን አባቶች መካከል በተሰጣቸው ድምፅና ቆጠራ መሰረት ምርጫ ተፈፅሟል።

በዚህም ፦
1. መጋቤ ሃዲስ ቆሞስ ኣባ ዘስላሴ ማርቆስ
2. መልኣከ ገነት ቆሞስ ኣባ ሃ/ሚካኤል ኣረጋይ
3. ሊቀ ኣእላፍ ኣባ እስጢፋኖስ ገ/ጊዮርጊስ
4. ንቡረ እድ ቆሞስ ኣባ መሓሪ ሃብቴ
5. ቆሞስ ኣባ ኤልያስ ታደሰ ገብረኺዳን በሀገር ውስጥ (በትግራይ) የሚያገለግሉ ኤጲስ ቆጶሳት ሆነው መመረጣቸው ተገልጿል።

1. ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደሳሙኤል
2. መልኣከ ገነት አባ ፅጌ ገነት ኪዳነ ወልድ
3. አባ ዘርኣ ዳዊት ብርሃነ
4. መልአከ ፀሃይ አባ የማነ ብርሃን ወልደሳሙኤል
5. መልአከ ፅሓይ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ከበደ ከአገር ውጭ የሚያገለግሉ ኤጲስ ቆጶሳት ሆነው መመረጣቸው ተነግሯል።

የኤጲስ ቆጶሳቱ ምርጫ ላይ የተሳተፉት አባቶች ፣ ታዛቢዎች ፣ ሌሎች የምዕመናን ሲሆኑ #በካርድ ለኤጲስ ቆጶሳትነት ከቀረቡት እጩዎች መካከል ምርጫ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስ የዛሬው ምርጫ ከመካሄዱ ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ፤ የኤጲስ ቆጶሳቱ ምርጫ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

በተጨማሪ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙ ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹ ጥሪ ቀርቦ ነበር።

ፎቶ ፦ ቴሌቪዥን ትግራይ / ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
👍1.15K👎750134😢100🕊25🥰19🙏4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው " - ቅዱስ ፓትርያርኩ

ቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን " ራስን በራስ የመሾም " አባዜ መገታት አለባቸው ሲሉ አሳሰቡ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ  ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ በተካሄደው ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ስርዓት ላይ ንግግር አሰምተው ነበር።

በንግግራቸው ላይም ፤ " በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው " ብለዋል።

" ማንኛውም ችግር በውይይትና በምክክር የተበደለውንም በትክክል በመካስ መፈታት ይገባዋል! " ያሉት ቅዱስነታቸው " ከዚህ ውጭ በጥፋት ላይ ጥፋት እየተከሠተ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚፈታተን ድርጊት ማቆም አለብን " ሲሉ አሳስበዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ቀኖና ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ባደረገው ጥረት፣ እንደዚሁም ኦርቶዶክሳዊው ሕዝበ ክርስቲያን ባቀረበው አቤቱታ ከዚህ ቀደም የተፈጸመው የቀኖና ጥሰት ታርሞ በዛሬው ዕለት ትክክለኛውን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ቀኖናዊ ሕግን የጠበቀ ሥርዓተ ሢመት መከናወኑን የገለፁት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህ በመሆኑ " ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን " ብለዋል።

" ለወደፊትም ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን አንድነት በሚጠቅም ጉዳይ ሁሉ ፤ በዚህ ዓይነት በውይይትና በምክክር ብቻ እየፈታን ሕዝባችን በመንፈስና በልማት የሚያድግበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በጋራ እንድንሰራ ጥሪያችንን እያቀረብን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።

(የቅዱስ ፓትርያርኩ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)

ፎቶ ፦ EOTC TV

@tikvahethiopia
👍2.48K👎380263🕊79😢62🙏25🥰22😱13
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የመውጫ ፈተና ውጤት እየታየ ይገኛል።

በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተመራቂ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ረፋድ ጀምሮ እየተመለከቱ ይገኛሉ።

ውጤቱ መታየት ከጀመረበት ሰዓት አንስቶ ለረጅም ሰዓታት በመንግስት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ብቻ ውጤታቸውን ማየት የቻሉ ሲሆን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ደግሞ #ከምሽት አንስቶ ውጤታቸውን ማየት ጀምረዋል።

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ " ውጤት መመልከቻው ድረገፅ ላይ ገብተው username ሲያስገቡ የሚያገኙት ምላሽ የተቋማቸው " የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም " የሚል እንዲሁም የአንዳንዶቹ " ያስገቡት ስም የማይሰራ " መሆኑን የሚገልፅ ነው።

ውጤታቸውን የተመለከቱ በርካታ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ደግሞ 50 እና ከዚያ በላይ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ቢሆንም " fail / ወድቀዋል " የሚል ምላሽ እያገኙ መሆኑን በመግላፅ ትምህርት ሚኒስቴር በሲስተሙ ላይ ያለውን ችግር #እንዲያስተካክል ጠይቀዋል።

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፤ የመውጫ ፈተና የተቀመጡት 72,203 ተማሪዎች ሲሆኑ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተው ያለፉት 12,422 ተማሪዎች ወይም 17.2 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ፤ በመውጫ ፈተና አመርቂ ውጤት ካልተመዘገበባቸው / እጅግ በርካታ ተማሪዎች ከወደቁባቸው የትምህርት ክፍሎች አንዱ የ " Accounting and Finance " ሲሆን በፈተናው ላይ  ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች የፈተናው ምዘና ድጋሚ እንዲፈተሽ ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ የ " Information Technology " ተማሪዎችም መሰል አቤቱታ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ የተሰጠው ፈተናው ከነበረው ዝግጅት ጋር የሚራራቅ እንዲሁም ደግሞ ከ ተሰጣቸው ' ብሉለሪንት ' ጋር የማይቀራረብ በመሆኑ ሚኒስቴሩ እንዲያይላቸው አቤቱታ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም የ ' መካኒካል ምህንድስና ' ተመራቂ ተማሪዎች ከፈተናው ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ማቅረባቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ወይም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ተማሪዎችን #ቅሬታ የሚያስተናግዱበት መንገድ ካለ ጠይቆ የሚያሳውቅ ይሆናል።

#ማስታወሻ ፦ የመውጫ ፈተና ውጤት የሚታየው በ result.ethernet.edu.et ላይ Username በማስገባት ነው።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
👍2.05K👎314251😢109😱41🕊35🙏33🥰28👏4
#ሳፋሪኮም_ኢትዮጵያ

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

#UnlimitedSafaricom
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
👍18537👎10🥰3👏2🙏2🕊2
#ኤክሶደስ

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ!

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት፤ አድራሻችን 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን። ስልክ ቁጥር 0979099909/ 0911039377
  √በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
👍10233👎11🙏8
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በመላ ሀገሪቱ በአንድ ቀን ውስጥ 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ ከጥዋት አንስቶ እየተካሄደ ይገኛል።

ዘመቻው እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ እንደሚቆይ ነው የተነገረው።

በችግኝ ተከላ ዘመቻው ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ እናቶች ፣ ህፃናት፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች፣ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች እና ሌሎችም እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ስራ የፖለቲካ ጉዳይ ፣ የፓርቲያቸው ፕሮግራም እንዲሁም የመንግሥት ጉዳይ እንዳልሆነ ከዚህ ቀደም ገልጸዋል።

ይህ ጉዳይ " የኢትዮጵያ ጉዳይ " እነደሆነና በዚህ የችግኝ ተከላ ዘመቻ አረንጓዴ የምትለብሰው ኢትዮጵያ መሆኗን ፤ ትርፉም ከእኛ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ መሆኑን አስረድተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፦
- ተራሮች፣
- የወንዝ ግራና ቀኞች፣
- የመንገድ አካፋዮች፣
- የመኖሪያ ቤት ግቢዎች፣
- የሠፈሮች ባዶ ሥፍራዎች፣
- የቤተ እምነቶች ቅጽረ ግቢዎች፣
- የየትምህርት ቤቱ እና የየመሥሪያ ቤቱ ግቢዎች፣
- ለግብርናና ለእንስሳት ግጦሽ የማይውሉ መሬቶች ሁሉ በደን መሸፈን እንዳለባቸው በማስገንዘብ ለዚህ ስራ ሁሉም ያለ ልዩነት ሊሳተፍና ሀገሩን አረንጓዴ ሊያለብስ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
👎1.46K👍732108🕊20🙏8😢6🥰5😱5