TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በትግራይ ያሉ አባቶች የፊታችን ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ/ም በቅድስት ከተማ አክሱም ፅዮን የኤጲስ ቆጾሳት ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።

በክልሉ ለሚገኙ ሚዲያዎችም በስነስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ጥሪ መቅረቡን ለማወቅ ተችሏል።

በትግራይ ያሉ አባቶች ከማዕከል በመነጠል " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤቤተክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል።

ከዚህ ቀደም የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንደሚያካሂዱ ያሳወቁት በትግራይ ያሉት አባቶች በአካሄዳቸው ፀንተውበት የፊታችን እሁድ በርእሰ አድባራት ወ ገዳማት ቅድስት ከተማ አክሱም ፅዮን የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እናካሂዳለን ብለዋል።

በርእሰ አድባራት ወ ገዳማት ቅድስት ከተማ አክሱም ፅዮን በሚከናወነው ምርጫ 10 ኤጲስ ቆጶሳትን እንደሚመርጡ ነው ያሳውቁት።

በትግራይ ያሉት ብፁዓን አባቶች ከቀናት በፊት ቅዱስ ፓትርያርኩ እና የሰላም ልዑካቸው ለውይይት ወደ መቐለ በተጓዘበት ወቅት ሊያገኟቸው ፣ ለመነጋገር ፣ አቀባበልም ሆነ አሸኛኘት ሊያደርጉላቸው ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ያሉ አባቶች ቤተክርስቲያኗ ሕገወጥ ያለቸውን የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ማድረጋቸውን ተከትሎ የሰው ህይወት ያለፈበት ፣ የተጎዳበት እና በርካቶች ለእስር የተዳረጉበት ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሶ እንደነበር ፤ በኃላም ችግሮች በብዙ ውይይት መስመር መያዛቸው የሚዘነገ አይደለም።

@tikvahethiopia
#EOTC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ፤ ዛሬ በይፋዊና በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ያወጣው " የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ "ን የተመለከተ መረጃ ግርታን ፈጥሯል።

መምሪያው ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እና በአዲስ አበባ አቅራቢያ ያሉ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ለሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት በቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ለአስቸኳይ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲገኙ መጥራቱን ይገልጻል።

ነገር ግን ይህን መረጃ ያሳወቀው ዛሬ ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ/ም ነው።

ስብሰባው ለትላንት (ረቡዕ) የተጠራ መሆኑን የሚገልፁ የተለያዩ መረጃዎች በትላንትናው ዕለት ወጥተው ነበር።

መምሪያው ጉባኤው ትላንት ተደርጎ እንደሆነ እና ስለ ተላለፈው ውሳኔ አልያም ያወጣው መረጃ የቀን ስህተት ያለበት መሆኑና ዛሬ የሚደረግ ጉባኤ እንደሆነ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

መምሪያው ባሰራጨው መረጃ ላይ ፤ የቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ እንዲተላለፍ ውሳኔውን ያሳለፈው  በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ባሳለፍነው ሰኞ ወደ ትግራይ ክልል ለእርቀ ሰላም ጉዳይ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የተጓዘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልዑካን ቡድን የገጠመውን እክል ከገመገመ በኋላ አሁን ያለው የቤተክርስቲያኗን ወቅታዊ ሁኔታ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውይይትና ውሳኔ እንደሚያስፈልገው በማመኑ ነው ብሏል።

በአስቸኳይ ጉባኤ ላይ በሚደርሰው ስምምነት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አህጉረ ስብከት ያሉ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሊጠሩ እንደሚችሉ ተገልጿል።

የመምሪያው መረጃ እስካሁን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ያለ ሲሆን አስቸኳይ ጉባኤው ትላንት ስለመደረጉ አልያም የወጣው መረጃ የቀን ስህተት ኖሮበት ዛሬ የሚደረግ ስለመሆኑ የተደረገ ማስተካከያ የለበትም።

(መምሪያው ያሰራጨው መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
የጤና ባለሞያዋን #ገድሎ የተሰወረው የቀድሞ ፖሊስ አባል የነበረ ግለሰብ እየተፈለገ ነው።

በቋራ ወረዳ ገለጉ ዙሪያ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ሽመል ዕግር " እየተባለ በሚጠራው ቦታ ትላንት በግምት ከረፋዱ 4:00 ላይ ወ/ሪት ቁብስ በየነ የተባለችን የጤና ኤክስቴሽን ባለሙያ ገድሎ የተሰወረ ግለሰብ እየተፈለገ ይገኛል።

ግለሰቡ ፤ በሰው መግደል ወንጀል ተጠርጥሮ የወንጀል አቤቱታ የቀረበበት ቢሆንም የመንግስትን የጦር መሳሪያ እንደያዘ ከአካባቢው የተሰወረ ሲሆን ተጠርጣሪውን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የማህበረሰቡ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ተብሏል።

አዱሱ ጌታነህ የተባለው ይኸው ተጠርጣሪ ፤ የወረዳው ፖሊስ አባል የነበረ ሲሆን በመልክ ፀይም ፤ ቁመቱ መካከለኛ ፤ ሰውነቱ ቀጭን፣ ለመጨረሻ ግዜ ለብሶ የታየው ነጭ ሸሚዝና ስማያዊ ሱሪ መሆኑን የቋራ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አሳውቋል።

ተጠርጣሪውን አየሁ የሚል ወይም አድራሻውን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለቋራ ወረዳ ስላምና ፀጥታ ጽ/ቤት እንዲሁም ለቋራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ጥቆማውን እንዲሰጡን ጥሪ ተላልፏል።

ስልክ፦ 0582710038 የቋራ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት / 0582710062 የቋራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት

@tikvahethiopia
" ተዘግተዋል "

በአዲስ አበባ የሚገኙ 12 ትምህርት ቤቶች ተዘጉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዋጅ 74/2014 በተሠጠው ተግባርና ኃላፊነት መሠረት የግል ት/ቤቶችን ለደረጃው በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ለተቋማት ፍቃድና እድሳት ይሰጣል፣ ስታንዳርዱን ያላሟሉና የህግ ጥሰት የፈጸሙ ተቋማት ላይ እርምጃ ይወስዳል፡፡

በዚህም በከተማው ውስር ያሉት ፦

1. አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛ - አቃቂ
2. ዜድኤም ቅድመ አንደኛ -አቃቂ
3. ግሎው ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ
4. ኤልሻዳይ ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ
5. ሰቆሬብርሀን ቅድመ አንደኛ - ንፋስ ስልክ
6. ማይድሪም ላንድ ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ
7. ቲፒፋይ ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ
8. ሮማናት ቅድመ አንደኛ - ንፋስ ስልክ
9. አዲስ ቪዥን ቅድመ አንደኛ -ቦሌ
10. አዲስ ቪዥን የመጀመሪያ ደረጃ - ቦሌ
11. ኢልመኑር ቅድመ አንደኛ -ኮልፌ ቀራንዮ
12. ስትራይቨርስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት - ንፋስ ስልክ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለደረጃው በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ተመዝነው የሚጠበቀውን መስፈርት ማሟላት ባለመቻላቸውና ከደረጃ በታች በመሆናቸው መዘጋታቸውን አሳውቋል።

ተቋማቱ በእውቅና ፍቃድና እድሳት መመሪያ ቁጥር 02/2012 እና ከደረጃ በታች የሆኑ ተቋማትን ለማሸግ በወጣው መመሪያ 01/2014 መሰረት ነው እንዲዘጉ ውሳኔ የተላለፈባቸው።

ት/ቤቶቹ ለ2016 ዓ/ም ማስተማር የማይችሉ ሲሆን ትምህርት ቤቶቹ የተማሪዎችን ውጤት የሚገልጽ መረጃ ለተማሪዎችና እውቅና ፍቃድ ለስጣቸው አካል እንዲያስረክቡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ በተማሪዎችና በተማሪ ወላቾች ላይ ለሚፈጠር እንግልት ት/ቤቶቹ ተጠያቂ ይሆናሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ #አዲስአበባ

ከመገናኛ ወደ ላምበረት በሚወስደው መንገድ እስራኤል ኤምባሲ አካባቢ የመሬት መንሸራተት በመከሰቱ ምክንያት መገናኛ አካባቢ ጭምር መንገድ ስለተዘጋ በዚህ አካባቢ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ እና እግረኞችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

(የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን)

@tikvahethiopia
#Tecno_Camon20Series
በምርጥ ዲዛይን የወርቅ ተሸላሚው ካሞን 20 ስልክን በእጆ ያስገቡ !

የቴክኖ ሞባይል አዲስ የሆነው የማጂክ ስኪን ቴክኖሎጂ ከፕዝል ዲኮንስትራክሽን ንድፍ ጋር በማዋሃድ የተመረተው አዲሱ ካሞን 20 የሞባይል ስልክ የ2023 የአለም አቀፉ ሙስ ሽልማትን (MUSE awards) በምርጥ ዲዛይን ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ የወርቅ ተሸላሚ አድርጎታል። ቴክኖ ሞባይል የማጂክ ስኪን የቴክኖሎጂን ከሴራሚክ ጋር በማዋሀድ ያመረተው ልዩ  የፐዝል ዲዛይን ለዓይን በሚማርክ እና ለአያያዝ በሚያመች ንድፍ ተላብሶ በሰማያዊ እና ጥቁር ቀለማት ለተጠቃሚዎች አቅርቧል ።

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Camon20Series #TecnoMobile #TecnoEthiopia
መግለጫ ፦ መኢአድ፣ ኢህአፓ፣ እናት ፓርቲ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ፤ " አገራችን ኢትዮጵያን ከከፋው የህልውና አደጋ ለመታደግ ለነገ የማይባልና ቁርጠኝነትን የተላበሰ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያስፈልጋል " ብለዋል።

(የፓርቲዎቹ የጋራ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ ያሉ አባቶች የፊታችን ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ/ም በቅድስት ከተማ አክሱም ፅዮን የኤጲስ ቆጾሳት ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። በክልሉ ለሚገኙ ሚዲያዎችም በስነስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ጥሪ መቅረቡን ለማወቅ ተችሏል። በትግራይ ያሉ አባቶች ከማዕከል በመነጠል " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤቤተክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ…
#EOTC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ/ም አስቸኳይ ስብሰባ ማካሄዱ የታወቀ ሲሆን ይህን ከስብሰባው መጠናቀቅ በኃላ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው :-

በትግራይ በሚገኙ አህጉረ ስብከት የተመደቡ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪን ቸል ከማለት ባሻገር ሐምሌ 9 እናደርገዋለን ያሉት የኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ የሚመለከታቸው አካላት ሂደቱን በማስቆም ከቤተክርስቲያን ጎን እንዲቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አቅርቧል።

ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ችግር የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሩን በውይይት የፈቱት መሆኑ እየታወቀ የሰላም ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማይቋረጥ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙ ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪውን አቅርቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያስተላለፈችውን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ ሆኖ አንድነቷ ጸንቶ ይኖር ዘንድ በጸሎት ተግጋችሁ ከቤተ ክርስቲያናችሁ ጎን እንድትቆሙ " ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ግብጽ

ዛሬ ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም የዓረብ ሪፐብሊክ ግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ተቀብለው አነጋግረዋል።

መሪዎቹ ባደረጉት ምክክር የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች የጋራ ጥቅም ባስጠበቀ እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የባህል የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሻሻል ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ይህ የመሪዎቹ ቁርጠኝነት በቀጠናው ሰላም እና ደኅንነትን ለማስፈን እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ባሻገር ሀገራቱ የሚያጋጥሟቸውን የጋራ ፈተናዎች ለመሻገርም ያስችላል።

ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ምክክር እልባት ያላገኘውን የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተም በተከታዮቹ ሁለት ነጥቦች ላይ ተስማምተዋል።

1) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌትን እና የአሠራር ደንቦችን በተመለከተ በግብፅ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል የሚካሄደውን ንግግር በፍጥነት ለማስጀመር እንዲሁም ንግግሩን በአራት ወራት ውስጥ አጠናቆ ከመግባባት ላይ ለመድረስ አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ተስማምተዋል።

2) ንግግሩ በሚካሄድበት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ በ2015-2016 ዓ.ም የግድቡ የውኃ ሙሌት ወቅት ግብፅ እና ሱዳን ከወንዙ በሚያገኙት የውኃ አቅርቦት ላይ የጎላ ችግር እንዳያጋጥም ለማድረግ ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።

(ኢዜአ)

@tikvahethiopia