TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አልተገኙም " - ባለስልጣን መ/ቤቱ

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ አስጠንቅቋል።

የግል እና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም መሰጠት ተጀምሯል፡፡

ይሁን እንጂ ባለሥልጣኑ ዛሬ ባደረገው ክትትል፤ አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳልተገኙ ገልጿል።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ተማሪዎቻቸው ሞዴል ፈተናውን እንዲወስዱ አለማድረጋቸውንም ባለሥልጣኑ ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በአቅራቢያቸው በሚገኙ ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ   የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን በመላክ ሞዴል ፈተና እንዲወስዱ ማድረግ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
" ጥቃቱ የተፈፀመው የ8ኛ ክፍል ፈተና ደህንነት ለመከታተል ወደ አባይ ሸለቆ ት/ቤት ሲጓዙ ነው " - የደጀን ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን

በዛሬው ዕለት መሰጠት የተጀመረውን የ8ኛ ክፍል ፈተና ደህንነት ለመከታተል ወደ አባይ ሸለቆ ትምህርት ቤት በመኪና ሲጓዙ የነበሩት የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው በጥይት ተመተው ተገደሉ።

በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው በተከፈተባቸው ተኩስ ሲገደሉ ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤትን ዋቢ በማድረግ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት፤ የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ጥቃት የተፈጸመባቸው ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ እንደሆነ ገልጿል።

ጥቃቱ የተፈፀመውም በግለሰብ አማካኝነት መሆኑን አመልክቷል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ መሰጠት የተጀመረውን የ8ኛ ክፍል ፈተና ደህንነት ለመከታተል ወደ አባይ ሸለቆ ትምህርት ቤት በመኪና እየተጓዙ በነበረበት ወቅት መሆኑን አሳውቋል።

የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፤ ሁለቱ የፖሊስ አዛዦች " ግልገሌ " የተባለች ቀበሌ ላይ ሲደርሱ " መንገድ ላይ ሲጠብቃቸው ነበር " በተባለ ግለሰብ ተኩስ እንደተከፈተባቸው በዚህም በጥይት የተመቱት የፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር ዘውዱ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ወዲያው ህይወታቸው ማለፉን አስረድቷል።

ሹፌራቸው እግሩን ተመትቶ ጉዳት እንደደረሰበትም አመልክቷል።

ጥቃቱን የፈጸመው ግለሰብ፤ ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ደጀን ከተማ ሲጓዝ የነበረን " ገልባጭ " መኪና በማስቆም ከአካባቢው ያመለጠ ሲሆን " ኪዳነ ምህረት የሚባል አካባቢ ሲደርስ ወርዶ የገልባጩን ሹፌር በጥይት እንደመታው የኮሚኒኬሽን ቢሮው ሀልጿል።

ሁለቱ በጥይት የተመቱ ሹፌሮች በአሁን ሰዓት በደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና ላይ እንዳሉ ተገልጿል።  

ለወረዳዋ ፖሊስ አዛዦች ህልፈት እንዲሁም ለሹፌቶቹ መቁሰል ምክንያት የሆነውን ተኩስ ከፍቷል የተባለ ተጠርጣሪን ለመያዝ ፍለጋ እየተከናወነ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@tikvahethiopia
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ምክክር መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

በመድረኩ፦
- የትምህርት ሚኒስቴር፣
- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣
- የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች እና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፤ ከሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በ102 የፈተና ጣቢያዎች የሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታውንና የክረምቱን የአየር ሁኔታ ያገናዘበ በርካታ የሰው ኃይል መመደቡን አሳውቋል።

ፈተናው ከሥርቆት በፀዳ መልኩ እንዲካሄድ ሁሉም ኃላፊነቱን ወስዶ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባም ኮሚሽኑ አሳስቧል።

በአማራና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች በፈተና ጣቢያዎች የፀጥታ ችግሮች እንዳይከሰቱ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቂ ዝግጅት ማድረጉንም ኮሚሽኑ አሳውቋል።

ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ፦

- የሀኪም ማዘዣ የሌለው መድሃኒት በሽሮፕም ሆነ በታብሌት፣
- የህክምና መስጫ መርፌ፣
- የአንገት ሀብል፣
- የፀጉርና የጆሮ ጌጥ፣
- ከጋብቻ ቀለበት ውጭ ፈርጥ ያለው የጣት ቀለበት እና የእጅ አንባር አድርገው መምጣት እንደማይችሉ ፖሊስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

በተጨማሪም ፦
- ተንቀሳቃሽ ስልክ፣
- አይ-ፓድ፣
- ታብሌት፣
- ላፕቶፕ፣
- ስማርት ሰዓት፣
- ሲዲ፣
- ሚሞሪ ሪደርና ኦ-ቲጂ ኮንቨርተር እንዲሁም ፎቶ የሚያነሱ እና ድምፅ የሚቀርፁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።

የተከለከሉ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲዎቹ ግቢ ውስጥም ሆነ በዙሪያው ይዞ መገኘት፣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ ግቢ ወስጥ በግልም ሆነ በቡድን ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው።

ይህንን ተላልፎ በተገኘ ተማሪ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ አንዳንድ የትራንስፖርት ችግሮችን ለመቅረፍ፣ ለተማሪዎች ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳና በዞን ትምህርት ቢሮ አማካኝነት የፈተና መመሪያ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

መረጃው የፌዴራል ፖሊስ ነው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ጊዜ ፔይ በማንኛውም ዓይነት ስልኮች መገልግል የሚችሉት የሞባይል ዋሌት አገልግሎት ነው። *817# በመደወል አገልግሎቱን ይጠቀሙ።

#BankofAbyssinia #BankingService #BankinginEthiopia #SavingAccount #EducationSaving #gizepay #mobilewallet #TheChoiceForAll #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሪሜዲያል

ትምህርት ሚኒስቴር ከአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና ጋር በተያያዘ ምን ውሳኔ አስተላለፈ ?

ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና አሰጣጥን በተመለከ ትላንት ሰኞ ምሽት ከፕሬዚደንቶችና የተቋማት ሃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኃላ ከፈተናው ጋር በተያያዘ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው አካል ለማወቅ ችሏል።

በዚሁ የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ የሬሜዲያል ፈተና አሰጣጥ በሚከተለው መልኩ እንዲከናወን ተወስኗል።

- በ26/10/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕርግራም ፈተናዎች #ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ እንዲደረግ ተወስኗል።

- ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ #ካምፓስ ያላቸውን #የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት ፈተና  ወደ ፊት ቀርቦ በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም  እንዲሰጥ እንዲደረግ ተወስኗል።

- በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች ፈተና መስጠቱን ወደ መስከረም ወር ማስተላለፉ በተማሪዎችና በተቋማት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት በማስገባት የተዘጋጁትን ፈተናዎች በመለወጥ ፈተናዎች ኢንክሪፕትድ ሆነው ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ደርሰው እንዲባዙና ሁሉም ፈተናዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ እንዲሰጡ እንዲደረግ።

- የፈተና ጥያቄዎች ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ከመድሳቸው በፊት ተማሪዎች #ከቀኑ_6 ሰዓት ላይ ተፈትሸው ወደ መፈተኛ አዳራሽ ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ በማድረግ እንዲፈፀም ውሳኔ ተላልፏል።

ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከላቸው ውሳኔ መሰረት ተማሪዎቻቸው #ከቀኑ_6 ሰዓት ተፈትሸው ወደመፈተኛ ክፍል ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ መልዕክት እያስተላለፉ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከየተቋማቱ የደረሰው መልዕክት ያስረዳል።

#TikvahFamily

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሪሜዲያል ትምህርት ሚኒስቴር ከአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና ጋር በተያያዘ ምን ውሳኔ አስተላለፈ ? ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና አሰጣጥን በተመለከ ትላንት ሰኞ ምሽት ከፕሬዚደንቶችና የተቋማት ሃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኃላ ከፈተናው ጋር በተያያዘ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው አካል ለማወቅ ችሏል። በዚሁ የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ የሬሜዲያል ፈተና አሰጣጥ…
#ይፋዊ

የትላንት የሬሜዲያ ፈተናዎች ተሰርዘዋል።

በሬሜዲያ ፈተና ሂደት ወቅት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔዎች አሳልፏል።

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ረሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ትናንት ሰኔ 26/2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ።

2) ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ።

3) በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት ይሰጣል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

NB. ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ ትላንት ፈተናው መሰጠት ከተጀመረ በኃላ ተፈጥረዋል ያላቸውን ችግሮችን በዝርዝር አላሳወቀም።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
#ኢትዮ_ቴሌኮም

ውጭ ሃገር ከሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶችዎ የሞባይል አየር ሰዓት ወይም ጥቅል በአጋሮቻችን በኩል ሲላክልዎ የሚያገኙት ስጦታ እስከ 100% ማደጉን በደስታ እንገልጻለን!

ለተጨማሪ መረጃ እና የሃገራት እና የአጋሮቻችንን ዝርዝር ለመመልከት bit.ly/3WZwbRH
#Icog

በዚህ ክረምት ልጆቼን ምን አይነት የክረምት ትምህርት ላስተምር ብለው እያሰቡ ነው?

iCog Anyone Can Code:
-AI, ሮቦቲክስ እንዲሁም የተለያዩ  አስደሳች የኮዲንግ ኮርሶች ይዞ ወደ ሀረር፣ ድሬዳዋ፣  ጅማ እና ባህርዳር እየመጣ ነው።እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ ለልጅዎ ቦታ ይያዙ።

ክልል ከተሞች-4000ETB
ለኦንላይን-4000ETB
ለአዲስ አበባ (በአካል)-5,500 ETB ብር ብቻ በመክፈል ልጅዎን ያስተምሩ።

ክፍት ቦታዎች በፍጥነት እየሞሉ ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ።

ለመመዝገብ: በስልክ ቁጥራችን
+251904262728/251901379478 በመደወል

ዌብሳይታችንን በመጎብኘት
https://icogacc.com/register

ወይም ቴልግራም ቦት ይጠቀሙ
@iCogACCsummercamp_bot

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችንን ይከተሉ
Facebook: facebook.com/icogacc
Instagram: instagram.com/icogacc
Twitter: twitter.com/icog_acc
Linkedin: linkedin.com/company/icog-anyone-can-code/
#ጀርመን

ጀርመን ውስጥ በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሁለት ሴቶችን በስለት የወጋው ኤርትራዊ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።

ጥገኝነት ጠያቂ የሆነው ይህ ኤርትራዊ በስለት ከወጋቸው ሁለት ታዳጊ ሴቶች መካከል የአንዷ ሕይወቷ አልፏል።

ኡቁባ ቢ በሚል ስም ብቻ የተጠቀሰው የ27 ዓመቱ ግለሰብ፣ ሁለቱ ታዳጊ ሴቶች ላይ ጥቃቱን የፈጸመው በዚህ ዓመት ኅዳር ወር ላይ " ኢሌራኪራቸበርግ " ተብላ በምትጠራ የጀርመን ከተማ ውስጥ ነው።

በጀርመን ከፍተኛ ቁጣን በቀሰቀሰው በዚህ የወንጀል ድረጊት ኤስ የተባለችው የ14 ዓመት ታዳጊ 23 ጊዜ በስለት ተወግታ ሕይወቷ ሲያልፍ፤ የ13 ዓመት ጓደኛዋ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል።

ዐቃቤ ሕግ ምን አለ ?

የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ኤርትራዊ ስለቱን የያዘው በአካባቢው በሚገኝ የኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት ውስጥ ሊጠቀመው አስቦት የነበረ ነው።

ነገር ግን ግለሰቡ የያዘውን ቢላ ታዳጊዎቹ ከተመለከቱበት በኋላ ጥቃት ሰንዝሮባቸዋል አንደኛዋን ለሞት ሲዳርጋት ሌላኛዋ ክፉኛ ጎድቷታል።

ዐቃቤ ሕግ እንዳለው ግለሰቡ ታዳጊ ሴቶቹ " ለፖሊስ ይጠቁሙብኛል " በሚል ድንገት ወንጀሉን ፈጽሞባቸዋል።

ግለሰቡ ወደ #ኢትዮጵያ ተጉዞ ጋብቻ ለመፈጸም ከጀርመን ባለሥልጣናት የጠየቀው የጉዞ ሰነድ ስላልተሰጠው በኢሚግሬሽን ኃላፊዎች ተበሳጭቶ ነበር።

በደቡብ ጀርመን የሚገኘው ፍርድ ቤት ኤርትራዊው የፈጸመው ወንጀል " እጅግ ከባድ " በመሆኑ ግለሰቡ 15 ዓመታት በእስር ከቆየ በኋላ እንኳን ከእስር የመለቀቅ ዕድሉ በጣም የጠበበ ነው ተብሏል።

ኤርትራዊው ጀርመን መች ገባ ?

ይህ ኤርትራዊ ጀርመን የገባው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ጦርነት እና እስርን በመሸሽ አውሮፓን ባጥለቀለቁበት ዓመት እአአ 2015 ላይ ነበር።

ኡቁባ ቢ ለፍርድ ቤት ምን አለ ?

ኡቁባ ቢ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት በፈጸመው የወንጀል ድርጊት #መጸጸቱን ገልጾ የተጎጂ ቤተሰቦች ይቅርታን ጠይቋል።

ይግባኝ ...

ግለሰቡ የተላለፈበትን ብይን ይግባኝ መጠየቅ ይችላል ተብሏል።

ፍርደኛው የሚያቀርበው ይግባኝ ውድቅ ከተደረገ ግን በእስር ጊዜው ወቅት ወደ ትውልድ አገሩ እንዲመለስ ሊደረግ እንደሚችል ዐቃቤ ሕግ ገልጿል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia