ለፈጣሪ የመታዘዝ እና የጽኑ እምነት ምሳሌ ለሆነው ኢድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል ከወዲሁ እንኳን በሰላም አደረሰዎ እያልን እስከ 32% ቅናሽ ያደረግንበትን አስደሳች ልዩ የኢድ አል- አድሃ (አረፋ) የሞባይል ጥቅል አቅርበናል!
በቴሌብር ሱፐርአፕ፣ ማይ ኢትዮቴል መተግበሪያዎች ወይም *999#
የበዓሉን ጥቅል ይግዙ፤ ወዳጅ ዘመድዎን ይዘይሩ!
(ኢትዮ ቴሌኮም)

June 27, 2023
Preliminary_Report_by_CECOE_Referendum_rerun_in_the_Wolaita_zone.pdf
649.8 KB
#CECOE : የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጀቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ) በወላይታ ዞን የተካሄደውን የድጋሚ ሕዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባና የድምጽ አሰጣጥ ሂደትን አስመልክቶ የሰጠው የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርት ልኮልናል።
በዚሁ የመጀመሪያ ደረጀ ሪፖርት ላይ ከድምፅ አሰጣጹ ጋር ተያይዞ አሳሳቢ ኹነቶች ተብለው የተዘረዘሩት ጉዳዮች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ፤ በተከለከሉ ቦታዎች ላይ የተቋቋመ የምርጫ ጣቢያዎች ፣ ያልተፈቀደላቸው ሰዎች በምርጫ ጣቢያዎች መገኘታቸው፣ የመራጮች ምዝገባ እና ድምፅ አሰጣት ሂደት የመቋረጥ ጉዳይ፣ የቁሳቁስ አለመሟላት የመሳሰሉት ይገኙበታል።
ሙሉ ሪፖርቱን ያንብቡ።
@tikvahethiopia

#እንዳትደናገጡ
ነገ የሚከበረውን የኢድ-አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ ማለዳ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ማሕበር ሕውነት ደቂ ሰብ ፤ በማሳደጊያው ውስጥ ያሉትን ከ60 በላይ ህፃናት እና ከድርጅቱ ውጪ የሚኖሩ በቀጥታ ድርጅቱ ድጋፍ ያደርግላችው የነበሩ ጧሪ የሌላቸውን ኣረጋውያን በሚገባቸው ልክ ሊደረስላቸው ስላልቻለ የእኛ የልጆቻቸውን ድጋፍ ጠይቋል።
ማሕበር ሕውነት ደቂ ሰብ ጥያቄውን ያቀረበው ለመላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦችና ለቀድሞ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባስተለለፈው መልዕክት ነው።
የቀድሞ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመቐለ ቆይታቸው በማሕበር ሕውነት ደቂ ሰብ (Human Beings Assocations of Brothers Hood) በመመላለስ የተለያዩ ማህበራዊ ግልጋሎቶችን በመስጠት ከድርጅቱ ጎን በመቆም በብዙ ቤተሰባዊ ፍቅር መልካም ጊዜያትን ከድርጅቱ ጋር አሳልፈዋል።
አሁን ላይ ድርጅቱ በወቅታዊው ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት በድርጅቱ ማሳደጊያ ውስጥ ያሉ ከ60 በላይ ህፃናት እና ከድርጅቱ ውጪ የሚኖሩ በቀጥታ ድርጅቱ ድጋፍ ያደርግላችው የነበሩ ጧሪ የሌላቸውን ኣረጋውያን በሚገባቸው ልክ መደገፍ ስላልቻለ የቲክቫህ ቤተሰቦች እንዲሁም የቀድሞ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድጋፍ እንዲደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
ድጋፉ የገንዘብ እና የኣይነት መሆን ይችላል።
የገንዘብ ድጋፉን " #ሕጋዊ በሆነው " በድርጅቱ የንግድ ባንክ ኣካውንት (Human Beings Assocation of Brothers Hood 👉1000016160664 በኩል ማድረግ ይቻላል።
የኣይነት ድጋፉን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ማድረስ ይቻላል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ከዓመታት በፊት በፀረ ጥላቻ ንግግር ዘመቻ የሰላም ጉዞ ወቅት ማሕበር ሕውነት ደቂ ሰብን ጎብኝተው ድርጅቱ ከሚያሳድጋቸው ልጆችም ጋር ጊዜ አሳልፈው ነበር።
ይህ መልዕክት የሚደርሳችሁ የቀድሞ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መልዕክቱን ለሌሎች እንድታጋሩና በምትችሉት አቅም ድጋፋችሁን እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

#MoE
ምንም እንኳን የተመራቂ ተማሪዎች " የመውጫ ፈተና " ሊሰጥ እጅግ አጭር ጊዜ የቀረው ቢሆንም እስካሁን ድረስ ፦
- ለተማሪዎቻቸው በቂ መረጃ ያላደረሱ፣
- የትና መቼ እንደሚፈተኑ ያላሳወቁ፣
- ተማሪዎቻቸው ከሚፈተኑባቸው የመንግስት ተቋማት ሥራ ኃላፊዎች ጋር ያልተወያዩ አንዳንድ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መኖራቸውን እንደደረሰበት ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ፤ ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶችና አመራሮች ባሰራጨው አስቸኳይ መልዕክት ነው።
የመጀመሪያ ድግሪ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር ፤ አንዳንድ ተቋማት እስካሁን ለተማሪዎቻቸው በቂ መረጃ ያላደረሱ፣ የትና መቼ እንደሚፈተኑ ያላሳወቁ፣ ተማሪዎቻቸው ከሚፈተኑባቸው የመንግስት ተቋማት ሥራ ኃላፊዎች ጋር ያልተወያዩ...ወዘተ ጉድለት እንዳለባቸው ባደረገው ክትትል እንዳወቀ ገልጿል።
እነኚህ ክፍተቶች በአጭር ጊዜ እንዲታረሙ ያሳሰበው ትምህርት ሚኒስቴር ፤ " ተማሪዎች መረጃ ባለማግኘት ለሚደርስባቸው እንግልትና ለሚከሰተው ችግር ኃላፊነቱ የተቋማቱ ነው " ሲል አስገንዝቧል።
ሚኒስቴሩ ጉድለት እንዳለባቸው በክትትል የደረሰባቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በስም አልጠቀሰም።
ተቋማቱ ለማንኛውም ድጋፍና ማብራሪያ ጡሪ ጭምዴሳ - 0911780497 ፣ ታምራት ከበደ - 0913566717 ፣ ብሩክ አሰፋ - 0913307730 ፣ አዲስ አለማየሁ- 0913715772 ፣ ፈሲል ፀጋዬ - 0911335683 የተባሉ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

#እንድታውቁት #AddisAbaba
ከለሊት 11:30 ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።
1444ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ ይከበራል፡፡
በዓሉን አስመልክቶ በ " አዲስ አበባ ስታዲዮም " ሃይማኖታዊ ስነ-ስርአት የሚካሄድ ሲሆን ይህ ስነስርዳት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቀ የትራፊክ መጨናነቅ እንደይፈጠር ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የሚዘጉ መንገዶች ፦
- ከፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ዋናው መንገድ ቴድሮስ አደባባይ
- ከጎተራ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ሪቼ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ እንዲሁም ለአነስተኛ ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ወይም የቀድሞ 4ኛ ክፍለ ጦር ጋር
- ከኬኬር ህንፃ ጀርባ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ የድሮ ለገሃር ግምሩክ
- ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ፣ በፖሊስ ሆስፒታል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አል ሳም ጨለቅለቅ በስርና በላይ መንገድ
- ከጎማ ቁጠባ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ
- ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ መብራት
- ከሜትሮሎጂ በጥቁር አንበሳ ወደ ፖስታ ቤት የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መ/ቤት
- ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ኦርማ ጋራዥ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት
- ከአራት ኪሎ እና ከእሪ በከንቱ የሚመጡ መንገዶች ፓርላማ መብራት ጋር
- ከሲግናል ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ
- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ ስታዲዩም የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ወይም ደንበል ሲቲ ሴንተር
- ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅድስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ ከላይና ከታች
- ከተክለ ኃይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል
- ከተክለ ሃይማኖት ጎላ ሚካኤል የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ
- ከጎፋ ፣ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር የሚወስደው አዲሱ መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊት 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናሉ፡፡
ህብረተሰቡ ከፖሊስ የተሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም ጥሪ ቀርቧል።
NB. የእምንቱ ተከታዮች በዓሉን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ ስታዲዮም ሲመጡ ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተረድተው እንደወትሮው ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል።
ማንኛውም አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ወይም የፖሊስ አገልግሎት ለማግኘት በአዲስ አበባ ፖሊስ የመረጃ ስልኮች 011-1 11-01-11 ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 መረጃ መስጠት ይቻላል።

#Telebirr #CBE
ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በአጋርነት በ " ቴሌብር " ተጨማሪ የፋይናንስ አገልግሎት መሰጠት ጀመሩ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ብድር እና ቁጠባ አገልግሎቶችን በቴሌብር አማካኝነት ለማቅረብ የሚያስችል አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል፡፡
አገልግሎቱ ፥ የግለሰብ ደንበኞች እና ተቋማት በቴሌብር የሚያከናውኗቸውን ግብይቶች መሰረት አድርጎ በሚሰራ የብድር ቀመር ስሌት (Credit Score) ብድር የሚያገኙበት ነው።
ከዚህም በተጨማሪ በ " ቴሌብር " ደሞዝ ተከፋይ መሆናቸውን መነሻ በማድረግ ያለ ማስያዥያ (nonCollateral) በአነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ ብድሮችን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡
በ2 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ34.05 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት የቻለው ቴሌብር ከዚህ ቀደም ከዳሽን ባንክ ጋር በዘረጋው አሰራር 3.9 ቢሊዮን ብር ማበደሩ ተገልጿል።
ዛሬ ይፋ የተደረጉት አገልግሎቶች ፦
#ስንቅ ፡- ደንበኞች ከወለድ ነጻ ወይም የተለያየ የወለድ ምጣኔ የሚታሰብባቸው የተንቀሳቃሽ እና የጊዜ ገደብ ተቀማጭ የቁጠባ አገልግሎት፣
#እንደራስ ፡- የግለሰብ ደንበኞች በቴሌብር እንደሚያከናውኑት የግብይት መጠን እስከ ብር 15,000 ድረስ የአነስተኛ ብድር አገልግሎት፣
#ድልድይ ፡- ለነጋዴዎች/ወኪሎች አነስተኛ ንግድ/ቢዝነስ እንዲጀምሩ ወይም እንዲያስፋፉ እስከ ብር 50,000 የሚደርስ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል አገልግሎት እንዲሁም፤
#አድራሽ ፡- ወርሃዊ ደመወዛቸው በቴሌብር ለሚከፈላቸው የግል እና የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ለደሞዝ መዳረሻ እስከ 50,000 ብር ድረስ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችሉ የብድር አማራጮች ናቸው፡፡
@tikvahethmagazine @tikvahethiopia

#አረፋ
(Tikvah 🕌 Family)
የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ በሀገራችን #ኢትዮጵያ እንዲሁም በተለያዩ ሀገራት ነው የተከበረ የሚገኘው።
የእስልምና ተከታይ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለበዓሉ አደረሳችሁ ፤ አደረሰን ለማለት እንወዳለን።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
ተጨማሪ ፎቶዎችን በ @tikvahethmagazine ላይ ይመልከቱ።

June 28, 2023