#ራያ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ፈፅመውታል ያሉትን ተግባር አጥብቀው ተቹ።
ምን ተፈጠረ ?
የአማራ ክልል እንዲሁም የትግራይ ክልል ጥያቄ ከሚያነሱባቸው አካባቢዎች አንዱ የራያ አካባቢ እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህ አካባቢ ከማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዘ የቆየ ጥያቄ ያለ ሲሆን አንዳንድ አካባቢዎች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከትግራይ አስተዳደር ወጥቶ ወደ አማራ ክልል ገብቷል።
ከትላንት በስቲያ የአሜሪካ ኤምባሲ ልዑካን ዲፕሎማቶች በራያ አለማጣ አካባቢ እንደነበሩ ተነግሯል።
ታዲያ የትግራይ አስተዳደር በ " ኃይል ተወረው ተይዘውብኛል " በሚለው አካባቢ ላይ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች መገኘታቸው እንዳስቆጣው ተሰምቷል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?
አቶ ጌታቸው ፤ " የአሜሪካ ኤምባሲ የዲፕሎማቶች ልዑካን ቡድን አላማጣ ነበር ፤ ምን ሲሰሩ እንደነበር ፈጣሪ ነው የሚያውቀው " ያሉ ሲሆን " ዲፕሎማቶቹ የአማራ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ በኃይል የያዙትን አካባቢ መጎብኘታቸው፣ የትግራይ ግዛቶች በጽንፈኛ ኃይሎች የኃይል ቁጥጥር ስር መሆኑን እንደመቀበል ይቆጠራል " ብለዋል።
ፕሬዜዳንቱ ፤ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በአካባቢው ላይ የተገኙት በሕገወጥ አስተዳደሩ ባለሥልጣናት በተቀነባበረ ድራማ ላይ መሆኑን ፤ ይህን ግን ለምን እንዳደረጉ ገልፅ እንዳልሆነ ጠቁመው ድርጊቱ አሜሪካ ለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ያላትን ቁርጠኝነት የሚጻረር በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ተቃውመዋል።
በሌላ በኩል ፦ ከሰሞኑን የፌደራል መንግስት ለሚቀጥለው በጀት ዓመት " በራያ እና አካባቢው ለሚገኙ መዋቅሮች የሚመድበው ድጎማ " ወደ ትግራይ ክልል እንዳይተላለፍ የ145 ሺህ ሰዎች ፊርማ ያለበት ሰነድ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መቅረቡን ከ " ኢትዮጵያ ኢሳይደር " ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፊርማውን አሰባስቦ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያስረከበው የ " ወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ " ነው።
ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በደብዳቤ የቀረበው ይህ ጥያቄ የሰሜኑ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ስር የነበሩ አራት መዋቅሮችን የሚመለከት ሲሆን እነዚህ መዋቅሮች በትግራይ ክልል ስር በነበሩበት ወቅት " የማንነት ጥያቄ ይነሳባቸው " እንደነበር ተገልጿል።
ነገር ግን የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ " ራሱን በራሱ ለማስተዳደር " መቻሉን ኮሚቴውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስገባው ሰንድ ላይ ገልጿል።
የወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የአካባቢው ህዝብ " ከፌደራል መንግስቱ ሊያገኝ ይገባ የነበረው በጀት " የሚላከው " በትግራይ ክልል በኩል ነው " በመባሉ ምክንያት እስካሁን የገንዘብ ድጎማ አለማግኘታቸውን ሰነዱ አስረድቷል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
* አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በክትትል ደርሼበታለሁ አለ። የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑ ያስታወሰው አስተዳደሩ፤ ማንኛውም…
የቤት ኪራይ ጉዳይ . . .
የነዋሪዎች ድምፅ !
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከወቅቱ የቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መልዕክቶችን ልከዋል።
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ የሚገልፁ መልዕክቶችን የላኩት ፤ ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በክትትል ደርሼበታለሁ ፤ ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር / ተከራይን ማስወጣት እንደማይችል ይወቀው " ካለ በኃላ ነው።
የከተማ አስተዳደሩ መመሪያ " እየተራዘመ " ዛሬ ድረስ የመጣ ሲሆን የእስካሁን ተግባራዊነት ምን ይመስል ነበር ? አሁንስ የቤት ኪራይ ጉዳይ ምን ላይ ነው ? በሚል ለአ/አ ቤተሰቦች ባቀረብነው ጥያቄ ከተከራዮች እንዲሁም ከአከራዎች በሺዎች የሚቆጠሩ መልዕክቶች መጥተዋል።
ከብዙ በጥቂቱ በዚህ አሰባስበን አስቀምጠናል።
ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-23

Telegraph
Tikvah-Ethiopia
የቤት ኪራይ . . . የነዋሪዎች ድምፅ ! በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከወቅቱ የቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መልዕክቶችን ልከዋል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ የሚገልፁ መልዕክቶችን የላኩት ፤ ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች…
TIKVAH-ETHIOPIA
የቤት ኪራይ ጉዳይ . . . የነዋሪዎች ድምፅ ! በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከወቅቱ የቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መልዕክቶችን ልከዋል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ የሚገልፁ መልዕክቶችን የላኩት ፤ ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ…
" የቤት ኪራይ ዋጋን ለመጨመር የሚሆን ምክንያት #ፈፅሞ የለም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ትላንት ምሽት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር።
በዚህ ቃለ ምልልስ ወቅትም ፤ ስለ " ጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከግብር ጋር በተያያዘም የቤት ኪራይ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ የቤት ኪራይ የመጨመርን ጉዳይ " #ስግብግብነት " ነው ብለዋል።
" [የኪራይ ጭማሪ] ምክንያት ፈልጎ ማህበረሰቡን የማስጨነቅ ሂደት ነው፤ ይሄ መታረም አለበት፤ የቤት ኪራይ ዋጋን ለመጨመር የሚሆን ምክንያት #ፈፅሞ የለም። ይሄን ማረጋገጥ እንችላለን። " ብለዋል።
አሁን እንዲከፈል የተባለው ግብርም ፤ " ከ45 ዓመት በፊት የነበረን ተመን ምናልባት ወደ ዛሬ 25 ዓመት በፊት ነው ያመጣነው ፤ አሁን የሚከፈለው ክፍያ መከፈል የነበረበት የዛሬ 25 ዓመት ነው ወደዛሬው ዋጋ መጠን እንኳን አላመጣነውም ፤ በአንድ ጊዜ ይከብዳል ብለን " ያሉት ከንቲባዋ ፤ " 50 ፐርሰንት ያለው ለዚህ ነው ፤ የመኖሪያ ቤት የተመኑን 50 ፐርሰንት ብቻ ክፈል ፤ መስሪያ ቤቶች እና ቢዝነስ ተቋማት 75 ፐርሰንት ብቻ ክፈል ያልነው ጫና እንዳይሳድር ነው ፤ ስለዚ በምን ምክንያት ነው የተለየ ግብር የከፈሉት ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
" አሁን የቤት ኪራይ እየጨመሩ ያሉት የግብር ስርዓቱ ውስጥ የሉም ፤ ኪራይ የሚጨምሩት የቤት ግብር እየከፈሉ አይደለም ፤ ከ800 ሺህ ውስጥ በጥቅሉ አሁን ከውሳኔው በኃላ የተጨመሩት 90 ሺህ ስንጨምር ወደ 200 ሺህ ያክል ብቻ ነው እየከፈለ ያለው 600 ሺው የለም እኮ፤ ስርዓቱ ውስጥ ድሮም አልነበረም ፤ ዛሬም የለም አሁንም አልገባም እንዴት ነው የቤት ኪራይ የሚጨምረው ? ይሄ የስግብግብነት መግለጫ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ከንቲባ አዳነች ፤ " አስተዳደሩ ለሁሉም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ መመሪያ አስተላልፈናል ፤ ማህበረሰቡ አቤቱታ ሰሚ የሚባል ክፍል ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ውስጥ አለ የተጨመረባቸው ግብር ከነመስሪያ ቤቱ ከነውላቸው ያስመዝግቡልን ፤ ውል ግዴታ አይደለም የተጨመረባቸው ግብር መነሻ እውነት መሆኑን የሚያሳይ መረጃ / የከፈሉበትን ድሮ እና አሁን የሚከፍሉትን እንዲከፍሉ የታዘዙትን ስንት ነው የሚለውን በአቤቱታ መልክ ያስገቡን ይሄን መነሻ አድርገን ህግ እና ስርዓት እንዲከበር ስራ እንሰራለን " ሲሉ አሳውቀዋል።
" ግብሩን እየከፈለ ያለው ዝቅተኛው ማህበረሰብ ነው ፤ የቤት ኪራይ የሚጨመርበትም እሱ ላይ ነው ጨማሪው የተሻለ ገቢ ያለው ነው ግብር የማይከፍለውም የተሻለ ገቢ ያለው ነው ከዚህ በላይ ኢፍትሃዊነት ምን አለ ? እንደ መንግሥት ይሄን የማስተካከል ግዴታ አለብን ግዴታችንን ለመወጣት ጥረት እናደርጋለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" የቤት ኪራይ ዋጋን ለመጨመር የሚሆን ምክንያት #ፈፅሞ የለም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትላንት ምሽት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር። በዚህ ቃለ ምልልስ ወቅትም ፤ ስለ " ጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከግብር ጋር በተያያዘም የቤት ኪራይ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። …
" ማህበረሰቡ መብቱን ያስከብር " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትላንት ምሽት ከብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ፤ የከተማው ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30 ድረስ [ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር እና ተከራይን ማስወጣት ] የሚከለክል ሕግ መኖሩን እንዲገነዘብ ብለዋል።
ከንቲባዋ ፤ " አሁንም የኑሮ ውድነቱ ቀጥሏል። " ያሉ ሲሆን " ማሻሻያ ለካቢኔ ይቀርባል ፤ የማሻሻያ ሃሳብ ቀርቧል ለካቢኔ የሚቀርበው ይሄን መነሻ በማድረግ ማህበረሰቡ መብቱን ያስከብር እላለሁ ፤ " ብለዋል።
" [ጭማሪ የሚያደርጉትና የሚያስወጡት] የከተማ አስተዳደሩን ደንብ ጭምር ነው የጣሱት " ሲሉ ተናግረዋል።

" ማህበረሰቡ መብቱን ያስከብር " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትላንት ምሽት ከብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ፤ የከተማው ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30 ድረስ [ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር እና ተከራይን ማስወጣት ] የሚከለክል ሕግ መኖሩን እንዲገነዘብ ብለዋል። ከንቲባዋ ፤ " አሁንም የኑሮ ውድነቱ ቀጥሏል። " ያሉ ሲሆን " ማሻሻያ ለካቢኔ ይቀርባል ፤…
" የቤት ኪራይ የተጨመረባችሁ ከሰኔ 20 ጀምሮ ቅሬታችሁን አቅርቡ " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የቤት ኪራይ የተጨመረባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እንዳያቀርቡ ጥሪ ቀረበ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ማንኛውም አከራይ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ የቤት ኪራይ መጨመር የማይችል መሆኑን መወሰኑን አስታውሷል።
በዚህም መሰረት ፤ የቤት ኪራይ የተጨመረባቸው የከተማው ነዋሪዎች ማስረጃዎቻቸውን በመያዝ ከፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሚኖሩበት ወረዳ የ " መልካም አስተዳደርና አቤቱታ ስራ ክፍል " እንዲሁም የ " ወረዳ ስራ አስፈፃሚ ቢሮዎች " በመገኘት ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

ጀርመን #ባለሞያ ሰራተኞችን ልትቀበል ነው።
የጀርመን ምክር ቤት በተለያዩ ሙያ የሰለጠኑ ከአዉሮፓ ህብረት (EU) ሃገራት ዉጭ የሆኑ ሰራተኞች ወደ ጀርመን እንዲገቡ የሚፈቅደዉን አዲስ ደንብ ዛሬ ማፅደቁ ተነግሯል።
አዲሱ ደንብ ባለሙያዎች፣ የጀርመንኛና የእንግሊዝኛ ቋንቋ እስከቻሉ ድረስ ያለ ብዙ ዉጣ ዉረድ ወደ ጀርመን እንዲገቡና ጀርመን ዉስጥ እንዲሰሩ የሚፈቅድ ነው ተብሏል።
ይህ ደንብ በጀርመን ለሚገኙ በርካታ ስደተኞች እድል የሚሰጥ ሴሆን በካናዳ ደንብና አሰራር መሠረት የተቀረፀ እንደሆነ ተነግሯል።
ደንቡ በተለይ እንደ መስተንግዶ፣ ጤና፣ ግንባታና ቴክኖሎጂን በመሳሰሉ መስኮች ጀርመን ያለባትን የባለሙያ እጥረት ለማቃለል ይረዳል ተብሏል።
መረጃው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

ብርሃን ባንክ በሀገራችን የመጀመርያውን የ’ኤም ፖስ’ ማሽን በስራ ላይ አዋለ !
ብርሃን ባንክ ከሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን ጋር በጋራ በመሆን የመጀመርያ የሆነውን የኤም ፖስ ማሽን ለተጠቃሚዎች በስራ ላይ አውሏል።
ባንካችን ያስጀመረው ይህ የኤም ፖስ ማሽን ለታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች እና የዲጂታል ደረሰኝ ለሚፈልጉ ለተለያዩ አነስተኛ ቢዝነሶች መዋል የሚችል ነው።
እነዚህ ማሽኖች ለአጠቃቀም እና ለአያያዝ እጅግ ቀላል ከመሆናቸው በላይ የኔት ወርክ ፍጥነታቸው ቀድሞ በገበያ ላይ ካሉት የፖስ ማሽኖች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ስለሆነ ተመራጭ በመሆን በተሻለ የአገልግሎት ተደራሽነት በከተማችን ውስጥ በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ እና ለሌሎችም በማሰራጨት ላይ እንገኛለን፡፡
#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!

ከወደ ካናዳ . . .
የዳቦ ዋጋ ሲጨምር የነበረው ዳቦ አምራች 50 ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በፍርድ ቤት ተቀጣ።
ካናዳ ውስጥ ሆን ብሎ የዳቦ ዋጋ የጨመረ / እንዲንር ያደረገ የዳቦ አምራች የ50 ሚሊዮን የካናዳ ዶላር ቅጣት መቀጣቱን ቢቢሲ ፅፏል።
ድርጅቱ " ካናዳ ብሬድ " የሚባል ሲሆን ለዓመታት የዳቦ ዋጋ ሲጨምር እንደነበር #አምኗል ተብሏል።
የካናዳ የገበያ ውድድር ቢሮ ፤ ዳቦ ቤቱን ጠርጥሮ ለበርካታ ዓመታት ምርመራ ሲያደርግበት መቆየቱ የተነገር ሲሆን ቢሮው ዳቦ ቤቱ ላይ የተጣለው ቅጣት ሲያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም ብሏል።
የቢሮው ሠራተኛ ማቲው ቦስዌል ናች ፤ " የዳቦ ዋጋን ሆነ ብሎ መጨመር፤ ሊያውም የካናዳዊያን የለተ ዕለት ማዕድ የሆነውን ዳቦ? ይህ ትልቅ ወንጀል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ዋጋ የሚጨምሩ ሌሎች ሰዎችንም እያሳደድን ለሕግ እናቀርባለን " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የገበያ ውድድር ቢሮ ፤ " ሌሎች ዋጋ የጨመሩ ዳቦ ቤቶች ካሉ የእጃቸውን እንዲያገኙ እናደርጋለን " ያለ ሲሆን " የአንድ ዳቦ ዋጋ ማንም ሳያስተውለው በ16 ዓመታት ውስጥ የ1 ዶላር ከሐምሳ ዋጋ ጭማሪ ማምጣቱን " ደርሼበታለሁ ብሏል።
በካናዳ በርካታ ቸርቻሪዎች የዳቦ ዋጋ ጨምራችኋል ተብለው በቢሮው ዓይን ውስጥ የገቡ ሲሆን አንዳቸውም ግን ጥፋታቸውን አላመኑም ተብሏል።
ቢሮው በቅርቡ ደግሞ የትኛው ' ሱፐርማርኬት ' የሸቀጥ ዋጋ እንደጨመረ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።

Photo
#Update #NEBE
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በ1,812 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያስፈጸመውንና 849,896 መራጮች ድምፅ የሰጡበትን የወላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ የውጤት ማዳመሩን ሥራ በዞኑ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሲያከናወን መቆየቱን ገልጿል።
በዛሬውም ዕለት ቦርዱ የውጤት የማመሳከሩንና የማዳመሩን ሥራ በማጠናቀቅ በዞን ደረጃ #የጊዜያዊ ውጤቱን ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት ፦
እርግብ ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #እንደግፋለሁ ያሉት የድምፅ ብዛት 👉 760,285
ጎጆ ቤት ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #አልደግፍም ያሉት የድምፅ ብዛት 👉 42,413
ከፍተኛ ቁጥር ያለው ድምፅ ያገኘ የሕዝበ ውሳኔ አማራጭ - #እርግብ መሆኑ ተገልጿል።

#ETHIOPIA ከትላንት ምሽት አንስቶ በኢትዮጵያ ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እንዲሁም ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንዲገደቡ መደረጉ ታውቋል። አገልግሎቶቹ በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ማለትም በኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም በሳፋሪኮም በኩል እየሰሩ እንዳልሆነ ለመረዳት ችለናል። ከማህበራዊ መገናኛዎቹ አገልግሎት መገደብ ጋር በተያያዘ በሌሎች ለአብነት በጎረቤት ሀገራት ውስጥ እስካሁን የታየ መቆራረጥ…
#ETHIOPIA
በኢትዮጵያ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ገደብ ከተጣለ ወራት ተቆጥሯል።
ይህን ሁሉ ጊዜ ማን ? ለምን ገደብ እንደተጣለ ? መቼ ገደቡ እንደሚነሳ ፤ የትኛውም የመንግሥት አካል ይፋዊ ማብራሪያ ለህዝብ አልሰጠም።
ይህን ገደብ ለማለፍ ሰዎች #VPN እየተጠቀሙ ይገኛሉ።
ትላንት በህ/ተ/ም/ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮ ቴሌኮምን የ2015 ዓ/ም የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀምን በገመገመበት ወቅት ከምክር ቤት አባላት በዚህ ገደብ ጉዳይ ጥያቄ ተነስቶ ነበር።
ከምክር ቤት አባል የተጠየቀ ጥያቄ ፦
" ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን መሰረት ተደርጎ አንዳንዴ የአጠቃቀም ገደብ ይጣላል። በተለይ የዳታ አጠቃቀም ገደቦች ይጥላሉ።
ባለፈው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን መሰረት በማድረግ ገደብ ተጥሎ ነበር ከዛ አንፃር አሁን ያለው ሁኔታ የተለያዩ ሶፍትዌሮችን የሚጠይቅ penetrate አድርገን እንዳንገባ የሚያደርግ ገደብ አለ።
ይሄ እስካሁን አልተለቀቀም፤ አንደኛ ይህ የግለሰቦችን የዳታ አጠቃቀም ላይ ገደብ እየጣለ ስለሆነ ፤ ሁለተኛ የሌሎች ሀራትን permission የሚጠይቅ ስለሆነ ይሄ ለምድነው እስካሁን ያልታረመው ?
ከዚህ ጋር ተያይዞ ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር አጠቃቀም ጀምሯል። ጥሩ ስራ ተጀምሯል፤ ቁጠባ፣ ከነዳጅ ጋር የተያያዘውም በጣም ውጤታማ ናቸው ፤ ግን እራሱ የተደረገው ገደብ ቴሌብር active እንዳይሆን እየከለከለው ነው። በተፈለገው direction እንዳይገባ እንዳይወጣ እያደረገው ነው ምክንያቱም ዳታ Permission ይጠይቅና ወደዛ ሲገበብ block እየተደረገ ያለበት ሁኔታ አለ እናተም ታውቃላችሁ ይሄን ችግር ለመቅረፍ ለምንድነው የማይሰራው ?
አሁንም ቢሆን ችግር አለ ወይ ? የምናውቀው ነገር ካለ በጋር መጋራት አለብን። "
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ምላሽ ፦
" ከVPN ጋር ተያይዞ የተነሳው ትክልል ነው።
በደንበኞቻችን ላይ እየፈጠረ ያለው ጥሩ ያልሆነ ተሞክሮ ነው።
ሁላችሁም እንደምትገነዘቡት ይሄ የኢትዮ ቴሌኮም Mandate አይደለም።
የሚመላከተው የመንግሥት አካል ከVPN ውጭ ኢንተርኔት access እንዲደረግ ፍቃድ ሲሰጠን ማስተካከያ እናደርጋለን።
የደንበኞቻችንን የኢንተርኔት አጠቃቀም ተሞክሮ ላይ ችግር እንደፈጠረ እኛም ተረድተናል።
በተለይ ጥሩ ማስፋፊያ እያደረግን የተሻለ ኔትዎርክ አጠቃቀም እንዲኖራቸው የ ' service experience ' የምንለው እንዲኖራቸው ነው የምንፈልገው።
በዚህ ምክንያት ቅሬታ እንዲኖራቸው አንፈልግም።
ከነዳጅ ግብይት እንዲሁም ሌሎችም ግብይቶች automate ከማድረግ አንፃር ቴሌ ብርን በሰፊው እየተጠቀምን ነው ለሱም እንቅፋት ይሆናል የተባለው ትክክል ነው።
ይሄን በሂደት የተዘጋበት / ይኽን እርምጃ የወሰደው የመንግሥት አካል ምክንያት አለው እንዲከፈት እና የተሻለ አገልግሎት ደንበኞቻችን እንዲያገኙ በእኛ በኩል አስፈላጊውን ስራ እንሰራለን። ግን ይህ mandate የኛ አይደለም። "

በየትኛውም የስልክ አማራጭ፣
እጅግ ቀላልና ፈጣን የነዳጅ መክፈያ ዘዴ ሆኖ በቀረበው ኮፔይ ኢብር በመጠቀም፣ ጊዜዎን ይቆጥቡ!
ለነዳጅ ማደያ ባለሙያው በኮፔይ-ኢብር መክፈል እንደሚፈልጉ ካሳወቁ፣ አስፈላጊውን መረጃ ማስገባቱን ለባለሙያው ይተውት፡፡
ሳይረፍድብዎ ወደ ጉዞዎ ይመለሱ!
መተግበሪያውን አውርደው ለመመዝገብ https://rb.gy/mdtd3
#Coopbank #DigitalPayment #Banking

#AddisAbaba
የቤት ግብር ተመን ማሻሻያው በአተገባበሩ ላይ ክፍተቶች እንዳሉበት የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ገለጸዋል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በበኩሉ ፤ ከማሻሻያው በፊት የነበረው የክፍያ መጠን እዚህ ግባ የማይባል እና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ የማያንጸባርቅ ነበር ብሏል።
ይህ የተባለው " አዲስ ቻምበር " የቤት ግብር ማሻሻያ ላይ የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረክ በሚል በካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ነው።
በመድረኩ ላይ ምን ተባለ ?
የንግድ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ወ/ ሮ መሰንበት ሽንቁጤ ፦
" ግብር ለከተሞች እድገት የጀርባ አጥንት ነው።
ሆኖም በግብር ዙሪያ የሚወጡ አዋጆችና ደንቦች ከመውጣታቸው በፊትም ሆነ ከወጡ በኃላ የሚመለከታቸውን አካላት ሲያሳተፉ አይታይም ከዚህ አንፃር ክፍተት አለ።
በመሆኑም ንግድ ም/ቤቱ የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረኮችን በማመቻቸት መንግስትና የግሉ ዘርፍ ቀርበው እንዲመክሩ መድረክ እያመቻቸ ነው።
ይህም በግብር ጉዳዮች ላይ መተማመን እንዲኖር እና ችግሮችም ካሉ ለመቅረፍ መንግስት የሚጠበቅበትን ገቢ እንዲሰበሰብ ያስችላል። "
የአዲስ አበባ የንብረት ግብር ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አስማማው ሙሉጌታ ፦
" የቤት ግብር አከፋፋል ላይ እሴትን ያገናዘበ ወቅታዊ ተደረገ እንጂ አዲስ አዋጅ አልወጣም።
በከተማዋ ከ285 ሺ በላይ ግብር ከፋዮች አሉ ፤ ከተማዋ የምትሰበሰበው ግብር ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር ግን አነሰተኛ ነው።
ናይሮቢ ከአጠቃላይ ግብር ውስጥ የቤት ግብር 20 በመቶ ሲሆን ፣ የዛምቢያዋ ዋና ከተማ ሉሳካ 74 በመቶ ይሰበስባሉ።
ይሁንና አዲስ አበባ ከተማ የምትሰበሰበው ከ1 በመቶ በታች 0 .08 ነው። "
የአዲስ ቻምበር የግልግል ተቋም ዳይሬክተር አቶ ዮሀንስ ወ/ገብርኤል ፦
" የበአዋጅ የወጣ የግብር ተመን ማሻሻያ የሚሻሻለው በአዋጅ ነው።
አዲስ ደንብም ሲወጣ በደንብ ይተካል። "
የኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ያሬድ ሀይለ መስቀል ፦
" ይህ የቤት ግብር ተመን ማሻሻያ ወቅቱን ያላገናዘበ እና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሊያስከትል የሚችል ነው። "
በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ፦
- ግብር መክፍሉን አንደግፋለን ነገር ግን አሁን ያለውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ታሳቢ ያደረገ አይደለም።
- የመከፍል አቅም የሌላቸው ዜጎች መክፍል አይችሉም እና እነርሱስ እንዴት ይታያሉ ?

" ህብረተሰቡ ላይ ተደራራቢ ችግር እንዳለ እንረዳለን።
ሆኖም የቤት ግብር ትመናው በጥናት ላይ የተመሰረተ ነው።
የመክፍል አቅም የሌላቸው ባለቤቶች መክፍል እንደማይችሉ ከተረጋገጠ ለአንድ አመት ከከፍያ ነፃ የሚሆኑበት አሰራር ተዘርግቷል። "
በዚሁ መድረክ ላይ ፦
- የአምልኮ ቦታዎች ፣
- ኢምባሲዎች ፣
- የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣
- መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የቤት ግብር ማሻሻያው የማይመለከታቸው መሆናቸው ተነግሯል።
(አዲስ ቻምበር)