TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በታጣቂዎች #ታግተው የነበሩት የሰዴን ሶዶ የወረዳ አመራር ተገድለው ተገኙ። በኦሮሚያ ክልል ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል። የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው መገኘታቸውን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት…
የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ።

ከመኖሪያ ቤታቸው በታጣቂዎች ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው የተገኙት የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃቻ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል።

አቶ በቀለ ፤ ባለፈው ቅዳሜ ታፍነው ከታገቱ በኃላ ያገቷቸው ታጣቂዎች እንዲለቀቁ ' 10 ሚሊየን ብር ' መጠየቃቸው ተሰምቷል።

የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቅ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ለተወሰኑ ሰዎች በወረዳው አስተዳዳሪ ስልክ ደውለው እስከ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን አመልክቷል።

አቶ በቀለ ታፍነው ተወስደው ከታገቱ በኃላ ማክሰኞ ዕለት ተገድለው አስክሬናቸው ተገኝቷል።

@tikvahethiopia
#Agew

ከ1 ዓመት በላይ ጊዜ ወስዷል የተባለው " አንታጉ " የተሰኘ የአገውኛ ፊልም ዛሬ ተመረቀ።

ለመጀመሪያ ጊዜ በ " አገወኛ ቋንቋ " የተሰራው " አንታጉ " የአገወኛ ፊልም የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንግዳ ዳኛውን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

በፊልሙ የምረቃ ስነሥርዓት ላይ አቶ እንግዳ ዳኛው ፤ " አንታጉ የአገውኛ ፊልም አገዎች የቀደምት  የጥበብ ባለቤት መሆናቸውን ማሳያ ነው " ብለዋል።

መረጃው ከአዊ ኮሚኒኬሽን የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

አፖሎ ዘመደ ብዙ ነው። ከየትኛውም አማራጭ ወደ አፖሎ አካውንትዎ ገንዘብ ተቀማጭ አድርገው ቀለል ብሎት ይገበያዩ ::

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
ቀደምቷ አርዲ ለዲጂታል መስተንግዶውም ቀደምት እና ቀልጣፋ ናት!

አገልግሎቶቻችንን በተመለከተ ለጥያቄዎ ፈጣን ምላሽ፣ ጥቅሎች መግዛት፣ የሂሳብ መረጃ መጠየቅንና ሌሎች አገልግሎቶችን በ5 ቋንቋዎች በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት በምቾት ልታስናግድዎ ዝግጁ ነች፤ ከደንበኞች አገልግሎት ባለሙያዎቻችን ጋርም ታገናኝዎታለች!

በድረገፅ - ethiotelecom.et/
በፌስቡክ - facebook.com/ethiotelecom እና በትዊተር - twitter.com/ethiotelecom በመልዕክት መላኪያ ላይ
በዋትስዓፕ - wa.me/251994000000?text
በቴሌግራም - t.iss.one/EthiotelecomChatBot አርዲን ይጠይቁ

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#ራያ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ፈፅመውታል ያሉትን ተግባር አጥብቀው ተቹ።

ምን ተፈጠረ ?

የአማራ ክልል እንዲሁም የትግራይ ክልል ጥያቄ ከሚያነሱባቸው አካባቢዎች አንዱ የራያ አካባቢ እንደሆነ ይታወቃል።

በዚህ አካባቢ ከማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዘ የቆየ ጥያቄ ያለ ሲሆን አንዳንድ አካባቢዎች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከትግራይ አስተዳደር ወጥቶ ወደ አማራ ክልል ገብቷል።

ከትላንት በስቲያ የአሜሪካ ኤምባሲ ልዑካን ዲፕሎማቶች በራያ አለማጣ አካባቢ እንደነበሩ ተነግሯል።

ታዲያ የትግራይ አስተዳደር በ " ኃይል ተወረው ተይዘውብኛል " በሚለው አካባቢ ላይ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች መገኘታቸው እንዳስቆጣው ተሰምቷል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

አቶ ጌታቸው ፤ " የአሜሪካ ኤምባሲ የዲፕሎማቶች ልዑካን ቡድን አላማጣ ነበር ፤ ምን ሲሰሩ እንደነበር ፈጣሪ ነው የሚያውቀው " ያሉ ሲሆን " ዲፕሎማቶቹ የአማራ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ በኃይል የያዙትን አካባቢ መጎብኘታቸው፣ የትግራይ ግዛቶች በጽንፈኛ ኃይሎች የኃይል ቁጥጥር ስር መሆኑን እንደመቀበል ይቆጠራል " ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በአካባቢው ላይ የተገኙት በሕገወጥ አስተዳደሩ ባለሥልጣናት በተቀነባበረ ድራማ ላይ መሆኑን ፤ ይህን ግን ለምን እንዳደረጉ ገልፅ እንዳልሆነ ጠቁመው ድርጊቱ አሜሪካ ለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ያላትን ቁርጠኝነት የሚጻረር በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

በሌላ በኩል ፦ ከሰሞኑን የፌደራል መንግስት ለሚቀጥለው በጀት ዓመት " በራያ እና አካባቢው ለሚገኙ መዋቅሮች የሚመድበው ድጎማ " ወደ ትግራይ ክልል እንዳይተላለፍ የ145 ሺህ ሰዎች ፊርማ ያለበት ሰነድ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መቅረቡን ከ " ኢትዮጵያ ኢሳይደር " ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፊርማውን አሰባስቦ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያስረከበው የ " ወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ " ነው።

ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በደብዳቤ የቀረበው ይህ ጥያቄ የሰሜኑ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ስር የነበሩ አራት መዋቅሮችን የሚመለከት ሲሆን እነዚህ መዋቅሮች በትግራይ ክልል ስር በነበሩበት ወቅት " የማንነት ጥያቄ ይነሳባቸው " እንደነበር ተገልጿል።

ነገር ግን የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ " ራሱን በራሱ ለማስተዳደር " መቻሉን ኮሚቴውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስገባው ሰንድ ላይ ገልጿል።

የወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የአካባቢው ህዝብ " ከፌደራል መንግስቱ ሊያገኝ ይገባ የነበረው በጀት " የሚላከው " በትግራይ ክልል በኩል ነው " በመባሉ ምክንያት እስካሁን የገንዘብ ድጎማ አለማግኘታቸውን ሰነዱ አስረድቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በክትትል ደርሼበታለሁ አለ። የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም  ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑ ያስታወሰው አስተዳደሩ፤ ማንኛውም…
የቤት ኪራይ ጉዳይ . . .

የነዋሪዎች ድምፅ !

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከወቅቱ የቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መልዕክቶችን ልከዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ የሚገልፁ መልዕክቶችን የላኩት ፤ ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በክትትል ደርሼበታለሁ ፤ ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር  / ተከራይን ማስወጣት እንደማይችል ይወቀው " ካለ በኃላ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ መመሪያ " እየተራዘመ " ዛሬ ድረስ የመጣ ሲሆን የእስካሁን ተግባራዊነት ምን ይመስል ነበር ? አሁንስ የቤት ኪራይ ጉዳይ ምን ላይ ነው ? በሚል ለአ/አ ቤተሰቦች ባቀረብነው ጥያቄ ከተከራዮች እንዲሁም ከአከራዎች በሺዎች የሚቆጠሩ መልዕክቶች መጥተዋል።

ከብዙ በጥቂቱ በዚህ አሰባስበን አስቀምጠናል።

ያንብቡ👇

https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-23
TIKVAH-ETHIOPIA
የቤት ኪራይ ጉዳይ . . . የነዋሪዎች ድምፅ ! በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከወቅቱ የቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መልዕክቶችን ልከዋል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ የሚገልፁ መልዕክቶችን የላኩት ፤ ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ…
" የቤት ኪራይ ዋጋን ለመጨመር የሚሆን ምክንያት #ፈፅሞ የለም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ትላንት ምሽት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህ ቃለ ምልልስ ወቅትም ፤ ስለ " ጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከግብር ጋር በተያያዘም የቤት ኪራይ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ የቤት ኪራይ የመጨመርን ጉዳይ " #ስግብግብነት " ነው ብለዋል።

" [የኪራይ ጭማሪ] ምክንያት ፈልጎ ማህበረሰቡን የማስጨነቅ ሂደት ነው፤ ይሄ መታረም አለበት፤ የቤት ኪራይ ዋጋን ለመጨመር የሚሆን ምክንያት #ፈፅሞ የለም። ይሄን ማረጋገጥ እንችላለን። " ብለዋል።

አሁን እንዲከፈል የተባለው ግብርም ፤ " ከ45 ዓመት በፊት የነበረን ተመን ምናልባት ወደ ዛሬ 25 ዓመት በፊት ነው ያመጣነው ፤ አሁን የሚከፈለው ክፍያ መከፈል የነበረበት የዛሬ 25 ዓመት ነው ወደዛሬው ዋጋ መጠን እንኳን አላመጣነውም ፤ በአንድ ጊዜ ይከብዳል ብለን " ያሉት ከንቲባዋ ፤  " 50 ፐርሰንት ያለው ለዚህ ነው ፤ የመኖሪያ ቤት የተመኑን 50 ፐርሰንት ብቻ ክፈል ፤  መስሪያ ቤቶች እና ቢዝነስ ተቋማት 75 ፐርሰንት ብቻ ክፈል ያልነው ጫና እንዳይሳድር ነው ፤ ስለዚ በምን ምክንያት ነው የተለየ ግብር የከፈሉት ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" አሁን የቤት ኪራይ እየጨመሩ ያሉት የግብር ስርዓቱ ውስጥ የሉም ፤ ኪራይ የሚጨምሩት የቤት ግብር እየከፈሉ አይደለም ፤ ከ800 ሺህ ውስጥ በጥቅሉ አሁን ከውሳኔው በኃላ የተጨመሩት 90 ሺህ ስንጨምር ወደ 200 ሺህ ያክል ብቻ ነው እየከፈለ ያለው 600 ሺው የለም እኮ፤ ስርዓቱ ውስጥ ድሮም አልነበረም ፤ ዛሬም የለም አሁንም አልገባም እንዴት ነው የቤት ኪራይ የሚጨምረው ? ይሄ የስግብግብነት መግለጫ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከንቲባ አዳነች ፤ " አስተዳደሩ ለሁሉም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ መመሪያ አስተላልፈናል ፤ ማህበረሰቡ አቤቱታ ሰሚ የሚባል ክፍል ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ውስጥ አለ የተጨመረባቸው ግብር ከነመስሪያ ቤቱ ከነውላቸው ያስመዝግቡልን ፤ ውል ግዴታ አይደለም የተጨመረባቸው ግብር መነሻ እውነት መሆኑን የሚያሳይ መረጃ / የከፈሉበትን ድሮ እና አሁን የሚከፍሉትን እንዲከፍሉ የታዘዙትን ስንት ነው የሚለውን በአቤቱታ መልክ ያስገቡን ይሄን መነሻ አድርገን ህግ እና ስርዓት እንዲከበር ስራ እንሰራለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ግብሩን እየከፈለ ያለው ዝቅተኛው ማህበረሰብ ነው ፤ የቤት ኪራይ የሚጨመርበትም እሱ ላይ ነው ጨማሪው የተሻለ ገቢ ያለው ነው ግብር የማይከፍለውም የተሻለ ገቢ ያለው ነው ከዚህ በላይ ኢፍትሃዊነት ምን አለ ? እንደ መንግሥት ይሄን የማስተካከል ግዴታ አለብን ግዴታችንን ለመወጣት ጥረት እናደርጋለን " ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የቤት ኪራይ ዋጋን ለመጨመር የሚሆን ምክንያት #ፈፅሞ የለም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትላንት ምሽት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር። በዚህ ቃለ ምልልስ ወቅትም ፤ ስለ " ጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከግብር ጋር በተያያዘም የቤት ኪራይ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። …
" ማህበረሰቡ መብቱን ያስከብር " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትላንት ምሽት ከብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ፤ የከተማው ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30 ድረስ [ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር እና ተከራይን ማስወጣት ] የሚከለክል ሕግ መኖሩን እንዲገነዘብ ብለዋል።

ከንቲባዋ ፤ " አሁንም የኑሮ ውድነቱ ቀጥሏል። " ያሉ ሲሆን  " ማሻሻያ ለካቢኔ ይቀርባል ፤ የማሻሻያ ሃሳብ ቀርቧል ለካቢኔ የሚቀርበው ይሄን መነሻ በማድረግ ማህበረሰቡ መብቱን ያስከብር እላለሁ ፤ " ብለዋል።

" [ጭማሪ የሚያደርጉትና የሚያስወጡት] የከተማ አስተዳደሩን ደንብ ጭምር ነው የጣሱት " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ማህበረሰቡ መብቱን ያስከብር " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትላንት ምሽት ከብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ፤ የከተማው ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30 ድረስ [ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር እና ተከራይን ማስወጣት ] የሚከለክል ሕግ መኖሩን እንዲገነዘብ ብለዋል። ከንቲባዋ ፤ " አሁንም የኑሮ ውድነቱ ቀጥሏል። " ያሉ ሲሆን  " ማሻሻያ ለካቢኔ ይቀርባል ፤…
" የቤት ኪራይ የተጨመረባችሁ ከሰኔ 20 ጀምሮ ቅሬታችሁን አቅርቡ " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የቤት ኪራይ የተጨመረባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እንዳያቀርቡ ጥሪ ቀረበ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ማንኛውም አከራይ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ የቤት ኪራይ መጨመር የማይችል መሆኑን መወሰኑን አስታውሷል።

በዚህም መሰረት ፤ የቤት ኪራይ የተጨመረባቸው የከተማው ነዋሪዎች ማስረጃዎቻቸውን በመያዝ ከፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሚኖሩበት ወረዳ የ " መልካም አስተዳደርና አቤቱታ ስራ ክፍል " እንዲሁም የ " ወረዳ ስራ አስፈፃሚ ቢሮዎች " በመገኘት ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

@tikvahethiopia