TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ3 ዓመት ህፃን ልጅ #አግቶ ቤተሰቦቹ 500 ሺህ ብር እንዲያመጡ ሲጠይቅ የነበረው አጋች በቁጥጥር ስር ዋለ።

በአማራ ክልል፤ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የቆላድባ ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ ደጀን አረጋ የ3 ዓመት ልጅ ህፃን አማኑኤል ወንድማገኝን ከደብረ ማርቆስ ከተማ 06 ቀበሌ በማገት ወደ ጠገዴ ወረዳ እርጎየ ቀበሌ ጫካ ውስጥ ይዞ ይገባል።

ህፃኑን በጫካው ውስጥ ለ7 ቀን ያክል ይዞ ቤተሰቦቹን 500 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ሲጠይቅ ከቆየ በኃላ ፖሊስ ባደረገው ኦፕሬሽን ህፃኑን ከአጓቾች እጅ ማስለቀቅ ችሏል።

ፖሊስ ህፃኑ ታግቶ የነበረበትን ጫካ በመክበብ እና የተኩስ ልውውጥ በማድረግ ለጊዜው ዋናው አጋች ቢያመልጥም የጉዳዩ ተባባሪ እንደሆነ የተነገረው ጣማለው አስፋ የተባለ ግለሰብ ህፃኑን እንደያዘ በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል።

ዋናው አጋች አቶ ደጀን አረጋን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው እንቅስቃሴም ግለሰቡን ሰኔ 14 በቁጥጥር ማዋል ተችሏል።

የሶሮቃ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ታግቶ የነበረውን ህፃን ለቤተሰቡ ካስረከበ በኃላ የማህበረሰቡ እሴትና ባህል መገለጫ ያልሆነ አፀያፊ ተግባር በዋና ተዋናይነት ፈፅሟል በሚል የተጠረጠረውን ደጀን አረጋን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተባባሪ አጋች ጣማለው አስፋ ቤተሰቦች ጉዳዩን በዋናነት እንዲከታተሉና ጥቆማ እንዲሰጡ ማድረጉን ገልጿል።

ሌሎች ልዩ ልዩ ዘዴዎችንም በመጠቀም ባደረገው ክትትል ሰኔ 14/2015 ዓ.ም ከአካባቢው ሚሊሻና ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ጠገዴ ወረዳ እርጎየ ቀበሌ ልዩ ስሙ " እምባ ጓዳድ " ከተባለ ቦታ ደጀን አረጋን በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል።

የሶሮቃ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤትም ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ተጠርጣሪውን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ሲባል የአካባቢው ማህበረሰብና መላው የፀጥታ መዋቅር ላደረገው ትበብር ምስጋና አቅርቧል።

በዚህና መሰል የወንጀል ተግባራት ላይ በሚሰማሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በቀጣይም በተጠናከረ መንገድ ርብርብ እንደሚደረግ አሳውቋል።

መረጃው የጠገዴ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#RosewoodFurniture

በዘመናዊ ማሽነሪ እና በ3D ዲዛይን የታገዘ፣ ለኣጠቃቀም ምቹ እና ወቅቱን የጠበቁ ዘመናዊ  የፈርኒቸር ስራዎች  ! 

ስራዎቻችንን ለማየት ቻናላችንን ይቀላቀሉ 
https://t.iss.one/R0seWood
https://t.iss.one/R0seWood
https://t.iss.one/R0seWood

👉🏼 ስልክ    :  📲 0905848586
👉🏼 ኣድራሻ : 📍4 ኪሎ አምባሳደር ሞል 2ኛ ፎቅ
                  📍ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ

ሮዝዉድ ፈርኒቸር 🙌
በታጣቂዎች #ታግተው የነበሩት የ " ሰዴን ሶዶ " የወረዳ አመራር ተገድለው ተገኙ።

በኦሮሚያ ክልል፤ ደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል።

የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃቻ ፤ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው አስክሬናቸው መገኘቱን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ወረዳው ለግድያው በክልሉ የሚንቀሳቀሰውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ተጠያቂ አድርጓል ፤ እስካሁን ከታጣቂ ቡድኑ ዘንድ የተሰጠ አስተያየት የለም።

አቶ በቀለ ፤ ከታገቱ በኃላ ያገቷቸው ታጣቂዎች እንዲለቀቁ ' 10 ሚሊየን ብር ' መጠየቃቸውን ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች መስማቱን ገልጿል።

የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቅ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ለተወሰኑ ሰዎች በወረዳው አስተዳዳሪ ስልክ ደውለው እስከ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን አመልክቷል።

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወረዳ ውስጥ ግለሰቦችን በታጣቂዎች እያታገቱ ከ200 ሺህ ብር አንስቶ እስከ 500 ሺህ ብር ድረስ እንደሚጠየቅባቸው ፤ ከዚህ ባለፈ ማሰቃየት እና ግድያ እንደሚፈፀም ከወረዳው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በታጣቂዎች #ታግተው የነበሩት የ " ሰዴን ሶዶ " የወረዳ አመራር ተገድለው ተገኙ። በኦሮሚያ ክልል፤ ደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል። የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃቻ ፤ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው አስክሬናቸው መገኘቱን የደቡብ ምዕራብ…
በታጣቂዎች #ታግተው የነበሩት የሰዴን ሶዶ የወረዳ አመራር ተገድለው ተገኙ።

በኦሮሚያ ክልል ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል።

የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው መገኘታቸውን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሃይሉ አብዶ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግረዋል።

አቶ ኃይሉ ፤ " አቶ በቀለ ቃቻ በአዳማ ከተማ ስብሰባ ላይ ነበሩ። ባለፈው ቅዳሜ ወደ ቤተሰብ ተመለሱ ፤ በዕለቱ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ከቤታቸው ባልታወቁ ሃይሎች ታፍነው ተወስደዋል "  ሲሉ ተናግረዋል።

ቅዳሜ ምሽት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው የተወሰዱት የወረዳው አስተዳዳሪ ላለፉት ሁለት ቀናት የት እንዳሉ ሳይታወቅ ቆይቶ ባለፈው ማክሰኞ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ ተገድለው ተገኝተዋል ሲሉ ገልጸዋል።

የአቶ በቀለ አስክሬን በቶሌ ወረዳ፣ ኢሉ ወረዳ እና በበቾ ወረዳ መካከል በፀጥታ ኃይሎች አሰሳ መገኘቱ ተመላክቷል።

አቶ በቀለ ፤ የወረዳው አስተዳዳሪ በመሆን ለሁለት አመታት ማገልገላቸው ፤ ከዚያ በፊት በትውልድ አካባቢያቸው በዳዎ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ማገልገላቸውን አቶ ኃይሉ ገልጸዋል።

አቶ ኃይሉ ፤ ለ ' ግድያው ተጠያቂው ' በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው መንግሥት " ኦነግ - ሸኔ " የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሃይል መሆኑን ጠቅሰዋል።

" አዎ፣ እንደ ህዝብ ጥቆማ እንደዛ የሚባል ነገር አለ። በተግባር ከወረዳችን ከተለያዩ ቦታዎች ሰዎች እየታገቱ ነው። የሚያግተው ይኸው አካል ነው። አንዳንድ ጠቆማዎችም አሉ፣ ታግተው የተለቀቁ ሰዎችም አሉ " ብለዋል።

መንግሥት 'ኦነግ ሸኔ' የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት  ስለ ውንጀላው እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።

በመንግስት ባለስልጣናት እና በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎችን በተመለከት ግን ታጣቂ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ነበር።

" 10 ሚሊዮን ብር ተጠይቋል "

የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ቅዳሜ ዕለት ከቤታቸው ከታገቱ ከአንድ ቀን በኋላ ታጣቂዎቹ አቶ በቀለ ቃቻ እንዲለቀቁ ' 10 ሚሊየን ብር ' መጠየቃቸውን ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች መስማቱን ገልጿል።

የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኃይሉ ፤ ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቅ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ለተወሰኑ ሰዎች በወረዳው አስተዳዳሪ ስልክ ደውለው እስከ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ ለወረዳው አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቀደም ብለው የሰጡት ማስጠንቀቂያ / ዛቻ አለ ? ወይንም በግላቸው ደውለውላቸው የጠየቁት ገንዘብ አለ ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ኃይሉ የአስተዳዳሪው ስልክ በታጣቂዎቹ እጅ ስለገባ ይሄን ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል።

" ዛቻ ወይም ማስጠቀቂያ እየተነዛበት እንደሆነ ሪፖርት ቀርቦ የሚያውቅ አይመስለኝም " ሲሉ አክለዋል።

ታጣቂዎቹ የወረዳውን አስተዳዳሪ ከእገታ ለማስለቀቅ የጠየቁት ገንዘብ ተሰጥቷቸው እንደሆነ ግልፅ  የሆነ ነገር ባይኖርም የተገደሉት " የጠየቁት ገንዘብ ስላልተሰጠ " ነው የሚል ግምት ግን አለ።

አቶ ኃይሉ ግን " ከዚህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ነገር ግን በቀጣይ ምርመራ ይታወቃል " ሲሉ ተናግረዋል።

በሁለት ቀናት ውስጥ የጸጥታ ሃይሎች አስተዳደሪውን ለማስለቀቅ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተገልጿል።

የተገደሉት አስተዳዳሪ ከ30ዎቹ - 40ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ባለትዳር እና የልጆች አባት ነበሩ።

" ለአንድ ግለሰብ 200 ሺህ፣ 300 ሺህ እና 500ሺ እየተጠየቀ ነው "

የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ኃይሉ ፤ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነን የሚሉ የታጠቁ ሃይሎች (መንግሥት ኦነግ - ሸኔ የሚላቸው) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወረዳ ውስጥ ግለሰቦችን እያገቱ ብዙ ገንዘብ እየጠየቁ በማሰቃየትና በመግደል ላይ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

" ፖለቲካ የማያውቁ እና ማንም ነገር ውስጥ የማይገቡ ገበሬዎችን በየቀኑ እያፈኑ ፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እየተጠየቀ ነው። " ያሉት አቶ ኃይሉ " ገንዘብ የሌለው ግለሰብ ሁለት መቶ ሺህ ፣ ሶስት መቶ ሺህ፣ አምስት መቶ ሺህ ብር ዘመዶቹ እየሰበሰቡ መስጠት የተለመደ ሆኗል " ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ፤ ልጆቻቸውን የማገትና በአሰቃቂ ሁኔታ የመግደል ሁኔታ መጨመሩንም አስረድተዋል።

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኃይሉ  አብዶ ፤ " መፍትሄው እርስ በእርስ ከመገዳደል ፤ አንድ ቋንቋ  እየተናገርን ከመጨራረስ ይልቅ በውይይት መፍታት ነው " ብለዋል።

መረጃውን ከ " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በታጣቂዎች #ታግተው የነበሩት የሰዴን ሶዶ የወረዳ አመራር ተገድለው ተገኙ። በኦሮሚያ ክልል ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል። የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው መገኘታቸውን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት…
የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ።

ከመኖሪያ ቤታቸው በታጣቂዎች ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው የተገኙት የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃቻ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል።

አቶ በቀለ ፤ ባለፈው ቅዳሜ ታፍነው ከታገቱ በኃላ ያገቷቸው ታጣቂዎች እንዲለቀቁ ' 10 ሚሊየን ብር ' መጠየቃቸው ተሰምቷል።

የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቅ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ለተወሰኑ ሰዎች በወረዳው አስተዳዳሪ ስልክ ደውለው እስከ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን አመልክቷል።

አቶ በቀለ ታፍነው ተወስደው ከታገቱ በኃላ ማክሰኞ ዕለት ተገድለው አስክሬናቸው ተገኝቷል።

@tikvahethiopia
#Agew

ከ1 ዓመት በላይ ጊዜ ወስዷል የተባለው " አንታጉ " የተሰኘ የአገውኛ ፊልም ዛሬ ተመረቀ።

ለመጀመሪያ ጊዜ በ " አገወኛ ቋንቋ " የተሰራው " አንታጉ " የአገወኛ ፊልም የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንግዳ ዳኛውን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

በፊልሙ የምረቃ ስነሥርዓት ላይ አቶ እንግዳ ዳኛው ፤ " አንታጉ የአገውኛ ፊልም አገዎች የቀደምት  የጥበብ ባለቤት መሆናቸውን ማሳያ ነው " ብለዋል።

መረጃው ከአዊ ኮሚኒኬሽን የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

አፖሎ ዘመደ ብዙ ነው። ከየትኛውም አማራጭ ወደ አፖሎ አካውንትዎ ገንዘብ ተቀማጭ አድርገው ቀለል ብሎት ይገበያዩ ::

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
ቀደምቷ አርዲ ለዲጂታል መስተንግዶውም ቀደምት እና ቀልጣፋ ናት!

አገልግሎቶቻችንን በተመለከተ ለጥያቄዎ ፈጣን ምላሽ፣ ጥቅሎች መግዛት፣ የሂሳብ መረጃ መጠየቅንና ሌሎች አገልግሎቶችን በ5 ቋንቋዎች በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት በምቾት ልታስናግድዎ ዝግጁ ነች፤ ከደንበኞች አገልግሎት ባለሙያዎቻችን ጋርም ታገናኝዎታለች!

በድረገፅ - ethiotelecom.et/
በፌስቡክ - facebook.com/ethiotelecom እና በትዊተር - twitter.com/ethiotelecom በመልዕክት መላኪያ ላይ
በዋትስዓፕ - wa.me/251994000000?text
በቴሌግራም - t.iss.one/EthiotelecomChatBot አርዲን ይጠይቁ

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#ራያ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ፈፅመውታል ያሉትን ተግባር አጥብቀው ተቹ።

ምን ተፈጠረ ?

የአማራ ክልል እንዲሁም የትግራይ ክልል ጥያቄ ከሚያነሱባቸው አካባቢዎች አንዱ የራያ አካባቢ እንደሆነ ይታወቃል።

በዚህ አካባቢ ከማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዘ የቆየ ጥያቄ ያለ ሲሆን አንዳንድ አካባቢዎች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከትግራይ አስተዳደር ወጥቶ ወደ አማራ ክልል ገብቷል።

ከትላንት በስቲያ የአሜሪካ ኤምባሲ ልዑካን ዲፕሎማቶች በራያ አለማጣ አካባቢ እንደነበሩ ተነግሯል።

ታዲያ የትግራይ አስተዳደር በ " ኃይል ተወረው ተይዘውብኛል " በሚለው አካባቢ ላይ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች መገኘታቸው እንዳስቆጣው ተሰምቷል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

አቶ ጌታቸው ፤ " የአሜሪካ ኤምባሲ የዲፕሎማቶች ልዑካን ቡድን አላማጣ ነበር ፤ ምን ሲሰሩ እንደነበር ፈጣሪ ነው የሚያውቀው " ያሉ ሲሆን " ዲፕሎማቶቹ የአማራ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ በኃይል የያዙትን አካባቢ መጎብኘታቸው፣ የትግራይ ግዛቶች በጽንፈኛ ኃይሎች የኃይል ቁጥጥር ስር መሆኑን እንደመቀበል ይቆጠራል " ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በአካባቢው ላይ የተገኙት በሕገወጥ አስተዳደሩ ባለሥልጣናት በተቀነባበረ ድራማ ላይ መሆኑን ፤ ይህን ግን ለምን እንዳደረጉ ገልፅ እንዳልሆነ ጠቁመው ድርጊቱ አሜሪካ ለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ያላትን ቁርጠኝነት የሚጻረር በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

በሌላ በኩል ፦ ከሰሞኑን የፌደራል መንግስት ለሚቀጥለው በጀት ዓመት " በራያ እና አካባቢው ለሚገኙ መዋቅሮች የሚመድበው ድጎማ " ወደ ትግራይ ክልል እንዳይተላለፍ የ145 ሺህ ሰዎች ፊርማ ያለበት ሰነድ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መቅረቡን ከ " ኢትዮጵያ ኢሳይደር " ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፊርማውን አሰባስቦ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያስረከበው የ " ወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ " ነው።

ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በደብዳቤ የቀረበው ይህ ጥያቄ የሰሜኑ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ስር የነበሩ አራት መዋቅሮችን የሚመለከት ሲሆን እነዚህ መዋቅሮች በትግራይ ክልል ስር በነበሩበት ወቅት " የማንነት ጥያቄ ይነሳባቸው " እንደነበር ተገልጿል።

ነገር ግን የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ " ራሱን በራሱ ለማስተዳደር " መቻሉን ኮሚቴውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስገባው ሰንድ ላይ ገልጿል።

የወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የአካባቢው ህዝብ " ከፌደራል መንግስቱ ሊያገኝ ይገባ የነበረው በጀት " የሚላከው " በትግራይ ክልል በኩል ነው " በመባሉ ምክንያት እስካሁን የገንዘብ ድጎማ አለማግኘታቸውን ሰነዱ አስረድቷል።

@tikvahethiopia