TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ ዛሬ ከንጋት 12 ሰዓት ጀምሮ በዎላይታ ዞን የድጋሜ የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ እየተካሄደ ይገኛል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በዎላይታ ሶዶ ምርጫ ጣቢያዎች የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

Photo Credit : NEBE & FBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa በሀዋሳ ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሜላት መሀመድ ትላንት ሰኔ 5/2015 ዓ.ም ቀትር ላይ በሁለት ተሽከርካሪ በመጡ ግለሰቦች 'መጠለፏን' ቤተሰቧቿ ተናግረዋል። የ14 ዓመት ከ 8 ወር ታዳጊዋ ሜላት ከትምህርት ቤት ወደ ወደ መኖሪያ ቤቷ በመመለስ ላይ እያለች በሀዋሳ ከተማ ሞኖፖል ተብሎ በሚጠራው አከባቢ " ቤት ልትደርስ ጥቂት ሜትሮች ሲቀራት " በሃይል ታግታ…
" የጠለፋ ወንጀሉ ሰለባ የሆነችው ታዳጊ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች " - የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ

ሐዋሳ ከተማ ውስጥ ታዳጊ ሜላት መሐመድን በመጥለፍ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪውን ግለሰብ ትናንት እሁድ ምሽት 5: 30 አካባቢ  ይርጋለም ከተማ ዉሃ ልማት ቀበሌ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ ተሸሽጎ መገኘቱን ረዳት ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ ተናግረዋል።

በጠለፋ ወንጀል የተጠረጠረው ሳምሶን ሸኑ የተለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የወንጀል ማጣራት ስራ እየተከናወ እንደሚገኝ ረዳት ኢንስፔክተር መልካሙ ገልጸዋል።

የጠለፋ ወንጀሉ ሰለባ የሆነችው ታዳጊ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዷን በማከል።

ታዳጊዋ ከጠለፋ መለቋቋን ታላቅ ወንድሟ እንዳልካቸው አስራትም አረጋግጧል።  ታዳጊዋ በሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት እያገኘች እንደምትገኝም ገልጿል።

ታዳጊ ሜላት መሐመድ ፤ ከቀናት በፊት በሐዋሳ ከተማ #በኃይል ወደ ተሽከርካሪ እንድትገባ ተደርጋ መወሰዷን ቤተሰቦቿ መግለፃቸው ይወሳል።

በወቅቱ የአካቢው ሰው ሊታደጋት መሞከሩን፤ ሜላት ስትጮህም ይዟት የጠፋውን መኪና የፊትለፊቱን መስታወት የአከባቢው ሰው መሰባበሩን ፤ ከዛ በኋላ እየበረረ ማመለጡን የታዳጊዋ ቤተሰቦች ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር በሚያቀኑ የጭነት የተሽከርካሪ ሾፌሮች እና ረዳቶች ላይ " እገታ ተፈፅሟል " ሲሉ የታጋች ቤተሰቦች ገለፁ። ድርጊቱ ዛሬ ንጋት 12 ሰዓት  " አሊዶሮ " በሚባለው አካባቢ ስለመፈፀሙ አንድ ወንድሜ ታግቷል ያለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ጠቁሟል። የታጠቁ አካላት " እስከ ሰላሳ / 30 የሚሆኑ ሰዎችን ከመኪናቸው አስወርደው አግተዋቸዋል ከነሱ ውስጥ ደግሞ አንዱ…
" ለማን ነው አቤት የምንለው ? "

በታጣቂዎች የታጋቱ ሹፌሮች እና ረዳቶች ገንዘብ እየተጠየቀባቸው መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ።

ከቀናት በፊት ሹፌሮች እና ረዳቶች ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር እና በተቃራኒው ጉዞ ላይ የነበሩ አዳራቸውን " አሊዶሮ " ላይ ካደረጉ በኃለ በታጣቂዎች መታገታቸውን ቤተሰቦች መግለፃቸው ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ድርጊቱ በተፈፀመበት ዕለት መልዕክት ካደረሱት ተጨማሪ የታጋች ወዳጆችን ፣የሚያውቋቸውን እንዲሁም በዕለቱ ጉዞ ላይ ከነበሩ አባላት መልዕክት ተቀብሏል።

አንድ በዕለቱ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ እየመጣ የነበረ የቤተሰባችን አባል ፤ ገብርጎራቻ 2 ሰዓት በደረሱበት ወቅት " አሊዶሮ " ላይ ወደ 14 መኪና ሹፌርና እርዳት መወሰዳቸውን እንደሰሙ ገልጿል። " ለ4 ሰዓታት ያህል ቁመን መከላከያ መጥቶ ነው መንገዱ ተከፍቶ ወደ አ/አ የሄድነው " ሲል አስረድቷል።

አንድ የቤተሰባችን አባል " የኔም ጓደኝዬ ከታገቱት አንዱ ነው " ሲል ቃሉ ሰጥቶ ትላንት ለቤተሰቡ ተደውሎ " አንድ ሚሊዮን ብር ላኩ " መባሉንና ቤተሰብም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

" ለማን ነው አቤት ምንለው ? " ሲልም አክሏል።

እንዲሁ ሌላ የቤተሰባችን አባል ፤ " አሊደሮ " ላይ ከታገቱት መካከል ሁለቱ የቻግኒ ልጆች እንደሆኑና  ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊየን ብር መጠየቁን እንደሚያቅ ፤ ለቤተሰቦችም ይህንን ብር ካላመጡ " እንገላቸዋለን " የሚል ማስፈራሪያ መላኩን አስረድቷል። በዚህም ምክንያት ቤተሰቦቻቸው በጭንቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

እገታው በተፈፀመበት ዕለት መልዕክቱን የላከልን አንድ ወንድሙ መታገቱን ያመለከተ የቤተሰባችን አባልም፤ አጋቾቹ ደውለው " 1 ሚሊዮን ብር አምጡ እኛ እነሱን አንፈልግም  " ማለታቸውን ገልጿል።

ሹፌሮች እና ረዳቶች መታገታቸው ከተነገረ ቀናት ቢያልፍም ከሚመላከታቸው የመንግሥት አካላት በኩል አንድም የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

Via @tikvah_eth_BOT

@tikvahethiopia
#Tigray

ቻይና ፤ ትግራይን #መልሶ_ለመገንባት ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የተመራ የልኡኳን ቡድን በትግራይ ክልል የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

ልዑኩ በጉብኝቱ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደት ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ መወያየቱ ተነግሯል።

በውይይቱ ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ የቻይና መንግስት የሰብአዊ ድጋፍ እና ትግራይን መልሶ በመገንባት ረገድ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ልኡኩም ፤ የቻይና መንግስት ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እና ትግራይን መልሶ ለመገንባት ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፁን ድምፂ ወያነ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ሻሸመኔ

ዛሬ በሻሸመኔ ከተማ ቆሻሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረ ቦምብ ፈንድቶ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ የሚተዳደሩ አራት ልጆች ህይወታቸው አለፈ፡፡

ልጆቹ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ ባለበት ሰዓት ከተጠራቀመ ቆሻሻ ውስጥ ቦምቡ መፈንዳቱን ፖሊስ ገልጿል።

በዚህም የአራት ልጆች ህይወታቸው ሲያልፍ፥ ሁለት ህፃናት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

Via OBN / FBC

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EthioOnlineMarket

የነዚህ ማጠቢያ ማሽኖች ዋጋ ፤ የብዙ ነገሮችን ጨዋታ ቀይሯል! ዋጋቸውን ለማየ : https://t.iss.one/EOMMarket

- የመረጡትን እቃ ይዘዙን፤ያሉበት ድረስ በነፃ  እናደርሳለን : 𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲  ☞0929181818 / 0909868788

ይምጡ የሽያጭ ማእከሎቻችን ይጎብኙ፤ ተደስተው ይመለሳሉ !
አድራሻችን፦
• ቁጥር 1:- መገናኛ, ቤተልሄም ፕላዛ  የሱቅ
                 ቁጥር  G-10 ግራውንድ 
•ቁጥር 2:- ሜክሲኮ, ኬኬር ህንፃ የሱቅ  
                ቁጥር #338
•ቁጥር 3:- አያት አደባባይ , AAT CITY   
                  CENTER G-11 ግራውንድ
𝕵𝖔𝖎𝖓 𝖔𝖚𝖗 𝖈𝖍𝖆𝖓𝖓𝖊𝖑 @EOMmarket
            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ዛሬ በዎላይታ ዞን ሲካሄድ የዋለው ያድጋሜ የሕዝበ ውሳኔ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒድት መጠናቀቁ ተገልጿል።

አሁን ላይ በየምርጫ ጣቢያዎቹ የድምጽ ቆጠራ እየተከናወነ  እንደሚገኝ ተነግሯል።

በነገው ዕለት ማለዳ የቆጠራው ውጤት ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በየምርጫ ጣቢያዎቹ የሕዝብ ፍሰት በመኖሩ የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ተራዝሞ መጠናቀቁን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ዋቢ በማድረግ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ NEBE

@tikvahethiopia