TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ

ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የነበረንን ጥያቄ ለማቅረብ በወጣንበት " የኃይል እርምጃ ተወስዶብናል " ሲሉ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅሬታ አቀረቡ።

ተማሪዎቹ ጥያቄ የነበረው ከመውጫ ፈተና በኃላ ለሚካሄደው ምርቃት " ምርቃቱ ላይ ለመገኘት የወደቀ ያለፈ መባል የለበትም ፤ አንድ ላይ መመረቅ አለብን ፤ ለ16 አመት ያክል የለፋንበት ፣ ቤተሰብም ብዙ የደከመበት ነው ይሄ ጉዳይ መልስ ያሻዋል " በሚል መሆኑን ገልጸዋል።

" ይህን ጥያቄያችንን ድንጋይ፣ ዱላ ሳንይዝ ምላሻ እንዲሰጠን ለመጠየቅ ሰልፍ ብናደርም የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም፣ ከፍተኛ ድብደባ በመፈፀም፣ የወንድ እና የሴቶች ዶርም ድረስ በመዝለቅ ጉዳዩን የማያውቁ ተማሪዎችን ጭምር በመደብደባ እና በማዋከብ ጥያቄያችንን ለማፈን ሞክረዋል " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኳቸው የቪድዮ ማስረጃዎች የፀጥታ ኃይሎች ተማሪዎችን በደቦ ሰደበድቡ ፣ ወደ ሴቶች ዶርም ዘልቀው ገብተው ተማሪዎችን በኃይል ሲያስወጡ ያሳያል።

ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋሙ ሰራተኞች በኩል ሃስብ ለመቀበል ጥረት አድርጓል። አንድ በሳምንት መጨረሻ ቀናት ለማስተማር በተቋሙ የተገኙ መምህር ጉዳዩን ውስጥ ሆነው ሲከታተሉ እንደነበር ገልጸዋል።

የፀጥታ ኃይሎች ወደ እርምጃ የገቡት ተማሪዎቹ የግቢ ውስጥ እየጮሁ የመማር ማስተማር ስራውን ሲያውኩ፣ መንገድ በድንጋይ ሲዘጉ፣ ንብረት ላይ ጉዳት ለማድረስ እንዲሁም በፀጥታ ኃይሎች ላይ ትንኮሳ ለመፈፀም በሞከሩበት ወቅት መሆኑን አመልክተዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጩ ቪድዮዎች የነበረውን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳይ አይደለም የሚሉት መምህሩ ግቢውን ለመረበሽ የሞከሩ ተማሪዎች እንዲሁም በተማሪዎች ላይ ከልክ ያለፈ እርምጃ የወሰዱ የፀጥታ ኃይሎችን እኩል ማውገዝ ይገባል ብለዋል።

" ተማሪዎቹን ንጹሕ፤ የጸጥታ ሀይሉን በመወንጀል የሚሰራ ዜና ሚዛናዊነት የሚጎድለው ሁኔታውን የማያስረዳ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላ አንድ የግቢው ሰራተኛ የፀጥታ ኃይሎች ወደ እርምጃ የገቡት የግቢው የመማር ማስተማር ስራ ሲታወክ እና ግቢው ሲረበሽ ነው ብለው የተወሰደው እርምጃ ግን ልክ ያለፈ መሆኑን ገልጸዋል።

መልዕክታቸውን የላኩ ተማሪዎቹ ግን በግቢው ሰራተኞች በኩል የተሰጠው ሃሳብ የማይቀበሉት ሲሆን አጠቃላይ የነበረው ሁኔታ ሰላማዊ እንደነበር፤ ተማሪዎች ግቢ ለመረበሽ ያደረጉት ሙከራ እንደሌለ፣ የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰድ በጀመሩበት ወቅት ግን መንገድ ለመዝጋት መሞከሩን አመልክተዋል።

አንድ የግቢው ተማሪ፤ " በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ከማቅረብ በዘለለ ድንጋይ በፀጥታ ኃይሎች ላይ ለመወርወር የሞከረ  ፤ ዓመታትን በተማረበት ተቋም ጥፋት ለማድረስ የሞከር ተማሪ አልነበረም ብሏል።

" በእርግጥ መንገድ ዘግተዋል መንገድ የዘጉበት ምክንያት ፖሊስ ተማሪን መምታት ሲጀመር ነው " ሲል ገልጿል።

በርካታ ተማሪዎች የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ መውሰዳቸው፤ ተቋሙ ለሰለማዊ ጥያቄ ከውይይት ይልቅ ኃያልን አማራጭ ማድረጉን የሚገልፅ መሆኑን እና በተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች መጎዳታቸውን፣ ንብረትም መዘረፉን አመልክተዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠንን ምላሽ ተከታትለን እናሳውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት እንደሚሰጥ የተማሪዎችን ምረቃ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት እንደሚካሄድ በመርሃግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ መሆናቸውን ማሳወቁ ይታወሳል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-11

@tikvahethiopia
" በባለፈው ጦርነት የተጎዳነው ሁላችንም ነን " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትግራይ ክልል ከ510 ሚሊየን ብር በላይ የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሌሎች የከተማው ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን መቐለ ተገኝተው ነው ያስረከቡት።

ድጋፉ ህዝቡንና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር የተበረከተ ሲሆን ከተደረገው ድጋፍ ከ218 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው የጥሬ ገንዘብ ሲሆን እና ቀሪ ደግሞ የተለያዩ ቁሳቁሶች ናቸው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ " ከሰላም እንጂ ከጦርነት ትርፍ ስለማይገኝ ሰላማችንን ማጽናት አለብን " ያሉ ሲሆን " በባለፈው ጦርነት የተጎዳነው ሁላችንም ነን " ብለዋል።

" በየትኛው የሀገሪቱ ጫፍ የሚያጋጥም ጉዳት የሁሉም ጉዳት በመሆኑ የወደመውን በትብብር መልሰን እንገነባለን " ሲሉም አሳውቀዋል።

የትግራይ ግዜያዊ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቃል በገባው መሠረት ለትግራይ ክልል ድጋፍ ለማድረግ ቅድሚያ ተነሳሽነቱን ወስዶ ተግባራዊ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።

" ተጋግዘን በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ወደ ልማት እና እድገት መመለስ አለብን " ብለዋል።

መረጃው ከAMN ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በባለፈው ጦርነት የተጎዳነው ሁላችንም ነን " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትግራይ ክልል ከ510 ሚሊየን ብር በላይ የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሌሎች የከተማው ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን መቐለ ተገኝተው ነው ያስረከቡት። ድጋፉ ህዝቡንና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር የተበረከተ ሲሆን ከተደረገው ድጋፍ ከ218 ሚሊየን…
#Tigray

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ አስተዳደር በትግራይ ክልል ለሚያስገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ በከንቲባ አዳነች አቤቤ እና አቶ ጌታቸው ረዳ ተቀምጧል።

የመሰረት ድንጋዩ የተቀመጠው ትምህርት ቤት " ሰማዕታት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት " የሚሰኝ ነው።

የትምህርት ቤቱ ሙሉ ወጪ የሚሸፈነው በአዲስ አበባ #ህዝብ እና መስተዳደር ነው ተብሏል።

Photo Credit : Demtsi Woyane

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #ባህርዳር

" ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

" ልዩነቶችን በሕግ፣ በሠላም እና በመነጋገር ለመፍታት የአማራ ሕዝብ ፍላጎት አለው " - ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

ባህር ዳር የሚገኙት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ልዑካቸው ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጋር እንዲሁም ከህብረተሰቡ ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ውይይት ላይ አቶ ጌታቸው ረዳ " ዋጋ የማይጠይቅ የሠላም አማራጭ ሳለ በፖለቲከኞች የጠብ ርሃብ ምክንያት በርካታ ጉዳቶች ተከስተዋል " ብለዋል፡፡

" ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው " ያሉ ሲሆን " አሁን የጦርነትን ምዕራፍ ዘግተን የሠላም አማራጮችን የምናይበት ጊዜ ነው " ብለዋል፡፡

" የሁከት እና ግርግር አጀንዳዎች የሚታያቸው ይኖራሉ፤ ነገር ግን ለሕዝብ ካሰብን እና ከሠራን ከሠላም ውጭ የተሻለ አማራጭ የለንም " ሲሉ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው ፤ " ልዩነቶች ይኖራሉ  ያሉትን ልዩነቶችን ግን በሕግ፣ በሠላም እና በመነጋገር መፍታት የአማራ ሕዝብ ፍላጎት ነው ብለዋል።

" የአማራ ክልል ሕዝብ እና መንግሥት ለሠላም አማራጮች ዝግጁ ነው " ሲሉም ተደምጠዋል።

" የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ወደ ቀደመው ሁኔታው መመለስ አለበት፣ ትራንስፖርት እና የንግድ እንቅስቃሴ መጀመር ይኖርበታል " ያሉት ዶ/ር ይልቃል " ተከባብረን እና ተደማምጠን ልዩነቶቻችን ለመፍታት መሥራት ይጠበቅብናል " ብለዋል።

የፖለቲካ አመራሩ የጀመረውን የሠላም ግንኙነት የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች በተለይ ደግሞ አዋሳኝ አካባቢ ያሉ የሁለቱም ክልል ሕዝቦች አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Via AMC

@tikvahethiopia
የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ
===========
ደንበኞች ከውጭ ሀገራት የተላከላቸውን ገንዘብ ወይም በባንኩ የሚመነዝሩትን የውጭ ሀገር ገንዘብ የሚያስቀምጡበት የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡

የቁጠባ ሂሳቡ በርካታ ጥቅሞች አሉት፡፡

• ከመደበኛው የቁጠባ ሂሳብ እጥፍ ወለድ ያስገኛል፤
• ደንበኞች ገንዘብ ከውጭ ሀገራት ሲላክላቸው ወይም በባንኩ ሲመነዝሩ የአየር ሰዓት ስጦታ ያገኛሉ፤
• የሂሳቡ ባለቤቶች ለውጭ ሀገር ጉዞ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎታቸው ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፤
• ደንበኞች ከባንኩ ጋር ከሚሠሩ ድርጅቶች ለሚያገኙት አገልግሎት ወይም ለሚገዙት እቃ በፖስ ሲከፍሉ ቅናሽ ያገኛሉ፤
• ሌሎችንም በርካታ ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡

ሂሳቡን በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ ይክፈቱ፤ ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ይደውሉ!

ይቆጥቡ፤ የበለጠ ያግኙ!

(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
#Update

የተሻሻለው የ " ንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያ " ሊወጣ ነው !

ከስልሣ ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ የወጣውን አዲሱን የንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያዎች ውስጥ እና የመጀመርያው የሆነው በዚህ ዓመት ፀድቆ ሥራ ላይ እንደሚውል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

የንግድ ሕጉ ማስፈጸሚያ ይሆናል የተባለው ይህ የመጀመርያው መመርያ የ " አክሲዮን ማኅበራት " ን የሚመለከት ነው፡፡

በዚሁ መሠረት ፤ " የአክሲዮን ማኅበራት ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር መመሪያ " በሚል የተዘጋጀው ረቂቅ መመርያ ተዘጋጅቶ በመጠናቀቁ በዚህ በጀት ዓመት ይፀድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

መመርያው ምን ይዟል ?

- በንግድ ሕጉ ላይ " የመተዳደሪያ ደንብ ያስፈልጋል ? አያስፈልግም ? " የሚለውን ጉዳይ ለማብራራትና በቀላሉ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎችና በሁሉም ፈጻሚ ተቋማት ወጥ በሆነ መንገድ እየተተረጎመ እንዲፈጸም ለማስቻል በሚረዳ መልኩ በመመርያው እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡

- መመርያው አክሲዮን ማኅበራት ሲደራጁ ገንዘብ ከሕዝብ የሚሰበሰብበት መንገድ ላይ ምን መሆን እንዳለበት በግልፅ ያመላክታል። ኅብረተሰቡ እንዳይበዘበዝ እንዴት መተዳደር እንዳለበት በዝርዝር የተቀመጡ አንቀጾችን አካቷል፡፡

አደራጆች የምሥረታ ሒደት ለማካሄድ የሚያስከፍሉት አስተዳደራዊ ወጪ የሚዋጣው ገንዘብ ከአምስት በመቶ መብለጥ እንደሌለት በረቂቅ መመርያው ተመላክቷል፡፡

በምሥረታ ሒደት ከፈራሚዎች አስተዳደራዊ ወጪን ለመሸፈን ገንዘብ የተሰበሰበ እንደሆነ፣ ማኅበሩ ሲመሠረት የምሥረታ ወጪን ለማኅበሩ ማስተላለፍ የሚቻለው የተሰበሰበው አስተዳደራዊ ክፍያ የምሥረታ ወጪውን ለመሸፈን ያልበቃ መሆኑን የምሥረታ ኦዲተር ካረጋገጠ ብቻ ነው።

በምሥረታ ኦዲተር ሪፖርት መሠረት ለአስተዳደራዊ ወጪ ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቀሪ ገንዘብ ያለ እንደሆነ ማኅበሩ ሲመሠረት ፣ ለማኅበሩ ገቢ መደረግ ይኖርበታል። ይህም ቀድሞ ለአገልግሎት ተብሎ የተሰበሰበን ገንዘብ ከብክነት ያድናል።

- አደራጆች በአክሲዮን ምሥረታ ወቅት ከፈራሚዎች ሚሰበሰበውን መዋጮ በባንክ በዝግ ሒሳብ ሲያስቀምጡ በገበያው ላይ ካለው የወለድ ምጣኔ አንፃር ተመጣጣኝ የሆነ ወለድ እንዲያፈራ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው።

- የማኅበሩ ምሥረታ በስኬት የተጠናቀቀ እንደሆነ ዋና ገንዘቡና ያስገኘው ወለድ ለማኅበሩ ገቢ መደረግ አለበት።

- የግል አክሲዮን ማኅበር ሚመሠረተው በመሥራቾች እንደሚሆን ይደነግጋል። መሥራቾች በባለአክሲዮንነት ከሚያገኙት መብት ውጪ በመሥራችነታቸው ምክንያት የሚከፈላቸው የአገልግሎት ክፍያ አይኖርም።

- በአክሲዮኖች ላይ #ከአንድ_መቶ_ብር (100) ያነሰ ዋጋ የተጻፈባቸው አክሲዮኖች ያላቸው ማኅበራት፣ ይህ መመርያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ ቢያንስ ወደ አንድ መቶ ብር በማሳደግ መመሥረቻ ጽሑፋቸውን አሻሽለው ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

- የአክሲዮን ኩባንያዎች የሚያደራጁ ሰዎች ያለባቸው ኃላፊነት ምንድነው የሚለውም በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን በአዲሱ የንግድ ሕግ የአክሲዮን ኩባንያዎች የኤሌክትሮኒክስ ስብሰባ ማድረግ የሚችሉ በመሆኑ፣ ይህንን ለማስፈጸም ዝርዝር ጉዳዩ በዚህ መመርያ ተገልጿል።

" የቦርድ ስብሰባ " የሚደረግበት የኤሌትሮኒክ ዘዴ የተሰብሳቢዎችን ማንነት ለመለየት የሚያስችል ፤ የውይይቱን የድምጽ ቅጂ በትክክል መያዝ የሚችል መተግበሪያ ያለውና ፤ ሚስጢራዊነትንም መጠበቅ የሚችል መሆን አለበት።

በመመስረቻ ጽሑፍ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በስተቀር እያንዳንዱ የቦርድ አባል በዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ ላይ በአካል የመገኘት መብት ያለው ሲሆን፣ የቦርድ ስብሰባን በኤሌትሮኒክ ዘዴ ለመሳተፍ ዳይሬክተሩ ጥያቄ ካላቀረበ በቀር፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊያስገድድ ወይም በአካል የመሳተፍ መብቱን ሊገድብ እንደማይችች ተቀምጧል፡፡

- ከመመርያው መውጣት በኋላ ብዙ አክሲዮን ያላቸው ኩባንያዎች በቀላሉ ስብሰባቸውን እንዲያካሂዱ ዕድል ይሰጣቸዋል።

- የአክሲዮን ዝውውሮችን በተመለከተ በዚህ መመርያ ግልጽ ድንጋጌ ያስቀመጠ ሲሆን፣ በተለይ የግለሰብ አክሲዮንን ለማስተላለፍ #የትዳር_አጋር_ስምምነት ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡

"በግል የአክሲዮን ማኅበር" ውስጥ በግለሰብ የተያዘ አክሲዮንን ፦
- በሽያጭ ፣
- በስጦታ ፣
- በመያዣ
- በሌላ በማንኛውም መንግድ ለማስተላለፍ በሕግ ወይም ደግሞ በመመሥረቻ ጽሑፍ ከተገለጹት ቅድመ ሁኔታዎች በተጨማሪ አስተላላፊው በአስገዳጅነት ያገባ ከሆነ የትዳር አጋሩ ውል ለማዋዋል እና ሰነድን ለመመዝገብ ' ሥልጣን ባለው አካል ፊት ቀርቦ ' ስምምነቱን መግለጽ አለበት።

ያላገባ ከሆነ / ከሆነች አግባብ ካለው የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ተገቢውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል በሚል መመርያው ይደነግጋል፡፡

- ሁሉም የአክሲዮን ማኅበራት ይህ መመርያ ተፈጻሚ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ድረገጽ ማበልጸግና በድረገጹ ላይ በሕጉ መሠረት ተገቢነት ያላቸውን መረጃዎች ማስቀመጥ አለባቸው። ይህንን ድንጋጌ የማይፈጽም የአክሲዮን ማኅበር የንግድ ፈቃዱ ሊታገድ እንደሚችልም ተደንግጓል፡፡

- አክሲዮን ለመሸጥ ስለሚወጡ #ማስታወቂያዎች በመመርያው ላይ ተቀምጧል።

ይህም ፤ " በማንኛውም በሕዝብ ማኅበር በምሥረታ ሒደት አክሲዮን ለመሸጥ በሚተላለፍ ማስታወቂያ ስለ ታሳበው የንግድ ሥራ አዋጭነት በጠቅላላው ከመግለጽ በስተቀር ስለሚያስገኘው የትርፍ መጠን በምን ያህል ጊዜ ለኢንቨስትምንት የተከፈለው ገንዘብ እንደሚመለስ ወይም ሌሎች በተጨባጭ ሊረጋገጡ የማይችሉ መረጃዎችን መስጠት አይቻልም " በሚል ተጠቅሷል፡፡

በማንኛውም #ዋና_ገንዘብ በማሳደግ ሒደት በግል ማኅበር ወይም በሕዝብ ማኅበር፣ ለሕዝብ አክሲዮን ለመሸጥ የሚደረግ ማስታወቂያ ማኅበሩ አስቀድሞ ያገኘውን ትርፍ የሚገልጽ ከሆነ፣ ያለፉትን ሦስት ተከታታይ ዓመታት የትርፍ ውጤት መግለጽ ግዴታ አለበት፡፡

ነገር ግን ማኅበሩ #ለወደፊት የሚኖረውን አትራፊነት በቁጥር ወይ በመጠን መግለጽ አይቻልም።

ሚኒስቴሩ (ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር) ወይም አግባብ ያለው ሌላ የመንግሥት መሥሪያ ቤት አሳሳች ናቸው ብሎ ከወሰነ፣ አክሲዮን ለመሸጥ ለሕዝብ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች እንዲቋረጡ ለማዘዝ ይችላል።

.
.
.

መመርያው በአጠቃላይ ከአክሲዮን ምሥረታ ጀምሮ እስከሚፈርስበት ጊዜ ድረስ #ዝርዝር የአሠራር ጉዳዮችን በመተንተን የቀረበ ነው።

በአዲሱ የንግድ ሕግ መመርያ የማውጣት ሥልጣን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፡፡

መመርያን ያዘጋጀው በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ሲሆን በተለይ #የሕዝብን_ገንዘብ ተቀብለው የሚያስተዳድሩ የአክሲዮን ማኅበራት ላይ መጠነኛና ቁጥጥር ለመዘርጋት የሚያስችል ነው፡፡

(ሪፖርተር ጋዜጣ የረቂቅ መመርያው ዝግጅት ተሳታፊ የሕግ ባለሙያ አቶ ፈቃዱ ጴጥሮስን ዋቢ በማድረግ ያወጣው)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ

ልክ እንደ 2015 ዓ/ም በጀት ሁሉ በ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የአዳዲስ የመንግሥት ሰራተኞች ቅጥር እንደማይፈፀም ተነግሯል። ይህም ከምክር ቤት አባላት በኩል ጥያቄ አስነስቷል።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ባለፈው ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወስኖ ወደ ፓርላማ የተላከውን የ2016 ዓ/ም የ801.65 ቢሊዮን ብር በጀት ረቂቅ ላይ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

በማብራሪያቸው ላይ የተያዘው በጀት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ1.9 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸው በጀቱ ሀገራዊ አቅምን የዋጋ ግሽበትን መከላከል ላይ ታሳቢ አድርጎ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

በጀቱ ለሚፈለጉ የተለያዩ የልማት ስራዎች በቂ ባለመሆኑ አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይጀመሩ እንዲሁም አዲስ የመንግስት ሰራተኞች ቅጥር እንደማይፈፅም አሳውቀዋል።

አቶ አህመድ ሽዴ ፦

" የ2016 መደበኛ በጀት በየመስሪያ ቤቱ ያለውን አዲሱን አደረጃጀት ታሳቢ በማድረግ የበጀት አጠቃቀም በቁጠባ እና በውጤታማነት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን እንዲሁም አዳዲስ የሰራተኞች ቅጥር እንደማይኖር ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው "

የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

የምክር ቤት አባላት ለሚኒስትሩ ከጠየቁት ጥያቄዎች አንዱ ዘንድሮም የአዲስ ሰራተኞች ቅጥር አለመኖሩን በተመለከተ ነው።

ጥያቄ ከጠየቁ የምክር ቤት አባል መካከል አንድ አባል " አንድ የመንግስት ኃላፊነት ለዜጎቹ ስራ መፍጠር ነው ያ ማለት የመንግስት ስራ ብቻ መፍጠር አይደለም በተለያየ መንገድ ግን ስራ መፍጠር የመንግስት ኃላፊነት ነው አንዱ ክፍል ምናልባት መንግስት በራሱ ሊቀጥር ይችላል ይሄንን ዘግተን በዘለቄታዊነት ልንዘልቅ አንችልም። ስለዚህ እነዚህ ነገሮች መታሰብ ስላለባቸው ከገቢ አሰባሰባችን እና ከወጪ አጠቃቀማችን ጋር ውጤታማ የሆነ ነገር መሄድ አለብን " ብለዋል።

ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል ደግሞ ፤ " በየዓመቱ አምናም እንደሚታወቀው በየመስሪያ ቤቱ አዳዲስ ሰራተኞችን መቅጠር አይቻልም በሚል ነበር በጀት የፀደቀው ዘንድሮም የቀረበው በየመስሪያ ቤቱ አዳዲስ ሰራተኞች መቅጠር እንደማይቻል ታሳቢ ተደርጎ ነው። እንደዚህ በየዓመቱ እያፀደቅን የምንሄድ ከሆነ አንደኛ የተማሩ ምሁራን ኃይሎችን ለስደት ልንዳርጋቸው እንችላለን ፤ ሁለተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ ሊቀጥል ይችላል እንደሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ፤ ሶስተኛ ምስኪን አርሶ አደሮች ብዙ መስእዋትነት ከፍለው ነው ልጆቻቸውን አስተምረው የሚያወጡት (ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት) " ስለዚህ የነዚህ ዕጣ ፋንታቸው ምንድነው ሲሉ ጠይቀዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ፤ " ስራ መፈጠር አለበት " የሚለው የሚያስማማ ሃሳብ ቢሆንም መንግሥት ግን በዋነኝነት የስራ ዕድል መፍጠሪያ አይደለም ብለዋል።

" መንግሥት ስራ መፍጠር አለበት በተቻለ መጠን ግን በዋነኛነት የግሉ ሴክተርን ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ይኖርብናል " ሲሉ ለቀረበው ጥያቄ መልሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ምን አለ ?

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨው ዜና " ግነት የበዛበት ነው " አለ።

ዩኒቨርሲቲው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ፤ ከዩኒቨሲቲው እውቅና ውጪ ባልተፈቀደ ሁኔታ በቀን 03/10/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) " አንፈተንም  "በሚል  በዋናው ግቢ በዉስን ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተሞክሮ ነበር ብሏል።

" የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ በጥቂት የማህበራዊ ሚዲያዎች የፀጥታ ችግር እንዳለና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መስተጓጎል እንዳለ በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጨ  እንዳለ ለመገንዘብ ችለናል " ብሏል።

" በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው ዜና ግነት የበዛበት " ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " የተፈጠረውን መጠነኛ ያለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲው ደህንነት ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከሀዲያ ዞን ፖሊስ፣ ከሌሞ ወረዳ ፖሊስ እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት በመስራት በአስተማማኝ ሁኔታ ሠላማዊ የሆነ የመማር ማስተማር ሥራ ማስቀጠል ተችሉዋል " ብሏል።

" በዩኒቨርሲቲው የተማሪ ረብሻ፣ የንብረት ዉድመት እንዲሁም የጎላ የፀጥታ ችግር በሌለበት አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች የሰላም አምባሳደር የሆነውን የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስም ሆነ ብሎ ለማጠልሸት ጥረት ማድረጋቸው ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናስገነዝባለን " ሲል ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ባስተላለፈው መልዕክት በነበረው መጠነኛ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በተማሪዎች ላይ " ምንም ዓይነት ጉዳት " ያለመድረሱንና ዩኒቨርሲቲው ወደተለመደው መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ መመለሱን አሳውቋል።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ላይ በቪድዮ እና በፎቶ ስለተያዙት ማስረጃዎች ምንም ያለው ነገር የለም።

የተቋሙን ወቅታዊ መግለጫ የተመለከቱ ተማሪዎች መግለጫው ፍፁም የነበረውን ሁኔታ በትክልል የማይገልፅ ፣ የሆነውን ነገር ሁሉ ኢትዮጵያውያን በቪድዮ ያዩት መሆኑን አስረድተው ከልክ ያለፈ እርምጃ / ድብደባ በተማሪዎች ላይ የፈፀሙ አካላት በህግ ሊጠየቁ እንደሚገባ አመልክተዋል።

More : @tikvahUniversity

@tikvahethiopia