TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ በአዲስ አበባ የቤት (የማይንቀሳቀስ) ንብረት ግብር ክፍያ ተጀምሯል።

ከመሬት ጋር ከተያያዘ ንብረት መንግሥት የሚያገኘው ገቢ አነስተኛ በመሆኑ በመሬት እና በሕንፃዎች ላይ ዋጋን መሰረት ያደረገ ግብር መጣል በማስፈለጉ በከተሞች አካባቢ ያሉ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ ግብር ለመሰብሰብ የሚያስችልን ሕግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀ ወራቶች አልፏል።

መንግሥት ከንብረት የሚሰበሰበውን ግብር ለከተሞች መሰረተ ልማቶች እና ፍላጎትን ለማጣጣም እንደሚያውለው ገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየሞችን እና ሪል ስቴቶችን ጨምሮ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ቤቶች የቤት ግብር እንዲከፍሉ ተወስኖ ሥራው ተጀምሯል።

ዛሬ በተለያዩ ክ/ከተማዎች ዜጎች የኮንዶሚኒየም ግብር ለመክፈል የተራዘመ ሰልፍ ይዘው ፣ ከሌሊት ጀምረው ወረፋ እየያዙ ፣ የነዋሪነት መታወቂያ ፣ የቤቱ ባለ እድል የሆኑበትን ወይም ግዢ የፈፀሙበትን እንዲሁም የባለቤትነት ካርታ ሰነዶችን እየያዙ ሲከፍሉ ውለዋል።

አገልግሎቱ ከፍተኛ መጨናነቅ የታየበት ሲሆን ይህንን መጨናነቅ ለመቅረፍ የየቤቱ ብሎክ ወረፋ እንዲወጣለት በማድረግ እንግልት ለመቀነስ ጥረት ስለመደረጉ ተነግሯል።

የንብረት ግብር ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ባለቤቶች ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል፣ የኪራይ ዋጋን በማናር የኑሮ ውድነትን ያንራል፣ ቋሚ ደሞዝተኛዎችን የበለጠ እንዲቸገሩ ያደርጋል ፣ ተበድሮ ቤት የመስራት ፍላጎትን ያቀዛቅዛል ፣ ነዋሪዎች ቤተሰብን ለማገዝ የሚያደርጉትን ጥረት ያዳክማል በሚል ይተቻል።

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ (ጋዜጠኛ ሰለሞን ሙጬ) ነው።

@tikvahethiopia
የንብረት ግብር . . .

" ግብር ከፋዮች የሚከፍሉት የንብረት ግብር ተከራይን የማይመለከትና ወደ ተከራይ መተላለፍ የሌለበት መሆኑን ማወቅ አለባቸው " - የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ

ነዋሪዎች ስለ ንብረት ግብር ምን አሉ ?

" የኑሮ ውድነቱ ከብዶ ባለበት ሁኔታ ግብሩ መሻሻሉ የመጨረሻ ጫናው ተከራዮች ላይ እንዳያርፍ ያደርጋል።

መንግሥት ገበያውን መቆጣጣር አለበት።

ግብርን መክፈል የሥልጣኔ መገለጫ ቢሆንም፣ የከፋዮች የገቢ መጠንና ሌሎች ጫናዎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት "

የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ፤ የንብረት ግብር ማስተግበሪያ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስማማው ሙልጌታ ፦

" የንብረት ግብር አሁን እንደ አዲስ እንዲታይ የሆነው በየወቅቱ ዓመታዊ የኪራይ ዋጋን መሰረት በማድረግ ሊሻሻል ሲገባ ለረጅም ጊዜ ሳይሻሻል ቆይቶ ዘንድሮ በመሻሻሉ ነው።

የንብረት ግብር በሀገራችን የተጀመረው በ1937 ዓ.ም በወጣው አዋጅ ሲሆን፣ አዋጁ በ1968 ዓ.ም አዋጅ ቁጥር 80/1968 ተብሎ ተሻሽሎ እስካሁን እየተጠቀምንበት ነው፡፡

መንግሥት በየዓመቱ ለሚያወጣው የመሰረተ ልማት ወጪ በጀት የሚሸፍነው በሚሰበስበው ገቢ ነው። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግን ይህ አልተቻለም።

ከዚህ ቀደም ሲከፈል የነበረው የንብረት ግብር ዝቅተኛ ነበር።

ለማሳያም አዲስ አበባ ውስጥ ፦
👉 ወደ 2 ሺህ 500 የቤት ባለቤቶች ከአንድ ብር በታች፤

👉 23 ሺህ 421 ግብር ከፋዮች ከ10 ብር በታች፤

👉 ወደ 84 ሺህ የሚሆኑት እስከ መቶ ብር ብቻ ሲከፍሉ ነበር።

96 በመቶ የሚሆኑት የንብረት ግብር ከፋዮችን ከ5 መቶ ብር በታች ይከፍሉ ነበር ፤ ይህ ደግሞ አዲስ አበባ ካለው ንብረት አንጻር በጣም ዝቅተኛ ነው።

የግብር ግመታው የተደረገው አዋጁ ዓመታዊ የኪራይ ግብርን መሰረት በማድረግ ከአንድ እስከ አራት በመቶ የግብር ጭማሪ ማድረግ እንደሚቻል ባስቀመጠው መሰረት ተሰልቶ ነው።

ግምቱ ንብረቱ አሁን ባለው ዋጋ ላይ ተመስርቶ የሚሰራ ሲሆን፣ የቦታ ደረጃ፣ የቤቱ ዓይነት እና የአገልግሎት ዓይነትን መሰረት በማድረግ ነው።

የግብር ግመታ ከመደረጉ በፊት ጥናት ተደርጎ ንብረቶቹ ወደ ተመሳሳይ ደረጃ በማምጣት ምደባ ተደርጓል፤ ግብር ከፋዮች በሚሞሉት የመሬት ስፋት መሰረት ግምቱ ይሰራል።

መንግሥት ግብርን መሰብሰቡ አንዱ የዋጋ ግሽበትን መከላከያ መንገድ ነው፤ ገቢ በሥርዓት ከተሰበሰበ የልማት ጥያቄዎች በትክክል መመለስ ስለሚቻል በቀጣይነት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ይቻላል።

ግብር ከፋዮች የሚከፍሉት የንብረት ግብር ተከራይን የማይመለከትና ወደ ተከራይ መተላለፍ የሌለበት መሆኑን ማወቅ አለባቸው፤ መንግሥትም የተከራዮችን ጫና ለመቀነስ ቋሚ ሥርዓት ለማበጀት እየሰራ ነው።

አቅመ ደካማ የሆኑ እና ገቢ የሌላቸው ሰዎች ካሉ በታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት የግብር ምህረት ስላለ በወረዳ ደረጃ ተጣርቶ የምህረቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ። "

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
* Update

በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ከኦሮሚያ ክልል አመራሮች ጋር 5 ሰዓታት የፈጀ ውይይት መደረጉ ተሰምቷል።

ዛሬ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በአቶ ሽመልስ አብዲሳ ከተመራ የኦሮሚያ ክልል የሥራ ሀላፊዎች ጋር በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ ከቀኑ 9:00 እስክ ምሽት 2:00 ሰዓት ድረስ አምስት ሰዓታት የፈጀ ሰፊ ዉይይት መደረጉ የገልጿል።

በዉይይቱ ማጠቃለያ ላይ በተደረሰባቸው ነጥቦች ላይ በነገው እለት ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ በፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ የተገለፀ ሲሆን ሁሉም ሚዲያዎች በስፍራው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።

Via ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

@tikvahethiopia
በሲቢኢ ብር መተግበሪያ ነዳጅ መቅዳት ይበልጥ ቀላል ነው!
***************
ወደ ሲቢኢ ብር መተግበሪያ ‘Quick Pay’ በመግባት ‘Fuel Payment’ የሚለውን የአገልግሎት አማራጭ መርጠው
• የነዳጅ ቀጂውን የተመዘገበ ስልክ ቁጥር፣
• የሚገዙትን የነዳጅ ክፍያ መጠን፣
• የነዳጅ አይነት፣
• የሰሌዳ ቁጥርዎን፣ እና
• የሚስጥር ቁጥርዎን አስገብተው ክፍያውን በማከናወን ነዳጅ መቅዳት ይችላሉ፡፡

ስለሲቢኢ ብር አገልግሎት በቂ መረጃ ለማግኘት ወደ 951 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ!
*********************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#Kaffmen

ተጨማሪ ውበትን የሚያላብሱ እጅግ ዘመናዊ እና ዘናጭ የወንዶች የመመረቂያ ሙሉ ልብስ እና ለክረምት የሚሆኑ አልያም የሚዘንጡበት ጃኬቶች !

ይደውሉ ፦ +251912727762 ወይም https://t.iss.one/kaffmens ይጠቀሙ!
📍Address: Megenagna, Bethelhem Plaza Ground floor 08.

#Boutique #Menclothes #Mensfashion #Menssuit #Mensjacket
TIKVAH-ETHIOPIA
* Update በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ከኦሮሚያ ክልል አመራሮች ጋር 5 ሰዓታት የፈጀ ውይይት መደረጉ ተሰምቷል። ዛሬ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በአቶ ሽመልስ አብዲሳ ከተመራ የኦሮሚያ ክልል የሥራ ሀላፊዎች ጋር በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ ከቀኑ 9:00 እስክ ምሽት 2:00 ሰዓት ድረስ…
#አሁን

" በሸገር ከተማ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ብዛት ያለው መስጂድ ፈርሷል " - ሼህ ሐጂ ኢብራሂም

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም የተመራ ልዑክ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የኦሮሚፓ ክልል የሥራ ሀላፊዎች ጋር በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ የደረሱበትን ሁኔታ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እየተሰጠ ነው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ባደረጉት ንግግር ፤ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ብዛት ያለው መስጊድ መፈረሳቸውን ገልፀዋል።

በንግግራቸው ፤ ድርጊቱን በመቃወም ሁሉም ሙስሊም ላደረገው ተጋድሎ በኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ስም አመስገነዋል እንዲሁም ለመላው ሙስሊም መፅናናትን እና ሰብረን ተመኝተዋል።

መግለጫው አሁንም ቀጥሏል።

Credit : Harun Media

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሸገር ከተማ በፈረሱ መስጂዶች ዙሪያ ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር የተደረገውን ውይይት ተከትሎ የተሰጠ መግለጫ ከላይ ተያይዟል። Via ኡስታዝ አቡበከር አህመድ @tikvahethiopia
በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ ከኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገው በዉይይቱ ላይ በሙስሊም ተወካዮች ከተነሱት ነጥቦች መካከል፦

- በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች የመስጂድ መሬትን በህጋዊ መንገድ የማግኘትና የመሥራት እንዲሁም ለተሠሩት መስጂዶች ካርታና የማስፋፊያ መሬት የማግኘት ሁኔታ ላይ በርካታ ችግሮች እንዳሉ በዝርዝር ተብራርተዋል።

- የሸገር ከተማ አሰተዳደር ከፕላን ዉጭ ተሠርተዋል ያላቸውን መስጂዶች ለማፍረስ ሲነሳ የሚመለከተውን የእስልምና ጉዳዮች አካላትን እንዳለወያየ፥ እንዲሁም በጉዳዩላይ እንወያይ በሚል በተደጋጋሚ ጊዜ የቀረበውን ጥያቄ ተቀብሎ ለማወያየት አለመሞከሩ ተገቢ አለመሆኑ በቅሬታ መልክ ቀርቧል።

- ሕዝበ ሙስሊሙ የሸገር ከተማ መስጂድ ፈረሳ ጋር በተያየዘ በተፈጠሩት ሁኔታዎች እጅጉን መጎዳቱንና ማዘኑን በማብራራት ተገቢውን #ካሳና #የሞራል ህክምና እንደሚያስፈልገው ተጠቅሷል፡

- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም ሆነ ሕዝበ ሙስሊሙ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ከተሞችን ለማዘመን የሚደረገውን እቅድን፥ ልማትንም ሆነ አድገትን የሚደገፍው እንጂ የሚቃወመው እንዳልሆነ ሆኖም እቅዱ በቂ የእምነት ተቋማትን ለአማኞች ማቅረብንና ሰው ተኮር መሆን እንደሚገባው ተብራርቷል።

- በሸገር ከተማ አስተዳደር ዉስጥ ያለ ፕላንና ሕጋዊነት ተሠርተዋል በሚል የፈረሱት 22 (ሃያ ሁለት) መስጊዶች መሆናቸውን በመጥቀስ ለሕዝበ ሙስሊሙ የመስጊጅ ጥያቄዎች በሙሉ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚገባ ተነስቷል

- ቀደም ብሎ በጉዳዩ ላይ ከጅምሩ በመነጋገር መፍታት እየተቻለ እስከ ትናንትናው እለት ድረስ መሰል ዉይይት ሳይደረግ መስጂዶችን ወደ ማፍረስ በመግባቱ በመንግስትና በሕዝብ መካከል ቅሬታ ፈጥሮ ጉዳዩ እስከ ነፍስ መጥፋት ማምራቱ እጅግ የሚያሳዝን መሆኑን፤

- የጸጥታ አካላት ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ በቀጥታ በመተኮስ ሙስሊሞችን መግደላቸውና ማቁሰላቸው ተገቢ አለመሆኑን እንዲሁም ንጹሃን ላይ በመተኮስ የገደሉና ያቆሰሉ አካለት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሸገር ከተማ ስለፈረሱት መስጂዶች ጉዳይ ከኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገው በዉይይቱ ላይ በሙስሊም ተወካዮች ከተነሱት ነጥቦች መካከል፦ - በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች የመስጂድ መሬትን በህጋዊ መንገድ የማግኘትና የመሥራት እንዲሁም ለተሠሩት መስጂዶች ካርታና የማስፋፊያ መሬት የማግኘት ሁኔታ ላይ በርካታ ችግሮች እንዳሉ በዝርዝር ተብራርተዋል። - የሸገር ከተማ አሰተዳደር ከፕላን…
#Update

" ሕዝበ ሙስሊሙ ያቀረባቸውና የሚያቀርባቸው የመስጂድ ጥያቄዎች #በፕላኑ መሠረት ምላሽ ይሰጣል " - አቶ ሽመልስ አብዲሳ

ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በተደረገው ውይይት በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኩል የተጠቀሱት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው ፦

1. ቀደም ብሎ በጉዳዩ ላይ ዉይይት አለመደረጉ ስህተት መሆኑን ገልጸዋል።

2. በተፈጠረው ሁኔታ ሕይወታቸውን ላጡት ሙስሊሞች ማዘናቸውን ገልጸዋል።

3. የሸገር ከተማ የሃይማኖትን እሴትን መሠረት አድረጎ እንደሚገነባ እና የእሰልምናን ጨምሮ የሌሎችም ቤተእምነቶችም ተቋማት በብዛት በሸገር ከተማ ፕላን ዉስጥ እንደተካተቱ።

4. አስፈላጊውን የቤተእምነት መሥሪያ መሬቶችን በፕላኑ መሠረት ለምዕመኑ እንደሚሰጥና በቆርቆሮ ሳይሆን የከተማዋን ፕላን የሚመጥን በርካታ ዘመናዊ መስጊዶች በከተማው እንዲሰሩ እንደሚፈልጉ።

5. በሸገር ከተማ ላይ በሀገር ደረጃ ሊጠቀስ የሚችል ትልቅና ዘመናዊ መስጂድና ለሌሎች እምነት ተቋማት መሥሪያ ቦታ እንደሚሰጥ።

6. በሸገር ከተማ ለኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ የሚሆን መሬት እንደሚሰጥ።

7. ሸገር ከተማ ከ20 እስከ 30 ሚሊዮን ነዋሪዎች ያላት፥ ዘመናዊና በፕላን ብቻ ግንባታ የሚካድባት ከተማ ሆኖ ለመግንባት ሕግ ወጥ ግንባታን መከላከል፥ የተገነቡትን #ማፍረስ_እንደሚቀጥል ለዚህ ሂደት የእምነት ተቋማት ተባባሪ እንዲሆኑ እንፈልጋለን ብለዋል።

8. አዲሱ የሸገር ከተማ ፕላን ወደ ተግባር እስኪገባ ድረስ ሙሉ ለሙሉ መኖሪያ ቤቶች ባልፈረሱባቸው አከባቢዎች ለሚኖሩ ሙስሊሞች በጊዜያዊነት የሚሰግዱባቸው መስጊዶች የኦሮሚያ ክልል መጅሊስና የሸገር ከተማ አስተዳደር በጋራ በመጋገር መስጂድ መሥሪያ ቦታ እንዲያዘጋጁ።

9. የሸገር ከተማ ማስተር ፕላን በመጪው ሀምሌ ወር ወደ ተግባር ማዋል ከመጀመሩ በፊት በማስተር ፕላኑ ለእምነት ተቋማት የተዘጋጀውን ስፍራዎችን የሙስሊም ተወካዮች ከክልሉ መንግስት ጋር በጋራ ቀድመው ፕላኑን እንዲመለከቱና እንዲያረጋግጡ፡፡

10. በሸገር ከተማ ሕዝበ ሙስሊሙ ያቀረባቸውና የሚያቀርባቸው የመስጂድ ጥያቄዎች በፕላኑ መሠረት ምላሽ እንደሚሰጥ።

11. ሸገር ከተማን ጨምሮ በመላው ኦሮሚያ ክልል ከዚህ ቀደም ሲደረግ እንደነበረው የእምነት ተቋማት እና የመቃብር ሥፍራ መስጠት እንደሚቀጥል።

12. በሸገር ከተማ ዉስጥ ካሉት ስምንት መቶ (800) የሁሉም እምነት ተቋማት መካከል 656(ስድስት መቶ ሀምሳ ስድስት) የሚሆኑት ከፕላን ዉጭ የተሠሩ በመሆናቸው እነዚህን የሚገነባውን ከተማ ፕላን የማይመጡትን የተለያዩ ቤተእምነቶችን ወደ በሕጋዊና ከተማውን በሚመጥኑ ተቋማት ለመተካት የሚደረገውን ሂደት የኦሮሚያ ክልል መጅሊስም ባለበት የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አቅሙን በማጠናከር በዉይይት የእምነት ተቋማቱ ራሳቸው መፍረስ ያለባቸውን እንዲያፈርሱ እንጂ ከአሁን በኋላ መንግስት በራሱ ማፍረስ እንደሚያቆም ገልጸዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ያለምንም ልዩነት የታሠሩ ሙስሊሞች በጠቅላላው እንደሚፈቱ እንጠብቃለን " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

የታሰሩ ሙስሊሞች ያለምንም ልዩነት እንደሚፈቱ እንደሚጠብቅ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገልጿል።

ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የታሠሩትን ሙስሊሞችን መፈታትን አስመልከቶ ዛሬ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ከፌደራልና አዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮች ጋር ዉይይት እንደሚደረግ ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ላይ ተነግሯል።

በዚህም ውይይት ፤ ያለምንም ልዩነት የታሠሩት ሙስሊሞች በጠቅላላው እንደሚፈቱ እንደሚጠብቅ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በአንዋር እና ኑር መስጂድ በሸገር ከተማ የፈረሱትን መስጂዶችን በመቃወም ላይ እያሉ የተገደሉ ሙስሊሞችን ቤተሰቦችን አላህ መጽናናቱን እንዲሰጣቸው ለሟቾች ደግሞ አላህ የሸሂደትነት (ሰማዕትነትን) ደረጃ እንዲለግሳቸው ምክር ቤቱ ተማፅኗል።

በሸገር ከተማ በፈረሱት መስጂዶች ምትክ ከሚሠሩት መስጂዶች መካከል አንዱ የ " ሸሒዶች መስጂድ " ተብሎ እነርሱን ለማስታወስ እንደሚሰየም ተገልጿል።

በመስጂዱ ቅጥር ጊቢ ዉስጥም የሟቾች ስም ዝርዝር በጉልህ በሚታይ መልኩ እንደሚፃፍ ተመላክቷል።

@tikvahethiopia