TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፀጋ በላቸው የት ናት ? ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ፤ ነዋሪነቷ በሀዋሳ ከተማ የሆነች የዳሽን ባንክ (ዋርካ አካባቢ) ሰራተኛ እንዲሁም የአላሙራ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነች ፀጋ በላቸው የተባለች ግለሰብ በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ታፍና መወሰዷና የት እንዳለች ማወቅ እንዳልተቻለ በስፋት እየተነገረ ይገኛል። ድርጊቱ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ/ም መፈፀሙ የተነገረ ሲሆን ድርጊቱን…
ፖሊስ ስለ ወ/ሪት ፀጋ በላቸው ምን አለ ?

" ከጠለፋ ወንጀል ጋር የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር አውያለሁ " - የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ

የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በፀጋ በላቸው ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል።

ፖሊስ በመግለጫው " የከተማች ነዋሪ በሆነችው ወ/ሪት ፀጋ በላቸው ላይ የደረሰባት የጠለፋ ወንጀል ጉዳዩን አስመልክተው ቤተሰቦቿ በእለቱ ለመናኸሪያ ፖሊስ በመቅረብ አቤቱታቸውን አሰምተዋል " ብሏል።

ይህን ተከትሎ መምሪያው ተፈፀመ በተባለው ወንጀል መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

የከተማው ፖሊስ ፤ የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ጭምር አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክቷል።

የተበዳይ ቤተሰብ በትዕግሥት እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርቧል።

የምርመራው ሂደት ምን ላይ ደርሷል ?

ፖሊስ እንዳለው ፤ የወንጀሉ ድርጊት የተፈፀመው በሀዋሳ ከተማ በመናኸሪያ ክ/ከተማ ሲሆን ወ/ሪት ፅጌ በላቸው የተባለች ግለሰብ በቀን 15/9/2015 ዓ.ም " ተጠልፋ የት እንደደረሰች አናውቅም " በማለት ቤተሰቦቿ ለመነኸሪያ ክ/ከተማ ፖሊስ ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ምርመራ ተጀምሯል ብሏል።

የምርመራው ሂደትም በቀጣይ በከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አማካይነት በቅንጅት ሊመራ መቻሉን አመልክቷል።

በኋላም የምርመራው እና ተበዳይን ለማግኘት እና ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክሉሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በቅንጅት የተመራ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።

ከወ/ሪት ፅጌ በላቸው የጠለፋ ወንጀል ጋር የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ አሳውቋል።

" ጥቆማው ከተደረገበት እለት ጀምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸውና የፀጥታ አካላትና ፖሊስ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪው ሣጅን የኋላ መብራቴ እና የተጠለፈችውን ወ/ሪት ፅጌ በላቸው ይዞ ከተሰወረበት ቦታ አድኖ ለመያዝ ጥረትና ክትትል እየተደረገ ይገኛል " ሲል አሳውቋል።

ወ/ሪት ፀጋን ከነተጠርጣሪው ለመያዝ ህብረተሰቡ የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ በነዚህም የስልክ ቁጥሮች 0964504677 / 0969415272 ጥቆማ እንዲሰጥ የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮ_ቴሌኮም

የኢትዮ ቴሌኮምን ዕለታዊ የድምጽ ጥቅሎቻችን በአነስተኛ ዋጋ ሱገዙ ተጨማሪ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ጥቅል ስጦታ ያገኛሉ!

ጥቅሎቹን በቴሌብር ከ10% ተጨማሪ ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል እና *999# ያገኟቸዋል
#EthiomartShopping

ሴኩሪቲ ካሜራ ሽያጭና ነፃ ገጠማ : 0911582926

security camera CCTV (ባለ 4 አና ባ 8 ካሜራ) ለቤትዎ፤ ለድርጅት፤ ለሱቅ፤ ለፋርማሲ፤ ለዳቦ ቤት፤ ለቡቲክ፤ ለህንጻዎ ፤ ለመጋዘንዎ አና ለንብረትዎ የአመታት ልምድ ባለው ድርጅታችን ሴኩሪቲ ካሜራ ያስገጠሙ።

- 4 ካሜራዎች :- 4 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች  35,000 ብር
-8 ካሜራዎች :- 8 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች 50,000 ብር

ቦሌ መድሀንያለም ቤዛ ህንጻ 208
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #የመውጫ_ፈተና ዘንድሮ 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል። በ2015 በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰበሰበው መረጀ መሠረት 240 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ይህ ያስታወቀው የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት እያቀረበ በመገኝበት…
#Update

በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 03 እስከ 13 /2015 ዓ.ም እንደሚከናወን ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ያደረገውን ወይይት ተከትሎ አገር አቀፍ የመውጫ ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡ በዚህም፡-

➤ በሰኔ 2015 ዓ.ም ሞዴል የመውጫ ፈተና ይሰጣል።

➤ የመውጫ ፈተናው ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

➤ ውጤት ከሐምሌ 09 እስከ 10/2015 ዓ.ም በተቋማቱ ይገለጻል፡፡ (ተማሪዎች ከሐምሌ 08 ጀምሮ የፈተና ቁጥራቸውን በማስገባት ኦንላይን ማየት ይችላሉ።)

➤ የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ከሐምሌ 10 እስከ 17/2015 ዓ.ም ይከናወናል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል ! ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች። ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ። ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ…
#Update

አሜሪካ ዩጋንዳ ላይ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል አስጠነቀቀች።

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ፤ ኡጋንዳ ትላንት ያፀደቀችውን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን #ወንጀል የሚያደርገውን ህግ " አሳፋሪ እና ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት " በማለት ተቃወሙ።

ባይደን ፤ " ይህ አሳፋሪ ድርጊት / ሕጉ መፅደቁን / በዩጋንዳ ውስጥ ያለው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ሙስና የቅርብ ጊዜ እድገት አመላካች ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንት ባይደን ፤ የአሜሪካ ብሄራዊ ደኅንነት ም/ ቤት የዩጋንዳው ሕግ አሜሪካ ከአገሪቱ ጋር ባሏት ግንኙነቶች ላይ ምን አንድምታ እንዳለው አጥንቶ እንዲያቀርብ አዘዋል ተብሏል።

ከህጉ ጋር በተያያዘ ፤ አሜሪካ ለኡጋንዳ የምትሰጠውን እርዳታና ኢንቨስትመንት ልታቆም እንደምትችል ባይደን አስጠንቅቀዋል።

የሕጉን ተፅኖ ከግምት በማስገባትም የዩጋንዳ የአጎዋ (AGOA) ተጠቃሚነት እንደሚገመገም አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንቱ በከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣ ወይም ሙስና ውስጥ በተሳተፈ ማንኛውም ሰው ላይ #ማዕቀብ እና ወደ አሜሪካ የመግባት #እገዳን ጨምሮ ተጨማሪ እርምጃዎችን እያጤኑ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ከባይደን በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ፤ ህጉን ተቃውመዋል ፤ መስሪያ ቤታቸውም የአሜሪካ ዜጎች ወደ ዩጋንዳ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ መመሪያ እንዲያወጣ አዘዋል።

የባይደን አስተዳደር የዩጋንዳ ፓርላማ አፈ ጉባኤ " አኒታ አሞንግ " አሁን ያላቸውን የአሜሪካ መግቢያ ቪዛ መሰረዙ ሮይተርስ ፣ እንዲሁም ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግበዋል።

ከዚህ ቀደም የዩጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፤ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ #በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ  " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉ ነበር የገለፁት።

ምንም እንኳን ምዕራባውያን ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት (ተመድን ጨምሮ) ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በዩጋንዳ ምድር የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል በሚያደርገው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን እንዳያኖሩና እንዳያፀድቁ ማስጠንቀቂያዎችን ቢሰጡም ፕሬዜዳንቱ ትላንት መጠነኛ ማሻሻያ የተደረገበትን ሕግ በፊርማቸው በማኖር #አቅፅድቀውታል

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

በሆቴሎች፤ በሱፐርማርኬቶችና በቅርንጫፎቻችን በሚገኙት የፖስ ማሽኖቻችን የቪዛና ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው ግብይትዎን ያቅልሉ፡፡

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተመረጠው ኮሚቴ ሥራውን በይፋ መጀመሩ ተገልጿል።

የግንቦት 2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በኦሮሚያና በደቡብ ኢትዮጵያ የሚሾሙ አባቶችን መልምሎ የሚያቀርብ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የተቋቋመው ኮሚቴ ዛሬ የመጀመሪያ ስብሰባውን በተሳካ ሁኔታ ያከናወነ ሲሆን ሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ/ም ምልመላውን ለማከናወን በሚያስችለው ጉዳይ ዙሪያ በመምከር ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Oromia

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፤ " የሕገ-ወጥ ቤቶች ፈረሳ ሒደት መስጅድ ላይ ያተኮረ አይደለም " አለ።

ዛሬ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ  አቶ ሃይሉ አዱኛ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት እየተካሄደ ስላለው የቤቶች ፈረሳ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸው ፤  ምንም እንኳን እነማን እንደሆኑ በግልፅ ያልተናገሩት " አንዳንድ አካላት " ሲሉ የጠሯቸው በኦሮሚያ ክልል ህገ ወጥ ግንባታዎችን የማፍረሱን ሥራ በአንድ ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ ማስመሰላቸው ፈጽሞ ትክክል አይደለም ብለዋል።

" የሕገ-ወጥ ቤቶች ፈረሳ ሒደት መስጅድ ላይ ያተኮረ አይደለም " ያሉት ኃላፊው " በክልሉ 600 በሚሆኑ ከተሞች በህገ-ወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶችን የማፍረስ ሒደት እንደሚከናወን ገልፀዋል።

ሕግ የማስከበር ስራው በዋናነት ህገ-ወጥነትን በዘላቂነት ለመከላከል ያለመ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ኃላፊው ይህ ስራ በሚሰራበት ወቅት የተለያየ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ፤ አካላት የአንድ ብሔርና ሃይማኖት እንደተጠቃ አድርገው በመገናኛ ብዙሃን የሚያራግቡት ትክክል አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ህገወጥ ግንባታ ሲካሄድ መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄም ፤ " መንግስት ኃላፊዎቹን ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን " ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ የተናገሩት አቶ ኃይሉ አዱኛ ፤ " የሃይማኖት ተቋማት እና የእምነቱ ተከታዮች እምነትን ተገን አድርገው ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላትን በጋራ ሊከላከሉ ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ በርካታ መስጅዶች እየፈረሱ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በተደጋጋሚ ማሳወቁ እንዲሁም መፍትሄ እንዲፈለግ ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ መፃፉ የሚዘነጋ አይደለም።

ምክር ቤቱ ከቀናት በፊት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ላይም በ " ሸገር ከተማ " ኢስላምንና ሙስሊሞችን በናቀ መልኩ በመስጂዶች ላይ እየተደረገ ያለው የጅምላ ፈረሳ ሂደት በአስቸኳይ እንዲቆም፥ እንዲሁም ለፈረሱት መስጊዶች የክልሉ መንግስት #ምትክ_ቦታ በመስጠት በአስቸኳይ ተመልሰው እንዲገነቡ በማድረግ ሕዝበ ሙስሊሙን በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ እንዲክስ ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል።

የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፤ በሸገር ከተማ አስተዳደር እስካሁን ከ19 በላይ መስጂዶች ፈርሰዋል ሲል መግለጫ መስጠቱ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሱዳን የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ እና ሱዑዲ አረቢያ አደራዳሪነት የተኩስ ማቆ ስምምነት ላይ ማድረሳቸው ቢነገርም እንደ ከዚህ በፊቶቹ ስምምነቶች ሁሉ ተጥሶ ካርቱም ትላትናም በፍንዳታ ስትናጥ መዋሏን ቪኦኤ ዘግቧል። የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ከሰኞ ምሽት ለአራት ሩብ ጉዳይ ይጀምራል የተባለና ለሰባት ቀናት የሚቆይ ነበር። ተኩስ ኡቅም ላይ ተደረሰ በተባለ በደቂቃዎች ውስጥ…
#Update

" ከዚህ ቀደም የተደረሱ የተኩስ አቁም ስምምነቶችን በተደጋጋሚ ተጥሰዋል " በሚል የሱዳን ጦር ከተኩስ አቁም ውይይቱ #ራሱን_ማግለሉ ተነገረ።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን የተኩስ አቁም ስምምነቶችን በመጣስ የከሰሰው የሱዳን ጦር በሰላም ንግግሩ ተሳታፊ አንሆንም ማለታቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በተደረሰው የአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከሆስፒታሎች እና ከመኖሪያ ህንጻዎች ለቀው እንዲወጡ የሚደነግግ ቢሆንም አንዱንም ተግባራዊ አላደረጉም ሲል ጦሩ ወቅሷል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱን በተደጋጋሚ በመጣሳቸው ጦሩ እዚህ ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የመንግሥት ባለስልጣን ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

ሰብዓዊ እርዳታን ተደራሽ ያደርጋል ተብሎ ከነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ጦሩ ራሱን ማግለሉንም ሮይተርስ የሱዳን የዲፕሎማቲክ ምንጭን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

በሱዳን ጦር መሪ መሪ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አርኤስኤፍ) መሪ ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄምቲ መካከል ጦርነቱ የተቀሰቀሰው ሚያዝያ 7/ 2015 ዓ.ም ነበር።

ጦርነቱ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በሺዎች የሞቱ ሲሆን እጅግ በርካቶች ወደ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ጨምሮ ወደ ሌሎችም ሀገራት ተሰደዋል።

ምንጭ፦ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ሮይተርስ ፣ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#TechnoMobile

በዓለም ላይ ግንባር ቀደም ከሆኑ የሞባይል ቴክኖሎጂ ብራንዶች አምራች የሆነው ቴክኖ ሞባይል በዛሬው እለት እጅግ ዘመናዊ የሆነውን የሞባይል ቴክኖሎጂ የደረሰበትን የመጨረሻ ግልጋሎቶችን የያዘውን የፋንተም ቪ ፎልድ (Phantom V fold) ሞዴል በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ባዘጋጀው ልዩ ስነስርዓት  አስተዋውቋል።

ቴክኖ ሞባይል የፋንተም ቪ ፎልድ (Phantom V fold) ሞዴል በኢትዮዽያ ገበያ ከመግባቱ አስቀድሞ ስለዚህ ሞዴል ልዩ ግልጋሎቶች ግንዛቤ እንዲያስጨብጥ እና ይዞኣቸው ስለሚመጣው አዳዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂዎች ለማስተዋወቅ በማሰብ ምርቱን የማስተዋወቅ ዝግጅት የኩባንያው ሀላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በታደሙበት ስነስርዓት ምርቱን አስመርቋል።

#ቴክኖ_ሞባይል