#ብርሃን_ባንክ
ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#MyWishEnterprise
DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።
• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT
+251-913-356384 +251-912-710661 +251-910-626917 +251-928-414395
+251-911-606068 +251-922-475851 +251-935-409319 +251-911-602664

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የሹመቱ ቀን #ወደፊት ይገለፃል " - ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን በተመለከተ አጭር መግለጫ ሰጥተዋል። ምን አሉ ? - የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ #በሰላም እና ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል። - ዛሬ የመጨረሻው አጀንዳ ላይ ብዙ…
#Update
የግንቦት 2015 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤ ባለ 10 ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
ዛሬ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን አለ ?
ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያኗ አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እና መንፈሳዊ ዕድገት ትኩረት በመስጠት ለቤተ ክርስቲያናን እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አሳውቋል።
ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል ፦
- በመላው አገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ካሉ ተቋማት ጋራ የሚሠራ፣ በሀገሪቱ መንግሥትም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የሚኖረው የሰላም ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
- በትግራይ ክልል በሚገኙት አህጉረ ስብከት ተቋርጦ የነበረው መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ግንኙነትን በተመለከተ ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ ተሠይሞ በሥራ ላይ የሚገኘው ልዑክ የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲቀጥል የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትን በማነጋገር ተልዕኮውን እንዲፈጽም ምልዓተ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡፡
- በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኖቻችን ያሉበትን ከፍተኛ ችግር ታሳቢ በማድረግ አስቸኳይ የሆነ ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ #ሃያ_ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ተወስኗል።
- በወቅታዊ ችግር ምክንያት በመላው ሀገራችን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ሁሉ በአጠቃላይ ችግሮቹን በጥናት በመለየት፣ ቤተ ክርስቲያኗ ምእመናን ልጆቿን በማስተባበር ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ የማጽናናትና የመጎብኘት መርሐ-ግብሮች እንዲደረጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
- መቐለ የሚገኘው የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የሠራተኞችን ደመወዝና የሥራ ማስኬጃ በጀት እንዲለቀቅና በ2016 በጀት ዓመት ተማሪዎችን በመቀበል መደበኛ የሆነ የመማር ማስተማሩ የሥራ ሂደት እንዲቀጥል መመሪያ ሰጥቷል፡፡
- በኦሮምያ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከት ተፈጥሮ በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በአህጉረ ስብከትና በአብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት ስለተቋረጠ፣ በርካታ ምእመናንና ካህናት በእስርና እንግልት ላይ ስለሚገኙ በዚሁ መነሻነት ችግሮች እንዲቀረፉና ወደ መደበኛው የአሠራር መዋቅር እንዲመለስ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን በመሠየም ከፌዴራልና ከኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመወያየት ችግሮች እንዲፈቱ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
- የመንፈሳዊ ኮሌጆች መከፈት እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከር በተመለከተ በኢሉ አባቦራ የመቱ ፈለገ ሕይወት የነገረ መለኮት መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲከፈት የተፈቀደ ሲሆን በሌሎች አህጉረ ስብከት ሊከፈቱ የታሰቡ ኮሌጆችን እና የአብነት ት/ቤቶችን መሠረታዊ ጥናት ተደርጎ ለ2016 ዓ.ም. የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
- ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ ክፍት በሆኑና በተደራቢነት በተያዙ፣ ጉልህና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው በኦሮምያ ክልልና በደቡብ ክልል ባሉ አህጉረ ስብከት ላይ 9 ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስመራጭ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡ ወደፊትም ተደርበው በተያዙና አስፈላጊ በሆኑ አህጉረ ስብከት እንደአስፈላጊነቱ በመንበረ ፓትርያርክ ተጠንቶ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

የሲቢኢ ብር ደንበኛ መሆን ቀላል ነው!
ባሉበት፣ በቀላሉ ይመዝገቡ!
=========
የነዳጅ ግዥ፣ የተለያዩ የአገልግሎት እና ሌሎች ክፍያዎችን በቀላሉ መፈፀም የሚያስችለው የሲቢኢ ብር አገልግሎትን እስካሁን መጠቀም ካልጀመሩ፣ አሁኑኑ የተንቀሳቃሽ ስልክዎን ተጠቅመው ባሉበት በቀላሉ ደንበኛ ይሁኑ፡፡
ደንበኛ ለመሆን፡
• ወደ *847# በመደወል፣ ወይም
• የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ በራስዎ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
በሲቢኢ ብር በቀን ውስጥ የሚያንቀሳቅሱትን የገንዘብ መጠን ገደብ ከፍ ለማድረግ ወደ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ አሊያም የሲቢኢ ብር ወኪል መታወቂያ ይዞ በመሄድ ምዝገባዎን ያጠናቁ!
************
የሲቢኢ ብር መተግበሪን ለማውረድ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

#EthiomartShopping
ሴኩሪቲ ካሜራ ሽያጭና ነፃ ገጠማ : 0911582926
security camera CCTV (ባለ 4 አና ባ 8 ካሜራ) ለቤትዎ፤ ለድርጅት፤ ለሱቅ፤ ለፋርማሲ፤ ለዳቦ ቤት፤ ለቡቲክ፤ ለህንጻዎ ፤ ለመጋዘንዎ አና ለንብረትዎ የአመታት ልምድ ባለው ድርጅታችን ሴኩሪቲ ካሜራ ያስገጠሙ።
- 4 ካሜራዎች :- 4 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች 35,000 ብር
-8 ካሜራዎች :- 8 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች 50,000 ብር
ቦሌ መድሀንያለም ቤዛ ህንጻ 208

#Update የግንቦት 2015 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤ ባለ 10 ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። ዛሬ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ምን አለ ? ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያኗ አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እና መንፈሳዊ ዕድገት ትኩረት በመስጠት ለቤተ ክርስቲያናን እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አሳውቋል።…
#ሰላም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ግጭቶች እና አለመግባባቶች በውይይት ይፈቱ ዘንድ የሰላም ጥሪ አቀረበች።
ይህን ጥሪ ያቀረበችው የ2015 ዓ/ም የግንቦት ርክበ ካህናት ጉባኤ መጠናቀቁን ተከትሎ ትላንት በሰጠችው መግለጫ ነው።
ቤተክርስቲያኗ በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታዩትን አላስፈላጊ ግጭቶች የዜጐች መፈናቀል፣ ስደት ተወግዶ ሁሉም ዜጋ በሀገሩ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት እንዲኖር፤ ለማድረግ ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ አስተላልፋለች።
ከዚህ በተጨማሪ ፤ ቤተክርስቲያኗ በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላም እና ዕርቅ እንዲሰፍን ተመኝታለች።

የቤት ማፍረስ ዘመቻው . . .
" ማካካሻ አለመሰጠቱ ወይም ጊዜያዊ መጠለያ አለመዘጋጀቱ አሳስቦናል " - የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም
በሸገር ከተማ አስተዳደር ፤ " ሕገ ወጥ ግንባታ " በሚል እየተካሔደ ካለው የቤቶች ፈረሳ ጋራ የተያያዙ፣ 100ሺሕ አቤቱታዎች እንደቀረቡለት፣ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እምባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ኃይሌ ለቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል አሳውቀዋል።
ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ምን አሉ ?
" በ2014 ዓ.ም. የበጀት ዓመት፣ ከመብት ጥሰት እና ከመልካም አስተዳደር ጉድለቶች ጋራ የተገናኙ ከ133 ሺሕ በላይ አቤቱታዎችን ተቀብለናል።
ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን አኀዝ የያዙት፣ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ ካለው የቤት ፈረሳ ጋራ የተያያዙ አቤቱታዎች ናቸው።
የሸገር ከተማ አስተዳደር ' ሕገ ወጥ ግንባታ ' እያለ ለሚያፈርሳቸው የመኖሪያ ቤቶች፣ ለነዋሪዎች ምትክ ቦታ አይሰጥም፣ ለተፈናቃዮችም ጊዜያዊ መጠለያ አያዘጋጅም።
ተቋማችን ፤ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት፣ በሕዝብ ላይ ለሚፈጽሟቸው አስተዳደራዊ በደሎች የመፍትሔ ሐሳብ በማቅረብ፣ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ይሠራል።
በዚህ ጉዳይ ላይ (በቤቶች ፈረሳ ጉዳይ) ከሸገር ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣናት ጋራ ብንወያይም በተጨበጭ መሬት ላይ እየሆነ ያለው ነገር በውይይቱ ከተነሣው የተለየ ነው።
' ሕገ ወጥ ግንባታ ' ተብለው የመኖሪያ ቤቶቻቸው ለሚፈርስባቸው ዜጎች የሚሰጥ ማካካሻ አለመኖር አሳስቦናል።
በሌሎች ታላላቅ ከተሞችም፣ ' ሕገ ወጥ ግንባታ ' በሚል ቤቶችን ማፍረስ የተለመደ ተግባር ነው፤ የችግሩ መንሥኤ፣ ከከተሞች መስፋፋት ጋራ ተያይዞ የመጣ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ማደግ ስለሆነ፣ መንግሥት ለጉዳዩ ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል።
በአሁኑ ጊዜ፣ በአገሪቱ ውስጥ፣ ወደ 20 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰብአዊ ርዳታ የሚሹ ተፈናቃዮች አሉ፡ በዚህ ላይ ተጨማሪ ሰዎችን ማፈናቀል አግባብ አይደለም። "
የሸገር ከተማ ምን አለ ?
የሸገር ከተማ አስተዳደር የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ያለውን ያህል ቅሬታ እንዳልቀረበለት ለሬድዮ ጣቢያው በሰጠው ቃል አሳውቋል።
የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉግሳ ደጀኔ፣ " 100 ሺሕ አቤቱታዎች የሚለው መረጃ፣ ውይይት ያልተደረገበት፣ በአግባቡ ያልተጣራና ከአንድ ወገን ብቻ የተገኘ ነው " ብለዋል።
የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ግን፣ በጉዳዩ ዙርያ ከከተማዋ ባለሥልጣናት ጋራ ውይይት መደረጉን ገልጿል፡፡
በተቋሙ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ሓላፊ ተወካይ አቶ ተሾመ ያሚ ፥ ከሕዝብ ቀረቡ ከተባሉት አቤቱታዎች ጋራ በተያያዘ፣ ከሸገር ከተማ ሓላፊዎች ጋራ ውይይት መደረጉን አረጋግጠዋል፡፡
Credit : VOA AMHARIC

#ጋምቤላ
በጋምቤላ ክልል በተፈጠረ የእርስ በእርስ ግጭት 9 ሰዎች ሲገደሉ ፤ 17 ሰዎች ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ክልሉ አሳወቀ።
ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል በኢታንግ ልዩ ወረዳና በጋምቤላ ከተማ የፀጥታ ችግር ተከስቶ እንደነበር የክልሉ ፕሬዜዳንት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።
የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በሰጡት መግለጫ ፤ " በክልሉ በኢታንግ ልዩ ወረዳና በጋምቤላ ከተማ ሰሞኑን ተከስቶ የነበረዉን የፀጥታ ችግር በክልሉና በፌዴራል የፀጥታ አካላት ቅንጅታዊ ስራ በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል " ብለዋል።
በኢታንግ ልዩ ወረዳ በፒኝዋ እና ሌር ቀበሌዎች በሚኖሩ ግለሰቦች መካከል የተነሳዉ አለመግባባበት ወደ ግጭት ማምራቱን የገለፁት የክልሉ ፕሬዜዳንት በዚህም በወረዳውና በጋምቤላ ከተማ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል።
በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ በተከሰተው የእርስ በርስ ግጭት የዘጠኝ (9) ሰው ህይወት ሲያልፍ 17 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ከፌዴራልና ከክልል የፀጥታ አካላት አስፈላጊው ኃይል ተጨምሮ የማረጋጋት ስራ መከናወኑን አመልክተዋል።
ፕሬዜዳንቱ ፤ " ለዘመናት በአብሮነትና ወንድማማችነት ተከባብሮ የኖረውን ህዝብ ለማለያየት የሚሞክሩ አካላት አሉ " ያሉ ሲሆን " በህብረተሰቡና በፀጥታ ሀይሎች ጥረት ሴራቸው ሳይሳካ ቀርቷል " ብለዋል።
የክልሉ ፕሬዜዳንት ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ የሀሰት መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀው አሻፈረኝ ባሉት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳውቀዋል።

ትላንት ሌሊት 10:30 ቡድናቸውን ለመደገፍ ወደ ሀዋሳ ሊያቀኑ የነበሩ የባህር ዳር ከተማ ደጋፊዎች ላይ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከክለቡ የደጋፍ ማህበር ለማጣራት እንደሞከረው ደጋፊዎቹ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ ቡድናቸውን ለማበረታት በሚያደርጉት ጉዞ ሙሉአለም አዳራሽ አካባቢ ላይ ጉዳቱ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ችለናል።
ሁለት ደጋፊዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ሲደረስ አንድ ደጋፊ የጭንቅላት ጉዳት ደርሶባት በአሁን ሰዓት በፅኑ ህሙማን መከታተያ ( ICU ) ውስጥ እንደምትገኝ ተገልፆልናል።
ጉዳት የደረሰባቸው ደጋፊዎች በባህርዳር ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።
በቦንብ ጥቃቱ የሞተ ሰው ባይኖርም ከ20 በላይ በሚሆኑ ደጋፊዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
@tikvahethiopia @tikvahethsport

የባህር ዳር አስተዳደር ምን አለ ?
የባህር ዳር ከተማ ከንቲባና የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በትላንትናው ለሊት ስለተፈፀመው የቦንብ ጥቃት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከንቲባው ፤ " ክለባችን ባህር ዳር ከነማ በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ዋንጫ ለማንሳት እየተፎካከረ ይገኛል " ብለዋል።
ይህንን መሠረት በማድረግ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ከሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ለሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው በአካል ተገኝተው ለመደገፍ ጉዞ ወደ ሀዋሳ ለማድረግ ዝግጅት ጨርሠው ወደ ተዘጋጀላቸው አውቶብስ እየገቡ ባሉበት ሁኔታ በተወረወረባቸው ቦንብ 23 የክለቡ ደጋፊዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል።
ከንቲባው ቦንቡን የወረወሩት " ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት " ናቸው ብለዋል።
ቀላልና ከባድ ጉዳት ያደረሰባቸው የክለቡ ደጋፊዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ከንቲባው ገልጸዋል።
ከንቲባው ፤ " ከጊዜ ወደ ጊዜ በከተማችን ላይ እየተፈፀመ ያለው የቦንብ ጥቃትና ግድያ የከተማችንን ነዋሪ በሠላም ወጥቶና ተንቀሳቅሶ የመስራት ፍላጎት የሚገድብ፣ የከተማችንን እድገትና ልማት የሚጎዳ፣ ብሎም የከተማችንን ገፅታ የሚያበላሽ የፀረ ሠላም እንቅስቃሴ በመሆኑ መላ ህብረተሠባችን ሊያወግዘው ይገባል። " ብለዋል።
" ከዚህ ባለፈ ህብረተሠቡ የፀጥታው ባለቤት በመሆን ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሠለፍ የከተማውን ሠላም የሚያውኩ አካላትን በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ ማድረግ ይገባል " ሲሉ አክለዋል።
ከንቲባው የከተማው የፀጥታ አካላት የከተማውን ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፁ ሲሆን " አሁንም እንደከዚህ ቀደሙ እንዚህን ወንጀል ፈፃሚወች ተከታትለው ለህግ የሚያቀርቡ ይሆናል " ብለዋል።

የስዕል ተስዕጦ ላላቸው የቀረበ ዕድል!
ሪድም ዘጀኔሬሽን USAID ጋር በመተባበር ዕድሜያቸው ከ18 -29 ለሆኑ ወጣቶች በቡድን ሆነው የሚሳተፉበት የስዕል ውድድር አዘጋጅቷል። ውድድሩ በሁሉንም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ 80 የሚሆኑ ወጣቶች ክህሎታቸውን ተጠቅመው ስለሰላም በጋራ እንዲሰሩ የሚያግዝና መልዕክት የሚያስተላልፉበት ነው።
ምዝገባው ከዛሬ ግንቦት 14 እስከ18 ድረስ የሚቆይ ሲሆን ተሳታፊዎች በሥራ ሰዓት በሪድም ቢሮ በአካል ወይም በኦላይን https://forms.gle/rQr7ojZ8jXkCrkA18 ላይ መመዝገብ ይችላሉ።
አንደኛ ለሚወጣው የሥዕል ሥራ የ60,000 ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፤ ሁለተኛ ለወጣው አሸናፊ ደግሞ የ40,000 ብር ሽልማት ያስገኛል። በማኅበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ላገኘው የሥዕል ሥራ ደግሞ የ10,000 ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።
ስለውድድሩ ዝርዝር መረጃና ለመሳተፍ ስለሚያስፈልጉ መስፈርቶች በቀጣዩ ሊንክ ይጠቀሙ https://telegra.ph/Call-for-Applicants-05-22
ለተጨማሪ መረጃ 0930098219 / [email protected] ላይ ይጠይቁ።