TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የገቢዎች ሚኒስቴር ግብር ከፋዮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ ፤ ማንነታቸው በውል ያልታወቁ ግለሰቦች እና ቡድኖች የተለያዩ የማደናገሪያ እና የማጭበሪያ መንገዶችን እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ስም እና ሀሰተኛ ማንነት በመጠቀም ግብር ከፋዮችን #እያጭበረበሩ ይገኛሉ ብሏል።

ይህ የማጭበርበር ተግባር እየተሰራ ያለው የግብር ከፋዩን የስልክ አድራሻ በመጠቀም እንደሆነም ገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል።

የማጭበርበር ተግባሩ የሚፈፀመው እንዴት ነው ?

የግብር ከፋዮችን አድራሻ በመጠቀም ፦

1.  ለታማኝ ግብር ከፋይ የሚሰጠውን ሽልማት እንድትሸለሙ እናስመርጣችኋለን፣

2. የኦዲት ውሳኔ #እናስቀንስላችኋለን

3.  ድርጅታችሁ #ወንጀል_መስራቱ ስለተደረሰበት በህግ እንዳትጠየቁ እናደርጋለን የሚሉና የመሳሰሉ #የማስፈራራት እና #የማግባባት ሙከራዎች እና ዘዴዎችን በመጠቀም ነው።

ገቢዎች ሚኒስቴር ይህ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑ በክትትል ለማወቅ እንደቻለ ገልጾ ግብር ከፋዮች የነዚህ መሰል የማጭበርበር ሙከራዎች ሰለባ እንዳይሆኑ አስጠንቅቋል።

ማንኛውም ግብር ከፋይ ይህ መሰል ሁኔታዎች ሲያጋጥሙትም በአቅራቢያው ለሚገኝ የግብር ሰብሳቢ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአፋጣኝ ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ጋምቤላ

10 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ቅዳሜ ዕለት ከደቡብ ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን የገቡ የ " ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች " 10 ሰዎችን ገድለው 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውን ከጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ታጣቂዎቹ ቅዳሜ ምሽት 3 ሰዓት ተኩል ገደማ ድንበር ጥሰው በመግባት በማኩዌይ ወረዳ ቢልኬች ቀበሌ እንዲሁም በዋንቱዋ ወረዳ መተሀር ከተማ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በፈፀሙት ጥቃት በአጠቃላይ 10 ሰዎችን ገድለው ፤ 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት አድርሰዋል።

በጥቃቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ወደ ጋምቤላ ጠቅላላ ሆስፒታል ለህክምና የተላኩ ሲሆን ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ደግሞ በኝንኛንግ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተነግሯል።

ከጥቃቱ በኃላ በጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኑዌር ዞን በሙርሌ ጥቃት የደረሰባቸውን ዜጎች ምልከታ አድርጓል።

አቶ ቴንኩዌይ ጆክ  ፤ በተደጋጋሚ ወቅትና ጊዜ እየጠበቁ ጥቃት የሚሰነዝሩት የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ታጣቂዎች፣ ትቅዳሜ ምሽት ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ነው ጥቃቱን ያደረሱት ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለማደን ጥረት እያደረገ ነው ያሉ ሲሆን ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፀም የተጠናከረ ጥበቃ ይደረጋል ብለዋል።

የክልሉ መንግስት በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደምም እነዚሁ ድንበር ጥሰው የሚገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በኑዌር ዞንና አኙዋ ዞኖች ገብተው የተለያዩ ጥቃቶችን ማድረሳቸው ይታወሳል።

ድንበሩ ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጓዳኝ ህብረተሰቡ በንቃት አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ወደ ባንክ ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅብዎ በቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን ከእሁድ እስከ እሁድ ለ24 ሰዓት የተሟላ የባንክ አገልግሎት ያግኙ።

#BankofAbyssinia #BankingServices #ITM #VirtualBanking #DigitalBanking #MoneyTransfer #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የተላለፈው ይዘት በቤተ ክርስቲያኗ ምእመናን መካከል እርስ በእርስ ግጭት የሚፈጥር ነው ብለን አናምንም " - ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን

ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ፤ ከመገናኛ ብዙኃን አዋጅ በሚቃረን ሁኔታ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን መታገዱን በመግለጽ አቤቱታውን ተቋሙን በበላይነት ለሚመራው ቦርድ አቀረበ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን " የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያካሄደውን ስብሰባ የሚያውክና ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት አሰራጭቷል ፤ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን ተላልፏል " በሚል ለማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቪዥንን እሑድ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም በተጻፈው ደብዳቤ በጊዜያዊነት እግድ አስተላልፏል።

ማኅበረ ቅዱሳን ፤ እግዱ የመገናኛ ብዙኃኑን አዋጅ የጣሰ ነው በማለት ተቋሙን በበላይነት ለሚመራው ቦርድ ቅሬታውን አቅርቧል።

የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ምን አለ ?

ትላንት የተላለፈው መግለጫ በኢ/ኦ/ተ/ቤ ቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እውቅና ያላቸው ከ10 በላይ ማኅበራት ያሉበት ዐቢይ ኮሚቴ መግለጫ መሆኑን ገልጿል።

ማህበረ ቅዱሳን መግለጫውን የማስተላለፍ ግዴታ አለብን ያለ ሲሆን ባለስልጣን መ/ቤቱ የወሰደው እርምጃ ግን በሃይማኖት የውስጥ ጉዳዮች ላይ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ የተላለፈው ይዘት ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር የሚገናኝ ነገር እንደሌለውም ፤ ማንኳሰስም የሌለበት እና መቻቻል እንዳይፈጠር የሚያደርግ ዘገባ እንዳልሆነ አስረድቷል።

ይዘቱ " የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ይከበር በአባቶች መካከል የሚስተዋለው መከፋፈል ይቅር " የሚል በመሆኑ በማንኛውም መንገድ በቤተ ክርስቲያኗ ምእመናን መካከል እርስ በእርስ ግጭት የሚፈጥር ነው ብለን አናምንም ሲል አክሏል።

" ዘገባው በተሠራ ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ማን ምን አይነት ቅሬታ እንዳቀረበ ለጣቢያችን አልተገለጸም። " ያለው ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን " በአዋጁ መሠረት ለባለሥልጣኑ የቀረበ ቅሬታ ካለም ጣቢያችን ዘገባውን የሠራበትን ምክንያት ሳይጠየቅና ሳያስረዳ በባለሥልጣኑ የተወሰደ ርምጃ ነው፡፡ ይህም በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ አንቀጽ 7 የተቀመጠውን የባለሥልጣኑን ገለልተኝነት እና ነጻነት የሚጋፋ ሆኖ አግኝተነዋል " ብሏል።

ጣቢያው ምንም እንኳን የሠራው ዘገባ ስሕተት ነው ብሎ እንደማያምን ቢገልጽ። ባለሥልጣኑ በተረዳው መንገድ ስሕተት ሆኖ ቢገኝ እንኳ በመገናኛ ብዙኃን አዋጁ አንቀጽ 73 የተቀመጠውን ከጽሑፍ ደብዳቤ እስከ የብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድን ፈቃድ እስከማገድ ያሉ 4 ደረጃዎችን በመጣስ ያለማስጠንቀቂያና ውይይት የአዋጁን አስተዳደራዊ ርምጃዎች ሂደት ያልተከተለ ውሳኔ አስተላልፏል ሲል ገልጿል።

በመሆኑም የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ቦርድ በቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ የተላለፈውን ጊዜያዊ እገዳ እንደገና በማየት በጣቢያውና በሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ የሚፈጥረውን አሉታዊ ተጽዕኖ በማገናዘብ እግዱን አንሥቶ ጣቢያው አገልግሎቱን እንዲቀጥል በፃፈው የአቤቱታ ደብዳቤ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
#Update

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ውሎው ችግር ባለባቸው እና አስፈላጊ በሆኑባቸው አህጉረ ስብከት 9 አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት #እንዲሾሙ ውሳኔ ማሳለፉን የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ውሎው ችግር ባለባቸው እና አስፈላጊ በሆኑባቸው አህጉረ ስብከት 9 አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት #እንዲሾሙ ውሳኔ ማሳለፉን የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ዘግቧል። @tikvahethiopia
#Update

" የሹመቱ ቀን #ወደፊት ይገለፃል " - ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር)

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን በተመለከተ አጭር መግለጫ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

- የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ #በሰላም እና ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል።

- ዛሬ የመጨረሻው አጀንዳ ላይ ብዙ ውይይት ተካሂዷል።

- በመጨረሻ ሁሉም አባቶች ተወያይተው ቤተክርስቲያንን የሚጠቅመው ምንድነው ? የሚለው ላይ በመምከር ዛሬ ውሳኔ ተላልፏል።

- የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲካሄድ ተወስኗል። የመጀመሪያው ችግር ያለባቸው ሀገረ ስብከት የሚል ሲሆን አሁን 7 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሟል እነሱ በሚያቀርቡት ጥናት ሹመት ይካሄዳል። የሹመቱ ቀን #ወደፊት ይገለፃል። ዋናው ነገር ለቤተክርስቲያን የሚጠቅመው የትኛው ነው ? የሚለውን የጉባኤው አባላት በሙሉ ተስማምቶ ፣ በአንድ ልብ፣ በአንድ ሃሳብ፣ በመነጋገር ውሳኔ ተላልፏል።

- ረቡዕ የማጠቃላይ መግለጫ በቅዱስ ፓትርያርኩ ይሰጣል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ፦

" ብዙ የተጨነቃችሁ ምዕመናን እንዳላችሁ እናውቃለን፤ ምዕመናን በሙሉ ተጨንቃችኃል፤ አንዳንድ ጊዜ እውነት ነው ሌላ ጊዜ ወሬም ብዙ ይበዛል በዚህ ሚዲያ በበዛበት ዘመን በጣም ብዙ የተጨነቃችሁ ምዕመናን እንዳላችሁ እናውቃለን ፤ በእውነት እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ግሩም የሆነ የትምህርት ጊዜ፣ ግሩም የሆነ የውይይት ጊዜ ፣ ቤተክርስቲያን ለይተን የምትፈልገው ምንድነው የሚለውን የተወያየንበት ጊዜ ነው ፤ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን !! "

@tikvahethiopia
#Tigray

ዛሬ ማክሰኞ ፤ በትግራይ ክልል ሰላማዊ ሰልፍ በመደረግ ላይ ይገኛል።

የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ባሰራጩት ዘገባ ሰልፉን እያካሄዱ ያሉት በትግራይ ጦርነት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ናቸው።

እነዚህ ወገኖች በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች " ድምፃችን ይሰማ " ሲሉ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ እንደሆነ ተመላክቷል።

በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የትግራይ ተፋናቃዮች ዛሬ እያካሄዱት ባለው ሰላማዊ ሰልፍ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በተሟላ መልኩ እንዲተገበር ጠይቀዋል ተብሏል።

ከፌዴራል ውጭ የሆኑ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡ ፣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቄያቸው እንዲመለዱ አደራዳሪ አካላት ሀላፊነታቸው እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ የተቋረጠው ሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀጠል የሰልፉ ተካፋዮች ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ሰላማዊ ሰልፎች እየተደረጉ የሚገኘው በክልሉ መዲና መቐለ፣ ሽረ እንደ ስላሰ ፣ ዓዲግራት፣ ዓብይ ዓዲ፣ ኣክሱም፣ እና ሌሎች አካባቢዎች ነው።

ፎቶ ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን / ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እግድ " የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቪዥን ጣቢያ " በመንግስት #በጊዜያዊነት ታገደ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዛሬ እሁድ በፃፈው ደብዳቤ " ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ " ን በጊዜያዊነት እንዳገደ አሳውቋል። ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም " ሰበር ዜና " በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን…
#እናት

" የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው እናሳስባለን " - እናት ፓርቲ

እናታ ፓርቲ ፤ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በማህበረ ቅዱሳን መገናኛ ብዙኃን ተቋም ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ ዳግም እንዲያጤነው አሳሰበ።

ፓርቲው ይህን ያሳሰበው ትላንት በላከልን መግለጫ ነው።

" በህግ ሽፋን በጊዜያዊነት እንዲዘጋ ዉሳኔ የተላለፈበት የማህበረ ቅዱሳን መገናኛ ብዙኃን ተቋም የሠራዉ ጥፋት ካለ በግልጽ ቀንና ሰዓቱ ተጠቅሶ ሕዝቡ እንዲያዉቀዉ ማድረግ ያስፈልጋል። " ያለው እናት ፓርቲ " ይህ ባልሆነበት ሁኔታ መገናኛ ብዙሃን ድርጅቱን በተለመደው አይነት ጥቅል ፍረጃና ካለ ተጨባጭ አሳማኝ ማስረጃ ማገድ ተገቢ አይደለም " ሲል ገልጿል።

" ህዝባችን መረጃዎችን በነጻነት የማግኘት መብቱን ሊነጠቅ አይገባም " ያለው ፓርቲው " የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው እናሳስባለን " ብሏል።

የማህበረ ቅዱሳን መገናኛ ብዙሃን ተቋም ኅብረተሰቡን የማገልገል መብቱ ተጠብቆለት የእግድ ትዕዛዙ በአስቸኳይ እንዲነሳለት እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia