TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኤክሳይዝ_ታክስ

አጠቃላይ የዕቃ አይነት ዝርዝሮች እና የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ከላይ ተያይዟል።

ዝርዝሩ ውስጥ ፦

- የአዲስና ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች  / መኪናዎች
- ጎማዎች
- ኬሮሲን / ቤንዚን/ ናፍጣ ነዳጆች
- ሽቶዎችና ለስላሳ ሽቶዎች
- የዓይን መኳያ ዝግጅቶች
- የከንፈር ቀለም ዝግጅቶች
- የእጅ ወይም እግር ማሳመሪያ ዝግጅቶች
- የፀጉር ቀለም
- ጨርቅና ልብስ
- ጌጣጌጦች
- ፀጉር እንዲሁም የሌሎችን እቃዎች የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔን መመልከት ይቻላል።

PDF ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/78549

Credit : የገቢዎች ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
የዋጋ ንረት . . . #ኢትዮጵያ

" አሁንም የዋጋ ንረቱ ደብል ዲጂትና #ጠንካራ ሆኖ ቀጥሏል " - አቶ አህመድ ሽዴ

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ረቡዕ ለህ/ተ/ም/ቤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውን እና ታጠሪ ተቋማትን የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ፥ በመጋቢት ወር አገራዊው አጠቃላይ የፍጆታ ዕቃዎች የዋጋ ግሽበት 33.7 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።

የምግብ ነክ ዋጋ ንረት 34.5 በመቶ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ዋጋ ንረት 32.5 በመቶ ደርሷል ሲሉ አመልክተዋል።

አሁንም የዋጋ ንረቱ ደብል ዲጂትና ጠንካራ ሆኖ መቀጠሉን ያሳያል ብለዋል።

" ይህም በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ጫና የሚያሳድር ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ ምን አደረጋችሁ ?

አቶ አህመድ ሽዴ ፦

- የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት ዘንድሮ የብር 17 ቢሊዮን ድጎማ ተደርጓል።

የማዳበሪያ ዋጋ በተለይ በዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ያለው ዋጋ እድገትን ተከትሎ የማዳበሪያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ነው ያደገው።

ይህም አንደኛ የውጭ ምንዛሬ ጫና በከፍተኛ ደረጃ አስከትሏል በሀገር ደረጃ። ሁለተኛ ሙሉ በሙሉ በብር ተመንዝሮ ወደ ገበሬው ይተላለፍ ቢባል የገበሬውን የመግዛት አቅም ታሳቢ በማድረግ ጫናው ከፍተኛ መሆኑ በመንግስት ታምኖበት 17 ቢሊዮን ብር ከበጀት ፀድቆ ድጎማ አድርገናል።

- ለአፈር ማዳበሪያ መግዣ ለክልሎች ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብር 56.7 ቢሊዮን ዋስትና ተሰጥቷል።

በየክልሉ ያሉ ገበሬዎች ማዳበሪያ እንዲቀርብላቸው ለማድረግ በክልሎቹ በቀረበ ጥያቄ 56.7 ቢሊዮን ብር ዋስትና ተሰጥቷል።

- #ነዳጅ ላይ አሁንም መንግስት በከፍተኛ ደረጃ እየደጎመ ነው ያለው። ከ180 ቢሊዮን ብር በላይ ተደጉሟል ባለፉት ዓመታት ፤ ዘንድሮም ያለው ከፍተኛ ነው ፤ ደረጃ በደረጃ ከአጠቃላይ ድጎማ ወጥተን ወደ targeted subsidy የመግባት ስራው ከአንድ ዓመት በላይ እየተሰራ ነው። መሉ በሙሉ ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት እየተሰራ ያለው ስራ የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ነው።

- መንግሥት በ97 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር 43 ሚሊዮን ሊትር የፓልም የምግብ ዘይት ለመግዛት ውል ገብቷል። ከዚህ ውስጥ በ33.8 ሚሊዮን ዶላር 15 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ከውጭ ተገዝቶ ወደ ሀገር ገብቷል።

- የሡፍ የምግብ ዘይት አቅርቦትን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ ነው።

- ዘይት፣ ሩዝ፣ ስኳር፣ ከውጭ ሲገቡ ሆነ በሀገር ሲመረቱ ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ታደርገዋል። የዋጋ ንረቱ ከዚህም ከፍ እንዳይል እያገዘ ነው።

- ለሀገር ውስጥ አምራቾች ከለላ ለመስጠት መኮሮኒ እና ፓስታ #ከተጨማሪ_እሴት_ታክስ ነፃ ታደርጓል። ይሄም የዋጋ ንረቱ እንዳይባባስ ለማድረግ ታልሞ የተሰራበት ነው።

- መሰረታዊ ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ ተደርጓል። በዚህም ምክንያት መንግሥት ብር 11.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ሳይሰበስብ ቀርቷል። ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉት መግባታቸው የዋጋ ንረቱ ከዚህ በላይ እንዳይባባስ ጥሩ ሚና አለው።

... በማለት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ወስደናቸዋል ስላሏቸው እርምጃዎች አስረድተዋል።

@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia
#MyWishEnterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664
#ETHIOPIA

ትላንት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ቻይናዊ ህይወት አለፈ።

በወላይታ ዞን ዱጉና ፋንጎ ወረዳ ውስጥ በደረሰ አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ጉዳት ደርሷል።

አደጋው የደረሰው የታርጋ ቁጥር ኢት 86294 ከባድ ሎባድ የጭነት መኪና በመገልበጡ ሲሆን የመገለበጥ አደጋ የደረሰበት የመኪናው ዘይት በመፍሰሱ ምክንያት ፍሬን ለመቆጣጠር ባለመቻሉ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

ተሽከርካሪው ከባድ #ብረት_ጭኖ ከጅንካ በወላይታ ሶዶ በሐዋሳ አድርገው ወደ አዲሰ አበባ ይጓዝ እንደነበር ተገልጿል።

በድጉና ፋንጎ ወረዳ ፤ በፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ በደረሰው አደጋ አንድ ቻይናዊ ህይወት አልፏል።

የመኪናው ሾፌር እና ረዳት ጉዳት እንደደረሰባቸው የዱጉና ፋንጎ ወረዳ የትራፊክ አደጋና መከላከል ማስተባበሪያ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

መረጃ ከወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
" አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ በመገልበጡ ነው ፤ ... እስካሁን የ15 መምህራን ህይወት አልፏል  " - የሮቤ ከንቲባ

ዛሬ ማለዳ ላይ 15 የመደ ወላቡ ዩንቨርሲቲ  መምህራን በትራፊክ  አደጋ  ህይወታቸው  ማለፉ ተሰምቷል።

የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን  ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰው የትራፊክ አደጋ  ህይወታቸው ማለፉ የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ንጋቱ ሞቱማ ገልጸዋል።

ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት ጋራ ዋሻ አካባቢ በመገልበጡ ፤ እስካሁን 15 የዩንቨርሲቲው መምህራን  ህይወት ማለፉን አመልክተዋል።

#OBN

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" አዲስ ተሽከርካሪዎች ገበያ ላይ የሚሸጡበት ዋጋ እና የሚቆርጡት ደረሰኝ ሰፊ ልዩነት እንዳለው በጥናት አረጋግጠናል " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጠን ጋር በመሆን በተሽከርካሪዎች ግብይትና አሰራር ዙሪያ ትላንት መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው የተሽከርካሪዎች ግብይት መሬት ላይ ያለው እውነታንና መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ መሠረት ያደረገ ጥናት ሲካሄድ መሠንበቱን ገልጿል።

በዚህም መነሻ ከአስመጪዎችና ከዘርፉ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት መደረጉንና ማንም በገበያ ዋጋ ደረሰኝ እንዲቆርጥና ገዢውም ትክክለኛ ደረሰኝ በመያዝ አገልግሎት ማግኘት እንዳለበት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አሳስቧል።

" መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ ለማግኘት ከግንቦት 03/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ  ወደ ተግባር ገብቷል " ያለው የአ/አ ገቢዎች ቢሮ " የህግ ማስከበር ስራዎች ተጠናክረው ስለሚቀጥሉ ገዢ ላወጣው ለከፈለበት ትክክለኛ ደረሰኝ መቀበል ፣ እንዲሁም ሻጭ ለሸጠበት ትክክለኛ ደረሰኝ መስጠት ይኖርበታል ፤ ሲጠየቁም ይህንን ትክክለኛ የግብይት ደረሰኝና የሂሳብ መዝገቦች ማቅረብ አለባቸው " ሲል አስገንዝቧል።

አዲስ ተሽከርካሪዎች ገበያ ላይ የሚሸጡበት ዋጋ እና የሚቆርጡት ደረሰኝ ሰፊ ልዩነት እንዳለው ጥናት በማድረግ አረጋግጠናል ያለው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገዢዎች ይዘውት የሚመጡት ደረሰኝ መሬት ላይ ያለውን ትክክለኛ የተገዛበትን ዋጋ መሆን እንዳለበት እና ሲገዙም በትክክል ያወጡበትን ዋጋ መቀበል አለባቸው ብሏል።

የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በበኩሉ ፤ በየአመቱ ወደ 40 ሺህ የሚጠጉ አዳዲስ መኪኖች እንደሚመዘገቡ ጠቁሞ ከዚህም መንግስት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እያገኘ እንዳልሆነ ጥናቶች በተጨባጭ አረጋግጠዋል ሲል አሳውቋል።

በተቋሙ ማንኛውንም አገልግሎት የሚፈልግ ሰው ለገዛው የመኪና ዋጋ ትክክለኛ ደረሰኝ ይዞ መገኘት አለበት ስሊ ያሳሰበው ባለስልጣን መ/ቤቱ ይህ ካልሆነ ግን በተጠናውና ወደ አሰራር በተገባው መሠረት የሚጠበቅበትን ከፍሎ አገልግሎት ያገኛል ባቧል።

በዘርፉ የመንግስትን ጥቅም ለማስከበር ሁለቱም ተቋማቶች በጋራ እየሰሩ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን ፦ ገዢም ሆነ ሻጭ ትክክለኛ የሂሳብ መዝገብ ፣ ትክክለኛ ደረሰኝ መቁረጥ እና ወደ ህጋዊ አሰራር መግባት  እንደሚኖርባቸውና ትክክለኛ ዋጋ ባለማቅረብ እና ዝቅ አርጎ ዋጋን ማቅረብ ስለሚያስጠይቅ ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡ በአፅንኦት አሳስበዋል።

መረጃው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia
We Are Hiring!
Berhan Bank seeks to hire applicants for the positions of
1. Electrician II
2. Network Engineer III
3. Network Engineer II
4. Security Engineer II
5. Compute Infrastructure Engineer II
6. Compute Infrastructure Engineer III
7. Database administrator III
8. Database administrator II
9. Database administrator I
10. IT Project Officer III
11. IT Project Manager
Use the link below to apply for the vacancy
Link; https://t.iss.one/berhanbanksc
የስራ ጥቆማ !

ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት #ጋዜጠኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል : https://careers.bbc.co.uk/job/Nairobi-Journalist-BBC-Amharic-Service-Nair-0-0100/771280902/
#ስፖርት

በመላው ዓለም እጅግ ከፍተኛ ተመልካች ያለው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ፍልሚያ የ " 2022/23 የውድድር ዓመት " ሻምፒዮን #ማንችስተር_ሲቲ መሆኑ ዛሬ ቅዳሜ ተረጋገጠ።

ማንችስተር ሲቲዎች ምንም እንኳን በውድድር ዓመቱ ቀሪ ጨዋታዎች ቢኖራቸውም ብርቱ ተፎካካሪያቸው #አርሴናል ዛሬ በኖቲንግሃም ፎረስት መሸነፉን ተከትሎ የዋንጫው ባለቤት መሆናቸውን ከወዲሁ አረጋግጠዋል።

ማንችስተር ሲቲዎች ለሶስተኛ ተከታታይ ዓመት የሊጉ ሻምፒዮናነትን ሲያሸንፉ በክለቡ ታሪክ ዘጠነኛው ሆኗል።

ተጨማሪ ፦ https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport