#big5construct
እጅግ በጉጉት የሚጠበቀው የግንባታው ዘርፍ ዓውደ ርዕይ በሀገራችን ሊከናወን ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል !
በቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ኢግዚቢሽን ላይ ለመታደም እና ከዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር ለመገናኘት፣ አዳዲስ ፈጠራዎችን እና የግንባታው ዘርፍ መፍትሔዎችን ለማግኘት ይዘጋጁ !
ዛሬውኑ በመመዝገብ ከግንቦት 10 እስከ 12 ድረስ በሚከናወነው ታላቅ ዝግጅት ላይ ይታደሙ! https://bit.ly/3oI8P6L

👍116❤30😢4
በቢሾፍቱ ምን ተፈጠረ ?
የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ትላንት ምሽት በከተማዋ ለረጅም ደቂቃ የተኩስ ድምፅ ሲሰሙ እንደነበር እና በዚህም ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ ገብተው እንደነበር ገልጸዋል።
የነበረውን ሁኔታ ዛሬ ጥዋት ለማጣራት ባደረጉት ሙከራም ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለ ጥቃት 4 የፖሊስ አባላት ህይወታቸውን እንዳጡ እንደሰሙ አስረድተዋል።
ሚ.ኤ የተባለ የቤተሰባችን አባል ትላንት ከለሊቱ 6 ሰዓት ላይ ከበድ ያለ የመሳሪያ ተኩስ እንደነበር ገልጿል።
" እኔ ቢያንስ ለ45 ደቂቃ የተኩሱን ድምፅ ሰምቻለሁ፤ በከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ ነበረን ፤ በኃላ ፀጥ ሊል ችሏል " ያለው ይኸው የቤተሰባችን አባል " ጥዋት ለማጣራት ባደረኩት ሙከራ ምን እንደሆነ ባላውቅም የ4 የፖሊስ አባላት ህይወት ማለፉን ሰምቻለሁ " ሲል አስረድቷል።
ሌላ አንድ የቢሾፍቱ ቤተሰባችን አባል (ጂ.ቲ) ፤ እኩለ ለሊት ላይ የቱኩስ ድምፅ ሲሰማ እንደነበር ገልጿል።
" ምንም እንኳን ከቤት ወደ ውጭ ወጥቼ የነበረውን ነገር ለማየት ባልችልም ፤ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንደነበር ፤ በኃላም አምቡላንሶች ሲመላለሱ ነበር " ሲል ገልጿል።
ቢ.ኬ ነኝ ያለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በበኩሉ ፤ " ትላንት ለሊት 6:00 አካባቢ ላይ ሰንሻይን በሚባለው አከባቢ ዋናው የአስፓልት መንገድ ላይ በሚገኘው ፖሊስ ጣብያ ላይ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ የ4 ፖሊሶች ሕይወት ሲያልፍ የተወሰኑት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ " ብሏል።
ጉዳት የደረሰባቸው በቢሾፍቱ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።
" ለሊት ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ ነበር፡፡ " ያለው ይኸው የቤተሰባችን አባል " አሁን ግን ሁሉም ነገር ሰላም ሆኖ፤ ሕዝቡ ወደ ተለምዶ እንቅስቃሴው ተመልሷል፡፡ " ሲል አስረድቷል።
ከዚህ በተጨማሪ ወደ ቢሾፍቱ መግቢያ ላይ ለደንነት ሲባል ጥብቅ ፍተሻ ስላለ ማንኛውምም ሰው ወደዚህ ሲመጣ መታወቂያ መያዙን ማረጋገጥ እንዳለበት ማሳወቅ እፈልጋለሁ ብሏል።
ሌሎች የቢሾፍቱ ቲክቫህ አባላት ትላንት የተኩስ ድምፅ ሲሰሙ እንደነበር በመግለፅ ዛሬ ጉዳዩን ለማወቅ ባደረጉት ሙከራ ፤ በአንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት 4 የፖሊስ አባላት መገደላቸውን እንደሰሙ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰብ አባላቱ በተጨማሪ በዝርዝር ጉዳዩን ለማወቅ ከከተማው አስተዳደር መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
ዝርዝር ጉዳዮችን እንዳገኘን እንልክላችኃለን።
Via @tikvah_eth_BOT
@tikvahethiopia

👍797😢162❤92🕊39😱34👎11🥰6🙏1
#ጥንቃቄ
ዛሬ ጥዋት ፤ በወላይታ ዞን #ከአረካ ወደ #ሶዶ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ይጓዝ በነበረ አንስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ላይ የመገልበጥ አደጋ ደርሷል።
በአደጋውም የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 4 ሰው ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
- አደጋ የደረሰበት ተሽከርካሪ ፦ ኮድ-3 ደቡብ 25715 በተለምዶ ሀይሩፍ እየተባለ የሚጠራው መኪና ነው።
- 17 ተሳፋዎችን ይዞ ከፍጥነት በላይ ሲጓዝ መሥመር በማሳት ከላሾ ከተማ ወረድ ብሎ በሚገኘው ካሬታ ሃታ/ወንዝ ውስጥ ገብቷል።
- በአደጋው የአንድ ሰው ህይወት ሲየልፍ በአራት ሰው ላይ ቀላል አደጋ ደርሷል።
የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ፤ የመኪና አሽከርካሪዎች ጊዜው #የዝናብ_ወቅት ስለሆነ በክፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያሽከረከሩ ጥሪ አቅርቧል።
መረጃው የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።
@tikvahethiopia @tikvah_Eth_BOT

😢448👍317❤69🕊28😱23👎11🙏10
(ደስታ የወለደው ሐዘን)
ለደስታ በሚል የተተኮሰው ጥይት የሙሽራውን እና የአባቱን ህይወት ቀጠፈ።
በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር ዞን በቋሪት ወረዳ ወይበኝ ቀበሌ ልዩ ቦታው በተለምዶ " አነሳት " እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ በባህሉ በወጉ መሰረት ልጃችንን ለልጃችሁ ተባብለው ሙሽሪትና ሙሽራው ሊጣመሩ የሙሽራው ቤተሰብና የሙሽሪት ቤተሰብ በስጋ ዝምድና ሊጣመሩ ቤት ባፈራው እንደአቅም ድግስ በመደገስ የሩቁና የቅርቡ ወዳጅ ዘመድ ልጃችንን ስለምንድር ልጃችንን መርቁልን ማለት የተለመደ ስርዓትና ወግ ነው፡፡
ታዲያ በዕለተ እሁድ ከሩቁ ከቅርብ የተጠራው ቤተዘመዱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሙሽራው መምጫ ሰዓት ደረሰ።
ሙሽራው ከነሚዜወቹ ደረሱ የሙሽሪት ቤተሰቦች በጣም ደስ አላቸው እልልታውን አቀለጡት ሙሽራው ሙሽሪትን በቤተሰብ አስመርቆ ወደቤቱ ሊመለስ ሲል ሞቅ ያለ ጭፈራ ሆታ ተነሳ በጭፈራው መሃል ቅልጥ ያለ የጥይት ተኩስም ተተኮሰ በድንገት ጭፈራ ሲጨፈር የነበረው ሰው ለግዜው ፀጥ አለ።
በጭፈራው መሃል በተተኮሰ ጥይት #ሙሽራው እና #የሙሽራው_አባት ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።
በተጨማሪ አንድ የሴት ሚዜ እንዲሁም ሰርጉን ለማድመቅ የተገኙ 4 ሰዎች በድምሩ አምስት ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን በተደረገላቸው ህክምና ህይወታቸው ሊተርፍ ችሏል።
ፖሊስ በዚህ የወንጀል ድርጊት የተሳተፉትን በቁጥጥር ስር አድርጎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳውቋል።
የፖሊስ መልዕክት ፦
(የወረዳው የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረ/ኢ/ር ተመስገን ሙሉነህ)
" ማህበረሰባችን በበሽታ ከሚሞተው ይልቅ በጀብድ ለቅሶ ላይ ሰርግ ላይ ክርስትና ላይ በሚተኮስ ጥይት ህይወቱን የሚያጣ ፤ ቁስለኛ የሚሆነው ሰው ቀላል ስላልሆነ እራሱን ቆም ብሎ ማሰብ መቻል አለበት፡፡
ህገ-ወጥ የጥይት ተኩስ ማንንም የሚጠቅም ስላልሆነ በየአካባቢው ያላችሁ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች በጀብድ የሚተኮስ የጥይት ተኩስ ብዙ ህይወቶችንን እየቀጠፈ ስለሆነ ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት እንድታስቆሙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን!! "
ምንጭ፦ የምዕራብ ጎጃም ፖሊስ መምሪያ

😢1.52K👍956❤126👎121😱78🕊28🥰20🙏16
#አቢሲንያ_ባንክ
ወደ ቅርንጫፎች መሄድ ሳያስፈልግ ባሉበት ሆነው የአቢሲንያ ባንክ አካውንት መክፈት እንደሚችሉ ያውቃሉ?
አፖሎ መተግበሪያን በማውረድ ካሉበት ሆነው አካውንት በቀላሉ ይክፈቱ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
Apollo Digital Product

👍194❤27👎20🕊5
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከአራት ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሬት ሊዝ ጨረታ መውጣቱን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአራት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሬት ሊዝ ጨረታ ያወጣ ሲሆን ለጨረታ የቀረቡት ይዞታዎች መነሻ ዋጋ ከፍተኛው 2,213 ብር መሆኑ ታውቋል።
የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓም ይፋ እንዳደረገው፣ በከተማዋ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች 297 ይዞታዎችን ለተጠቃሚዎች በሊዝ ለማስተላለፍ ጨረታ ውጥቷል።
በሊዝ ጨረታ እንዲተላለፉ የተዘጋጁት 297 ይዞታዎች አጠቃላይ ካሬ ሜትር 143 ሺህ (14 ነጥብ 3 ሄክታር) ሲሆኑ፣ ይዞታዎቹ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ናቸው ብሏል።
ለጨረታ ከሚቀርቡ ቦታዎች መካከል ከዚህ ቀደም በምደባና በጨረታ ወስደው ያላለሙና እርምጃ የተወሰዳባቸው፣ በተለያዩ ጊዜያት በህገ ወጥ መንገድ የተወረሩና ወደ መሬት ባንክ የገቡ መሬቶች እንደሚገኙበት አስታውቋል።
ለጨረታ የቀረቡት ይዞታዎች ዝቅተኛው የጨረታ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር 960.21ብር ሲሆን፣ ከፍተኛ የተባለው መነሻ ዋጋ 2,213. 25 ብር መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ከግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ከግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በመገኘት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መሳተፍ እንደሚችሉ ገልጿል።
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ይዞታ የተቀመጠውን መነሻ ዋጋ መሠረት በማድረግ ከአጠቃላይ ዋጋው 20 በመቶውን ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።
በዚህ ጨረታ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ግለሰቦች ፣ የንግድ ማኅበራት ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆኖ መወዳደር እንደሚቻል አመልክቷል።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክፍለ ከተማ አዳራሽ እንደሚከፈት አስታወቋል።
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

👍1.41K👎330❤196🥰30🙏23😢20😱13🕊12
#big5construct
Join us as we explore the potential of low-carbon engineered cementitious composites as a sustainable alternative to traditional structural materials. Dr. Esayas G.yohannes, an esteemed Associate Professor in Civil and Environmental Engineering at Addis Ababa University, will share his expertise on this topic.
20 May 2023 | 11:10 - 11:40
Register now and get your free certificate: https://bit.ly/3LyI5OT

👍147❤30👎5😢5🙏4😱3
#AddisAbaba
" በወንጀል ድርጊት እየተሳተፈ ነው የሚል ጥቆማ ደርሶናል " በሚል እጅ ወደላይ ያነሳን ግለሰብ ከኋላ ተኩሶ የገደለው ፖሊስ በእስራት ተቀጣ።
" የኬብል ስርቆት ወንጀል እየተፈፀመ ነው የሚል ጥቆማ ደርሶናል " በሚል ቦታው ላይ ተገኝቶ ሟችን ወንጀል ከፈጸሙት ሰዎች መካከል ነው በሚል በያዘው ታጣፊ ክላሽ ተኩሶ የገደለውና ሟችን በስቶ የወጣው የጥይት እርሳስ አካባቢው ላይ ቆሞ በነበረው ተበዳይ ላይ ጉዳት አድርሶበታል በተባለው ግለሰብ ላይ በፍትህ ሚኒስቴር ክስ መስርቶበት በ9 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ1ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተደርጓል
የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ከሆነ ኮ/ል ወንድወሰን ተስፋዬ የተባለው ተከሳሽ በዐቃቤ ሕግ ሁለት ክሶች ቀርቦበታል።
ጥር 16/2014 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሶፍያ ሞል እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ኬብል ስርቆት ወንጀል እየተፈፀመ ነው የሚል ጥቆማ ደርሶናል በሚል ቦታው ላይ ተገኝተው ሟች ሱራፌል መስፍን ወንጀል ከፈጸሙት ሰዎች መካከል ነው በሚል ካሯሯጠው በኋላ ደርሶበት በእጁ ትክሻውን እና በእግሩ ታፋውን ከመታው በኋላ ሟች ሁለቱንም እጁን ወደ ላይ ሲያደርግ ይዞት በነበረው ታጣፊ ክላሽ ተኩሶ ከኋላው በኩል ጎኑን፣ ደረቱ እና ሆዱ ላይ በመምታቱ ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።
ከዚህም ባለፈ ፤ ሟችን በስቶት የወጣው የጥይት እርሳስ አካባቢው ላይ ቆሞ የነበረውን ተበዳይ ማቴዎስ ወጋየሁ በግራ ጀርባው አካባቢ በስቶ በመግባት በግራ በኩል ሆዱ በመውጣት ጉዳት የደረሰበት አንጀቱ ክፍል ተቆርጦ እንዲወጣ ሆኗል።
በዚህም የኢፌዲሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 ስር እና 559/2/ ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ በፈጸመው የግድያ እና በቸልተኝነት ከባድ አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ሁለት (2) ክሶች ተመስርተውበት በክርክር ሂደት ቆይቷል።
በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት የቀረበው ተከሳሽ የተከሰሰበት ክስ በችሎት ተነቦለት " ድርጊቱ ተፈፅሟል ጥፋተኛ ግን አይደለሁም ስርቆት ሲፈፅሙ ነበር እኔንም ሊመቱኝ ነበር " በማለት ቃሉን አስመዝግሿል።
ተከሳሽ ጥፋተኛነቱን ባለማመኑ እንደክህደት ቃል ተቆጥሮ ዐቃቤ ህግ ስለ ጥፋተኛነቱ ማስረጃዎችን በማቅረብ በበቂ ሁኔታ ያረጋገጠ ሲሆን እንዲከላከል በተሰጠው ብይን መሰረት 3 የመከላከያ ምስክር አቅርቦ ቢያሰማም የዐቃቤ ህግን ምስክሮችንና ማስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻ ተከሳሹ ይከላከል በተባለበት ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ ተብሏል፡፡
ችሎቱም 6 የቅጣት ማቅለያዎችን በመያዝ በሁለቱም ክሶቹ በእርከን 28 ስር በማሳረፍ ተከሳሽን ያርማል በሚል በ9 ዓመት ጽኑ እስራትና በ1ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል፡፡
ምንጭ፦ የፍትሕ ሚኒስቴር

👎807👍577❤79😢69😱9🙏8🥰6
ማዳበሪያ . . .
" ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬዎች ማዳበሪያ ሲጨምርም / ሲጠፋ መንግስትን ትኩረት እንዲያደርግ ልትጠይቁ ይገባል " - አብራራው
(በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል - አብራራው)
" ሰላም ለእናንተ ይሁን !!
አንድ አሳሳቢ ሀገራዊ ጉዳይ አለ ፤ ነገር ግን ማንም ትኩረት ሰጥቶት ሲሰራ አላየውም ፤ እናም የሚመለከተው አካል ተመልክቶ መፍትሄ እንዲሰጥበት ይህን ጥሪ አቀርባለው።
ይህ ጉዳይ በገበሬዎች ላይ የሚያተኩር ነው። ገበሬወች ለማምረት ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ ያስፈልጋቸዋል።
በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ለማግኘት በህገወጥ ነጋዴወች በኩል በስንት መከራ በጣም በውድ እንዲገዙ እየተገደዱ ነው።
ይህ ችግር የተፈጠረው #አምና ሲሆን ዘንድሮ ይበልጥ ማዳበሪያ ሚባል ለገበሬወች አልደረሰም።
ገበሬወች እንደሚሉት ከሆነ አሁን ላይ የዘር ወቅት ስለሆነ ከአንዳንድ ነጋዴወች ላይ ኩንታል እስከ አስር ሺህ ብር እየገዛን ነው ብለዋል ፤ ይህ ማለት አንድ ገበሬ አስር ኩንታል ዳፕ ቢፈልግ መቶ ሺህ ብር ሊያወጣ ነው ማለት ነው። ካሁን በፊት የአንድ ኩንታል ዋጋ ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር በላይ ሁኖ አያውቅም።
ስለዚህ በኃላ የእህል ምርት አቅርቦት እንዳይቀንስ ከሆዲሁ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ማዳበሪያ ቢያቀርብ መልካም ነው።
ይህ ካልሆነ ግን እመኑኝ ቀጣይ አመት የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ከዘንድሮው እጥፍ ይጨምራል።
ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬውች መዳበሪያ ሲጨምርም መንግስትን ልትጠይቁ ይገባል።
በዋነኝነት መንግሥት ልዩ የሆነ ትኩረት ሰጥቶ እንዲቆጣጠሯቸው ምፈልገው የወረዳ አመራሮችን እና የቀበሌ አስተዳዳሪወችን ነው ምክንያቱም እኒህ አመራሮች ከነጋዴወች ጋር በመስማማት ሚገባውን ማዳበሪያ ቀጥታ ነጋዴወች በውድ እንዲሸጡት ይሰጥቸዋል ፤ ለገበሬው ደግሞ #ማዳበሪያ_አልገባም እያሉ የዘር ወቅት ሳያልፍ ከነጋዴ ገዝተው እንዲዘሩ ይነገሯቸዋል።
ስለዚህ ይህን ችግር ለመፍታት ትኩረት መሰጠት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ሰወች ጥናት ቢያደርጉበት መልካም ነው።
ትኩረት ለገበሬወች !! "
Via @tikvah_eth_BOT
ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

👍1.76K❤120🙏76👎36😢34😱9🕊9🥰6
ሶስት ዓመት ያለ መብራት . . .
• " የመብራት መቋረጥ የከፋ የኢኮኖሚ ችግር እየፈጠረብን ነው ፤ ስራ የነበራቸው ሁሉ ስራ ፈላጊ ሆነዋል " - ነዋሪዎች
• " ችግሩ ከወረዳው መንግስት አቅም በላይ ነው። የዞንና የክልል አመራሮች በአስቸኳይ መልስ ይስጡን " - የከለላ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ታደሰ
ለሶስት ዓመታት መብራት የተቋረጠባት የከለላ ወረዳዋ ከተማ ነዋሪዎች የመፍትሄ ያለ እያሉ ይገኛሉ።
በከለላ ወረዳ የ01 ደገር ከተማ ነዋሪዎች ባለፉት ሶስት ዓመታት የመብራት አገልግልት በመቋረጡ የከፋ ኢኮኖሚያዊ ችግር እየፈጠረባቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
የከተማ ነዋሪዎቹ አገልግሎት እየሰጠ የነበረው መብራት ከሶስት ዓመት በፊት መቋረጡን ገልጸው በዚህ ምክንያት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ማለትም ፦
- በብረታ ብረትና ጣውላ ስራ፣
- በምግብና ሻይ ቤቶች
- በጸጉር ቤቶች ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች #ስራቸውን_አቋርጠው ስራ ፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ነዋሪዎቹ እንዳሉት የመብራት አለመኖር በሚያከናውኑት የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንደፈጠረባቸውና #የኑሮ_ውድነት እንዲባባስ በማድረግ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተጽዕኖ እንዳደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡
የወረዳው መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩን እንዲፈታላቸውም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡
ይህንን በተመለከተ የከለላ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ታደሰ ፤ በከተማዋ የመብራት አገልግሎቱ መቋረጥ ለተከታታይ ሶስት ዓመታት በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ የፈጠረና በተደጋጋሚ የሚነሳ ጥያቄ ሲሆን የወረዳው መንግስትም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከዞን እስከ ክልል ድረስ በማነጋገር መፍትሄ እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል ብለዋል፡፡
" የመብራት መቆራረጡ በከተማው ነዋሪዎች እና በከተማዋ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ " ነው ያሉት ኃላፊው ችግሩ ከወረዳው መንግስት አቅም በላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው የዞን እና የክልል አመራሮች በአስቸኳይ መልስ እንዲሰጡ አቶ ሁሴን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
መረጃው ከከለላ ወረዳ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

👍1.03K😢230❤136😱58👎44🥰16🕊14