TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቱርክ

ቱርካውያን የቀጣይ አምስት ዓመታት መሪያቸውን ለመምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ ዋሉ።

ዛሬ የቱርክ ፕሬዝዳንታዊና የፓርላማ አባላት ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን የድምፅ አሰጣጡም ተጠናቆ ወደ ድምፅ ቆጠራ ተገብቷል።

በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ፕሬዝዳንት ሬስፕ ጣይብ ኤርዶሃን እና ዋነኛ ተቀናቃኛቸው ከማል ክሊችዳሮግሉ ብርቱ ተፎካካሪ ናቸው።

የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ዛሬ እሁድ ወደ በኃላ ይታወቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይፋዊው ውጤት ለማረጋገጥ ግን እስከ ሶስት ቀናት ሊወስድ ይችላል ተብሏል።

አንድ ተወዳደሪ ለማሸነፍ በመጀመሪያ ዙር ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ያስፈልገዋል።

ተወዳዳሪዎች 50 በመቶውን ድምፅ ማለፍ ካልቻሉ ፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሁለተኛ ዙር ምርጫ ይገናኛሉ።

እስካሁን ያለው ውጤት ምን ይመስላል ?

64.36 በመቶ የምርጫ ሳጥን ተከፍቶ የተቆጠረ ሲሆን ፤ ኤርዶጋን በ51.40 በመቶ እየመሩ ናቸው።

ተቀናቃኛቸው ክሊችዳሮግሉ 42.77 በመቶ ድምፅ አስመዝግበዋል።

ምንጭ፦ አናዱሉ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በወዳጅነት አደባባይ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የዘማሪት ሂሩት በቀለ የሽኝት ፕሮግራም ወደ ሀገር ፍቅር ትያትር መቀየሩ ተነግሯል።

በሀገር ፍቅር በሚኖረው ስነስርዓት በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የፀሎት ስነሥርዓት የሚካሄድ ሲሆን የአበባ ማስቀመጥ ስነስርዓትም ይከናወናል።

ከዚህ የሀገር ፍቅር ትያትር ስነስርዓት ቀደም ብሎ ዘማሪት ሂሩት መኖሪያ ቤት (ሻላ መናፈሻ ጀርባ) 4 ሰዓት ላይ የአስክሬን ሽኝት  ይከናወናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቱርክ ቱርካውያን የቀጣይ አምስት ዓመታት መሪያቸውን ለመምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ ዋሉ። ዛሬ የቱርክ ፕሬዝዳንታዊና የፓርላማ አባላት ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን የድምፅ አሰጣጡም ተጠናቆ ወደ ድምፅ ቆጠራ ተገብቷል። በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ፕሬዝዳንት ሬስፕ ጣይብ ኤርዶሃን እና ዋነኛ ተቀናቃኛቸው ከማል ክሊችዳሮግሉ ብርቱ ተፎካካሪ ናቸው። የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ዛሬ እሁድ ወደ በኃላ ይታወቃል ተብሎ የሚጠበቅ…
#Update

የቱርክ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እጅግ ብርቱ ፉክክር እየተደረገበት ይገኛል።

እስካሁን 90.61 በመቶ የድምፅ ቆጠራ የተካሄደ ሲሆን ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ምንም እንኳን ያገኙት ድምፅ ከ50 በመቶ ቢወርድም ምርጫውን እየመሩ ናቸው።

እስካሁን ባለው ቆጠራ ኤርዶጋን ፤ 49.86 በመቶ ድምፅ ያገኙ ሲሆን ተቀናቃኛቸው ክላችዳሮግሉ 44.38 በመቶ ድምፅ አግኝተዋል።

አንድ ተወዳደሪ ለማሸነፍ በመጀመሪያ ዙር ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ያስፈልገዋል።

ተወዳዳሪዎች 50 በመቶውን ድምፅ ማለፍ ካልቻሉ ፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሁለተኛ ዙር ምርጫ ይገናኛሉ።

@tikvahethiopia
#TheBig5ConstructEthiopia

Join us as we explore the role of project management in the built environment. Dr. Abraham Assefa Tsehayae, an esteemed Assistant Professor in the School of Civil and Environmental Engineering, will share his insights on the major challenges to successful program implementation, the impact of a Project Manager's personality on project delivery, and the importance of adapting project tools and systems to meet client needs. Don't miss out on this informative discussion!

19 May 2023 | 10:30 - 11:00

Register now: https://bit.ly/3oI8P6L
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ለትክሻ፣ለወገብ ህመም;ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች ፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች ፣ በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ !

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት
አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን።

ስልክ ፦ 0979099909/ 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 99.38 በመቶ ድምፅ የተቆጠረ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከ50 በመቶ በላይ ድምፅ ያገኘ እንደሌለ የሚወጡት ሪፖርቶች አሳይተዋል።

በምርጫው ትልቅ ግመት የተሰጣቸው ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ፤ 49.42 ድምፅ ያገኙ ሲሆን ተቀናቃኛቸው ከማል ኪሊዳሮግሉ 44.95 ድምፅ አገኝተዋል።

በሌላ በኩል ትላንት ምሽት ፕሬዜዳንት ኤርዶጋን በፓርቲያቸው ፅ/ቤት ለደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገው ነበር።

ምን አሉ ?

- የመጀመሪያ ደረጃ ውጤቶች በሰፊ ልዩነት እየመራን መሆኑን ያሳያሉ።

- የሀገር ውስጥ እንዲሁም የውጭ ድምፅ ቆጠራው ይቀጥላል። (በቱርክ ምርጫ በውጭ ያሉ የቱርክ ዜጎችም ድምፅ የሚሰጡበት መንገድ ያለ ሲሆን በአሁንም ምርጫ ድምፃቸውን ሰጥተዋል)

- እነሱ (ተቃዋሚዎች) " እየመራን ነው " እያሉ ሰዎችን ለማሞኘት እየሞከሩ ነው።

- ፕሬዜዳንታዊ ምርጫው በመጀመሪያው ዙር ይጠናቀቅ እንደሆነ እስካሁን #አናውቅም

- ከእኛ የቅርብ ተቀናቃኝ በ2.6M ድምጽ ርቀናል።

- በመጀመሪያው ዙር እንደምናሸንፍ እናምናለን።

- በታሪካችን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምርጫ ነበር የተሳተፈው።

በቱርክ ምርጫ ላይ አንድ ተወዳደሪ ለማሸነፍ በመጀመሪያ ዙር ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ያስፈልገዋል።

ተወዳዳሪዎች 50 በመቶውን ድምፅ ማለፍ ካልቻሉ ፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሁለተኛ ዙር ምርጫ ይገናኛሉ።

አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫው ወደ ሁለተኛ ዙር የማምራቱ እድል ሰፊ መሆኑ ተነግሯል።

መረጃው የአናዱሉ እና የቲአርቲ ወርልድ ነው።

@tikvahethiopia
#ዲጅታል_ክፍያ

ከሐምሌ ወር ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ የመብራት አገልግሎት ክፍያ በዲጅታል ስርዓት እንደሚከናወን ተገልጸ።

በአዲስ አበባ ደግሞ ከዚህ ወር ጀምሮ የድህረ መብራት ክፍያ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ይሆናል ተብሏል፡፡

ይህ ያሳወቀው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው።

እስካሁን 30 በመቶ ብቻ የሚሆን ተገልጋይ የድህረ ክፍያ በዲጂታል የክፍያ አማራጭ የሚከፍል መሆኑን የገለፀው አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ከዚህ ወር ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የድህረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በዲጂታል እንዲከፍሉ ይደረጋል ብሏል።

በቀጣይም ከሐምሌ 1 ጀምሮ በመላ አገሪቱ የሚገኙ አገልግሎት መስጫዎች ድህረ ክፍያ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል አማራጭ እንዲያደርጉ ይደረጋል ሲል አሳውቋል።

አገልግሎቱ በማህበራዊ ትስድር ገፁ ደንበኞቹ የተጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በተዘረጉ የክፍያ አማራጮች (በሞባይል ባንኪንክ፣ በሲቢኢ ብር እና ቴሌ ብር) በመጠቀም እንዲፈፅሙ ጥሪ አቅርቧል።

" ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ሲጠቀሙ አስፈላጊ ካልሆነ ወጪና እንግልት ያድናል ፤ ኑሮንም ያቃልላል " ያለው አገልግሎቱ " በጥሬ ገንዘብ ለመክፈል ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመምጣት ጊዜዎትን፣ ጉልበትዎትንና ገንዘብዎትን አያባክኑ፡፡ #ካሉበት_ሆነው በተዘረጉ ቀላልና ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ ብቻ ይጠቀሙ " ብሏል።

መረጃው የኢፕድ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
#MoE

" የትምህርት ሥርአቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ይዞ መቀጠል አይቻልም " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ውጤትና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትና ውጤት የጥናት ውጤት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ መድረክ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ " በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ የለውጥ ስራዎች እየተሠሩ ነው ፤ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም ይገባል " ብለዋል።

" የትምህርት ሥርአቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ይዞ መቀጠል አይቻልም " ያሉት ሚኒስትሩ " በሚታዩት ውጤቶች ሳንደናገጥ ዘርፉን ለመለወጥ ጠንክሮ መሥራት ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።

👉 የተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት ማነስ ፣
👉 ተስፋ መቁረጥ፣
👉 የመምህራን እጥረትና ተነሳሽነት አለመኖር፣
👉 የትምህርት ቤቶች መሠረተልማት መጓደልና ለመማር ማስተማር ምቹ ያለመሆን
👉 የትምህርት ቤቶች አመራር መጓደል #ለውጤቱ_መውደቅ ምክኒያቶች መሆናቸው በጥናቱ ተመላክቷል።

የትምህርት ጥራቱን ለማረጋገጥም የትምህርት ዘርፍ ችግሮችን ፈጥኖ  ማረም እንደሚገባም ተገልጿል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በቀጣይ ወር የሚጀመር ሀገራዊ  ንቅናቄ እንደሚኖር እና ማህበረሰቡን በማስተባበር ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ሥራ እንደሚሰራ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በዚህ ሂደት ወላጆች የትምህርት ቤቶች ባለቤቶች መሆናቸውን እያረጋገጡ መሄድ እንደሚገባቸውና  ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ውጤት(NLA)  እና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትና ውጤት በባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ምንጭ፦ የትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#መርዓዊ

ጠፍታ በፖሊስ ስትፈለግ የቆየችው ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ተቀብራ ተገኘች፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን በመርዓዊ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ በተለምዶው ሚካዔል ቁጥር 1 (150 ሰፈር) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ወረቀት አደመ አመራ የተባለች ግለሰብ ግንቦት 02/2015 ዓ.ም እንደጠፋች ከሟች ዘመድ ለፖሊስ ጥቆማ ይደረሳል፡፡

ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ባደረገው ክትትል ግንቦት 06 ቀን 2015 ዓ/ም በቤቷ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ ተቀብራ ተገኝታለች፡፡

የሟች አስከሬን ቤተሰቦቿ ፤በአካባቢው ነዋሪዎችና በፖሊስ አባላት ተቆፍሮ ወጥቶ  መርዓዊ ከተማ የመጀመሪያ ሆስፒታል ምርመራ የተደረገ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹን ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ የመርዓዊ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#ኮንስትራክሽን

አስገዳጁ ረቂቅ አዋጅ . . .

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ ትላልቅ #ተቋራጮች ከአነስተኛ የግንባታ ተቋራጮች ጋር በጥምረት እንዲሠሩ #የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ረቂቁ በከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ቀርቦ እንደሚገመገም ተገልጿል።

ረቂቁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #እንዲጸድቅ ሲደረግ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማረም በአገሪቱ የሚገኙ ትላልቅና ዋና ዋና ተቋራጮች ከአነስተኛ ትናንሽ ተቋራጮች በጥምረት እንዲሠሩ ዕድሉን የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ረቂቅ ህጉን #በአስገዳጅነት እንዲዘጋጅ የተደረገው አነስተኛ አቅም ያላቸው ተቋራጮች ሰፊ ልምድና አቅም ካላቸው ተቋራጮች ጋር በመሥራት ልምድ እንዲያገኙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ በማሰብ ነው ተብሏል።

አነስተኛ ደረጃ ያላቸው ተቋራጮች ያልተገባ ተግባር ሲፈጽሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና #ክፍያ ላይም ምንም ዓይነት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያስችል ሕግ መሆኑ ተገልጿል።

አዋጁን በማርቀቅ ሂደት ፦
- የሕንፃ አማካሪ ድርጅቶች፤
- የሕንፃ ተቋራጭ ማህበራት፤
- በአገሪቱ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች፤
- ፕሮጀክት ያላቸው አካላት፤
- የገንዘብ ሚኒስቴር፤
- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
- በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሠሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንደተሳተፉበት ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ፤ አነስተኛ ደረጃ ያላቸው የግንባታ ተቋራጮች እራሳቸውን ብቁ አድርገው መንግሥት በሚያሰማራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ድርሻ ይዘው ለመሥራት ከወዲሁ ዝግጅት ያድርጉ ብሏል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የዘማሪት ሂሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።

@tikvahethiopia