TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

ቦርዱ የህወሓትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው " ይነሣልኝ " ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

ህወሓት ያቀረበው ጥያቄ ምንድነው ?

ህወሓት የፓርቲውን ህጋዊ ሰውነት ስረዛ፤ የፓርቲው ሃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ እና የፓርቲው ንብረት ተጠርቶ ፓርቲው ዕዳ ካለበት ለዕዳ መሸፈኛ እንዲውል፤ ቀሪው ገንዘብና ንብረት ለሥነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲውል ከዚህ በፊት በምርጫ ቦርድ የተላለፈው ውሳኔ እንዲነሳ ሲል በደብዳቤ ጠይቋል።

ለቦርዱ ውሳኔ ምክንያት የሆነው ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመፅ ተግባር አሁን ላይ ባይኖርም እንደገና ህጋዊ ሰውነቱን ለፓርቲው ለመመለስ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ 1162/2011 ተደንግጎ አይገኝም ሲል ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በዚህም የህጋዊ ሰውነት ጥያቄ የማስመለስ ጉዳይ በህግ የተደገፈ ሆኖ እንዳላገኘው ቦርዱ አመልክቷል።

ፓርቲው ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በአዋጅ 1162/2011 አንቀፅ 66 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ህጉን መሰረት አደርጎ ሲፈቅድ መሆኑን ቦርዱ ወስኗል።

የፓርቲው አመራሮች እና ንብረትን በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ፓርቲው ላይ የሰጠው የስረዛ ውሳኔ ውጤቶች በመሆናቸው እንደአዲስ ሊጠየቁ የሚችሉ አይደሉም ያለው ምርጫ ቦርድ በዚህ በኩልም የተጠየቀውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

(ደብዳቤው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ #ኔትዎርክ ተቋርጧል። በትግራይ ክልል ከምሽት 12 ሰዓት አንስቶ የኔትዎርክ አገልግሎት መቋረጡን በዚህም ምክንያት " ምን ተፈጥሮ ነው ? " በሚል ጭንቀት እንደገባቸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰቡን አባላት መልዕክት ይዞ ኢትዮ ቴሌኮምን አነጋግሯል። ኢትዮ ቴሌኮም ፤ እውነት ነው ኔትዎርክ ተቋርጧል ሲል አረጋግጦልናል። " ኔትዎርክ የተቋረጠው ፋይበር ተቆርጦ…
#Update

ኢትዮ ቴሌኮም በ " ፋይበር መቆረጥ " ምክንያት በትግራይ ተቋርጦ የነበረውን የኔትዎርክ አገልግሎት ለማስቀጠል ሲያከናውን የነበረውን የጥገና ስራ ማጠናቀቁንና አገልግሎት መመለሱን አሳውቆናል።

ኢትዮ ቴሌኮም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ ፤ ሰራተኞቹ ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ በሁለት ቦታዎች ላይ የነበረውን የፋይበር መቆረጥ በመጠገን ወደነበረበት መመለስ ችለዋል።

የፋይበር መቆረጥ ያጋጠመው በ " አላማጣ " እና በ " ሰመራ " በኩል ሲሆን በምን ምክንያት ሊቆረጥ እንደቻለ የማጣራት ስራ ለመስራት እየተሞከረ ነው ተብለናል።

" የፋይበር መቆረጥ በተለያዩ ቦታዎች አልፎ አልፎ ያጋጥማል " ያለን ኢትዮ ቴሌኮም በሁለቱ ቦታዎች ያጋጠመውን የፋይበር መቆረጥ ምክንያት ለማወቅና " በዚህ ነው ሊቆረጥ የቻለው " የሚለውን ለመለየት እየተሰራ ነው ሲል አስረድቶናል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ባይቶና

ቦርዱ ባይቶና መስራች ጉባኤ እንዲየከናውን ወሰነ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፤ የብሔራዊ ባይቶና ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ፓርቲ አደራጅ ኮሚቴ ዐዋጁን መሠረት በማድረግ የመሥራች ጉባዔውን እንዲያከናውን ውሳኔ አሳልፏል።

ቦርዱ ፤ ዛሬ ለነ ኪዳነ አመነ በላከው ደብዳቤ ፓርቲው ጥቅምት 23 ቀን 2012 ዓ.ም ያደረገው የመስራች ጉባኤ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 የተቀመጡትን መስፈርቶች በማሟላት የተከናወነ ባለመሆኑ በጉባኤ የተከናወኑ የአመራር ምርጫም ሆነ የፀደቁ ሰነዶችን እውቅና ያልሰጠ መሆኑን አሳውቋል።

ምርጫ ቦርድ፤ የፓርቲው አደራጅ ኮሚቴ አዋጁን መሰረት በማድረግ የመስራች ጉባኤውን እንዲያከናውን ወስኗል።

(ይህ ውሳኔ የተላለፈበት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ በአዲስ አበባ የተወሰኑ መንገዶች #ይዘጋሉ

" የሚጠብቁንን ጀግኖች እናክብር " በሚል መሪ ቃል በዓለም ለ24ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ2ኛ ጊዜ የሚከበረውን ' የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቀን ' ክብረ በዓልን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ ዙሪያ ለተወሰነ ሰዓት  መንገድ ዝግ ይደረጋል ተብሏል።

በመስቀል አደባባይ ዙሪያ መንገዶች ዝግ የሚደረጉት ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል።

የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ፤

- ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ፤

- ከላንቻ ወደ መስቀል አደባባይ አራተኛ ክፍለ ጦር ዝግ የሚደረግ ሲሆን #ለከባድ ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል።

- ከከፍተኛው ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ  መስቀል አደባባይ ለገሐር መብራት ፤

- ከጎማ ቁጠባ በብሔራዊ ቴአትር ወደ  መስቀል አደባባይ ቴሌ መስቀለኛ ወይም ክቡ ባንክ፤

- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል መስቀለኛ ፤

- ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ ፤ ከማለዳው 12:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ 5:00 ሠዓት ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ሌሎች #አማራጭ_መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

" ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ሕንፃዎች በቴክኖሎጂ የበለፀገ ዘመናዊ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በመገንባት ለአዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ ብርሃን እና ውበት እንጨምራለን " - አቶ ግሩም ፀጋዬ

ብርሃን ባንክ የዋና መ/ቤት ህንጻ አርኪቴክቸራል ዲዛይን ውድድር በማካሄድ አሸናፊ ለሆኑ የሽልማት መርሃግብር አካሂዷል፡፡

መርሃግብሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጉማቸው ኩሴ፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ግሩም ፀጋዬ፣  የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ባለ አክሲዮኖች፣ የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል፡፡

በዕለቱም የዚሁ ህንፃ ግንባታ የመጀመሪያው አካል የሆነውን የህንፃውን ዲዛይን የመምረጥ ሂደት በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ ያሸነፈው ድርጅት የተለየ ሲሆን ከ1ኛ-3ኛ ለወጡት ተወዳዳሪዎች ዕውቅና የመስጠት መርሃግብር ተካሂዷል፡፡

የብርሃን ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ግሩም ፀጋዬ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት፤ ባንኩ በአዲስ አበባ የፋይናንስ ተቋማት መገኛ በሆነው ሰንጋተራ አካባቢ 5400 ካ.ሜ ስፋት ያለው መሬት ተረክቦ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ የዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ግንባታውን ለማከናውን በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አክለውም ቀጣይ ሂደቶች ሲጠናቀቁ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ሕንፃዎች በቴክኖሎጂ የበለፀገ ዘመናዊ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በመገንባት ለአዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ ብርሃን እና ውበት በመጨመር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል፡፡

https://t.iss.one/berhanbanksc
#ቢግ_5_ኮንስትራክት_ኢትዮጵያ

መቀመጫውን በዱባይ ሻርጃ ያደረገውና ላለፉት 20 ዓመታት ዘመናዊ እና አስተማማኝ የግንባታ መፍትሔዎችን ለግንባታው ዘርፍ ሲያቀርብ የቆየውን MEMAAR BUILDING SYSTEMS FZC በቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ኢግዚቢሽን ላይ ያግኙ!  የሜማር ምርቶች የግንባታ ፕሮጀክቶችን ፍጥነት፣ ቅልጥፍና እና ዘላቂነት ለማጎልበት ታስበው የተነደፉ ናቸው።

ስለሥራዎቻቸው እና ምርቶቻቸው የበለጠ ለማወቅ በቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ዐውደ ርዕይ ላይ ዛሬውኑ በመመዝገብ ይሳተፉ ! 

ለመመዝገብ ይሄን ይጫኑ ፡ https://bit.ly/3oI8P6L

የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይከተሉ: https://t.iss.one/big5ethiopia
የቤት ፈረሳ ጉዳይ ...

(በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል - ጆሲ)

" የቲክቫህ ቤተሰቦች እንደምታውቁት ' ሸገር ሲቲ ' በሚል ምክንያት በነበረ የቤት ማፍረስ ዘመቻ ብዙ ሰዎች እንደተፈናቀሉ የሚዘነጋ አይደለም።

ግን ለጥቂት ጊዜ የመቆም አዝማምያ አሳይቶ ነበር፤ አሁን ላይ ግን ከሚባለው በላይ በአስከፊ ሁኔታ ቀጥሏል።

በጣም #በሚያፀይፍ_ሁኔታ በሚባል መልኩ እንደሚታወቀው ወቅቱ የዝናብ ወቅት ነው ህዝቡ በዚ ወቅት እንኳን መፈናቀል አይደለም እንደፈለገ ወጥቶ መግባት እንኳን የማይችልበት ወቅት ነው ታድያ በዚህ ወቅት ይህ ህዝብ የት ይጠለል ?

ህፃናት ልጆች አሉ ፤ አረጋውያን አሉ ፤ ነፍሰ ጡሮች አሉ ታድያ ይሄንን እንኳን ከግምት ውስጥ ያላስገባ የልማት ዘመቻ በየትኛው ወገን ነው ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው ?

እሱ ይቅር እኔ ባለሁበት አካባቢ እየተደረገ ያለው ነገር እጅግ አፀያፊ ተግባር ከሰው ልጅ ማንነት የማይጠበቅ ፤ ሰብዓዊነት የጎደለው ተግባር ነው።

እባካቹ የሚመለከተው አካል ይህንን ቅሬታችን ይስማን ። "

Via @tikvah_eth_Bot

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#PNG

" የህዝቡን ገንዘብ አባክነዋል " የተባሉ ሚኒስትር ስራቸውን አቆሙ።

ከሰሞኑን እንግሊዝ ፣ ሎንዶን ውስጥ ለተካሄደው የንጉሥ ቻርልስ በዓለ ሲመት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች  ፣ ባለስልጣናት ተጉዘው ነበር።

ከነዚህም ውስጥ የፓፕዋ ኒው ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀስቲን ታካቺንኮ አንዱ ሲሆኑ በንጉሥ ቻርልስ በዓለ ሲመት ወቅት ገንዘብ አባክነዋል የሚል ውዝግብ መነሳቱን ተከትሎ ሥራ ማቆማቸው ተሰምቷል።

አገሪቱ ሚኒስትሩን በይፋ ለበዓለ ሲመቱ በላከችበት ገንዘብ ማባከናቸው ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የ25 ዓመት እድሜ ካላት ልጃቸው ሳቫና ጋር ነበር ለበዓለ ሲመቱ የተጓዙት ተብሏል ፤ ልጃቸው የመጀመሪያ ደረጃ የአውሮፕላን በረራቸውንና በሲንጋፖር ያደረጉትን ግብይት በቲክቶክ ገጿ ስታጋራ ነበር።

ልጅቷን የተቹ ሰዎችን ሚኒስትሩ " ኋላ ቀር እንስሳት " ብለዋቸዋል። ንግግራቸውን ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ነበር።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጄምስ ማራፔ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ " ከሥራ ለመልቀቅ " እንደተስማሙ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የሕንዱ ጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ ወደ አገሪቱ ጉብኝት ሲያደርጉ ውዝግቡ እክል እንዳይፈጥር ሥራ እንደለቀቁ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ፤ " ስለ ጉዳዩ የተነዛው ሐሰተኛ ወሬ እንደጠራም ለማሳወቅ እወዳለሁ " ብለዋል።

የአገሪቱ ጋዜጣ እንደዘገበው ወደ አንድ ሚሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጭ ሚኒስትሩ ከ10 ባለሥልጣኖች ጋር በበዓለ ሲመቱ ላይ ተገኝተዋል።

የመንግሥት ቃል አቀባይ ቢል ቶራሶ 10 ባለሥልጣኖች ከ10 እንግዶች ጋር ወደ ለንደን እንደተጓዙ ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ልጅ በለቀቀችውና አሁን ከገጿ በጠፋው ቪድዮ ቅንጡ የፋሽን መደብሮች ስትገባ ይታያል።

ለሕዝብ አገልግሎት መዋል ያለበት ገንዘብ እየባከነ ነው በሚልም ቁጣ ተነስቷል።

አባቷ ግን " በእነዚህ ሰዎች ልጄ ተጎድታለች። ቅናት መጥፎ ነው። እነዚህ ሰዎች ለአገራቸው የሚያገለግሉ ሰዎችን ከማጠልሸት ውጭ ሥራ የላቸውም " ብለዋል።

ይህንን ንግግር ካደረጉ በኋላ መልሰው ለንግግራቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ሕዝቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ይቅርታ እንዲቀበል ጠይቀዋል።

Credit : BBC NEWS

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ቢሯቸው ወስጥ በስራ ላይ እያሉ በጥይት ተመተው  የተገደሉት የአቶ አለባቸው አሞኜ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ።

በአ/አ ከተማ የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለባቸው አሞኜ ዛሬ ስርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙን ከክ/ከተማው ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

አቶ አለባቸው ፤ እድሜያቸው 33 የነበረ ሲሆን ባለትዳር እንዲሁም የአንድ ወንድ እና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበሩ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ አቶ አለባቸውን የገደላቸው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል መሆኑንና በቁጥጥር ስር መዋሉን ማሳወቁ ይታወሳል።

ፎቶ፦ የቂርቆስ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia