TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የወረዳ አመራሩ ተገደሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለባቸው አሞኜ በዛሬው ዕለት በቢሮአቸው ውስጥ ተገደሉ።

የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ባሰራጨው መረጃ ፤ " አቶ አለባቸው አሞኜ ቢሯቸው ውስጥ ቁጭ ብለው የህዝብ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ከአንድ #ተገልጋይ በደረሰባቸው #ጥቃት ህይወታቸው አልፏል " ብሏል።

ክ/ከተማው ምንም እንኳን ግድያውን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ ባያደርግም ጥቃት ያደረሰው ተጠርጣሪ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን አመልክቷል።

ተገቢው የምርመራ ሂደት ተከትሎ ተጠያቂነት የማስፈን ስራ ይሰራልም ብላል።

" አቶ አለባቸው በስራ ቁርጠኝነት የሚታወቁ " ናቸው ያለው የቂርቆስ ክ/ከተማ " በበርካታ መንግስታዊና ህዝባዊ ተግባራት አርዓያነት ያለው ስራ የሰሩና ያስተባበሩ አመራራችን ነበሩ " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ቴሌብር

በጉዞ ላይ ሆነው ነዳጅ ቢያልቅብዎ፤ በቴሌብር አካውንትዎ በቂ ገንዘብ ባይኖር ምን ማድረግ ይችላሉ?
አይጨነቁ… #ቴሌብር_እንደኪሴ እያለ የነዳጅ ታንከርዎ ባዶ አይሆንም!

የጎደሎትን በቴሌብር አሟልተው፤ ነዳጅዎን ሞልተው ጉዞዎን ይቀጥሉ፤ ታዲያ ለነዳጅ ክፍያዎ ቴሌብርን የሁልጊዜ ምርጫዎ ያድርጉ።

ቴሌብርን ይዞ .. የተሳካ ጉዞ!
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ግድያውን የፈፀመው የፖሊስ አባል ነው " - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባቸው አሞኜ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ #በፖሊስ አባል መገደላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳወቀ።

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል መሆኑን ፓሊስ ገልጿል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ግድያውን የፈፀመው ግለሰብ ፤ የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ያመለክታል፡፡

ወረዳው ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም " ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ " በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ ገድሏቸዋል።

ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@tikvahethiopia
በትግራይ #ኔትዎርክ ተቋርጧል።

በትግራይ ክልል ከምሽት 12 ሰዓት አንስቶ የኔትዎርክ አገልግሎት መቋረጡን በዚህም ምክንያት " ምን ተፈጥሮ ነው ? " በሚል ጭንቀት እንደገባቸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰቡን አባላት መልዕክት ይዞ ኢትዮ ቴሌኮምን አነጋግሯል።

ኢትዮ ቴሌኮም ፤ እውነት ነው ኔትዎርክ ተቋርጧል ሲል አረጋግጦልናል።

" ኔትዎርክ የተቋረጠው ፋይበር ተቆርጦ " ነው ያለው ኢትዮ ቴሌኮም " ሰራተኞቻችን በጥገና ላይ ናቸው " ብሏል።

" ከማዕከል የሚያገናኘው ፋይበር ሁለት ቦታ ተቆርጧል፤ ዋናው እና የመጠባበቂያውን ጨምሮ " ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ከመቐለ ፣ ከደሴ እና ከሰመራ ሰራተኞች ተሰማርተው በርብርብ እየሰሩ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል።

የጉዳቱን መጠን በተመለከተ ላቀረብነው ጥያቄ " ምሽት በመሆኑ የጉዳቱን መጠን ማረጋግጥ አልተቻለም " ተብለናል።

@tikvahethiopia
#MyWishEnterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
0913356384 / 0912710661  0910626917 / 0928414395
0911606068 / 0922475851  0935409319 /0911602664
TIKVAH-ETHIOPIA
አርቲስት ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የክላርኔት ሙዚቃ ተጫዋቹ ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ። የአርቲስቱን ህልፈት ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬድዮ ጣቢያ ከቅርብ ወዳጆቹ ማረጋገጡን አሳውቋል። አርቲስት ዳዊት ፍሬው ለሙዚቃ ስራ ወደ ጣሊያን ሀገር ተጉዞ እንደነበር የሬድዮ ጣቢያው ዘገባ ያለመለክታል። ክላርኔት ተጫዋቹ እና ሙዚቀኛው ዳዊት ህይወቱ አልፎ የተገኘው #በተኛበት_ክፍል…
#Update

ለሙዚቃ ስራ ወደ አውሮፓ ሄዶ ጣልያን ፣ ሮም ከተማ ባረፈበት ክፍል ህይወቱ አልፎ የተገኘው የአርቲስት ዳዊት ፍሬው አስክሬን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብቷል።

ትላንት በሮም ደብረ ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የፍታት እንዲሁም የአስክሬን ሽንት ፕሮግራም ተካሂዷል።

የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ነገ ግንቦት 6 /2015 ከቀኑ 6 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት  ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን የሚፈፀም ሲሆን ከዛ ቀደም ብሎ ረፋዱን በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የሽኝት እና የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ይካሄዳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተከፋፈለ ሲኖዶስ የለም " የ2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት የሁለተኛው ቀን ጉባኤ ዛሬ ሲካሄድ ውሏል። ይህ አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባባቢዋ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ብፁዕነታቸው በሁለተኛው ቀን በነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሁለት ርዕሰ ጉዳዮች መወያያየቱን ገልጸዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ…
#EOTC

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ   ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዎስቆሮስ የደቡብ ትግራይ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና መተከል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቀደም ሲል ያገለግሉባቸው በነበሩ አህጉረ ስብከቶች አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ወስኗል።

ይህን ውሳኔ የተላለፈው ትላንት በነበረው የምልዓተ ጉባኤው ሶስተኛ ቀን ውሎ ነው።

ከዚህ ባለፈ ጉባኤው በትላንት ውሎው እንዲነጋገርበት ተይዞ የነበረው #የኤጲስ_ቆጶሳት ምርጫ ጉዳይ የጉባኤው የመጨረሻ አጀንዳ እንዲሆን የአጀንዳ ሽግሽግ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።

ጉባኤው ትላንት የዋልድባ ዳልሻህ ኪዳነምሕረት ማህበረ ደናግል ገዳምን በተመለከተ የያዘው አጀንዳ ላይ መወያየቱ የተገለፀ ሲሆን ለውሳኔ በይደር እንዲቆይ ተደርጓል።

የመረጃው ምንጭ ፦ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ለኢኦተቤ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሰጡት ማብራሪያ ነው።

@tikvahethiopia
" ... በመንግስት አሰራሮች ላይ በሚያቀርቡት የፖለቲካ ትችት ምክንያት መንግሥት ያሰራቸውን ግለሰቦች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ ጠይቃለሁ " - አቶ ክርስቲያን ታደለ (የህ/ተ/ም/ቤ አባል)

የፓርላማ አባሉ በመንግስት ታስረዋል ያሏቸው የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስታያን ታደለ ፤ መንግስት በፖለቲካ አመለካከታቸውና በመንግስት አሰራሮች ላይ በሚያቀርቡት የፖለቲካ ትችት ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች ያሰራቸው ግለሰቦች መኖራቸውን በመግለፅ እነዚህን እስረኞች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ ጠይቀዋል።

አቶ ክርስቲያን ፤ በእስር ላይ ይገናኛሉ ካሏቸው ግለሰቦች አንዱ አቶ ዘሪሁን ገሰሰ ናቸው።

" ፓርቲ የመሰረትነው መንግስትን መቼና እንዴት መተቼት እንዳለብን ከራሱ ከመንግስት አቅጣጫ እየተቀመጠልን ለመንቀሳቀስ አይደለም " ያሉት አቶ ክርስቲያን " በተለይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በትንሹ የራሱን አባላት ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታውን በወጉ እንዲወጣም እጠይቃለሁ። " ብለዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ ከአብን መስራቾች አንዱ እና ፓርቲውን ወክለው በህዝብ ተመርጠው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ሲሆኑ ከዚህ ቀደም ከፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት መልቀቃቸውን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

ቦርዱ የህወሓትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው " ይነሣልኝ " ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

ህወሓት ያቀረበው ጥያቄ ምንድነው ?

ህወሓት የፓርቲውን ህጋዊ ሰውነት ስረዛ፤ የፓርቲው ሃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ እና የፓርቲው ንብረት ተጠርቶ ፓርቲው ዕዳ ካለበት ለዕዳ መሸፈኛ እንዲውል፤ ቀሪው ገንዘብና ንብረት ለሥነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲውል ከዚህ በፊት በምርጫ ቦርድ የተላለፈው ውሳኔ እንዲነሳ ሲል በደብዳቤ ጠይቋል።

ለቦርዱ ውሳኔ ምክንያት የሆነው ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመፅ ተግባር አሁን ላይ ባይኖርም እንደገና ህጋዊ ሰውነቱን ለፓርቲው ለመመለስ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ 1162/2011 ተደንግጎ አይገኝም ሲል ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በዚህም የህጋዊ ሰውነት ጥያቄ የማስመለስ ጉዳይ በህግ የተደገፈ ሆኖ እንዳላገኘው ቦርዱ አመልክቷል።

ፓርቲው ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በአዋጅ 1162/2011 አንቀፅ 66 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ህጉን መሰረት አደርጎ ሲፈቅድ መሆኑን ቦርዱ ወስኗል።

የፓርቲው አመራሮች እና ንብረትን በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ፓርቲው ላይ የሰጠው የስረዛ ውሳኔ ውጤቶች በመሆናቸው እንደአዲስ ሊጠየቁ የሚችሉ አይደሉም ያለው ምርጫ ቦርድ በዚህ በኩልም የተጠየቀውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

(ደብዳቤው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia