TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sudan

የጎረቤት ሱዳን ዜጎች በሰላም እጦት ሳቢያ የገዛ ሀገራቸውን ለቀው እየተሰደዱ ይገኛሉ።

ሱዳን አሁንም በጦርነት እየታመሰች ሲሆን ተዋጊዎቹ ኃይሎች ውጊያ የማቆም ፍላጎት እያሳዩ አይደለም።

በተደጋጋሚ በተለያዩ ሀገራት ጥረት የተኩስ አቁም እንዲደረግ እንዲሁም ዳጋሎ እና አል ቡርሃን ችግሩን እንዲፈቱ ጥረት ቢደረግም ውጤት አላስገኘም።

ዛሬም በርካቶች የሱዳን ዜጎች ሀገራቸውን ጥለው እየሸሹ ናቸው። የውጭ ሀገር ዜጎችም ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሱዳንን ምድር እየለቀቁ ይገኛሉ።

በሱዳን ጦርነት ምክንያት እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ በመተማ በኩል ፤ የ61 ሀገራት ዜጎች የሆኑ 7726 ሰዎች ገብተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የዓለም ጤና ድርጅት በቻይና የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው በሚል አወጀ። ድርጅቱ ቫይረሱን በዓለም አቀፍ የጤና ስጋትነት ያወጀው ከቻይና ውጭ ወደ ሌሎች ሀገራት መዛመቱን ተከትሎ ነው ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳስታወቁት፥ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ጤና ስጋትነት የታወጀበት ዋነኛው ምክንያት በቻይና እየሆነ ባለው ሳይሆን…
#NewsAlert

የዓለም ጤና ድርጅት ከ3 ዓመት በኃላ ኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ አጣዳፊ የጤና ስጋት መሆን #ማብቃቱን ይፋ አደረገ።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከዚህ ቀደም አውጀውት የነበረው የኮቪድ-19 የምድራችን አጣዳፊ የጤና ስጋት አሁን ላይ ማብቃቱን አሳውቀዋል።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ትላንት ለዚሁ ጉዳይ የተቋቋመው ኮሚቴ ለ15ኛ ጊዜ በመገናኘት ባደረገው ስብሰባ ወቅት ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ ገልጸው በዚህም መሰረት የኮሚቴውን ምክረ ሃሳብ በመቀበል የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ አጣዳፊ የጤና ስጋትነት ማብቃቱን አውጀዋል።

ይህ ማለት ግን ኮቪድ አብቅቷል ማለት እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት እኤአ ጥር 20/2020 ላይ ነበር ኮቪድ-19 የዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ብሎ ያወጀው።

ይኸው ወረርሽኝ በትንሹ 20 ሚሊዮን ሰዎችን ገድሏል (እንደ WHO መረጃ) ፣ በርካቶችን ቤተሰብ አሳጥቷል ፤ የዓለምን ኢኮኖሚ እንዳልነበር አድርጓል።

@tikvahethiopia
የብር የምንዛሬ ለውጥ ሊደረግ ነው ?

" የሚናፈሰው ወሬ ሁሉ ሀሰት ነው " - አቶ ማሞ ምህረቱ

በኢትዮጵያ " የገንዘብ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያ ሊደረግ ነው " በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።

የባንኩ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ ፥ " እስከዛሬ ድረስ / እስካሁን ድረስ በአንድ ጊዜ የሚደረግ የብር የምንዛሬ ተመን ለውጥ / one time devaluation / ለማድረግ የተደረገ ውይይትም፣ የተወሰነ ውሳኔ ፈፅሞ የለም " ብለዋል።

የብር የምንዛሬ ለውጥን / devaluation በተመለከተ የተደረገ ውይይት ወይም የተወሰነ ውሳኔ የለም ያሉት አቶ ማሞ ዜጎች በተረጋጋ ሁኔታ በገበያ ስርዓቱ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

አቶ ማሞ ምህረቱ ፥ " በማህበረሰቡ ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ መንግሥት የብር የውጭ ምንዛሬን ለውጥ በማድረግ devaluation ሊያደርግ ነው የሚል ብዙ ወሬ አለ ፤ ይሄን ተከትሎ ገበያ ውስጥ ስካር በሚባል ሁኔታ ሰዎች አንዳንዴ እቃ ይይዛሉ፤ አንደንዴ ደግሞ መሰረታዊ በሚባሉት እቃዎች ላይ አላስፈላጊ የሆነ ዋጋ ይጨምራሉ ከዛም አልፎ የኢኮኖሚ ጥቅም በሌለው ጉዳይ ላይ ያላቸውን ገንዘብ ኢንቨስት ያደርጋሉ ይሄ ፈፅሞ ትክልል ያልሆነና ሊስተካከል የሚገባው ጉዳይ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን በተለይ በመዲናዋ መንግሥት የብር የውጭ ምንዛሬን ለውጥ በማድረግ devaluation ሊያደርግ ነው በዚህም መሰረታዊ እና ሌሎች ቁሶች ዋጋ ሊጨምር ይችላል የሚል ወሬ በስፋት እየተሰራጨ ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቢግ_5_ኮንስትራክት_ኢትዮጵያ

አስደሳች ዜና!

ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ የንግድ ትርዒት ተከታታይ የሆኑ የCPD- ዕውቅና ያላቸው የኢንዱስትሪ ውይይቶችን በ አምስት መሪ አጀንዳዎች፡- በቴክኖሎጂ፣ ፕሮጀችት አስተዳደር፣ ስነ-ህንፃ እና ንድፍ፣ በኢንዱስትሪ ዘላቂነት እንዲሁም ምህንድስና ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን ይዞላችሁ መጥቷል።
እነዚህ ውይይቶች በዘርፉ ባለሞያዎች የሚመሩ መሆናቸው ጠቃሚ ዕይታዎችን እና አመለካከቶችን ለማግኘት ምቹ መድረክ ናቸው።

ይህን ጠቃሚ የመማሪያ አጋጣሚ ለማግኘት አሁኑኑ ይመዝገቡ፡ https://bit.ly/3oI8P6L

የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይከተሉ: https://t.iss.one/big5ethiopia
#NedajApp

ነዳጆን በነዳጅ !
ነዳጅ ይቀላል !

1⃣🅾🅾🅾ሺ  በላይ በመላሀገሪቱ በተመዘገቡ የነዳጅ ማደያዎች በነዳጅ አፕሊኬሽን ይጠቀሙ ‼️

💥ቀላል፣ፍጣን እና ለአገልግሎት ምቹ

💥እንድ ጌዜ በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ  አካውንቶን Link አርገው የሚጠቀሙበት

💥በነዳጅ STANDBY( ፈጣን) ፈጣን አግልግሎት የሚያገኙበት ‼️

🚀አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#Nedaj #nedajapp
ሰሞነኛው ዝናብ ...

በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከሰሞኑን እየጣለ ያለው ዝናብ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ፥ ጎፋ ዞን ዑባ-ደብረፀሃይ ወረዳ ዛባ ቀበሌ በጣለው ከባድ ዝናብ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 21 ሰዎች መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል። በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በህይወት የተረፉ ዜጎ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲጠለሉ የተደረገ ሲሆን ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መገባቱ ተሰምቷል።

ተጎጂ ወገኖችን ለመደገፍም በዞኑ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ማቋቋሚያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000511561276 ላይ ድጋፍ እንዲደረግ ተጠይቋል።

#Amhara

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ 02 አዋተል ቀበሌ ሚያዚያ 27/2015 ዓ.ም ምሽት ለተከታታይ 30 ደቂቃ የጣለው በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በእንስሳት፣ በሰብልና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ከ37 ሄክታር መሬት በላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።

#Gambella

በጋምቤላ ክልል ፤ በዲማ ወረዳና አጎራባች ወረዳዎች ከሚያዝያ 25 /2015 ዓ.ም ጀምሮ እየጣለ ባለው ሃይለኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ በሚሊየን የሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የጎርፍ አደጋው እስካሁን ባለው መረጃ በወረዳው ከ70 በላይ መኖሪያ ቤቶች በውሃ ያጥለቀለቀ ሲሆን በሰብል ላይም ጉዳት አድርሷል።

ጎርፉ በዲማ ከተማ ወንዝ ዳር የነበረውን የከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ መሳቢያ ጀነሬተርና ፖምፕ ግንብ ቤቱን ጨምሮ በሚሊዮን በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ታውቋል።

በዚህም ችግር ሳቢያ የከተማው ንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት መቆሙ ተነግሯል።

በተመሳሳይ በዲፕ (መርከስ) ቀበሌ የሚገኘው የእኩጉ ስደተኞች መጠለያ ጣብያና የአካባቢው ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት መሳቢያ ጀነሬተሮች በጎርፍ መወሰዱ ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአኮቦ ወንዝ እስከጫፉ ድረስ በመሙላቱ ዲማ ወረዳን ጨምሮ ሁለት አጎራባች ወረዳዎች የሚያገናኝ የአኮቦ ብረት ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በደረሰው አደጋ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለማገዝ የክልሉ መንግሥትን ጨምሮ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃ ምንጮች ፦ የጎፋ ዞን ፣ የለገሂዳ እና የዲማ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የአዲስ አበባ ጸጥታ ቢሮ ይህን ጥያቄ ይዛችሁ አደባባይ አትወጡም አለን " - አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) መንግስት የገቢ ግብርን እንዲቀንስ ለመጠየቅ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አቅዶ የነበር ቢሆንም መንግሥት ሰልፉን እንዳይደረግ መከልከሉን አሳውቋል። የኮንፌደሬሽኑን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ እንዳሳወቁት ፤ ዛሬ የሚከበረውን የሰራተኞች…
መንግሥት የከለከለው ሰልፍ ...

በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ በአደባባይ ሊከበር የነበረው የሰራተኞች በዓል (ሜይዴይ) በመንግስት መከልከሉ ይታወሳል።

በዚህ ዙርያ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ምን አሉ ?

አቶ ካሳሁን ፎሎ ፦

" የእኛ አላማ የነበረው የሰራተኛውን ጥያቄ ይዘን በመላው ከተማ ሳይሆን በመስቀል አደባባይ ብቻ ማክበር እና ጥያቄዎቻችንን በሰላም ማቅረብ ነበር።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊዋ ግን ከበአሉ አንድ ቀን በፊት እሁድ ምሽት ይህን ማድረግ እንደማንችል ነገሩን፣ የሰራተኞች ቀንን ልታከብሩ ሳይሆን መንግስትን ልትጠይቁ አስባችኋል፣ ይህን ጥያቄ ይዛችሁ አደባባይ አትወጡም ተብለናል። እንዲህ ብለው ተቆጡ፣ መጥቼ በአካል ላስረዳ ብልም አልቻልኩም፣ ደንብ እናስከብራለን ከፈለጋችሁ ሚሊኒየም አዳራሽ ሂዱ አሉኝ።

ልናቀርባቸው የነበሩት ሶስት ጥያቄዎች ፦

1. በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ሰራተኛው እየተቸገረ ነው፣ በተለይ ደግሞ ደሞዝ ተከፋዩ። መንግስት መፍትሄ ይስጠን። አብዛኛው ሰራተኛ በቀን አንዴም ለመብላት እየተቸገረ ነዉ።

2. የስራ ግብር ይቀነስልን።

3. የዛሬ አራት አመት ወጥቶ የነበረው የዝቅተኛ ደሞዝ ማስተካከያ አዋጅ እስካሁን ደንብ ሳይወጣለት ቆይቷል። ይህም ትኩረት ይሰጠው፣ በ600 ብር እየኖረ ያለ ሰው አለ፣ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ ደሞዝ በአማካኝ ከ800 - 1,200 ብር ነው።

4. የአሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲዎች ከደምበኛቸው ከሚቀበሉት ክፍያ ለሰራተኛው 80 ፐርሰንት ከፍለዉ ቀሪውን 20 ፐርሰንት እንዲወስዱ በሚል የወጣዉ መመሪያ አለመከበር በኤጀንሲ በተቀጠሩ  ሰራተኞች ላይ ተመልካች ያጣ የጉልበት ብዝበዛ እየተካሄደ ነው፣ መንግስት ትኩረት ያርግበት የሚል ነው።

እነዚህን ህገ-መንግስታዊ እና የመብት ጥያቄዎች ለማቅረብ ብንፈልግም ተከልክለናል። "

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
ምስል /ተ.ቁ. 2 - አዲስ ማለዳ ጋዜጣ/ 

@tikvahethiopia