TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#USA

አሜሪካ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ለማብቃት በተደረሰው ስምምነት መሠረት ውጤታማ ትጥቅ የማስፈታት እና ተያያዥ ተግባራትን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ተቆጣጣሪዎች እንዲሰማሩ ጠየቀች።

ይህንን የጠየቀችው በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረሰው ስምምነትን ስድስተኛ ወር ምክንያት በማድረግ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምን አለ ?

- የሰላማዊ ሰዎችን ጥበቃ እና ውጤታማ ትጥቅ የማስፈታት፣ ታጣቂዎችን የማሰናበት እና ከኅብረተሰቡ ጋር መልሰው የሚቀላቀሉበትን ሂደት የሚከታተሉ ተቆጣጣሪዎች በማሰማራት በስምምነቱ ላይ የተቀመጡ ሃሳቦች መቋጫ ሊያገኙ ይገባል።

- የኤርትራ ጦር እና ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ውጪ ያሉ ኃይሎች ሙሉ ለሙሉ ከትግራይ እንዲወጡ መደረግ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የፈጸሙ እና ተሳታፊዎችን ተጠያቂ ማድረግን ጨምሮ ተአማኒ የሽግግር ፍትሕ ሂደት በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው።

- ባለፉት ስድስት ወራት በስምምነቱ ትግበራ በርካታ አውንታዊ እርምጃዎች ተወስደዋል።

• በትግራይ ተቋርጠው የቆዩ መሠረታዊ አገልግሎቶች መልሰው ሥራ መጀመራቸው፣

• የሰብአዊ እርዳታ ያለገደብ መቅረቡ፣

• ህወሓት ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ማስረከቡ፣

• እስረኞች መፈታታቸው፣

• ሁሉን አካታች የሽግግር ፍትህ ሂደት መጀመር እና በትግራይ ጊዜያዊ መስተዳደር መቋቋሙ የተወሰዱ አውንታዊ እምርጃዎች ናቸው።

በሌላ በኩል ፥ አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከናወነው ስኬታማ የሰላም ሂደት በኦሮሚያ ክልል ሰላም ለማምጣት ዕድል መፍጠሩን አሳውቃለች።

ሀገሪቱ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል የተጀመረውን ንግግር አድንቃለች።

ሁለቱም ወገኖች ለሁሉም ተቀባይነት ያለው ስምምነት ላይ ለመድረስ በቅን ልቦና እንዲደራደሩ አበረታታለሁ ብላለች።

@tikvahethiopia
#USEmabssyAA

" የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው ወይም ኢሜይል / ቴክስት የምንልከው ከሚሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ " - በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ

የአሜሪካ ኤምባሲ የዲቪ (DV) 2024 አሸናፊዎች ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ይፋ ይደረጋል ብሏል ፤ መመልከቻውም ow.ly/9E7A50O7plm መሆኑን ገልጿል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፤ ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ድቪ (DV) ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ይፋ አድርጓል።

የዲቪ (DV) 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎች መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን የፊታችን ቅዳሜ ከሚያዚያ 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ አመልክቷል።

በዲቪ (DV) ሎተሪ ድረገጽ ow.ly/9E7A50O7plm ላይ በመግባት አመልካቾች ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት ማወቅ ይችላሉ ተብሏል።

በሌላ በኩል፤ " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው / ኢሜይል / ቴክስት የምንልከው "  በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁም ኤምባሲው አሳስቧል።

አመልካቾች ለዲቪ (DV) ሎተሪ ደርሷቸው እንደሆነ ወይም እንዳልደረሳው በራሳቸው እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር በዚህ ድረገፅ ow.ly/9E7A50O7plm ማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ መሆኑን ገልጿል።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 50 ሺህ ሰዎችን በድቪ ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

መረጃው የአል አይን ኒውስ እና በአ/አ የአሜሪካ ኤምባሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ቢሆንም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በዚህኛው የውይይት ስምምነት ላይ አልተደረሰም " - መንግሥት

በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ዛሬ ተጠናቀቀ።

በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በማስወገድ ሰላምን ለማምጣት ያለመውና በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ዛሬ መጠናቀቁን መንግሥት አሳውቋል።

ውይይቱ በምን በምን ጉዳዮች ላይ እንደነበር በዝርዝር ያልገለፀው መንግሥት " ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ቢሆንም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ግን በዚህኛው የውይይት ምዕራፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ አልተቻለም " ብሏል፡፡

" መግባባት ላይ አልተደረሰባቸውም " የተባሉ ጉዳዮችንም መንግሥት በግልፅ አላሳወቀም።

ግጭቱን በዘላቂነትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስቆም እንዲቻል ግን ሁለቱም አካላት የሰላም ውይይቱን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑ ላይ ተግባብተዋል ተብሏል።

መንግሥት በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና እስካሁን ሲመራባቸው በነበሩ መሠረታዊ መርሖች መሠረት ግጭቱን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት መንግስት የጸና አቋም እንዳለው አረጋግጧል።

መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ የሚጠራው ታጣቂው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ውይይቱን በተመለከተ የሚሰጠውን ማብራሪያ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ቢሆንም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በዚህኛው የውይይት ስምምነት ላይ አልተደረሰም " - መንግሥት በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ዛሬ ተጠናቀቀ። በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በማስወገድ ሰላምን ለማምጣት ያለመውና በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ዛሬ መጠናቀቁን መንግሥት አሳውቋል።…
#Update

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራው የታጠቀ ቡድን / በተናጠል ባወጣውና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተመሳሳይነት ባለው መግለጫ ፤ በታንዛኒያ ሲካሄድ የነበረው የመጀመሪያው ምዕራፍ የሰላም ንግግር ዛሬ መጠናቀቁን አሳውቋል።

በአንዳንድ አንኳር የሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መደረሱን የገለፀው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነገር ግን ቁልፍ በሆኑ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በዚህኛው ምዕራፍ ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉን አስረድቷል።

ግጭቱን በዘላቂነትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስቆም እንዲቻል የሰላም ውይይቱን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑ ላይ መግባባት መደረሱን አሳውቋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል።

መንግሥት ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ የታንዛኒያው የመጀመሪያ ምዕራፍ የሰላም ንግግር አውንታዊ እንደነበር እና በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ አሳውቋል።

ነገር ግን ውይይቱ መቀጠል ላይ ስምምነት መደረሱንና ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል።

ሁለቱም ተደራዳሪ አካላት በምን ጉዳዮች እንደተነጋገሩና መግባባት ላይ እንደደረሱ እንዲሁም በምን በምን ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልቻሉ ባወጡት መግለጫ በዝርዝር አላሳወቁም።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
#ማይዊሽ_ኢንተርፕራይዝ

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664
#እናት #ኢሕአፓ #መኢአድ

እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ ዛሬ በሰጡት የጋራ መግለጫ መንግሥት በአማራ ክልል ህገወጥ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን በመግለፅ እንቅስቃሴውን እንዲያቆም ጠይቀዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ በሕወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል የተከናወነው ከባድ የእርስበርስ ጦርነት አገርንና ህዝብን ከፍተኛ ጉዳት ላይ መጣሉ አስታውሰዋል።

" ጦርነቱ የትግራይ ፣ የአማራ፣ የአፋር ህዝብን የበለጠ  ጎድቶታል " ያሉት ፓርቲዎቹ " ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ወገኖቻችን  የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል፤ በመቶ ሺ የሚቆጠሩት የአካል ጉዳተኛ ተደርገዋል፡፤ ዜጎች በገዛ ሐገራቸው ተፈናቃይና ስደተኛ ሆነዋል፤ የመሠረተ-ልማት አውታሮችና ተቋማት ወድመዋል " ብለዋል።

ህዝቡ ገና ከጦርነቱ ቁስል አላገገመም ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት መክፈቱን የገለፁት ፓርቲዎቹ " ይህ አይነቱ አካሄድ አገር አፍራሽ በመሆኑ ከወዲሁ ጊዜው ሳይሄድ መንግስት እጁን ሊሰበስብ ይገባል " ብለዋል።

አሁን ላይ ነገሮች በተወሳሰቡበት ሁኔታ የፌዴራል መንግሥት ችግሩን በሚያባብስ መልኩ ወደ አማራ ክልል ሠራዊት አዝምቶ ' ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን መቆጣጠርና ትጥቅ ማስፈታት ' በሚል ሽፋን በየቦታው በከባድ መሣሪያ ጭምር በዜጎች ላይ ተኩስ ከፍቷል ሲሉ ሶስቱ ፓርቲዎች በመግለጫቸው ላይ ገልጸዋል።

" የተረጋጋና አስተማማኝ ሁኔታዎች ሳይፈጠሩ፣ ተቻኩሎ፣ በኃይል ትጥቅ ለማስፈታት መሞከር ሌላ ጦርነት ከመቀስቀስ የተለየ ውጤት የለውም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ሠላም የተነፈጉና እየተሳደዱ ያሉ ዜጎችን፣ በቅድሚያ ትጥቅ ማስወረድ ለምን አስፈለገ ? " ሲሉ የጠየቁት እነዚህ ሶሶት ፓርቲዎች " ኢትዮጵያ ከተዘፈቀችበት #የጎሰኝነት አረንቋ ሳትወጣ፣ በዘውግ በተደራጁ ሃይሎች በሚመራ መንግሥት የሚወሰዱ ማናቸውም እርምጃዎች ወደ ሌላ ችግር የሚያስገቡ ናቸውና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ " መንግስት በአማራ ክልል ዉስጥ የጀመረውን ህገ-ወጥ ጥቃት በአስቸኳይ አቁሞ ውይይትን መሰረት ባደረጉ አካሄዶች ብቻ ችግሮችን እንዲፈታ አጥብቀን እናሳስባለን " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

(የፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OromiaRegion

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል ሲካሄድ የነበረው የሰላም ንግግር ዛሬ መጠናቀቁ ይታወቃል።

ይህንን የሰላም ንግግር በተመለከተ ሁለቱም አካላት በተናጠል ባሰራጩት መግለጫ ውይይቱ አንውታዊ / በአንዳድን ጉዳዮች መግባባት ላይ የተደረሰበት እንደነበር እና በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ሳይቻል መቅረቱን አመልክተዋል።

ተደራዳሪ አካላቱ ስለምን እንደተነጋገሩ፣ በምን ጉዳዮች ላይ እንደተግባቡ እና በምን ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ ምንም ያሉት ነገር የለም።

ቢቢሲ የሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎችን ዋቢ በማድረግ ከዛው ዛንዚባር ባሰራጨው መረጀ ፤ መንግሥትን እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ካላስማሙ ጉዳዮች መካከል አንዱ " የጋራ የሽግግር መንግሥት ምሥረታ " ጉዳይ መሆኑ ታውቋል።

አንድ ስማቸው ይፋ እንዳይሆን የፈለጉ የውይይቱ ተሳታፊ ፥ " ተደራዳሪዎቹን ካላስማሟቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የጋራ የሽግግር መንግሥት መቋቋም ነው " ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ፥ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን እና ብልጽግናን ጨምሮ ሌሎች ፓለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተ የጋራ የሽግግር መንግሥት ይቋቋም ሲል መጠየቁን ከእኚሁ ተሳታፊ ማረጋገጡን ቢቢሲ አማክቷል።

የጋራ የሽግግር መንግሥት ምሥረታው በፌደራል መንግሥቱ ተደራዳሪዎች በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱን ተነግሯል።

ተሳታፊዎቹ እንደገለጹት የሽግግር መንግሥት በዋነኝነት የሚቋቋመው በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል መተማመን እንዲኖር እና አገሪቱ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ እንድትችል የማሻገር ኃላፊነትን እንዲወጣ ለማድረግ ነበር።

መንግስት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የአሁኑ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሰላም ንግግር ቢጠናቀቅም የውይይቱ መቀጠል ላይ ስምምነት መደረሱንና ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጫ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DigitalLottery

አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል።

3 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 0102013522 ሆኖ ወጥቷል።

👉 3 ሚሊዮን ብር - 0102013522
👉 1,200,000 ብር - 0100663609
👉 800 ሺህ ብር - 0100706800
👉 400 ሺህ ብር - 0100750353

(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)

ምንጭ፦ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ በትግራይ ክልል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ተመለሱ። ላለፉት ዓመታት በትግራይ ክልል አንድም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኃላም በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ትምህርት ዛሬ ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓ/ም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል። የትግራይ ትምህርት ቢሮ ትምህርት የሚጀመረው ሁሉ ነገር ተሟልቶ ፤ ችግሮች ሁሉ ተፈተው ሳይሆን ትውልድን ለማስቀጠል ሲባል መሆኑን ከዚህ ቀደም አሳውቆ…
#Tigray

በትግራይ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ ትምህርት ከሠኞ ጀምሮ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል።

ትምህርት የተጀመረው አዳዲስ አሰራሮችን  ተግባራዊ በማድረግ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ  ምን አሉ ?

" ትምህርቱ ከሚያዚያ 24 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2015 ድረስ ለ2 ወር ተኩል በማካሄድ  የመጀመሪያው መንፈቅ ይጠናቀቃል። ይህም እንደ አንድ ወሰነ ትምህርት ጊዜ ይይዛል።

እንዲህ ያለው የትምህርት ዘዴ ወይም (Accerated Learning Program) ተማሪዎች እድሜያቸው መድረስ በሚገባቸው የትምህርት እርከን ላይ እስኪደርሱ በዓመት ሁለት ደረጃ ትምህርቶችን እንዲያልፉ ተደርጎ ተሰርቷል።

በዚህም አንድ ዓመት 4 የወሰነ ትምህርት ጊዜ በማድረግ ሁለት ደረጃ ትምህርት በአንድ ዓመት እንዲጨርሱ ይደረጋል። "

በሌላ በኩል ቢሮው ፥ በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ጉዳት በመድረሱ የልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ቁጥራቸው  በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨምር አሳውቋል።

የጉዳቱን መጠን በመረዳት የፌዴራል መንግስት፣ ትምህርት ሚኒስቴር ፣ ዓለም አቀፍ  የእርዳታ ድርጅቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ድጋፍ  እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እርዳታው የተቋረጠው የተፈፀመውን ስርቆት ለማጣራት ውሳጣዊ ምርመራ ለማካሄድ ነው " - የረድኤት ሰራተኞች የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ውስጥ የሚያቀርበውን የምግብ እርዳታ ማቋረጡን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ 4 የረድኤት ሠራተኞች ለአሶሺየትድ ፕሬስ ተናግረዋል። እርዳታው ለምን ቆመ ? እንደ ረድኤት ሰራተኞቹ ቃል ፤ ድርጅቱ የእርዳታ አቅርቦት ያቋረጠው ከሳምንታት በፊት ለተረጂዎች በሚቀርብ…
#Tigray

የአሜሪካ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት (USAID) በትግራይ ውስጥ ተከስቷል ከተባለው የእርዳታ ምግብ ስርቆት ጋር በተያያዘ በክልሉ ውስጥ የሚያካሂደውን የእርዳታ ሥራ ለጊዜው አቋርጧል።

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው " በትግራይ ውስጥ ረሃብ በሚመስል ሁኔታ እየተሰቃዩ ላሉ ሰዎች የታለመው የምግብ እርዳታ " ከታለመለት አላማ ውጪ ገበያ ላይ ለሽያጭ መቅረቡን በመረዳቱ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም ሳቢያ " አስቸጋሪ ያለውን ውሳኔ " ለማሳለፍ መገደዱን በማመልከት፣ ተጨማሪ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስ፣ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚካሄዱ በድርጅቱ የሚደገፉ የምግብ እርዳታ አቅርቦቶች እንዲቋረጥ መደረጉን አሳውቋል።

በተመሳሳይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለተረጂዎች በሚቀርብ የምግብ እርዳታ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ስርቆት ለማጣራት ውስጣዊ ምርመራ ለማካሄድበ ትግራይ ክልል ውስጥ የሚያቀርበውን የምግብ እርዳታ ማቋረጡ ከቀናት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በትግራይ ክልል በስርቆት ምክንያት እርዳታ መቆሙን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተቋማት ያሳለፉትን ውሳኔ በተመለከተ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ  የእርዳታ ምግብ አቅርቦት ለሌላ አላማ መዋሉን በተመለከተ ከዲፕሎማቶች፣ ከእርዳታ ድርጅት ተወካዮች እና ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር ሲነጋገሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

ከችግሩ ከፍተኛነት እና ባሉ በርካታ ማስረጃዎች መሠረትነት የድርጊቱን ፈጻሚዎችን ማንነት በመለየት ተጠያቂ ለማድረግ በከፍተኛ የክልሉ ኃላፊዎች የሚመራ ምርመራ መጀመሩን አስታውቀዋል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia