TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Metema
የምዕራብ ጎንደር ዞን ፥ ከ6 ሺህ በላይ የሱዳን ተፈናቃዮች በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን አስታውቋል።
ዞኑ ፥ በሱዳን በተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት የ42 ሀገራት ዜጎች በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ነው ያመለከተው።
ወደ አካባቢው ሊገባ የሚችለውን ተፈናቃይ ለመቀበል በሚቻልበት ጉዳይ ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀው ዞኑ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ብቻ ከ6 ሺህ በላይ የ42 ሀገራት ዜጎች መግባታቸውን አመልክቷል።
ከዚህ ውስጥ ደግሞ 941 #ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጿል።
ተፈናቃዮቹ የጤና ችግር እንዳይገጥማቸው የጤና ባለሙያ በመመደብ አገልግሎት እየተሰጠ ነው ያለው ዞኑ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በኩል መካከለኛና ከፍተኛ ተሽከርካሪዎች ተመድቦ ተፈናቃዮች ወደ የሚፈልጉት አካባቢ የመሸኘት ሥራ ተሠርቷል ብሏል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበርም ውኃና ብስኩት በማቅረብ እያገዘ እንደሆነ ዞኑ ገልጿል።
በቀጣይ ችግሩ እየሰፋ የሚሄድ ከኾነ ወደ ቀጣናው ሊገባ የሚችለውን ስደተኛ ሊያስተናግድ የሚችል ቦታ የመለየት ሥራ መሰራቱን ዞኑን ማስታወቁን አሚኮ ዘግቧል።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia

#እናት_ፓርቲ
እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ልኮልናል።
ፓርቲው በዚህ መግለጫው፤ መንግሥት " ኦነግ ሸኔ '' እያለ ከሚጠራው የታጠቀ ቡድን ጋር በታንዛኒያ እያደረገው ያለው ድርድር ከሴራ ፖለቲካ በፀዳ መልኩ ተከናውኖ እንዲጠናቀቅ ምኞቱን ገልጿል።
እናት ፓርቲ ፤ " ካለ ፍትሕ ሰላምን ማስፈን አስቸጋሪ መሆኑን ብናምንም ድርድሩ ከተለመደው የሴራ ፖለቲካ በጸዳ መልኩ ተከናውኖ በስቃይ ውስጥ የሚገኘውን ሕዝባችንን ሊታደግ በሚችል መልኩ እንዲቋጭ እንመኛለን፡፡ " ብሏል።
መንግስት ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ሀሳብ ካላቸው ፓርቲዎች ጋርም የጋራ መግባባትን ለማስፈን የሚያስችል ውይይት እንዲያደርግ ፓርቲው ጥሪ አስተላልፏል።
ከዚህ ባለፈ የአማራ ክልል ብልጽግና ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ግድያን ተከትሎ መንግስት አሁንም " ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች" ን ትጥቅ በማስፈታት " ሰላም አስከብራለሁ " በሚል በአማራ ክልል የጀመረው እንቅስቃሴ ከሕወሓትና " ኦነግ ሸኔ " ጋር የታለፈበትንና አገርን ውድ ዋጋ ያስከፈለ አካሄድ የሚደግም ነው ብሎታል።
" መንግስት ካለፈ ስህተቱ መማር ሲገባው ወደ ሌላ የግጭት አዙሪት አገርንና ሕዝብን የሚከት፤ የክልሉን ወጣት ለአመጽ የሚጋብዝ " ነው ያለው ፓርቲው " በዚህም ከቀደሙት መደበኛ ጦርነትና የሽምቅ ውጊያ ሂደቶች ትምህርት ያልወሰደ፣ የሚያስከትለውንም መጠነ ሰፊ ጉዳት እና መዘዝ በአግባቡ ያላገናዘበ አደገኛ የማንአለብኝነት አካሄድ እየተከተለ ነው " ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።
ስለዚህ መንግሥት ከጀመረው የጅምላ እስር፣ የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ፣ የድርጅቶችን የንግድና የገንዘብ እንቅስቃሴ የማገድ ሂደት ወዘተ. በእሳት ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ አካሄዶች ራሱን አቅቦ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ሊፈቱ በሚችሉበት ሁኔታዎች ላይ ብቻ እንዲያተኩር አጽንዖት ሰጥቷል።
ከዚህ ውጭ የድርድርና የውይይት ፍኖትን ባለመሻት መንግሥት በማንአለብኝነት አካሄዱ ቀጥሎ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥፋትና ውድመት ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ እናት ፓርቲ በጽኑ እንደሚያምን ገልጿል።
እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ ፥ በአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦች መፅናናት ተመኝቶ ፤ ምርመራ ባልተካሄደበትና ጥፋተኞች በአግባቡ ባልተለዩበት ሁኔታ የሚደረጉ ፍረጃዎች የፍትህ አሰጣጡን እንደሚያዛባው ገልጿል።
(ፓርቲው የላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#Tigray ከዓመታት በኃላ በትግራይ ያሉ #ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ምዝገበ እየተካሄደ ይገኛል። የትግራይ ትምህርት ቢሮ ለዓመታት በኮቪድ-19 እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ከሚያዚያ 18 ጀምሮ ምዝገባ እንደሚከናወን እና ሚያዚያ 23 ትምህርት እንደሚጀመር ማሳወቁ የሚዘነጋ አይደለም። ተማሪዎች ያለፋቸውን ጊዜ ለማካካስ በሳምንት 3 የትምህርት…
#ትግራይ
በትግራይ ክልል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ተመለሱ።
ላለፉት ዓመታት በትግራይ ክልል አንድም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኃላም በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ትምህርት ዛሬ ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓ/ም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል።
የትግራይ ትምህርት ቢሮ ትምህርት የሚጀመረው ሁሉ ነገር ተሟልቶ ፤ ችግሮች ሁሉ ተፈተው ሳይሆን ትውልድን ለማስቀጠል ሲባል መሆኑን ከዚህ ቀደም አሳውቆ ነበር።
ዛሬ ትምህርት ከተጀመረባቸው ት/ቤቶች መካከል የኤርትራ ጦር ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰበት የተነገረው " ማይመኸደን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም በእንደርታ ወረዳ የሚገኘው ሓሬና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ይጠቀሳሉ።
ምንም እንኳን በርካታ ችግሮች ያሉ ቢሆንም በተማሪዎች ሆነ በወላጆች ዘንድ ትምህርት መጀመሩ ደስታን እና ተስፋን ፈጥሯል።
በትግራይ 85 በመቶ ትምህርት ቤቶች ከባድ ወይም ከፊል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ባለው ነገር ትምህርት ቢጀምሩም አሁንም የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተፈናቃይ ዜጎችን አስጠልለው ይገኛሉ።
ፎቶ ፦ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት
#BringTigrayChildrenBacktoSchool

#ቴክኖ_ሞባይል
ስለ አዲሱ ቴክኖ ስፓርክ 10 ሲሪየስ ሳያቁ ስልክ መግዛት አንዳያስቡ!
በባለ 50 ሜጋ ፒክስል ዋና ካሜራ እና 32 ሜጋ ፒክስል የፊት ለፊት ካሜራ ፣ ረጅም የባትሪ ቆይታ ጊዜ ፣ አስገራሚ ፍጥነት ያለው የጌሚንግ ፕሮሰሰር ፣ ከፍተኛ ጭረት የሚቋቋም ዲዛይን ጨምሮ ሁሉ በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘውን ስፓርክ 10 ሲሪየስ ሞባይል በሁሉም የስልክ መሸጫ መደብሮች ያገኙታል።
በየትኛውም የስልክ መሸጫ መደብሮቻችን ያገኙታል።
ለበለጠ መረጃ: Facebook, Instagram, Tiktok
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark10Series #TecnoMobile #Ethiopia #Spark10pro

" እርዳታው የተቋረጠው የተፈፀመውን ስርቆት ለማጣራት ውሳጣዊ ምርመራ ለማካሄድ ነው " - የረድኤት ሰራተኞች
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ውስጥ የሚያቀርበውን የምግብ እርዳታ ማቋረጡን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ 4 የረድኤት ሠራተኞች ለአሶሺየትድ ፕሬስ ተናግረዋል።
እርዳታው ለምን ቆመ ?
እንደ ረድኤት ሰራተኞቹ ቃል ፤ ድርጅቱ የእርዳታ አቅርቦት ያቋረጠው ከሳምንታት በፊት ለተረጂዎች በሚቀርብ የምግብ እርዳታ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ስርቆት ለማጣራት ውሳጣዊ ምርመራ ለማካሄድ ነው።
የእርዳታ ምግብ ተገቢ ላልሆነ አላማ እየዋለ መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ድርጅቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ትግራይ የሚያደርገውን የእርዳታ አቅርቦት በጊዜያዊነት አቋርጧል።
ከሳምንታት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በሚያካሂደው የሕይወት አድን የእርዳታ ሥራ ላይ የተፈጸመ የምግብ አቅርቦት ስርቆትን እየመረመረ እንደሚገኝ ገልጸ ነበር።
በወቅቱም የድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ክላውድ ጂቢዳር ፤ በአገሪቱ ላሉ አጋር ድርጅቶች በጻፉት ደብዳቤ " በአንዳንድ ገበያዎች የታየው መጠነ ሰፊ የሆነ የእርዳታ ምግብ ሽያጭ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ስጋት እንዲገባው አድርጓል " ብለዋል።
ለእርዳታ የተባሉ ምግቦች ለገበያ መቅረባቸው በተቋሙ ስም ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ከማሳደሩም በላይ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እርዳታ የማሰባሰብ አቅም ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸው ነበር።
ስለዚህም በአገሪቱ በእርዳታ የሚሰጥን ምግብ " አላግባብ መጠቀምን እና ከታለመለት ዓላማ ውጪ መውሰድ በአስቸኳይ ማስቆም እጅግ ወሳኝ ነው " ሲሉ አስገንዝበው ነበር።
#BBC

" የእኛን ጉዳይ ለእኛ ትተው በርከት ያለ ያልሰሩት ጉዳይ ስላላቸው ስራዎቻቸውን #በምድራቸው ላይ መስራት እንዲችሉ አሳስባለሁ " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ እየገቡ መፈትፈት የሚፈልጉ ያሏቸውን ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰቡ።
ይህንን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት ትላንት የ " ኮይሻ ፕሮጀክት " አካል የሆነውን የሃላላ ኬላ ሪዞርት ሲመርቁ ባሰሙት ንግግር ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንድነው ያሉት ?
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦
" ኮሽ ባለ ቁጥር በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ እየገቡ መፈትፈት የሚፈልጉ ኃይሎች በተለይም ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲሰበሰቡ / እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ እወዳለሁ።
ኢትዮጵያን በማበጣበጥ፤ በማባላት የሚገኝ ትርፍ እንደሌለ አውቀው የእኛን ጉዳይ ለእኛ ትተው በርከት ያለ ያልሰሩት ጉዳይ ስላላቸው ስራዎቻቸውን #በምድራቸው ላይ መስራት እንዲችሉ የእኛን ጉዳይ ለእኛ መተው እንዲችሉ ማሳሰብ እፈልጋለሁ። "
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የጠቀሷቸው ኢትዮጵያን የማበጣበጥ እና የማባላት ፍላጎት ያላቸው በተለይ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች የትኞቹ እንደሆኑ በግልፅ ከመናገር ተቆጥበዋል።
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በትላንትናው ንግግራቸው ከሰሞኑን የተገደሉት የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በሀሳብ ብልጫ ፍላጎታቸውን ማስፈፀም በተሳናቸው አካላት የተገደሉ መሆኑንም ገልጸዋል።
ድርጊቱን የፈፀሙትን ኃይሎች " ጅግና መሳይ ፈሪዎች " ሲሉ የገለጹት ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " ይህን አይነት ልምምድ ለኢትዮጵያ አደገኛ ነው ኖረንበታል ከዚህ ቀደም በቀይ ሽብር በነጭ ሽብር የሆነው ይሄ ነው ፤ ሰው ዝም ብሎ መኪና ውስጥ እየሄደ ገድሎ በሰላም መኖር ይቻላል ብሎ ማሰብ ያስቸግራል ፤ ሰው ገሎ ስልጣን ማግኘት ይቻላል ብሎ ማሰብም ያስቸግራል " ብለዋል።
ስልጣንም ሆነ ሌሎች ፍላጎቶችን ለማሳካት ሀሳብ ማመንጨት ፣ ለብዙሃን መሸጥ ሀሳቡ ተቀባይነት ካገኘ ያንን ማስፈፀም ይቻላል ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " በመገዳደል፣ በመሰዳደብ፣ በመናናቅ ለማሳካት የሚፈልግ የፖለቲካ አላማ የከሰረ ፤ ወደ ድል የማይወስድ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በዚህ ጉዳይ ላይ በስም ያልገለጿቸው ባለሀብቶች ፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በሀገር ውስጥ ያሉ ወጣቶች እንደሚሳተፉ በመግለፅ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል። መንግሥታቸውም ህግን የማስከበር ኃላፊነቱን እንደሚወጣም ገልጸዋል።

#እንድታውቁት
" ከግንቦት 1 ጀምሮ ያለ ዲጂታል መታወቂያ ሞተር ማሽከርከር አይቻልም " - የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ
በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ዲጂታል መታወቂያ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደማይቻል የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡
በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ የሞተር ብስክሌት ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች የመንቀሳቀሻ ፈቃዳቸውን ጂፒ ኤስ ባስገጠሙበት ተቋም የዲጂታል መታወቂያውን እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲወስዱ ተጠይቀዋል፡፡
ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሞተር ብስክሌቶች ላይ በሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር ያለ ዲጂታል መታወቂያ በሚንቀሳቀሱት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲል ኤጀንሲው አሳስቧል።