TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትዊተር

ለጥንቃቄ ...

የትዊተርን አዲስ አሰራር ተከትሎ የበርካታ ታዋቂ ሰዎች እና ተቋማት #የማረጋገጫ_ምልክት ከትላንት ጀምሮ ተነስቷል።

ታዋቂው ቱጃር ኤሎን መስክ በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን ከገዛው በኋላ በመተግሪያው ላይ የመጡ ለውጦች በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ እየሆኑ ይገኛል።

ከዚህም ውስጥ አንዱ ትዊተር ታዋቂ ግለሰቦች የሚሰጠውን የማረጋገጫ መልክት (Twitter verification) በክፍያ መጀመሩ ዋነኛው ነው።

ለግለሰብ በወር 8 ዶላር ለድርጅት ደግሞ 1000 ዶላር ማስከፈል የጀመረው መተግበሪያው ከትላንት ጀምሮ ክፍያ ያልፈጸሙ ያላቸውን አካውንቶች የማረጋገጫ ምልክታቸውን አንስቷል።

የማረጋገጫ ምልክታቸው የተነሳው በሀገራችን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ታዋቂ ሰዎች ፣ የሚዲያ ተቋማት ፣ ትልልቅ የመንግስት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ መስሪያ ቤቶች ነው።

በርካቶች ይሄንን ውሳኔ  በተመሳሳይ ስም የሚከፈቱ " የማረጋገጫ ምልክት " የሚኖራቸው አካውንቶች እንዲኖሩ እድሉን ይከፍታል በሚል የተቃወሙት ቢሆንም ውሳኔው ግን ተግባራዊ ተደርጓል።

ይህም ሀሰተኛ መረጃን ያባብሳል ተብሎ ተሰግቷል።

በተለይ አሁን ላይ የማረጋገጫ ምልክቱን በቀላሉ ማግኘት መቻሉ ለአጭበርባሪዎች (Scammers) በር በመክፈት በርካቶችን ሊጎዳ ይችላል።

የገጾችን ትክክለኛነት ለማሳየት የምንጠቀምበት ይህ የማረጋገጫ ምልክት ከዚህ በኋላ ለማረጋገጫነት ብዙም ጥቅም የሚኖረው አይመስልም።

የገጹ ተከታይ ብዛት እንደ ማረጋገጫ መውሰድ ብንችልም እንደ ሀገራችን የሀሰተኛው ገጽ ተከታይ ቁጥር ከትክክለኛው በሚበልጥበት ሁኔታ የገጹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥም አዳጋች ያደርገዋል።

ከዚሁ ከትዊተር ማረጋገጫ ምልክት መነሳት ጋር በተያያዘ ጦርነት ውስጥ ባለችው ሱዳን የሆነ አንድ ጉዳይን እናጋራችሁ።

በጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ (RSF) የትዊተር አካውንት ያለው ሲሆን አካውንቱም 82.7K ተከታይ እና የሰማያዊ ማረጋገጫ ምልክት ነበረው።

ትዊተር ትላንት ይህንን የማረጋገጫ ምልክት ባነሳበት ሰዓታት ውስጥ የሰማያዊ ምልክት #የገዛ በተመሳሳይ በRSF ስም የተከፈተ 26 ሺ ተከታዮች ያሉት ገፅ ጄነራል መሀመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) በጦርነቱ ላይ #እንደተሞቱ አድርጎ አንድ ፅሁፍ አስራጭቷል።

የዚህን የማረጋገጫ ምልክት ከትዊተር የገዛ ገፅ ያወጣውን ሀሰተኛ ፅሁፍ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች አይተውታል ፤ ይህን ሀሰተኛ ፅሁፍ ያመኑም አልጠፉም።

ውድ ቤተሰቦቻችን በትዊተር አዲስ አሰራር ሁሉም ሰው ሰማያዊ የማረጋገጫ ምልክት እየገዛ በመሆኑ የሰማያዊ ምልክት ያላቸው አካላት ናቸው የሚያሰራጩት በማለት ሁሉንም የምታዩትን መረጃዎች አትመኑ፤ መረጃዎችን መርምሩ፣ አጣሩ። እናመሰግናለን !!

#TikvahFamily

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
#ምርጥ_ዕቃ

እርስዎን የሚመጥኑ ምርጥ የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎችን መግዛት ሲፈልጉ እኛ ጋር ይምጡ።

አድራሻ ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቁጥር ፦ 376

ለበለጠ መረጃ፦ t.iss.one/MerttEka / 0944-22-23-24
#MyWishEnterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዶሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ https://t.iss.one/MYWISHENT
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የመታሰቢያ መርሃ ግብር ...

እሁድ ሚያዚያ 1 በቆቦ አካባቢ በተከሰተው ግጭት በሥራ ላይ ህይወታቸውን ላጡ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሁለት የሥራ ባልደረቦች የመታሰቢያ መርሃግብር ተካሄደ።

በግጭቱ ህይወታቸው ያለፉት አቶ ቾውል ቶንጎይክ እና አቶ አማረ ክንደያ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙበት ወቅት በመከላከያ ሰራዊት እና በአማራ ክልል ልዩ ኃይል መካከል በነበረ #የተኩስ_ልውውጥ ተመተው ህይወታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አስታውሳለች።

አደጋው በተፈጠረበት ወቅት ቆቦ የሚገኙ የካፑቺን አባቶች በቦታው በመድረስ የሟቾቹን አስከሬን ወደቤታቸው በመውሰድ እና በማዘጋጀት ወደቤተሰቦቻቸው እንዲላክ ማድረጋቸውን ከቤተክርስቲያኗ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ሚያዝያ 1 ቀን /2015 ዓ/ም ባስተላለፉት መልዕክት " ይህ ግጭት፣ ሰቆቃ፣ ስደት እና የእርስ በእርስ ጦርነት ሊቆም ይገባል። ችግሮችንም ሰከን ባለ መልኩ በውይይት ብቻ ልንፈታ ይገባል። ባለፉትም የነበሩትን ግጭቶች እና ጦርነቶች የፈታናቸው በውይይት ነው " ብለዋል። 

ብፁዕ ካርዲናል ለሟች ቤተሰቦች ሁሉ መጽናናትን እንዲሰጣቸው ተመኝተው ለሞቱት ነፍሳቸውን በአብርሃም በይሳቅ በያዕቆብ አጠገብ እንዲያኖር ጸሎታቸውን አቅርበዋል።

ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የካቶሊክ ተራዕዶ ድርጅት አቶ ቾውል እና አቶ አማረ  የመታሰቢያ መርሃግብር አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ያካሄደ ሲሆን በዕለቱም የሟቾቹ ቤተሰቦች በተገኙበት የመታሰቢያ ጸሎት በብጹዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን መሪነት ተካሂዷል።

በተጨማሪም ድርጅት ከ4 አመት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መከስከት ምክንያት ህይወታቸውን ያጡትን አራቱን ሠራተኞቹን በማስታወስ ጸሎት ተደርጓል።

ምንጭ፦ የአትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን

@tikvahethiopia
ወደ ትግራይ የየብስ ጉዞ ተጀመረ።

" ሰላም ባስ " ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ / ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ሲሰጠው የነበረውና በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የትራንስፓርት አገልግሎት ጀምሯል።

ከሁለት ዓመታት በኋላ የሰላም ባስ የመንገድ ትራንስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ጉዞ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪ በዛሬው ዕለት 51 ተጓዞችን በመያዝ ወደ አዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀመሩን ለማወቅ ተችሏል።

ድምፂ ወያነ ፤ አገልግሎት መጀመሩን ተከትሎ ትኬት ሲቆርጡ አገኘኃቸው ያላቸው ደንበኞች ፥ ወደ አዲስ አበባ የየብስ ትራንስፖርት በመጀመሩ ደስተኞች መሆናቸውን በመግለፅ ወደ ሌሎች አጎራባች ክልልሎችም ተመሳሳይ አገልግሎት ቢጀመር ሰላሙን ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ " ሰላም ባስ " የትራንስፖርት አገልግሎት ባገኘው መረጃ በየቀኑ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እና ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ የተጀመረ ሲሆን ጉዞው የሚደረገው #በአፋር በኩል ነው።

ፎቶ፦ ሰላም ባስ / ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሱዳን ጦር በ72 ሰዓታቱ የተኩስ አቁም ተስማማ። ጦሩ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀን ድረስ ዜጎች የኢድ አልፈጥር በዓልን እንዲያከብሩ፣ እና ለሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት መሳለጥ ሲባል የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማቱን ዛሬ ማምሻውን አሳውቋል። በጄነራል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር " አማፂያን " ሲል የጠራቸው የRSF ኃይሎች የተኩስ አቁሙን እንዲያከብሩና ይህንን የሚያደናቅፉ ማንኛውም ወታደራዊ…
#SUDAN

የሱዳን ተዋጊ ኃይሎች የተኩስ አቁም ቢያውጁም ውጊያው አሁንም መቀጠሉ ታውቋል ፤ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት ሩጫ ላይ ናቸው።

ትላንት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የ72 ሰዓታት የተኩስ አቁም ማወጁ፤ የሱዳን ጦርም ምሽት ላይ በተኩስ አቁሙ እንደተስማማ አሳውቀው እንደነበር ይታወሳል።

ነገር ግን ዛሬም በሱዳን የተለያዩ ቦታዎች ውጊያ መኖሩ ተሰምቷል። በካርቱም ካለፉት ቀናት ጋር ሲነፃፀር በተለየ መልኩ የተኩስ ድምፅ ቀንሶ ታይቷል።

በሌላ በኩል ፤ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት ሩጫ ላይ ናቸው። ተዋጊ ኃይሎቹም የውጭ ዜጎች እንዲወጡ ለማመቻቸት ቃል ገብተዋል ተብሏል።

የሱዳን ጦር ፤ የውጭ ዜጎች እና ዲፕሎማቶች ከአሜሪካ ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ቻይና በጦር አውሮፕላኖች ከካርቱም ኤርፖርት የማስወጣት ስራ በሰዓታት ውስጥ ይጀምራል ብሏል።

ከዚህ ባለፈ በሀገሪቱ የሚገኙ የሳዑዲ አረቢያ ዲፕሎማቶች ከካርቱም ወደ ፖርት ሱዳን ከዚያም ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንዲወጡ መደረጉን አስታውቋል። የጆርዳን ዲፕሎማቶችም ዛሬ ወደበኃላ ላይ በተመሳሳይ መንገድ ከአገሪቱ ይወጣሉ ሲል ገልጿል።

በሱዳን የተካሄደ ያለው ውጊያ እጅጉን የከፋው በትልልቅ ከተሞች፣ የዜጎች የመኖሪያ መንደሮች፣ የስራ ቦታዎች ላይ እየተደረገ መሆኑ ሲሆን የሀገሬው ዜጋ እና የሌሎችም ሀገራት ዜጎች ያለ ውሃ ፣ ምግብ ፣ መብራት ቤታቸው ውስጥ ከሳምንት በላይ እንዲቀመጡ አድርጓል።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

በሆቴሎች፤ በሱፐርማርኬቶች እና በቅርንጫፎቻችን በሚገኙት የፖስ ማሽኖቻችን የቪዛና ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው ግብይትዎን ያቅልሉ፡፡

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነሲሓ " ነሲሓ የበጎ አድራጎት እና የልማት ድርጅት " በደብረ ብርሃን የመጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ እያሰባሰበ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል። ድጋፉ " ዘካተል ፊጥራችንን ለወገኖቻችን" በሚል መሪ ቃል የሚሰበሰብ መሆኑን አመልክቷል። የበጎ አደራጎት ድርጅቱ " ሙስሊሞች የምታወጡትን #ዘካተል_ፊጥር በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ይሆን ዘንድ በሚከተሉት አካውንቶች እያሰባሰበን…
#ደብረብርሃን

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት በደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ድርጅቱ ከማኅበረሰቡ ባሰባሰበው ድጋፍ 210 ኩንታል ፉርኖ ዱቄት ከፋብሪካ የገዛ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ለ1800 አባወራ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን አመልክቷል።

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና ልማት ድርጅት ድጋፍ ለሰጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች ምስጋናውን አቅርቧል። ድርጅቱ ከቀናት በፊት በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።

ከዚህ ቀደም በደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፕ በርካታ ወገኖቻችን ተጠልለው እንደሚገኙ መግለፁ ይታወሳል፤ አሁንም ከድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ቢሆንም የሚመለከተው አካል ግን ዜጎች ወደ ቀደመ ህይወታቸው እንዲመለሱ ማድረግ አለበት።

@tikvahethiopia
#ዘሪሁን_ወዳጆ

አንጋፋው አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

በሙዚቃ ስራዎቹ ለኦሮሞ ህዝብ ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ የሚነገርለት አርቲስት ዘሪሁን በህንድ አገር በሕክምና ላይ እያለ ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ፤ አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆች በህይወት በነበረበት ወቅት ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገሩ ስራዎችን መስራቱንና ለበርካታ አርቲስቶችም ምሳሌ መሆን የቻለ ከህዝብ አእምሮ የማይጠፋ አርቲስት እንደበር ገልጿል።

@tikvahethiopia
#MekelleUniversity

ትግራይ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ቀደመው የመማር ማስተማር ስራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከነዚህም ውስጥ የኣክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው መማር ያልቻሉ ተማሪዎች በአጭር ቀናት ውስጥ በስልክ እየደወሉ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለማስታወሻ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/77964

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ለሁሉም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ላልተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች ቀጥሎ የተቀመጡትን መረጃዎች ከሚያዝያ 16-20/2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ሰዓታት ብቻ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም መረጃዎች እንዲያቀብሉ ጠይቋል።

ተፈላጊ መረጃዎቹ ምንድናቸው ?

👉 ሙሉ ስም
👉 የመታወቅያ ቁጥር
👉 ትምህርት ክፍል
👉 የስንተኛ ኣመት ተማሪ መሆንዎ

እነዚህን መረጃዎች የመላኪያ ስልክ ቁጥሮች ፦

1. EiTM - 0984026089 / 0984026059
2. MIT - 0984026727
3. CHS - 0984023986
4. CVS - 0984024072
5. CLG - 0984023987
6. CSSL - 0984023985
7. CBE - 0984024069
8. IPHC - 0984025512
9. CDAaNR - 0984025593
10. CNCS - 0984025582
11. Other Universities - 0984025589

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፅሁፍ መልእክቱን ሲልኩ #በእንግሊዘኛ እንዲልኩ አሳስቧል።

ዩኒቨርሲቲው በሌሎች የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩና በጦርነቱ ምክንያት ያቋረጡ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ከላት የተጠየቁትን መረጃዎች ፤ከዛ በተጨማሪ ሲማሩበት የነበረውን የዩኒቨርሲቲ ስም በማከል መረጃ እንዲያሳውቁ ጥሪውን አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፥ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹን በቅርብ ጊዜ እንደሚጠራ ገልጿል።

@tikvahethiopia