TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሱዳን ጎረቤቶች የእርስ በርስ ጦርነትን አይፈልጉም " - ኦቪግዌ ኢግዌጉ የጂኦፖለቲካ እና የፀጥታ ጉዳይ ተንታኝ ኦቪግዌ ኢግዌጉ ለአልጀዚራ በሰጡት ቃለ ምልልስ ፤ የሁሉም ቀጠናዊ ሀገራት ዋና ጉዳይ በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት ወደ " ሙሉ የእርስ በርስ ጦርነት " እንዳይቀየር ማረጋገጥ ነው ብለዋል። " ለዚያ #ቅርብ ነን ነገር ግን በእውነቱ በዚያ ደረጃ ላይ አይደለንም። " ያሉት ተንታኙ ፤ ከሱዳን…
#Update

በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች እየተገደሉ ናቸው።

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፤ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ሲቪሎች ለጉዳት መዳረጋቸውና ህይወትም እየተቀጠፈ መሆኑን ገልጿል።

ከእነዚህ መካከል #ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት መረጃዎች እንደደረሱት አመልክቷል።

ኤምባሲው ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ እና እንደተጎዱ በዝርዝር አልገለፀም።

ነገር ግን በኢትዮጵያውያን ሞት እና ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እደተሰማው እና ለሟች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።

" ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ ኢትዮጵያዊን የተቻላቸውን ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በድጋሜ እናሳስባለን " ብሏል።

መረጃ ለመለዋወጥ እና ለምክክር የኤምባሲው ባልደረባ የሆኑትን አቶ ነጅብ አብደላ በስልክ ቁጥር +249911646547 ማነጋገር እንደሚቻል በሱዳን ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፥ ከትላንት ምሽት አንስቶ በሱዳን የማህበራዊ መገናኛዎች ላይ አንድ ቪድዮ ሲሰራጭ ነበር (ከላይ ተያይዟል) ።

ቪድዮው በመድፍ የተመታ ቤትን የሚያሳይ ሲሆን በቤቱ ውስጥ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን እንደነበሩና ሁሉም ወዲያው ህይወታቸው እንዳለፈ ተነግራል። ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ የተገለፀ ነገር የለም።

ስለተሰራጨው ቪድዮ እና ስለደረሰው ጉዳት ትክክለኝነት በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያለው ነገር የለም።

በሱዳን እየተካሄደ ያለው ውጊያ በከተማ ውስጥ እየተደረገ መሆኑ በዛው የሚኖሩ የሀገራችንን ዜጎች ጨምሮ የመላው ሱዳናውያንን ደህንነት አደጋ ላይ ጥሏል።

@tikvahethiopia
#DigitalElectronicsPLC

ለሚሰሩዋቸው ፕሮጀክቶች እና የፈጠራ ስራዎች የሚያገለግሉ የተለያዩ ኤሌክትሪካል እና ሜካኒካል እቃዎች እንዲሁም ማሽነሪዎች እናቀርባለንⵆ
#join ቴሌግራም ቻናል @ethioinvention
website https://digitalelectronicsplc.com/
📌Contact
📱0914-839754
📱0703-839754
📌#ኣድራሻችን4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ፡ 1ኛ ፎቅ ቢ.ቁ 103ለ
@ethioinvention
#ነሲሓ

" ነሲሓ የበጎ አድራጎት እና የልማት ድርጅት " በደብረ ብርሃን የመጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ እያሰባሰበ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ድጋፉ " ዘካተል ፊጥራችንን ለወገኖቻችን" በሚል መሪ ቃል የሚሰበሰብ መሆኑን አመልክቷል።

የበጎ አደራጎት ድርጅቱ " ሙስሊሞች የምታወጡትን #ዘካተል_ፊጥር በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ይሆን ዘንድ በሚከተሉት አካውንቶች እያሰባሰበን ነውና መስጠት ትችላላችሁ !! " ብሏል።

ድርጅቱ በሁሉም ባንኮች የአካውንት ስሙ ነሲሓ በጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን የገለፀልን ሲሆን ቁጥሮች፦
- ንግድ ባንክ 1000328070778
- ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል 1357377300001
- ዳሽን ባንክ 7913417861611
- ንብ ኢንተርናሽናል 7000016912412
- ዘምዘም ባንክ 0001040310301
- አዋሽ ባንክ 01410797317600 ናቸው።

ለበለጠ መረጃ ደግሞ በ 0972747474 ብትደውሉልን ማንኛውም አይነት ዝርዝር መረጃ መስጠት እንችላለን ብሏል።

@tikvahethiopia
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መልዕክት መለዋወጫ !

ከዚህ ቀደም ተከፍተው አገልግሎት ላይ የነበሩት የመልዕክት መቀበያዎች በተደጋጋሚ በቴሌግራም ቴክኒንክ ችግር አገልግሎታቸው እየተደነቃቀፈ ነው።

በዚህም ምክንያት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚመጡትን መልዕክቶች ለማግኘት ችግር ሆኗል ፤ ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ችግሩን ለመቅረፍ እና በየትኛውም መልኩ ነፃነቱ የተጠበቀ ለቲክቫህ አባላት ብቻ የሚያገለግል የሀሳብ መለዋወጫ በቅርቡ ይፋ የምናደርግ ሲሆን እስከዛው ድረስ ግን በዚህ አዲስ መልዕክት መቀበያ ላይ ብቻ መልዕክት ማጋራት ይቻላል  👉@tikvah_eth_BOT

በተጨማሪ @tikvah_Ethiopia_Fam ወይም ደግሞ 0703313630 መደወል ይቻላል።

በቲክቫህ ቤተሰብ ውስጥ ማስተላለፍ የሚቻሉ መልዕክቶች ምን አይነት ናቸው ?

- የፀጥታ ችግሮች፣ የደህንነት ስጋቶች፣ የወንጀል ድርጊቶች በመንግስት አካላት / ተቋማት የሚፈፀሙ ማንኛውም አይነት አስተዳዳራዊ በደሎች፤
- የየመንገድ ፣ የውሃ፣ እንዲሁም የኑሮ ውድነት፣ የኢኮኖሚና የሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎች፤
- በግልም ሆነ በጋር የማያጋጥሙ ችግሮች፣ ሊበረታቱ የሚግባቸው ተግባራት፣
- ለሀገር እና ለትውልድ ጠቃሚ ናቸው የሚባሉ ሃሳቦችን፣
- የእርስ በእርስ እገዛዎች ፣ የበጎ አድራጎት ስራዎች፣
- ጥቆማዎችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ይሄ ነገር ለቤተሰቡ ቢጋራ መልካም ነው የምትሉትን (ዜና ፣ መረጃ) ሁሉ ማቅረብ ትችላላችሁ።

ምን መላክ አይቻልም ?

ስድብ፣ የጥላቻ ንግግር ፣ የማንኛውም የግለሰብ ማንነትን በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የሚነካ ፣ ህዝብን በጅምላ የሚፈርጅ፣ ፣ ህዝብ ላይ ጥላቻን የሚያሰርፅ፣ ሀገር ሊያስጣ የእርስ በእርስ ግጭት የሚያባብስ፣ ሀሰተኛ መረጃ ፅሁፍ / መልዕክት መላክ በፍፁም አይቻልም። በየትኛውም አካል ላይ ትችትም ይሁን ቅሬታ ለመግለፅ የሚፈልግ የቤተሰቡ አባል የሚጠቀማቸውን ቃላት የመምረጥ ግዴታ አለበት።

ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛውም መልዕክት ስትልኩ የራሳችሁ የግላችሁ መልዕክት መሆኑን በማስረጃ አስደግፋችሁ ላኩልን። እናተ ያላረጋገጣችሁትንና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስላያችሁት የራሳችሁ በማስመሰል ማንኛውም መልዕልት መላክ ፍፁም አይቻልም።

ማስታወሻ ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት #በፌስቡክ#ዩትዩብ#ቲክቶክ ላይ ምንም አይነት የመሰባሰቢያ መድረክ (ገፅ) የላቸውም።

ትዊተር ፦ https://twitter.com/tikvahethiopia?t=jZrpieALuIGzw6OM-HWgEw&s=09

ሀሳባችን ስንገልፅ ቃላትን እንምረጥ !!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ!!
#TikvahFamily

@tikvah_eth_BOT
We Are Hiring !

Berhan Bank seeks to hire applicants for the positions of
1. Assistant Branch Manager I
2. Senior Customer Service Officer
3. Customer Service Officer
4. Junior Customer Service Officer

Use the link below to apply for the vacancy
Link; https://www.facebook.com/berhanbanksc

Telegram : https://t.iss.one/berhanbanksc
ስለ ሀገሬ ምን ያህል አውቃለሁ ?

" ፊቼ ጨምባላላ "

የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት ያከብራል ፤ ይኸው በዓል ፊቼ ጨምበላላ ነው የሚባለው።

እንደ ሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች " ፊቼ ጫምባላላ " መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።

በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ በድምቀት ሲከበር ቆይቷል፤ አሁንም እየተከበረ ይገኛል።

ፊቼ ጨምበላላ በዓል የሚከበርበት ቋሚ ቀን የለውም። በዓሉ የሚከበርበት ቀን በአያንቱዎች ጥቆማ መሰረት ነው የሚቃረጠው።

'የፊቼ ጨምበላላ ዋነኛ ትርጉም ሰላም ነው' ፤ አንድነትና ፍቅር የበዓሉ መለያ ነው። በዚህ በላይ የተጣሉ ሰዎች ይታረቃሉ። ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።

በዚህ በዓል ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ወደቀዬው ይመለሳል፤ ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን #መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይ ይሰማራሉ።

ሌላው በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ #ነውር ነው፤ ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን #የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

" ፊቼ " የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ሲሆን፤ " ጨምበላላ " ደግሞ የአዲስ ዓመት መጀመሪያው ቀን ሲሆን የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመትን ሲቀበል፤ ዓመቱ የብልጽግና እንዲሆንላቸው 'ፊቼ ጄጂ' ይላሉ።

ፊቼ ጄጂ !
#ኢትዮጵያ
#ሲዳማ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ " ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት #በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈፀማል " - የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ከሚያዚያ 16 ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ #በኤሌክትሮኒክስ_የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ…
#እንድታውቁት

ከሚያዚያ 16 ጀምሮ በመላው አዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅነት በ " ቴሌብር " ብቻ ተግባራዊ ይደረጋል ሲል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

በ " ቴሌብር " ነዳጅ ስለ መቅዳት አሸከርካሪዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች ምንድናቸው ?

☞ በቅድሚያ የ " ቴሌብር "ተጠቃሚ መሆን፤
☞ በቂ ክፍያ የቴሌብር አካውንት ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ፤
☞ የ " ቴሌብር " የሚስጥር ቁጥርዎን ማስታወስና በአግባቡ መያዝ፤

የአከፋፈል ሁኔታው ምን ይመስላል ?

‣ የነዳጅ ማደያ ሰራተኞች የተጠቃሚውን ስልክ ቁጥርና የሚከፍሉትን የገንዘብ መጠን ሞልተው ሲጨርሱ የእርስዎ ስልክ ላይ የሚስጥር ቁጥርዎን እንዲያሥገቡ የሚጠይቅ አጭር መልዕክት ይመጣሎታል፤

‣ በመቀጠል የሚስጥር ቁጥርዎን ከማስገባትዎ በፊት ከደረስዎት መልዕክት ላይ የተቀመጠ ገንዘብ መጠን ትክክል መሆኑን ያረጋግጡ፤ ካረጋገጡ በኃላ የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ፤

‣ በመጨረሻም ክፍያው ከተፈፀመ በኃላ የክፍያውን ማረጋገጫ አጭር የመልዕክት ቁጥር ወዲያውኑ ይደርሶታል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ፤ የተሽከርካሪ ነዳጅ ግብይት ከሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም ጀምሮ በ " ቴሌ ብር " ብቻ የሚፈፀም በመሆኑ ሁሉም አሽከርካሪ እንዳይጉላላ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

@tikvahethiopia
#ኢዜማ

ጉምቱው ፖለቲከኛ ከፓርቲያቸው ለቀቁ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መስራቾች አንዱ የሆኑት ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ አንዱዓለም አራጌ ከፓርቲው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።

የመልቀቂያ ደብዳቤው በትላንትናው እለት ለሚመለከተው አካል ገቢ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።

አቶ አንዱዓለም አራጌ ፓርቲውን ለምን ለቀቁ ? የመልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ በዝርዝር አስረድተዋል ፤ ከላይ ተያይዟል ያንብቡት !

ምንጭ፦ የተረጋገጠው የማህበራዊ ትስድር ገፃቸው

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች እየተገደሉ ናቸው። በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፤ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ሲቪሎች ለጉዳት መዳረጋቸውና ህይወትም እየተቀጠፈ መሆኑን ገልጿል። ከእነዚህ መካከል #ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት መረጃዎች እንደደረሱት አመልክቷል። ኤምባሲው ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ እና እንደተጎዱ በዝርዝር አልገለፀም።…
#Update

በሱዳን እየተካሄደ ያለው ውጊያ ዛሬ 5ኛ ቀኑን ይዟል።

ምን አዳዲስ ጉዳዮች አሉ ?

- ትላንት የሱዳን ጦርና RSF ለ24 ሰዓታት የሚዘልቅ ለሰብዓዊነት ተኩስ የማቆም ስምምነት ላይ ደርሰናል ቢሉም ምንም አልተከበረም። እንደውም ከዛ በኃላ 36 ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

- የሱዳን ጦር ለተኩስ ማቆም ስምምነቱ መጣስ RSFን ተጠያቂ አድርጓል።

- 5ኛው ቀን ውጊያ በቀጠለበት በዚህ ሰዓት የሱዳን ጎረቤት የሆኑ የሦስት አገራት መሪዎች (ሳልቫ ኪር፣ ኢስማኤል ኦማር ጌሌ እና ዊሊያም ሩቶ) ሁለቱን የጦር ጀነራሎች ለማደራደር ካርቱም ይገባሉ መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

- ዛሬ በማዕከላዊ ካርቱም በጦሩ ዋና መስሪያ ቤት፣ በፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት፣ እና ካርቱም ኤርፖርት አቅራቢያ ውጊያ እየተደረገ ነው።

- የሱዳን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 16 ሆስፒታሎች ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸውን በመግለፅ በጤና ስርዓቱ ላይ ጠቅላላ ውድቀት እየመጣ መሆኑን አስጠንቅቋል።

- ጃፓን ዜጎቿን በጦርነት ከምትታመሰው ሱዳን ለማስወጣት በዝግጅት ላይ መሆኗን የሀገሪቱ መንግሥት ገልጿል። ጃፓን ዜጎቿን ከሱዳን የምታስወጣበት መንገድ ከተሳካ ዜጎቿን ከሱዳን ያስወጣች የመጀመሪያዋ የውጭ ሀገር ትሆናለች።

- ካርቱም ውስጥ ነዋሪዎች ያለ ውሃ እና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቤት ውስጥ ይገኛሉ፤ ነዋሪዎች ከቤት መውጣት ያልቻሉ ሲሆን በርካቶችም የሚበሉት ማጣታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" በር አልሰበር ሲላቸው በፈንጂ ሰብረው በመግባት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል " - የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጥንታዊው የ " ሶደሬ ፈለገ ሰላም መድኃኔዓለም ገዳም " ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ በታጠቁ ኃይሎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገለፀ።

ጥንታዊውና በ1963 ዓ.ም የተመሠረተው የሶደሬ ፈለገ ሰላም  መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከአዳማ 25 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ነው የሚገኘው።

ትናንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ከ50 በላይ የሚሆኑ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ኃይሎች የቤተክርስቲያኑን በር አልሰበር ሲላቸው በፈንጂ ሰብረው በመግባት ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሱ የ " ምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት " አሳውቋል።

የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት የሀገረ ስብሰቱ ጽ/ቤት ልዑካንን የላከ ሲሆን ወደ ቦታው ያቀኑ ልዑካን የሀገረ ስብከቱ ም/ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ልዩ ፀሐፊን ጨምሮ ሌሎች አባቶች እና ሓላፊዎች  ናቸው።

ልዑኩ በደረሰው ጉዳት ከልብ ማዘኑን ያሳወቀ ሲሆን ካህናትና የአካባቢውን ምዕመናን እንዳፅናኑ ተመላክቷል።

በጥቃቱ ምን ጉዳት ደረሰ ?

የ " ምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት "ይፋ ባደረገው መረጃ በታጣቂዎቹ ጥቃት ፦
- በርካታ ነዋየ ቅድሳት ተቃጥለዋል፤
- የቤተክርቲያኑ ቅዱሳት ስዕላት በእሳት አረር ተለብለበዋል።
- የቤተክርስቲያኑን አስተዳዳሪ መኖሪያ ቤት በመጠየቅ ቤት ሰብሮ በመግባት በወቅቱ አስተዳዳሪው ባይኖሩም በቤት እቃዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
- የአንድ አገልጋይ ካህናት መኖሪያ ቤት  ሙሉ ለሙሉ ተቃጥሏል።
- በቤተክርስቲያን ተጠግተው የሚገኙ ምዕመናን ከፍተኛ ማዋከብ ተፈጽሞባቸዋል።

ሀገረ ስብከቱ ይኸው የታጠቀ ኃይል የደብሩን ገንዘብ ያዥ የሆኑትን አቶ ተስፋ ደሳለኝን አስገድደው እንደወሰዷቸውና ልዑካኑ አስከተገኙበት ሰዓት እንዳልተለቀቁ ገልጿል።

ፎቶ / መረጃ፦ የ ምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት

@tikvahethiopia