TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

በጎረቤት ሱዳን ያለው ውጊያ ዛሬ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል።

ከካርቱም ጨምሮ ከሌሎች ከተሞች በወጡ መረጃዎች ዛሬም በከባባድ መሳሪያ የታገዘ የከተማ ውስጥ ውጊያ እየተካሄደ ነው።

በተለይም በካርቱም ሰሜናዊ እና ደቡባዊ ክፍል የከባድ መሳሪያ ውጊያ እንዳለ ተነግሯል።

የሠራዊቱ ጠቅላይ ዋና መሥሪያ ቤት በር ፊት ለፊት ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን አርኤስኤፍ (RSF) ከቅዳሜ ጀምሮ ይህንን ትልቅ የሰራዊት ተቋም ለመቆጣጠር እየሞከረ ነው ተብሏል።

ይህንን ተቋም መቆጣጠር በራሱ ሰራዊቱን እንደመቆጣጠር ነው የሚታሰበው።

በሌላ በኩል ፤ በሜሮዌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ግጭት መኖሩ ተገልጿል። ይህ ግጭት እንደገና የተቀሰቀሰ ሲሆን የከባድ መሳሪያ ድምፆችም ይሰማሉ ተብሏል።

በሜሮዌ የሚገኙ ሆስፒታሎች በተጎዱ ሰዎች የተሞሉ መሆናቸውን ከህክምና ምንጮች ለማወቅ መቻሉን አልጀዚራ ዘግቧል።

ተጨማሪ መረጃዎች ፦

- በካርቱም ውጊያ በመኖሪያ መንደሮች ጭምር እየተደረገ ነው።

- በሱዳን ባለፉት ሶስት ቀን የሞቱ ሰላማዊ ሰዎች ከ100 ተሻገረዋል። እጅግ በጣም በርካታ ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል።

- የRSF የፖለቲካ አማካሪ የሱፍ ኢዛት ለአልጀዚራ በሰጡት ቃል ማንኛውም የተኩስ አቁም ለማድረግ በሠራዊቱ ውስጥ የ "አመራር መኖር"ን ይጠይቃል ብለዋል። " ሠራዊቱ ምንም ዓይነት አመራር የለውም። " ያሉት አማካሪው " የተኩስ አቁም መቼ እንደሚሆን የምንወስነው እኛ ብቻ ነን " ብለዋል።

-  RSF " ወንጀለኛ ናቸው " ሲል የጠራቸውን አልቡርሃንን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፍለጋ ላይ መሆኑን አሳውቋል።

- በጄነራል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር የRSF ሚሊሻዎች ሰላማዊ ሰዎችን ከለላ አድርገው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በመግለፅ ሰላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ጥብቅ በሆነ ወታደራዊ ጥንቃቄ ኦፕሬሽኑን እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

Photo Credit : Aljazeera

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በሚዲያ ጥፋት የተጠረጠሩ ታሳሪዎች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊለቀቁ ይገባል " - ኢሰመኮ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችንና አባላትን፣ የሚዲያ አባላትንና የማኅበረሰብ አንቂዎችን ዒላማ ያደረገ እስር እና ወከባ በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል። ኢሰመኮ በተለያየ ዓይነት ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ከተያዙ ሰዎች ውስጥ በተለይ የሚዲያ አባላትን፣ የተቃዋሚ…
" የዜጎች መብት በፍትሕ አካላት በተደጋጋሚ እየተጣሰ ነው " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ ቤት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጋዜጠኞች ከሕግ አግባብ ውጪ ታፍነው እየታሰሩ እና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብርበራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ምክር ቤቱ ፤ በሚዲያ አማካኝነት ተፈጽሟል በተባለ ወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑ ጋዜጠኞች በፖሊስ ሲያዙም ሆነ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ባለመሆኑ ባለሙያዎች ስራቸውን በነጻነት እንዳይሰሩ ከማድረጉ በላይ የፕሬስ ምህዳሩ እንዲጠብ እያደረገው ነው ሲል ገልጿል።

በሚዲያ አማካይነት የወንጀል ድርጊት በመፈፀም የተጠረጠረ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት የሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በዓቃቤ ሕግ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለበት ምክር ቤቱ አዋጅ ቁጥር 1238/13 ጠቅሶ አስታውሷል።

ይሁን እንጂ ጋዜጠኞች እንደ ማንኛውም ተከሳሽ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠይቆባቸው ለፖሊስ በመፍቀድ እንዲታሰሩ ማድረግ በምንም መለኪያ ተቀባይነት የለውም ብሏል።

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ም/ቤት የዜጎች መብት በፍትሕ አካላት በተደጋጋሚ እየተጣሰ ነው ያለ ሲሆን ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጠይቋል።

መንግሥት መንግሥታዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ተግባሩ ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን በማያጠብና የዜጎችን የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ተሳትፎ በማያቀጭጭ መልኩ ሊሆን ይገባልም ብሏል።

የፍትሕ ሥርዓቱ በመገናኛ ብዙሃን አዋጁ ድንጋጌ ብቻ በመመራት ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታውን እንዲወጣ ምክር ቤቱ ጠይቋል። #ቢቢሲ

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የመቐለ ከተማ ሙስሊም ማህበረሰብ ዛሬ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነ ስርዓት አካሂዷል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተው እንደነበር ድምፂ ወያነ ዘግቧል።

የፎቶ ባለቤቶች ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን / ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጎረቤት ሱዳን ያለው ውጊያ ዛሬ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል። ከካርቱም ጨምሮ ከሌሎች ከተሞች በወጡ መረጃዎች ዛሬም በከባባድ መሳሪያ የታገዘ የከተማ ውስጥ ውጊያ እየተካሄደ ነው። በተለይም በካርቱም ሰሜናዊ እና ደቡባዊ ክፍል የከባድ መሳሪያ ውጊያ እንዳለ ተነግሯል። የሠራዊቱ ጠቅላይ ዋና መሥሪያ ቤት በር ፊት ለፊት ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን አርኤስኤፍ (RSF) ከቅዳሜ ጀምሮ…
#Sudan

በሱዳን የአሜሪካ ኤምባሲ ተሽከርካሪ በጥይት ተደበደበ።

በሱዳን ፣ ካርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብረት ለበስ ተሽከርካሪው " ሆን ተብሎ " በጥይት መደብደቡን አስታወቀ።

ድርጊቱን የፈፀመው ሄሜቲ የሚመሩት RSF ቡድን መሆኑን ኤምባሲው ለአል አረቢያ ገልጿል።

ኤምባሲው ተሽከርካሪው በ100 ጥይት መደብደቡን ገልጾ ድብደባው ያደረሰው ምንም ጉዳት የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካ መንግሥት ጦርነት ውስጥ ካለችው ሱዳን ዜጎቹን የማስወጣት እቅድ እንደሌለው ዋይትሃውስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#SUDAN

በሱዳን የEU አምባሳደር ጥቃት ተፈፀመባቸው።

በሱዳን ካርቱም ሚገኙት የአውሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተሰማ።

አምባሳደሩ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያሳወቁት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ናቸው (በትዊተር ገፃቸው)።

ቦሬል ስለ ጥቃቱ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ባይገልጹም አምባሳደሩ ግን " ደህና ናቸው " ብለዋል።

የዲፕሎማቲክ ቦታዎችን እና ሰራተኞችን ደህንነት ማስጠበቅ የሱዳን ባለስልጣናት ቀዳሚ ኃላፊነት ነውም ሲሉ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ቦሬል ፤ በሱዳን የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ስም ባይፅፉም ስማቸው አይዳን ኦሃራ የሚባሉ ሲሆን የ #አየርላንድ ዲፕሎማት ናቸው።

ቦሬል ካርቱም ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት ፤ በሌሎች ሀገራት የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ጥበቃን የሚደነግገውን የተመድ ስምምነት የ " ቪይና ኮንቬንሽን " በእጅጉ የጣሰ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ለAFP በሰጡት ቃል " የሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብለዋል፤ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ከካርቱም እንዲወጣ እንዳልተደረገ ተናግረዋል።

ቃል አቀባይዋ ፤ በሱዳን ያለው የፀጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እየተገመገመ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
#DigitalElectronicsPLC

ለሚሰሩዋቸው ፕሮጀክቶች እና የፈጠራ ስራዎች የሚያገለግሉ የተለያዩ ኤሌክትሪካል እና ሜካኒካል እቃዎች እንዲሁም ማሽነሪዎች እናቀርባለንⵆ
#join ቴሌግራም ቻናል @ethioinvention
website https://digitalelectronicsplc.com/
📌Contact
📱0914-839754
📱0703-839754
📌#ኣድራሻችን4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ፡ 1ኛ ፎቅ ቢ.ቁ 103ለ
@ethioinvention
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EOMmarket

የልጅዎን ውሎ እና የቤትዎን ደህንነት በየትኛውም ቦታ ሁነው በቀጥታ መከታተል የሚችሉበት ድንቅ የደህንነት ካሜራ!

ህይወትዎን ቀላልና ዘመናዊ የሚያደርጉ ጥራት ያላቸው እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበት ትልቁ ገበያ 👇https://t.iss.one/EOMMarket

የመረጡትን እቃ ይዘዙን፤ያሉበት ድረስ በነፃ  እናደርሳለን 𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲  ☞ 0929181818 / 0909868788

ይምጡ የሽያጭ ማእከሎቻችን ይጎብኙ፤ ተደስተው ይመለሳሉ !! አድራሻችን፦
ቁጥር 1:- መገናኛ, ቤተልሄም ፕላዛ  የሱቅ ቁጥር  G-10 ግራውንድ [ እንደገቡ በስተቀኝ በኩል ]
ቁጥር 2:- ሜክሲኮ, ኬኬር ህንፃ የሱቅ ቁጥር #338

𝕵𝖔𝖎𝖓 𝖔𝖚𝖗 𝖈𝖍𝖆𝖓𝖓𝖊𝖑 : @EOMmarket
     
" የኢትዮጵያ መንግስት የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን ይልቀቅ " - አምንስቲ ኢንተርናሽናል

የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዉሞን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብትን እንዲያከብርና የታሰሩ የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን እንዲፈታ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ትናንት ባወጣዉ መገለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ባለፈዉ ሳምንት አማራ ክልል በተፈጠረዉ ሁከት ምክንያት ያሰሯቸዉን 7 የመገናኛ ዘዴ ባልደረቦች ባስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ከእስረኞቹ ባንዷ ላይ ተፈፀመ የተባለዉን አካላዊ ጥቃት እንዲያጣሩ ጠይቋል።

መግለጫዉ እንዳለዉ  ባለስልጣናቱ " ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትንና ሁሉም ወገን በሰላማዊ መንገድ የመቃወም መብቱን ማስከበር አለባቸዉ። "

ባለፈዉ ሳምንት በአማራ ክልል የመብት ጥሰትና ሁከት መቀስቀሱ እንዳሳሰበዉ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታዉቋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉ፣ የሰብአዊ ርዳታ አቀባይ ድርጅት ሰራተኞችን ጨምሮ ሰዎች መገደላቸዉ፣ አዲስ አበባ ዉስጥ ሰዎች በጅምላ መታሰራቸዉንም ድርጅቱ «አሳሳቢ» ብሎታል።

የመንግስት ኃይላትም ሆኑ #ሌሎች ታጣቂዎች " የሰብአዊ ርዳታ ሰራተኞችን ያለማጥቃት ኃላፊነት አለባቸዉ። " ብሏል አምነስቲ።

የኢትዮጵያ መንግስት " አስቸኳይ፣ ጥልቅ፣ ገለልተኛና ዉጤታማ ምርመራ አድርጎ ተጠያቂዎችን ለፍርድ ማቅረብ አለበት " እንደ መግለጫዉ።

በምስራቅ አፍሪቃ፣ በአፍሪቃ ቀንድና በታላላቅ ሐይቆች አካባቢ የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ምክትል ተጠሪ ፍላቪያ ምዋንጎቭያ «ዘግናኝ» ያሉት የገነት አስማማዉ፣ ጌትነት አረጋዊ፣ አራጋዉ ሲሳይ፣መስከረም አበራ፣ አባይ ዘዉዱ፣ ዳዊት በጋሻዉና ቴዎድሮስ አስፋዉ መታሰር ሐሳብን በነፃነት በመግለጥ መብትና በመገናኛ ዘዴ ነፃነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነዉ።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት 7 የመገናኛ ዘዴ ሰራተኞች ባስቸኳይ እንዲለቁና የተመሰረተባቸዉን ክስ እንዲነሱም ምዋንጎቭይ ጠይቀዋል።

በሌለ በኩል ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በተመረጡ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የጣለዉን ማዕቀብ እንዲያነሳም ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠይቋል።

አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግስት እገዳዉን ከጣለ 3ኛ ወሩን ይዟል።

እገዳዉ ሰዎች መረጃ እንዳያገኙ መገደብን ጨምሮ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀምና ያለመጠቀም የሰብአዊ መብትን የሚጥስ ነዉ።

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia