TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

" የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ሁሌም ቢሆን አዲስ አበባ በሯ ክፍት ነው " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ኢትዮጵያ በሱዳን የተከሰተውን ግጭት በትኩረት እየተከታተለችው እንደምትገኝ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የሱዳን ወንድማማች ፓርቲዎች ወደ ሰላም ንግግር እንዲመለሡ ጥሪ ባቀረቡበት የአረብኛ ቋንቋ መግለጫ ነው።

ዶ/ር ዐቢይ በመልዕክታቸው የሱዳን ወንድማማች ፓርቲዎች ከግጭት አባባሽ ድርጊቶች ተቆጥበው ፤ የተፈጠረውን ግጭት በውይይት እንዲፈቱ እና ግጭቱን እንዲያረግቡ የሰላም ጥሪ አቅርበውላቸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስትም የተፈጠረውን ግጭት በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን አሳውቀዋል።

የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት እና የአፍሪካን ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ ለመስጠት አዲስ አበባ ሁሌም ቢሆን በሯ ክፍት እንደሆነ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ ፦ ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመሩት RSF (ፈጥኖ ደራሽ) በሰሜን ሱዳን ሜሮዌ " የተማረኩ " ናቸው ያላቸውን #የግብፅ_ወታደሮችን የሚያሳይ ቪዲዮ አጋርቷል። የግብፅ ወታደሮች በ " ሜሮዌ "  ስለነበሩበት ሁኔታ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ ባይኖርም የግብፅ እና የሱዳን ወታደሮች ከኢትዮጵያ ጋር በተፈጠረ ዲፕሎማሲያዊ ዉጥረት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል አልፎ አልፎ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ…
#Update

የግብፅ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጋሪብ አብደል ሃፌዝ ፥ በሱዳን ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን ነው ብለዋል።

ቃል አቀባዩ ሱዳን ውስጥ ልምምድ የሚያደርጉ የግብፅ ሃይሎች ስለመኖራቸው ተናግረው ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ የቃል አቀባዩ ማብራሪያ የተሰጠው ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመሩት RSF (ፈጥኖ ደራሽ) በሰሜን ሱዳን ሜሮዌ " ውስጥ የግብፅ ወታደሮች ' #መማረካቸውን ' በቪድዮ ካሳየ በኃላ ነው።

@tikvahethiopia
#ትንሣኤሎተሪ ፦ የትንሳኤ ሎተሪ ዕጣ በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በህዝብ ፊት ወጣ።

10 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 0416607 ሆኖ ወጥቷል።

ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል።

ምንጭ፦ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግብፅ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጋሪብ አብደል ሃፌዝ ፥ በሱዳን ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን ነው ብለዋል። ቃል አቀባዩ ሱዳን ውስጥ ልምምድ የሚያደርጉ የግብፅ ሃይሎች ስለመኖራቸው ተናግረው ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ይህ የቃል አቀባዩ ማብራሪያ የተሰጠው ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመሩት RSF (ፈጥኖ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሱዳን ነገር ከቁጥጥር እየወጣ ይሆን ?

የአል-ሱዳኒ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ያሲር አብዱላህ ሀገሪቱ ወደ ከፋ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራች እንደሆነ አስጠንቅቋል።

በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው ብሏል።

እስር በርስ የሚደረገውን ግጭት ለማስቆም በሰራዊት አመራሮች በኩል ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ከሌለ ሁኔታው እጅግ ወደ ከፋ ሙሉ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራ ነው ሲል ገልጿል።

ይህ ሁኔታ በአጠቃላይ ሀገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን የገለፀው ያሲር አብዱላህ በዚህ ውስጥ ማንም አሸናፊ የለም ብሏል።

ዛሬ ካርቱም ውስጥ በሱዳን ጦር እና RSF (ፈጥኖ ደራሽ) መካከል የከፋ የከተማ ውስጥ ውጊያ ጭምር ሲካሄድ ነበር።

ሁለቱም ወገኖች በየፊናቸው ድል እየተቀዳጁ መሆኑንና አንዱ የአንዱን መሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተፈላለጉ መሆኑን በሚያወጧቸው መግለጫዎች እያሳወቁ ይገኛሉ።

በጄነራል አል - ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር በሄሜቲ የሚመራውን RSF " አማፂ " ቡድን ብሎ በይፋ ጠርቶታል። ዳጋሎም (ሄሜቲ) ተሸሽገው የሚገኙ በህግ የሚፈለጉ ወንጀለኛ ናቸው በማለትም ማንኛውም ዜጋ ከእሳቸው ጋር ግንኙነት እንዳይኖረው አሳስቧል።

ጦሩ RSF እስካልፈረሰ ድረስ በምንም ለድርድርም ይሁን ለንግግር እንደማይቀመጥ አስገንዝቧል።

በጄነራል ሄሜቲ የሚመራው RSF በበኩሉ ድል እየተቀዳጀ መሆኑንና " ወንጀለኛ ናቸው " ያላቸውን አል ቡርሃንን #ለማሰር እያሳደዳቸው መሆኑን ገልጿል ያሉበትንም ደርሼበታለሁ ብሏል፤ ቡርሃን ግራውንድ ስር #ተደብቀው የህዝብ ልጆችን እንዲዋጉ እየገፋፉ ነው ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሱዳን ነገር ከቁጥጥር እየወጣ ይሆን ? የአል-ሱዳኒ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ያሲር አብዱላህ ሀገሪቱ ወደ ከፋ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራች እንደሆነ አስጠንቅቋል። በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው ብሏል። እስር በርስ የሚደረገውን ግጭት ለማስቆም በሰራዊት አመራሮች በኩል ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ከሌለ ሁኔታው እጅግ ወደ ከፋ ሙሉ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራ ነው ሲል ገልጿል።…
#ጥንቃቄ

ሱዳን ለምትገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት !

የሱዳን አየር ኃይል የRSF ኃይሎች ይገኙባቸዋል ባላቸው አካባቢዎች ቅኝት እንደሚያካሂድ አሳውቋል።

አየር ኃይሉ ሁሉም በሱዳን ውስጥ ያሉ ዜጎች / ሰዎች በቤት ውስጥ የመቆየት / ከቤታቸው እንዳይወጡ አስጠንቅቋል።

በሱዳን ያላችሁ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን እራሳችሁን እና የምትወዷቸውን ሁሉ እንድትጠብቁ ፤ የሚወጡትን ትዕዛዞችን እየተታተላችሁ እንድትፈፅሙ አደራ እንላችኃለን።

@tikvahethiopia
#ትንሳኤ

እንኳን አደረሳችሁ !

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።

በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።

የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን !

መልካም በዓል !
#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
#SUDAN

ሱዳን ውስጥ እየተደረገ ያለው ግጭት መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል።

በተለይም በዋናነት በካርቱም ሰሜናዊ አቅጣጫ ግጭት እየተካሄደ እንደሆነ ተሰምቷል።

ከትላንት አንስቶ በነበረው ግጭት የሟቾች እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። እስካሁን ባለው 56 ሰላማዊ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ኃይሎች በፖርት ሱዳን ጦራቸው #ከውጭ_አውሮፕላኖች ጥቃት እንደረሰበት ገልጸዋል። እነዚህ የውጭ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልፅ አልተነገረም።

የውጭ ኃይሎች ከጣልቃ ገብነት እራሳቸውን እንዲያርቁ እና እጃቸውን እንዲሰበስቡ RSF አስጠንቅቋል።

የሱዳን ጦር በRSF ይዞታዎች ላይ የአየር ላይ የቦንብ ጥቃቶችን ስለማድረሱ ለመስማት ተችሏል። ዋና ዋና የሚባሉትን የጦር ሰፈሮችንም መቆጣጠሩ እየተነገረ ነው።

የRSF አዛዥ ጀነራል መሐመድ ሀምዳን ደጋሎ ለሚዲያ በሰጡት ቃል ፤ እስካሁን ከ "አል-ቡርሃን" ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል። " አል-ቡርሃን ተከቧል " ያሉት ዳጋሎ " ያለው አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው " ብለዋል።

ሱዳን ውስጥ የምትገኙ ቤተሰቦቻችን ነገሮች እስኪረጋጉ እራሳችሁን እንድትጠብቁ የሚወጡ ትዕዛዞችንም እንድትፈፅሙ አደራ እንላችኃለን።

ቪድዮ ፦ በሱዳን ከተማ ውስጥ ሲቪል ሰዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ያሳያሉ።

@tikvahethiopia
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦ ለአንገት ፣ ለትክሻ ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር ፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር ፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል ፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣  ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች ፣ በአጠቃላይ ከነርቭ ፣ ከጡንቻ ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ !

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት

አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን፤ ስልክ 0979099909/ 0911039377

በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EOMmarket

ምግብ ለመስራት ሁለት ጊዜ ማሰብ የለብዎትም !

ህይወትዎን ቀላልና ዘመናዊ የሚያደርጉ ጥራት ያላቸው እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበት ትልቁ የኦንላይን ገበያ !

https://t.iss.one/EOMMarket

የመረጡትን እቃ ይዘዙን፤ያሉበት ድረስ በነፃ  እናደርሳለን
𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲  : 0929181818 / 0909868788

ይምጡ የሽያጭ ማእከሎቻችን ይጎብኙ፤ ተደስተው ይመለሳሉ ! አድራሻችን፦
ቁጥር 1:- መገናኛ, ቤተልሄም ፕላዛ  የሱቅ ቁጥር  G-10 ግራውንድ [ እንደገቡ በስተቀኝ በኩል ]

ቁጥር 2:- ሜክሲኮ, ኬኬር ህንፃ የሱቅ ቁጥር #338

𝕵𝖔𝖎𝖓 𝖔𝖚𝖗 𝖈𝖍𝖆𝖓𝖓𝖊𝖑 : @EOMmarket
     
#ቦንጋ

ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ትምህርት መስክ የተማሩ ተማሪዎች ሊመረቁ ነው።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፤ በ2015 የትምህርት ዘመን መጨረሻ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 37 ተማሪዎችን በ " ቡና ሳይንስ " የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የቡና ምርት ኢትዮጵያ ትልቁ የውጭ ምንዛሬ የምታገኝበት ሸቀጥ በመሆኑ በ2015 ዓ.ም መጨረሻ 37 ተማሪዎችን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ ይመረቃሉ ብሏል።

ኢትዮጵያ ቡናን ለዓለም ያበረከተች ሀገር ብትሆንም እስካሁን ድረስ የቡና ትምህርት መስክ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት አዳጋች ሆኖ ነበር ያለው ተቋሙ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቡና ሳይንስ ትምህርት ክፍል እራሱን ችሎ በ2012 ዓ.ም እንዲከፈት ማድረጉን አስታውሷል ።

በቡና ምርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመመርመር ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን ቡናን በትምህርትና ምርምር አስደግፎ ለመምራት ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የቡና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል በማቋቋም ነው ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኘው።

በሚቀጥለው ዓመት በሁለተኛ ዲግሪ በቡና ሳይንስ ተማሪዎች የሚመረቁ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ጊዜትም የቡና ሳይንስ ትምህርት መስክን በዶክትሬት ዲግሪ ደረጃ ማስተማር እንደሚጀምር ዶክተር ጴጥሮስ ጠቁመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ካለው 200 ሄክታር መሬት ውስጥ በ150 ሄክታሩ ላይ የግብርና ምርቶችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ተፈናቃዮች መቼ ወደ ቄያቸው ይመለሳሉ ?

በትግራይ ጦርነት እጅግ በርከታ ሰዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ውስጥ ይገኛሉ። እነዚህ ወገኖች ከቄያቸው ከመፈናቀላቸው ባለፈ በቂ ትኩረት ድጋፍ አያገኙም።

ምንም እንኳን የሰላም ስምምነት ቢፈረምም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው አልተመለሱም፤ መቼ ነው ወደ ቄያቸው ተመልሰው መደበኛ ህይወታቸውን የሚነሩት ? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው ለመመለስ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት እየሰራ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ አሳውቀዋል።

አቶ ጌታቸው ይህን ያሳወቁት ባሳለፍነው ሳምንት በጦርነቱ ምክንያት ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ተፈናቅለው መቐለ ፤ " 70 ካሬ " በሚባለው መጠለያ የሚገኙ ዜጎችን በጎበኙበት ወቅት ነው።

ተፈናቃዮች ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፥ ድጋፍ በጊዜው እንደማይደርሳቸው፣ ትኩረት ተነፍገው ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረው አስተዳደሩ ወደ ቄያቸው እንዲመልሳቸው እና ዘላቂ መፍቴ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል።

በመጠለያ ጣቢያው ያለው ተፈናቃይ ቁጥር እና የሚደረገው ድጋፍ የሚመጣጣም እንዳልሆነ ተፈናቃዮች የገለፁ ሲሆን አስተዳደሩ ወደ ቦታቸው መልሷቸው ሰርተው እንዲበሉ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ፥ " ከችግራችሁ በላይ እኛ ላይ ተስፋ መጣላችሁ ለእኛ ትልቅ አቅም ነው የሚፈጥርልን ፤ በቀላሉ የሚፈቱ ችግሮችን ለመፍታት እንሞክራለን " ብለዋል።

" ዋናው ዘላቂ መፍትሄ 25 ኪሎ እርዳታ ማግኘት ሊሆን አይገባም ይህ ኑሯችሁን ሊቀይረው ስለማይችል " ያሉት አቶ ጌታቸው " ይልቁንም ወደ ቄያችሁ ተመልሳችሁ እራሳችሁ ጥራችሁ ግራችሁ የምታገኙበት ሃብት እራሳችሁን ችላችሁ ለቤተሰቦቻችሁ እና ለወገኖቻች የምትሆኑበትን መንገድ ይፈጥራል እኛም ይህ እንዲሆን እንሰራለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" እስከዛ ድረስ ሁለት ሳምንት ይሁን አንድ ወር ለምትቆዩበት ጊዜ የበጎ አድራጊዎች ድጋፍ በተገቢው ሁኔታ እንዲደርሳችሁ እንጥራለን " ሲሉ አክለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

በጎረቤት ሱዳን ያለው ውጊያ ዛሬ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል።

ከካርቱም ጨምሮ ከሌሎች ከተሞች በወጡ መረጃዎች ዛሬም በከባባድ መሳሪያ የታገዘ የከተማ ውስጥ ውጊያ እየተካሄደ ነው።

በተለይም በካርቱም ሰሜናዊ እና ደቡባዊ ክፍል የከባድ መሳሪያ ውጊያ እንዳለ ተነግሯል።

የሠራዊቱ ጠቅላይ ዋና መሥሪያ ቤት በር ፊት ለፊት ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን አርኤስኤፍ (RSF) ከቅዳሜ ጀምሮ ይህንን ትልቅ የሰራዊት ተቋም ለመቆጣጠር እየሞከረ ነው ተብሏል።

ይህንን ተቋም መቆጣጠር በራሱ ሰራዊቱን እንደመቆጣጠር ነው የሚታሰበው።

በሌላ በኩል ፤ በሜሮዌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ግጭት መኖሩ ተገልጿል። ይህ ግጭት እንደገና የተቀሰቀሰ ሲሆን የከባድ መሳሪያ ድምፆችም ይሰማሉ ተብሏል።

በሜሮዌ የሚገኙ ሆስፒታሎች በተጎዱ ሰዎች የተሞሉ መሆናቸውን ከህክምና ምንጮች ለማወቅ መቻሉን አልጀዚራ ዘግቧል።

ተጨማሪ መረጃዎች ፦

- በካርቱም ውጊያ በመኖሪያ መንደሮች ጭምር እየተደረገ ነው።

- በሱዳን ባለፉት ሶስት ቀን የሞቱ ሰላማዊ ሰዎች ከ100 ተሻገረዋል። እጅግ በጣም በርካታ ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል።

- የRSF የፖለቲካ አማካሪ የሱፍ ኢዛት ለአልጀዚራ በሰጡት ቃል ማንኛውም የተኩስ አቁም ለማድረግ በሠራዊቱ ውስጥ የ "አመራር መኖር"ን ይጠይቃል ብለዋል። " ሠራዊቱ ምንም ዓይነት አመራር የለውም። " ያሉት አማካሪው " የተኩስ አቁም መቼ እንደሚሆን የምንወስነው እኛ ብቻ ነን " ብለዋል።

-  RSF " ወንጀለኛ ናቸው " ሲል የጠራቸውን አልቡርሃንን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፍለጋ ላይ መሆኑን አሳውቋል።

- በጄነራል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር የRSF ሚሊሻዎች ሰላማዊ ሰዎችን ከለላ አድርገው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በመግለፅ ሰላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ጥብቅ በሆነ ወታደራዊ ጥንቃቄ ኦፕሬሽኑን እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

Photo Credit : Aljazeera

@tikvahethiopia