#BREAKING
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብን ይፋ አደረገ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቁት የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብ
1. የሶሻል ሳይንስ ሴቶች መግቢያ ውጤት 164 እና በላይ
2. የሶሻል ሳይንስ ወንዶች መውጤት ውጤት 174 እና በላይ
3. የናቹራል ሳይንስ ወንዶች መግቢያ ውጤት 176 እና በላይ
4. የናቹራል ሳይንስ ሴቶሽ መግቢያ ውጤት 166 እና በላይ
5. ለግል ተፈታኞች ለወንዶች 190 እና ከዚያ በላይ
6. ለግል ተፈታኞች ሴቶች 185 እና ከዚያ በላይ
7. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ናቹራል ወንዶች 166
8. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ናቹራል ሴቶች 156 እና ከዚያ በላይ
9. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ማህበራዊ ሳይንስ ወንዶች 164 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 154 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም መስማት ለተሳናቸው በተፈጥሮ ሳይንስ ወንዶች 120 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 115 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ማየት ለተሳናቸው ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ወንዶች 110 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 105 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም በመንግስት እና በግል ተቋማት በግላቸው ከፍለው ለሚማሩ ተፈታኞች በሁለቱም መስክና ጾታ 140 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተፈታኞች መማር ይችላሉ ተብሏል።
በአጠቃላይ በዘንድሮው ዓመት 142 ሺህ 821 ተማሪዎች ወደ መንግስት ዩንቨርሲቲዎች ይገባሉ ተብሏል።
Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ግብፅ❓
"...አሁን ቢሆን እንድትገነባ አንፈቅድላትም" አብዱል ፋታህ አልሲሲ
የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የጀመረችው አሁን ቢሆን እንድትገነባ አንፈቅድላትም ነበር አሉ። ፕሬዘዳንቱ ኢትዮጵያ ከ8 ዓመት በፊት የተካሄደውን የግብጽ አቢዮት ተጠቅማበታለች ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት በትላንትናው እለት በካይሮ በተደረገ ብሔራዊ የወጣቶች መድረክ ላይ ነው። ግብጻዊያን ከ8 ዓመት በፊት የሆስኒ ሙባረክን አገዛዝ ለመገርሰስ ወደ አደባባይ በወጡበት ወቅት ኢትዮጵያ ይሄነን አጋጣሚ በመጠቀም የህዳሴውን ግድብ መጀመሯን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ የጀመረችው አሁን ቢሆን ኖሮ እንከለክላት ነበር ሲሉ ለተሰብሳቢዎቹ መናገራቸውን የአገሪቱ የህትመት ሚዲያ አህራም ኦን ላየን የተሰኘው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ አስነብቧል። ግብጽ በአብዮቱ ጊዜ የሰራችው ስህተት ዋጋ እያስከፈላት ነው ያሉት ፕሬዘዳንት አልሲሲ ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት የሚፈልጉ ግብጻያን ወጣቶች እንዳሉም ተናግረዋል።
#ETHIO_FM
https://telegra.ph/ETH-09-15

5ሺ ዶላር የሚየሸልም ውድድር ይፋ ተደረገ!
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 5ሺ የአሜሪካን ዶላር የሚያሸልም ውድድር ይፋ አደረገ። ሚኒስቴሩ ከአይቢኤ ኢትዮጲያ ከተሰኘ የግል ኩባንያ ጋር በመተባበር አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ ‹‹አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት›› በሚል ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22ቀን 2012 ድረስ በአዲስ አበባ አካሂዳለሁ ብሏል፡፡
ስለሆነም ችግር ፈቺ፤ ሀብት ፈጣሪና ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየር የሚችል የፈጠራ ስራ ያላችሁ በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሀገራችሁን ወክላችሁ እንድትወዳደሩና የፈጠራ ውጤቶቻችሁን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች፤ ለቬንቸር ካፒታል ተቋማት እና ለሌሎች የፋይናስ ምንጮች በማስተዋወቅ ወደ ምርትና አገልግሎት እንድትቀላቀሉ ይጋብዛል፡፡ በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆኑ አምስት ከፍተኛ የፈጠራ ወይም የምርምር ስራዎች እያንዳንዳቸው 5ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
ሌሎችም ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ #ሽልማቶች እንደሚበረከትላቸው በተገለጸው በዚህ ውድድር ላይ ለመካፈል ዘመናዊ ከተሞች እና አዳዲስ የመኖሪያ ቴክኖሎጂዎች፤ ዲጂታላይዜሽን፤ የኢንተርኔት ንግድ ስርዓት፤ የግብርና፤ የጤናና የህክምና ቴክኖሎጂ፤ መስተንግዶና ቱሪዝም፤ የማምረቻና እና የማዕድን ኢንደስትሪ አመልካቾች የፈጠራ ስራ ፕሮፖዛላችሁን ስከ መስከረም 16ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብላችኋል።
በዚህ ውድድር ላይ የመወዳደሪያ ሀሳባችሁን [email protected] ላይ በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

#update የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን በማስመልከት ለማካሄድ ላቀደው ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክቶችን ይፋ አደረገ። ቦርዱ በመጪው ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን በማስመልከት ለማካሄድ ላቀደው ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።
Via #ETHIO_FM
@tsrgabwolde @tikvahethiopia
Via #ETHIO_FM
@tsrgabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጅ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ከጸጥታ አካላት እና ከአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ።
ውይይቱ ትኩረቱ የነበረው በአ/አ ከተፈጠረው ክስተትና ከንግድ ቤት መታሸግ ጋር በተያያዘ ነበር።
የትግራይ ተወላጅ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የንግድ ቤቶቹ መታሸግ ከማንነት ጋር የተያያዘ አንድምታ እየፈጠረባቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ መቐለ ከተማን ሰኔ 21 ቀን 2013 ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ በሚገኙ ፣ ሆቴሎች ፣ መጠጥ ቤቶች እና ምሽት ቤቶች ብጥብጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በመደገፍ የተጠረጠሩ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።
እርምጃ የተወሰደባቸው ቤቶች በከተማዋ የዘር ፍጅት እንዲከሰት ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በሆቴል ቤታቸው በማስቀመጥ ድጋፍ አድርገዋል በሚል ሲሆን ከነበረው ክስተት ጋር በተያያዘ መንግስት ከ8 በላይ ባለ ኮከብ ሆቴሎች እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ክለቦች እንደዚሁም ምግብ ቤቶችን ጨምሮ በድርጊቱ ተሳትፎ የነበራቸው ከረንቦላ ቤቶች ታሽገዋል።
ከትግራይ ተወላጅ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተካሄደው ውይይት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ የሴክተር ተቋማት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት ሰለሞን ኃይሌ ፥ ሰላማዊ የሆነው የንግዱ ማህበረሰብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብቱ ይጠበቃል ፤ ከንግዱ ማህበረሰብ የሚጠበቀው እራሱን ከህወሓት ቡድን ማራቅ ብቻ ነው ብለዋል፡፡
"የትግራይ ተወላጅ የሆነ በሙሉ በሀገር የተከሰተውን ህመም ሊጋራ ይገባል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/Addis-Ababa-07-28
Credit : #ETHIO_FM
@tikvahethiopia

#Ethio_Sudan
የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ወቅታዊ ችግር ለመፍታት በተመረጡ የሀገር ሽማግሌዎች ውይይት ተደረገ።
ከሁለቱም ሀገራት የተመረጡ የሀገር ሽማግሌዎች በመተማ ዮሃንስ ከተማ በሀገራቱ መሀል ባለው ችግር ዙርያ ምክክር መደረጉን የመተማ ዮሃንስ ከተማ ኮሚኒኬሽን ማምሻውን አስታውቋል።
ኮሚኒኬሽኑ እንዳስታወቀው ከነበሩት የውይይት አጀንዳዎች መሀል፣
1.ችግሮቻችን ምን ምን ናቸው የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፣
2. የኢትዮ-ሱዳን ግንኙነትን ለማጠናከር ከኛ ምን ይጠበቃል፣
3. በቀጠናው የሚታዩ ሰው የማገትና ሌብነትን እንዴት እንከላከል፣
4. ድንበሩ ከዚህ በፊት እንደነበረው ግንኙነት እንዲፈጠር ከኛ ምን ይጠበቃል፣
5.ህዝባችን ሰላሙ የተጠበቀ እንዲሆን የሀገር ሽማግሌዎች እስከ ባህር ዳር ድረስ እንዲቋቋምና
ግንኙነቶችን ለማጠናከር ህብረተሰባችን ላይ የግንዛቤ ትምህርት በመስጠት ስራ መስራት እንደሚገባ የሚሉ ሃሳቦች ተገልፀዋል።
ለዚህም የጋራ የሆነ ትብብር 20 ሽማግሌዎችን በመምረጥ ውይይትን ማድረግ እንደሚችሉ ወስነዋል። ሌላው የሁለቱንም መንግስታት ጠንካራ ግንኙነትን በመፍጠር የህብረተሰብን ችግሮች ለመቅረፍ የጋራ ጥንካሬ ያስፈልጋል ሲሉ የሀገር ሽማግሌዎች ገልፀዋል።
Via የመተማ ዮሀንስ ኮሚኒኬሽን / Elias Meseret

ለስድስት ወራት የተዘጋው በመተማ - ጋላባት በኩል ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው መንገድ ነገ ክፍት ይሆናል ተብሏል።
ዛሬ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች እና የሁለቱ ሀገራት አጎራባቸው አስተዳደሮች ማለትም የምዕራብ ጎንደርና በሱዳን በኩል ደግሞ የጋላባት አካባቢ አስተዳደር ተወካዮች በመተማ ተወያይተዋል፡፡
ይህን በተመለከተ የመተማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብቴ አዲሱ ለአል ዐይን አማርኛ ክፍል በሰጡት ቃል ሐምሌ17 ቀን 2013 ዓ.ም የመተማ-ጋላባት መንገድ በሱዳን በኩል ተዘግቶ ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።
የሱዳን መንግስት መንገዱን የዘጋው አንድ ወታደራዊ አመራር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ተገድሎብኛል ብሎ በማሰቡ መሆኑን አቶ ሀብቴ ተናግረዋል፡፡
ከንቲባው እንዳሉት መንገዱ አለምአቀፍ መስመር ስለሆነ እንዲከፈት በአካባቢው አስተዳደር እና በሀገር ሽማግሌዎች ለማስከፈት ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡
በስብሰባው ላይ መንገዱ ተክፍቶ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንዲቀጥል መግባባት ላይ መደረሱን የገለጹት አቶ ሀብቴ ከዚህ በተጨማሪም ለሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችም ተነስተዋል ብለዋል፡፡
በሱዳን ግዛት ውስጥ ሚንቀሳቀሱ የህወሓት ኃይሎች መኖራቸውንና ያሉበትን ቦታ ጭምር በመጥቀስ እና ትክክል እንዳልሆነ ለሱዳን ወታደራዊ አመራር እንደተነገራቸው ከንቲባው ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
ፎቶ ፦ የምዕራብ ጎንደር ዞን

በሱዳን ኃይሎች የተያዘው የአልፋሽቃ መሬት ሰላማዊ መፍትሄ ካላገኘ በኢትዮጵያ በኩል በኃይል የመፍታት እድል ይኖረው እንደሆነ ከጀርመን ሬድዮ የተጠየቁት የመከላከያ ሰራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ጄነራል ባጫ ደበሌ፥ "በእኛ በኩል መንግስታችን ከሱዳን ጋር ተዋጉ የሚል ትዕዛዝ አልሰጠንም" ብለዋል።
አክለውም፥ "እኛ የያዝነው ውጊያ አለ፤ ከእነዚህ ሰዎች (ከሱዳኖች) ጋር ድሮውንም እንዳልነው ነው በውይይት የምንፈታው ነገር ነው። እነሱ ከነበሩበት የቀጠሉት የለም። ስለዚህ ትኩረት የተነፈገው አይደለም። በሚገባ እየተከታተልን ነው ያለነው" ሲሉ ገልፀዋል።
ጄነራል ባጫ፥ " ሁሉንም ድስት ጥደህ አንዱንም ሳታማስል ሊያርብህ አይገባም። ሆኖም በየትኛውም አካባቢ በኢትዮጵያ ድንበር ላይ የሚመጣ ችግር ካለ ግን ይሄን መመለስ የሚችል አቅሙ አለን " ብለዋል።
በሌላ በኩል ከአል ዓይን ኒውስ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ጀማል አል ሼክአምባሳደር ጀማል አል ሼክ፤ በሱዳን ቁጥጥር ስር ስለሚገኘውና የይገባኛል ጥያቄና ክርክር እየተነሳበት ስላለው ስፍራ የሱዳንን አቋም አንፀባርቀዋል።
አምባሳደሩ፥ "አሁን ክርክር እያስነሳ ያለው መሬት ሱዳን የኔ ነው ብላ ታምናለች" ያሉ ሲሆን " ሱዳን ጉዳዩ ከፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ ውጭ በሌሎች አማራጮች ይፈታል ብላ አታምንም " ብለዋል።
አምባሳደሩ፥ " እነዛ ቦታዎች የሱዳን ናቸው፤ ለዚህ ማስረጃም እንደፈረንጆቹ 1902 በሁለቱም ሀገራት የተደረሰው ታሪካዊ ስምምነት እንዳለ ይታወቃል፤ ስለዚህም የድንበር ውዝግቡ የስምምነቱን ዋና ዋና ጉዳዮች መሰረት በማድረግ ሊፈታ ይችላል የሚል እምነት አለኝ" ሲሉ ተናግረዋል።
ሱዳን ጉዳዩን በዲፕሎማሲ እና ፖለቲካዊ ውይይት ለመፍታት ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።

#ethio_telecom
ኪስዎ ሳይጎዳ ወሩን ሙሉ የሚወዷቸው ጋር ደውለው ይጨዋወቱ!
ለዘመድ ለጓደኛዎ እንዲሁም ለስራ አጋርዎ ያለገደብ እንደሻዎ ወሩን ሙሉ የሚጠቀሙበት የድምፅ ጥቅል በ999 ብር ብቻ ከተጨማሪ የፅሁፍ መልዕክት ጋር በቴሌብር እና ማይ ኢትዮቴል መተግበሪያዎች አንዲሁም *999# ገዝተው ይጠቀሙ።

የኢትዮ ቴሌኮምን አዲስ ሲም ካርድ ይበልጥ ተሻሽለው ከቀረቡት የሲም ካርድ ማስጀመሪያ ጥቅሎች ጋር ሲገዙ ከ15 ብር የአየር ሰዓት በተጨማሪ እስከ 3 ጊ.ባ የሚደርስ የዳታ ስጦታ እንዲሁም ለአንድ ወር የሚያገለግል የጥሪ ማሳመሪያ አገልገሎት በነፃ ያገኛሉ
ሁሌም የተሻለውን፤ ምርጥ ምርጡን ለናንተ!
#SPECIALOFFER!!! #buyandgetbonus