#ATTENTION
በአማራ ክልል ፤ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር ጥብቅ ክልከላዎች ተጣሉ።
የኦሮሞ ዞን ኮማንድ ፖስት ምን ክልከላዎችን ጣለ ?
- የሰአት እላፊ ገደብ (ባጃጅ 1:00፤ የሰው እንደ አካባቢና እንደ ሚፈጠር ችግር ይወሰን ፆም በመሆኑ ተብሏል) ።
- ስምሪት ከተሰጠው ሃይል ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተገልጿል።
- በማንኛውም ሆቴል መሳሪያ ይዞ መግባት የተከለከለ ሲሆን ፤ በሁሉም ሆቴሎች ፍተሻ እንዲጠናከር ታዟል።
- የፀጥታ ሃይሉን መጠርነፍና ለግዳጅ ዝግጁ ማድረግ ፖሊስና ሚሊሻ ፤ ከፌደራልና መከላከያ ጋር በቅንጅት መስራት አለባቸው ተብሏል።
- የኬላ ላይ ፍተሻ እንዲጠናከር ታዟል።
- የህዝብ ግንኙነት ስራ በተደጋጋሚ እንዲሰራ ታዟል ፤ በዋናነት በመስመር መዝጋት እየተጎዳ ያለው ህዝብ መሆኑ ተመላክቷል።
- ህብረተሰቡ በቀበሌ፣ በመንደር፣ በሰፈር፣ በኬላ፣ በተቋማት ጥበቃ ላይ ተደራጅቶ አካባቢውን የመጠበቅና ለሰላም ለሚከፈል ዋጋ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ታዟል።
- የተሳሳተ መረጃ የሚነዙ፣ በአሉቧልታ ህዝብን የሚያሸብሩ፣ ወንጀለኞችን ለመንግስት አጋልጦ እንዲሰጥ ሁሉም በጥብቅ ተማምኖ መንቀሳቀስ አለበት ተብሏል።
- ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እንዲደረግ ፤ በየደረጃው ያለው አመራርና ህዝቡ ከፀጥታ ማዋቅሩ ጋር መረጃ መለዋወጥ እንዳለበት ታዟል።
- የመንግስት ተቋማት፣ ባንኮችን ፣ የሀይማኖት ተቋማትን የጥበቃ ሁኔታን እንዲጠናከር ታዟል።
- የአካባቢውን ሁኔታና የዞኑን ክልከላ በማይጣረስ መንገድ ተጨማሪ ክለከላዎችን በወረዳና ከተማ አስተዳደር ኮ/ፖስት ማወጅ እንደሚቻል ተገልጿል።
መረጃው የኦሮሞ ዞን ኮማንድ ፖስት ነው።
@tikvahethiopia

#Mekelle
በዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑክ መቐለ ገባ።
በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ዛሬ መቐለ ገብቷል።
ልዑኩ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገር ይጠበቃል።
ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ

#አቢሲንያ_ባንክ
አፖሎ የሞባይል መተግበሪያን ተጠቅመው ከዲጂታል አካውንትዎ የዲኤስቲቪ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም ኢንተርኔት እና ሌሎች ክፍያዎችዎን በቀላሉ መፈፀም ይችላሉ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

#ኢትዮ_ቴሌኮም
ለትንሳኤ በዓል ከባህር ማዶ ከወዳጅ ዘመድ በአጋሮቻችን #Talkremit #Worldremit #Azimo #MasterRemit #Majority #Moneytrans #Remitly #ria #Taptapsend በኩል የሚላክልዎትን ገንዘብ ያለ ውጣ ውረድ እና እንግልት ባሉበት ሆነው በቴሌብር ሲቀበሉ የተላከልዎትን ገንዘብ መጠን 5% እንዳሻዎ ለማንኛዉም ክፍያ ሊጠቀሙ የሚችሉበት የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ!
ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ
ቴሌብር ሃዋላ የሩቁን ያቀርባል!
መልካም በዓል

#Update
አማራ ክልል ከ " ክልል ልዩ ኃይል " ጋር በተያያዘ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን ለማውቅ ተችሏል።
ከቀናት በፊት አንስቶ በተነሳው ተቃውሞ ክቡር የሆነው የሰዎች ህይወት አልፏል፣ አካላዊ ጉዳት ደርሷል፣ የንግድ እንቅስቃሴ ተቋርጧል፣ ትራንስፖርት እና መሰረታዊ አገልግሎት ለማግኘት ችግር ሆኗል።
ዛሬ በክልሉ መዲና ባህር ዳር ተቃውሞው ቀጥሎ መዋሉ በኮምቦልቻ ከተማ በነበረ ተቃውሞ ደግሞ የሰዎች ህይወት መጥፋቱን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።
አንድ የኮምቦልቻ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ " ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ከፀጥታ ሀይሎች ጋር ተጋጭተው የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል " ብሏል።
እስካሁን በአማራ ክልል ከመንግሥት ተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በተለያዩ አካባቢዎች የሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ አዳጋች ሆኗል።
የክልል ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀትን በተመለከተ መንግስት እንዲሁም የተቃዋሚ ኃይሎች በየፊናቸው የተለያዩ መግለጫዎችን እያወጡ ይገኛሉ።
የአማራ ክልል ነዋሪዎች ፤ የመንግሥትን ውሳኔ አጥብቀው እየተቃወሙ ያሉት ልዩ ኃይል የአማራ ህዝብ ዋስትና እንደመሆኑ የተወሰነው ውሳኔ ተገቢ አይደለም ፣ የህዝቡ ደህንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ይህ ውሳኔ መወሰኑ ተቀባይነት የለውም ፣ ሌሎች ለአማራ ህዝብ የደህንነት ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቡድኖች ትጥቅ ሳያወርዱ ልዩ ኃይሉን ለመበተን መወሰን ፍፁም ተገቢነት የሌለው ውሳኔ ነው በሚል ነው።
ፎቶ ፦ ዛሬ በባህርዳር ቀበሌ 8 ዊዝደም እና ቀበሌ 7 ስላሴ አካባቢ የነበረው ሁኔታ (ላሎ - ባህርዳር - ቲክቫህ ቤተሰብ) ።

#Woldia
በወልድያ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ ፤ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎችም ተጥለዋል።
ወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ እና ክልከላ ማስቀመጡ ተገልጿል።
ክልከላዎቹ ፦
- ጭፈራ ቤቶች፥ ካፍቴሪያዎች፣ ሬስቶራንቶች እና የመሳሰሉት ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም።
- ለባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ፤ ከተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ለጸጥታ ሥራ ከተመደቡ ተሽከርካሪዎች ውጭ በዚህ ምደባ ስምሪት ያልታቀፉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2:00 እስከ ጧቱ 12:00 ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።
- የሰው እንቅስቃሴ ለጸጥታ ሥራ ከተመደበው ሰው ውጭ ከምሽቱ 3:00 እስከ ጧቱ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
- በማንኛውም ቦታና ጊዜ ለጸጥታ ሥራ ስምሪት ከተመደበ አካል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።
- አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ሥራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።
- የመንግሥትን የታጠቀ ኀይል ያስከዳ፣ በተለያየ መንገድ አማሎ የጦር መሳሪያ የገዛ፣ የለወጠ፣ ባልተገባ መንገድ መታወቂያ የሰጠ፣ መንገድ የመራ ማንኛውም አካል በሕግ ተጠያቂ ይሆናል ተብሏል።
- የመንግሥት የጸጥታ ኀይል ሕግና ስርዓትን ለማስከበር በሚያከናውናቸው ተግባሮች ዙሪያ ማንኛውም ሰው የመተባበር ግዴታ ተጥሎበታል ፤ የማይተባበር በሕግ ይጠየቃል ተብሏል።
የኮማንድ ፖስቱ በአብዛኛውን በሌሎች ከተማዎች የተጣሉ ክልከላዎችን አይነት ይዘት ያለው ክልከላ ነው የጣለው። (#ሙሉ ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል)
ኮማንድ ፖስቱ ይህ ውሳኔ የተላለፈባቸው ምክንያቶች ፦ በከተማው የተጀመሩ ልማቶችን " አመጹን መቀላቀል ሲገባህ ልማትን እያስቀጠለክ " በሚል ዛቻ ልማትን የማደናቀፍ ፤ በሙስና፥ በሌብነት፥ እና በተለያዩ ብልሹ ወንጀሎች ስጋት ያለባቸው አካላት የዕለት ጉርስ ፈላጊዎችን በገዘብ በመግዛት ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠርና ለማባባስ የሚያደርጉት ሙከራ በመረጃ ደረጃ የተገኘ በመሆኑ ነው ብሏል።
ከዚህ ባለፈ የትንሳኤ እና የረመዳን ሃይማኖታዊ ሁነቶችን በሰላም ለማጠናቀቅ ለዕኩይ ዓላማ የተሰማሩ ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠር ነው ሲል አሳውቋል።
(የወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

TIKVAH-ETHIOPIA
#Woldia በወልድያ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ ፤ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎችም ተጥለዋል። ወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ እና ክልከላ ማስቀመጡ ተገልጿል። ክልከላዎቹ ፦ - ጭፈራ ቤቶች፥ ካፍቴሪያዎች፣ ሬስቶራንቶች እና የመሳሰሉት ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም። - ለባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች…
#ኮምቦልቻ
ከዛሬ ጀምሮ ኮምቦልቻ ውስጥ ሰልፍ ማድረግ አድማ መጥራት ተከለከለ ፤ የሰዓት እላፊም ታውጇል።
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ከተወያየ በኋላ ክልከላዎች አውጥቷል።
ምን ክልከላዎች ተጣሉ ?
1ኛ. ከዛሬ ሚያዚያ 3/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሰልፍ ማድረግ አድማ መጥራት ተከልክሏል።
2ኛ. ከተፈቀደላቸው የመንግስት የጸጥታ መዋቅሮች ውጭ ማንኛውም ሰው የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
3ኛ. ከተፈቀደላቸው የመንግስት ተሽከርካሪዎች እና አምቡላንሶች ውጭ ማንኛውም ባለ ሁለትና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ ተከልክለዋል።
4ኛ. የመጠጥእና ምግብ ቤቶችም አገልግሎት መስጠት የሚችሉት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ብቻ ነው ተብሏል።
5ኛ. የሰዎች እንቅስቃሴን በተመለከተ የተርሃዊ ሶላት ከመኖሩ ጋር ተያይዞ እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ብቻ መንቀሳቀስ የተፈቀደ ሲሆን ከ3:00 ሰዓት ውጭ የማንኛውም ግለሰብ እንቅስቃሴ ተገድቧል።
6ኛ. በህግ ከተፈቀደላቸው የጸጥታ መዋቅሮች ውጭ የጸጥታ መዋቅሮችን ልብስ ለብሶ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
ክልከላዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
መረጃው የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ነው።

" ሁለት ሰራተኞቼ ተገድለውብኛል " - CRS CRS ሁለት ሠራተኞቹ አማራ ክልል ውስጥ መገደላቸውን አስታወቀ። የካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት (CRS) ሠራተኞቹ የተገደሉበት ባለፈው እሁድ መሆኑን ባወጣው የሀዘን መግለጫ አሳውቋል። ድርጅቱ ባወጣው የሀዘን መግለጫ ፥ እሁድ ዕለት ከመስክ ሥራ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አማራ ክልል ውስጥ የተገደሉት ሠራተኞች ቹል ቶንግይክ የደኅንነት ኃላፊ እና ሹፌሩ አማረ ክንደያ…
#CRS
ስራ ላይ ከቆዩበት ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ መንገድ ላይ በጥይት ተመተው የተገደሉት የካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት (CRS) ሰራተኞች እነማን ናቸው ?
#ቹኦል_ቶንጎይክ ፦ የድርጅቱ የደህንነት ኃላፊ የነበሩ ሲሆን ባለትዳር እና የ4 ወንድ እና የ1 ሴት ልጅ አባት ነበሩ።
ድርጅቱን በደህንነት ኃላፊነት በታህሳስ 1 /2021 የተቀላቀሉ ሲሆን ወደ ድርጅቱ ከገቡበት ጊዜ አንስቶ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከራስ ወዳድነት ነፃ በመሆን ሲያገልግሉ ነበር።
ቹኦል የድርጅቱ ሰራተኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ 24 ሰዓት ሲሰሩ እንደነበር የገለፀው ድርጅቱ የጀግንነት ስራቸው ሁሌም ሲታወስና ሲዘከር ይኖራል ብሏል።
#አማረ_ክንደያ ፦ ባለትዳር እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ። ድርጅቱን የተቀላቀሉት በጥር 1 /2019 ከመቐለ ቢሮ ነበር።
የተቸገሩ ሰዎችን ያለምንም ማመንታት በመርዳት ወደተፈለገበት ቦታ በማጓጓዝ መስራታቸውን እና የድርጅቱ ሰራተኞች አስፈላጊ ስራዎችን ለማከናወን በየቀኑ በእሱ ላይ ጥገኛ እንደነበሩ ድርጅቱ ገልጿል።
ሁለት ውድ ሰራተኞቹን ያጣው ድርጅቱ መሪር ሀዘን ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፤ ከምንም በላይ ደግሞ ቤተሰቦቻቸው የሚወዷቸውን እንደተነጠቁ የገለፀው ድርጅቱ መፅናናትን ተመኝቶ ሁሉም ሰራተኛ በፀሎት ከእነሱ ጋር መሆናቸውን አሳውቋል።

#AmharaRegion ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ከተማ የሚወስደው መንገድ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ደጀን ከተማ ላይ ተዘግቷል። በዚህ ምክንያት የሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጣል። በዛሬው ዕለት ደግሞ የንግድ እንቅስቃሴ መቆሙ እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መዘጋታቸው ተገልጿል። ጉዳዩን በተመለከተ የከተማው የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ዘውዱ ተከታዩን…
#ደጀን
የደጀን ከተማ ኮሚኒኬሽን ላለፉት ቀናት ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ ዛሬ ጠዋት ከሁለት ሰዓት ገደማ ጀምሮ መከፈቱን አሳውቋል።
መንገዱ መከፈቱን ተከትሎ ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል።
የከተማው ኮሚዩኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ሞኙ ሆዴ አሳየ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ በሰጡት ቃል መንገዱ የተከፈተው፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬ ጠዋት ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ተከትሎ ነው።
በደጀን ከተማ የተለያዩ ቦታዎች መንገድ ለመዝጋት ተቀምጠው የነበሩ ድንጋዮች፤ በመከላከያ ወታደሮች እና በአካባቢው ነዋሪዎች አማካኝነት መነሳቱን የገለፁት ሞጁ ሆዴ ፤ መንገዱ በዶዘር ከተጠረገ በኋላ ክፍት መደረጉን ገልጸዋል።
ዛሬ ጠዋት የከተማዋ መንገድ ሲከፈት እና ድንጋዮች ሲነሱ በነዋሪዎች ዘንድ ተቃውሞ እንዳልነበር አክለዋል።
ቃላቸውን ለድረገፁ የሰጡ አንድ የከተማዋ ነዋሪ፤ " መከላከያው ሲገባ ምንም ተቃውሞ አልነበረም። ቀጥታ ነው የገባው። መንገድ ላይ የሚያገኛቸውን [ድንጋዩን] አንሱት እያለ እያዘዘ ነው ያስነሳው " ብለዋል።
ሌላ ነዋሪ በበኩላቸው " ምንም ችግር ነገር አልነበረም። መንገዱ ሲከፈት ወጣቱ በየመንገዱ ዳር ቆሞ ነበር " ብለዋል።
ለቀናት የተዘጋው መንገድ በመከላከያ ሰራዊት አባላት አማካኝነት መከፈቱን ተከትሎ፤ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ቆሞ የነበረው የደጀን ከተማ የንግድ እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዳግም መጀመሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ከደጀን ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገውን የመንገደኞች ጉዞ አቁሞ የነበረው " ዋልያ " ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ዛሬ ከከተማዋ ወደ አዲስ አበባ አውቶብስ ማሰማራቱ ተሰምቷል።
ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ለሚደረግ ጉዞ የተሳፋሪዎች ትኬት መቁረጥ እንዳልጀመሩ ለማወቅ ተችሏል።
በሌላ በኩል በተቃውሞ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩ ባንኮች ከሰዓት በኋላ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩ የደጀን ኮሚዩኒኬሽን ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ አሳውቋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ ነው።
የፎቶ ባለቤት ፦ የደጀን ፖሊስ

#ደጀን የደጀን ከተማ ኮሚኒኬሽን ላለፉት ቀናት ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ ዛሬ ጠዋት ከሁለት ሰዓት ገደማ ጀምሮ መከፈቱን አሳውቋል። መንገዱ መከፈቱን ተከትሎ ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል። የከተማው ኮሚዩኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ሞኙ ሆዴ አሳየ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ በሰጡት ቃል መንገዱ የተከፈተው፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬ ጠዋት ወደ ከተማዋ መግባታቸውን…
ፖሊስ ስለ " ደጀን መንገድ " መከፈት ምን አለ ?
የደጀን ወረዳ ፖሊስ፤ ተዘግቶ የነበረው የአዲስ አበባ - ደጀን አገር አቋራጭ መንገድ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።
የደጀን ፖሊስ ፤ " በደጀን ወረዳ እና በደጀን ከተማ በፀጥታ ችግር ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የፌደራል መንገድ በመከላከያ ድጋፍ እና በሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ትብብር ከዛሬ 03/08/15 ዓ.ም ከረፋዱ 3:30 ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል " ብሏል።
የወረዳው ፖሊስ " በየትኛውም መንገድ ቢሆን የአገር አቋራጭ መንገድ በመዝጋት ለውጥ ማምጣት ይቻላል ወይ ? " ሲል የጠየቀ ሲሆን " እባካችሁ ህዝባችንን ወደ ድህነት እና ስቃይ ህይወት አንክተተው ! የሚመለከተው ሁሉ ለህግ መከበር የድርሻውን ይወጣ እንላለን ! " ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EOMMarket
ህይወትዎን ቀላልና ዘመናዊ የሚያደርጉ ጥራት ያላቸው እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበት ትልቁ ገበያ 👇
https://t.iss.one/EOMMarket
- የመረጡትን እቃ ይዘዙን፤ያሉበት ድረስ በነፃ እናደርሳለን
𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲 ☞ 0929181818 / 0909868788
ይምጡ የሽያጭ ማእከሎቻችን ይጎብኙ፤ ተደስተው ይመለሳሉ !
አድራሻችን፦
ቁጥር 1:- መገናኛ, ቤተልሄም ፕላዛ የሱቅ ቁጥር G-10 ግራውንድ [ እንደገቡ በስተቀኝ በኩል ]
ቁጥር 2:- ሜክሲኮ, ኬኬር ህንፃ የሱቅ ቁጥር #338
𝕵𝖔𝖎𝖓 𝖔𝖚𝖗 𝖈𝖍𝖆𝖓𝖓𝖊𝖑 : @EOMmarket