TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።

ፓርቲው በዛሬው መግለጫ የብልጽግና ፓርቲ ትናንት ሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ላወጣው መግለጫ ምላሽ ሰጥቷል።

ብልፅግና ትላንት ባወጣው መግለጫ የክልል ልዩ ኃይል ፖሊሶችን ' መልሶ የማደራጀት ' ውሳኔ በብዙ ጥናት፣ በጥልቅ ውይይት፣ በሰከነ ንግግር እና በጋራ መግባባት የተደረሰበት ውሳኔ መሆኑን ገልጿል።

ልዩ ኃይልን ትጥቅ የማስፈታት ሳይሆን የተሻለ የማስታጠቅ ፤ የመበተን ሳይሆን በጠንካራ መሰረት ላይ የማደራጀት ሥራ ላይ መሆኑን ብልፅግና ገልጿል።

የልዩ ኃይል አባላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የተለየ አክብሮት እና ፍቅር እንዳለው፤ ውሳኔው በአማራ ክልል ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተመሳሳይ የጊዜ መስመር የሚተገበር መሆኑን በትላንት መግለጫው አሳውቋል።

አብን ፤ የብልጽግና ፓርቲ ያወጣው መግለጫ እውነታን የካደ እና አሁንም ገዥው ፓርቲ ለመፍትሄው ዝግጁ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው ብሎታል።

ገዥው ፓርቲ ውሳኔው በአማራ ክልል ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተመሳሳይ የጊዜ መስመር የሚተገበር ነው ቢልም ከአማራ ክልል በቀር በየትኛውም ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላትን ትጥቅ የማስፈታት ወይም በገዥው ፓርቲ አነጋገር “መልሶ የማደራጀት” እንቅስቃሴ አልተደረገም ሲል ገልጿል።

አብን " ገዥው ፓርቲ ሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የተስማሙበት ውሳኔ ነው እያለ ቢሰነብትም ፣ የአማራ ክልልን ጨምሮ የየትኛውም ክልል ካቢኔ ወይም ምክር ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ ያደረገው ውይይት ሆነ ያሳለፈው ሕጋዊ ውሳኔ የለም " ብሏል።

ለዚህም ፓርቲው ማስረጃዎች ያላቸውን እንደሚከተለው አቅርቧል ፦

- የማስፈጸሚያ እቅድ ነው የተባለው ሰነድ በፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ደረጃ ውይይት የተደረገበት በቀን 30/07/2015 ዓ.ም ነው።

- የሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈው በቀን 02/08/2015 ዓ.ም መሆኑ መገለጹ፣ ገዥው ፓርቲ ያወጣው መግለጫ እውነትነት የራቀው መሆኑን የሚያጸና ነው ብሏል።

ገዥው ፓርቲ የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የተለየ አክብሮት እና ፍቅር እንዳለው ቢገልጽም በአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ላይ የተደረገው እና የሆነው ግን የመግለጫውን ቃል ከምጸት የሚያስቆጥረው ነው ብሎታል።

አብን የአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላት ከፍተኛ አመራሮች ፣ የብርጌድ እና የክፍለጦር አዛዦች በድንገት ከሥራ ውጭ መደረጋቸውን ፤ የልዩ ኃይሉ የእዝ ሰንሰለት እንዲፈርስ መደረጉን፣ የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት ስንቅ ፣ ሎጂስቲክ እና ደሞዝ ተነፍገው ለርሃብ እና ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸው እና ከካምፕና ከግዳጅ ምድብ ቦታቸው እህል ውሃ ወደሚያገኙበት ቦታ ለመድረስ በርካታ መቶ ኪሎሜትሮችን በእግራቸው ለመጓዝ የተገደዱበት ሁኔታ መስተዋሉን ገልጿል።

አብን ፓርቲ፤ የገዥውን ብልፅግና ፓርቲ ውሳኔ በመቃወም የክልሉ ሕዝብ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተቃዉሞ እያሰማ መሆኑን አመልክቷል።

በብልፅግና የተሳሳተ ውሳኔ ምክንያትም ላለፉት በርካታ ቀናት በአማራ ክልል ፦
- መደበኛ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለዋል
- በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ የጸጥታ መደፍረስ የሰው ህይወት አልፏል
- የክልሉ ዋና ዋና ከተሞች የቀውስ አስተዳደር ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ተገደዋል ሲል አሳውቋል።

አብን ፓርቲ የፌደራል መንግስት እና የአማራ ክልል መንግስት የክልሉ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ያቀረበውን ጥያቄ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ደብረብርሃን

ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ መግቢያ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን የደብረ ብርሃን ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ በዚህ አይነት መንገድ ሰዎች ይጎዳሉ፣ ንፁሃን ይሞታሉ ፣ በአካባቢውም ተማሪዎች ይኖራሉና አስቸኳይ መፍትሄ ሊፈለግ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሌላኛው የደብረብርሃን ቤተሰባችን የሚመለከተው አካል ሁሉ ችግሮች አሁን ካሉበት ተባብሰው የሰዎችን ህይወት እንዳይቀጥፉ የሚቻላቸውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው ፤ የአማራ ክልል አካባቢዎች ከዚህ በፊት በነበረው አስከፊ ጦርነት ብዙ ዋጋን የከፈሉ በመሆናቸው አሁንም ተጨማሪ የንፁሃን ሞት ፣ መፈናቀል ፣ ጉዳት እንዳይፈጠር በሰከነ መንገድ መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
" ሁለት ሰራተኞቼ ተገድለውብኛል " - CRS

CRS ሁለት ሠራተኞቹ አማራ ክልል ውስጥ መገደላቸውን አስታወቀ።

የካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት (CRS) ሠራተኞቹ የተገደሉበት ባለፈው እሁድ መሆኑን ባወጣው የሀዘን መግለጫ አሳውቋል።

ድርጅቱ ባወጣው የሀዘን መግለጫ ፥ እሁድ ዕለት ከመስክ ሥራ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አማራ ክልል ውስጥ የተገደሉት ሠራተኞች ቹል ቶንግይክ የደኅንነት ኃላፊ እና ሹፌሩ አማረ ክንደያ እንደሚባሉ ገልጿል።

ሠራተኞቹ በድርጅቱ ተሽከርካሪ እየተጓዙ እንዳለ በጥይት መገደላቸውን የገለፀው ድርጅቱ  ግድያውን የተመለከተ የሚታወቅ ዝርዝር መረጃ እንደሌለ ባወጣው የሀዘን መግለጫ ላይ አመልክቷል።

የተገደሉበት ሁለቱ ሠራተኞች ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳሉ መገደላቸውን እንጂ በትክክል የት ቦታ ጥቃቱ እንደተፈጸመባቸው ያለው ነገር የለም።

መረጃውን የካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት (CRS)ን ዋቢ በማድረግ የዘገበው ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#ATTENTION

በአማራ ክልል ፤ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር ጥብቅ ክልከላዎች ተጣሉ።

የኦሮሞ ዞን ኮማንድ ፖስት ምን ክልከላዎችን ጣለ ?

- የሰአት እላፊ ገደብ (ባጃጅ 1:00፤ የሰው እንደ አካባቢና እንደ ሚፈጠር ችግር ይወሰን ፆም በመሆኑ ተብሏል) ።

- ስምሪት ከተሰጠው ሃይል ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተገልጿል።

- በማንኛውም ሆቴል መሳሪያ ይዞ መግባት የተከለከለ ሲሆን ፤ በሁሉም ሆቴሎች ፍተሻ እንዲጠናከር ታዟል።

- የፀጥታ ሃይሉን መጠርነፍና ለግዳጅ ዝግጁ ማድረግ ፖሊስና ሚሊሻ ፤ ከፌደራልና መከላከያ ጋር በቅንጅት መስራት አለባቸው ተብሏል።

- የኬላ ላይ ፍተሻ እንዲጠናከር ታዟል።

- የህዝብ ግንኙነት ስራ በተደጋጋሚ እንዲሰራ ታዟል ፤ በዋናነት በመስመር መዝጋት እየተጎዳ ያለው ህዝብ መሆኑ ተመላክቷል።

- ህብረተሰቡ በቀበሌ፣ በመንደር፣ በሰፈር፣ በኬላ፣ በተቋማት ጥበቃ ላይ ተደራጅቶ አካባቢውን የመጠበቅና ለሰላም ለሚከፈል ዋጋ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ታዟል።

- የተሳሳተ መረጃ የሚነዙ፣ በአሉቧልታ ህዝብን የሚያሸብሩ፣ ወንጀለኞችን ለመንግስት አጋልጦ እንዲሰጥ ሁሉም በጥብቅ ተማምኖ መንቀሳቀስ አለበት ተብሏል።

- ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እንዲደረግ ፤ በየደረጃው ያለው አመራርና ህዝቡ ከፀጥታ ማዋቅሩ ጋር መረጃ መለዋወጥ እንዳለበት ታዟል።

- የመንግስት ተቋማት፣ ባንኮችን ፣ የሀይማኖት ተቋማትን የጥበቃ ሁኔታን እንዲጠናከር ታዟል።

- የአካባቢውን ሁኔታና የዞኑን ክልከላ በማይጣረስ መንገድ ተጨማሪ ክለከላዎችን በወረዳና ከተማ አስተዳደር ኮ/ፖስት ማወጅ እንደሚቻል ተገልጿል።

መረጃው የኦሮሞ ዞን ኮማንድ ፖስት ነው።

@tikvahethiopia
#Mekelle

በዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑክ መቐለ ገባ።

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ዛሬ መቐለ ገብቷል።

ልዑኩ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገር ይጠበቃል።

ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

አፖሎ የሞባይል መተግበሪያን ተጠቅመው ከዲጂታል አካውንትዎ የዲኤስቲቪ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም ኢንተርኔት እና ሌሎች ክፍያዎችዎን በቀላሉ መፈፀም ይችላሉ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።

https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#ኢትዮ_ቴሌኮም

ለትንሳኤ በዓል ከባህር ማዶ ከወዳጅ ዘመድ በአጋሮቻችን #Talkremit #Worldremit #Azimo #MasterRemit #Majority #Moneytrans #Remitly #ria #Taptapsend በኩል የሚላክልዎትን ገንዘብ ያለ ውጣ ውረድ እና እንግልት ባሉበት ሆነው በቴሌብር ሲቀበሉ የተላከልዎትን ገንዘብ መጠን 5% እንዳሻዎ ለማንኛዉም ክፍያ ሊጠቀሙ የሚችሉበት የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ!

ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ

ቴሌብር ሃዋላ የሩቁን ያቀርባል!
መልካም በዓል
#Update

አማራ ክልል ከ " ክልል ልዩ ኃይል " ጋር በተያያዘ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን ለማውቅ ተችሏል።

ከቀናት በፊት አንስቶ በተነሳው ተቃውሞ ክቡር የሆነው የሰዎች ህይወት አልፏል፣ አካላዊ ጉዳት ደርሷል፣ የንግድ እንቅስቃሴ ተቋርጧል፣ ትራንስፖርት እና መሰረታዊ አገልግሎት ለማግኘት ችግር ሆኗል።

ዛሬ በክልሉ መዲና ባህር ዳር ተቃውሞው ቀጥሎ መዋሉ በኮምቦልቻ ከተማ በነበረ ተቃውሞ ደግሞ የሰዎች ህይወት መጥፋቱን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።

አንድ የኮምቦልቻ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ " ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ከፀጥታ ሀይሎች ጋር ተጋጭተው የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል " ብሏል።

እስካሁን በአማራ ክልል ከመንግሥት ተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በተለያዩ አካባቢዎች የሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ አዳጋች ሆኗል።

የክልል ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀትን በተመለከተ መንግስት እንዲሁም የተቃዋሚ ኃይሎች በየፊናቸው የተለያዩ መግለጫዎችን እያወጡ ይገኛሉ።

የአማራ ክልል ነዋሪዎች ፤ የመንግሥትን ውሳኔ አጥብቀው እየተቃወሙ ያሉት ልዩ ኃይል የአማራ ህዝብ ዋስትና እንደመሆኑ የተወሰነው ውሳኔ ተገቢ አይደለም ፣ የህዝቡ ደህንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ይህ ውሳኔ መወሰኑ ተቀባይነት የለውም ፣ ሌሎች ለአማራ ህዝብ የደህንነት ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቡድኖች ትጥቅ ሳያወርዱ ልዩ ኃይሉን ለመበተን መወሰን ፍፁም ተገቢነት የሌለው ውሳኔ ነው በሚል ነው።

ፎቶ ፦ ዛሬ በባህርዳር ቀበሌ 8 ዊዝደም እና ቀበሌ 7 ስላሴ አካባቢ የነበረው ሁኔታ  (ላሎ - ባህርዳር - ቲክቫህ ቤተሰብ) ።

@tikvahethiopia
#Woldia

በወልድያ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ  ፤ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎችም ተጥለዋል።

ወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ እና ክልከላ ማስቀመጡ ተገልጿል።

ክልከላዎቹ ፦

- ጭፈራ ቤቶች፥ ካፍቴሪያዎች፣ ሬስቶራንቶች እና የመሳሰሉት ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

- ለባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00  ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ፤ ከተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ለጸጥታ ሥራ ከተመደቡ ተሽከርካሪዎች ውጭ በዚህ ምደባ ስምሪት ያልታቀፉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2:00 እስከ ጧቱ 12:00  ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።

- የሰው እንቅስቃሴ ለጸጥታ ሥራ ከተመደበው ሰው ውጭ ከምሽቱ 3:00 እስከ ጧቱ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በማንኛውም ቦታና ጊዜ ለጸጥታ ሥራ ስምሪት ከተመደበ አካል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ሥራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

- የመንግሥትን የታጠቀ ኀይል ያስከዳ፣ በተለያየ መንገድ አማሎ የጦር መሳሪያ የገዛ፣ የለወጠ፣ ባልተገባ መንገድ መታወቂያ የሰጠ፣ መንገድ የመራ ማንኛውም አካል በሕግ ተጠያቂ ይሆናል ተብሏል።

- የመንግሥት የጸጥታ ኀይል ሕግና ስርዓትን ለማስከበር በሚያከናውናቸው ተግባሮች ዙሪያ ማንኛውም ሰው የመተባበር ግዴታ ተጥሎበታል ፤ የማይተባበር በሕግ ይጠየቃል ተብሏል።

የኮማንድ ፖስቱ በአብዛኛውን በሌሎች ከተማዎች የተጣሉ ክልከላዎችን አይነት ይዘት ያለው ክልከላ ነው የጣለው። (#ሙሉ ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል)

ኮማንድ ፖስቱ ይህ ውሳኔ የተላለፈባቸው ምክንያቶች ፦ በከተማው የተጀመሩ ልማቶችን " አመጹን መቀላቀል ሲገባህ ልማትን እያስቀጠለክ " በሚል ዛቻ ልማትን የማደናቀፍ ፤ በሙስና፥ በሌብነት፥ እና በተለያዩ ብልሹ ወንጀሎች ስጋት ያለባቸው አካላት የዕለት ጉርስ ፈላጊዎችን በገዘብ በመግዛት ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠርና ለማባባስ የሚያደርጉት ሙከራ በመረጃ ደረጃ የተገኘ በመሆኑ ነው ብሏል።

ከዚህ ባለፈ የትንሳኤ እና የረመዳን ሃይማኖታዊ ሁነቶችን በሰላም ለማጠናቀቅ ለዕኩይ ዓላማ የተሰማሩ ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠር ነው ሲል አሳውቋል።

(የወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Woldia በወልድያ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ  ፤ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎችም ተጥለዋል። ወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ እና ክልከላ ማስቀመጡ ተገልጿል። ክልከላዎቹ ፦ - ጭፈራ ቤቶች፥ ካፍቴሪያዎች፣ ሬስቶራንቶች እና የመሳሰሉት ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም። - ለባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች…
#ኮምቦልቻ

ከዛሬ ጀምሮ ኮምቦልቻ ውስጥ ሰልፍ ማድረግ አድማ መጥራት ተከለከለ ፤ የሰዓት እላፊም ታውጇል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ከተወያየ በኋላ ክልከላዎች አውጥቷል።

ምን ክልከላዎች ተጣሉ ?

1ኛ. ከዛሬ ሚያዚያ 3/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሰልፍ ማድረግ አድማ መጥራት ተከልክሏል።

2ኛ. ከተፈቀደላቸው የመንግስት የጸጥታ መዋቅሮች ውጭ ማንኛውም ሰው የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

3ኛ. ከተፈቀደላቸው የመንግስት ተሽከርካሪዎች እና አምቡላንሶች ውጭ ማንኛውም ባለ ሁለትና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ ተከልክለዋል።

4ኛ. የመጠጥእና ምግብ ቤቶችም አገልግሎት መስጠት የሚችሉት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ብቻ ነው ተብሏል።

5ኛ. የሰዎች እንቅስቃሴን በተመለከተ የተርሃዊ ሶላት ከመኖሩ ጋር ተያይዞ እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ብቻ መንቀሳቀስ የተፈቀደ ሲሆን ከ3:00 ሰዓት ውጭ የማንኛውም ግለሰብ እንቅስቃሴ ተገድቧል።

6ኛ. በህግ ከተፈቀደላቸው የጸጥታ መዋቅሮች ውጭ የጸጥታ መዋቅሮችን ልብስ ለብሶ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

ክልከላዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

መረጃው የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሁለት ሰራተኞቼ ተገድለውብኛል " - CRS CRS ሁለት ሠራተኞቹ አማራ ክልል ውስጥ መገደላቸውን አስታወቀ። የካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት (CRS) ሠራተኞቹ የተገደሉበት ባለፈው እሁድ መሆኑን ባወጣው የሀዘን መግለጫ አሳውቋል። ድርጅቱ ባወጣው የሀዘን መግለጫ ፥ እሁድ ዕለት ከመስክ ሥራ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አማራ ክልል ውስጥ የተገደሉት ሠራተኞች ቹል ቶንግይክ የደኅንነት ኃላፊ እና ሹፌሩ አማረ ክንደያ…
#CRS

ስራ ላይ ከቆዩበት ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ መንገድ ላይ በጥይት ተመተው የተገደሉት የካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት (CRS) ሰራተኞች እነማን ናቸው ?

#ቹኦል_ቶንጎይክ ፦ የድርጅቱ የደህንነት ኃላፊ የነበሩ ሲሆን ባለትዳር እና የ4 ወንድ እና የ1 ሴት ልጅ አባት ነበሩ።

ድርጅቱን በደህንነት ኃላፊነት በታህሳስ 1 /2021 የተቀላቀሉ ሲሆን ወደ ድርጅቱ ከገቡበት ጊዜ አንስቶ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከራስ ወዳድነት ነፃ በመሆን ሲያገልግሉ ነበር።

ቹኦል የድርጅቱ ሰራተኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ 24 ሰዓት ሲሰሩ እንደነበር የገለፀው ድርጅቱ የጀግንነት ስራቸው ሁሌም ሲታወስና ሲዘከር ይኖራል ብሏል።

#አማረ_ክንደያ ፦ ባለትዳር እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ። ድርጅቱን የተቀላቀሉት በጥር 1 /2019 ከመቐለ ቢሮ ነበር።

የተቸገሩ ሰዎችን ያለምንም ማመንታት በመርዳት ወደተፈለገበት ቦታ በማጓጓዝ መስራታቸውን እና የድርጅቱ ሰራተኞች አስፈላጊ ስራዎችን ለማከናወን በየቀኑ በእሱ ላይ ጥገኛ እንደነበሩ ድርጅቱ ገልጿል።

ሁለት ውድ ሰራተኞቹን ያጣው ድርጅቱ መሪር ሀዘን ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፤ ከምንም በላይ ደግሞ ቤተሰቦቻቸው የሚወዷቸውን እንደተነጠቁ የገለፀው ድርጅቱ መፅናናትን ተመኝቶ ሁሉም ሰራተኛ በፀሎት ከእነሱ ጋር መሆናቸውን አሳውቋል።

@tikvahethiopia