TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መንግስት ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት የጀመረውን ተግባር የሚቃወሙ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ዛሬም መቀጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ዛሬ በጎንደር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን የሰልፉ ተካፋዮች " የአማራ ልዩ ኃይል ለአማራ ህዝብ የጀርባ አጥንት ነው ፤ " የእርስቶቻችን ጉዳይ ለአፍታ የምንረሳው አይደለም " የሚሉና ሌሎችም መልዕክቶችን በማስተላለፍ የመንግሥትን ተግባር ተቃውመዋል።

በላሊበላ ከተማ በተመሳሳይ " የአማራ ልዩ ኃይል የጀርባ አጥንታችን ነው፤ ከልዩ ኃይል ላይ እጃችሁን አንሱ " በሚል የመንግሥትን ውሳኔ የሚቃወሙ መልዕክቶች የተላለፉበት ሰልፍ መደረጉ ተሰምቷል።

ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያዎች

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ዛሬ እሁድ ባወጣው መግለጫ መንግሥት ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘ ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ በመግፋቱ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ መቀስቀሱን ገልጿል።

ፓርቲው እስካሁን ድረስ ለሀገራዊ አንድነት እና ሰላም ሲባል ጉዳዩን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ሲከታተል መቆየቱን ገልጾ ይሁንና መንግስት ችግሩን በሰከነ መንገድ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ከዕለት ወደ ዕለት የለየለት የኃይል ፣ የአፈና እና የማደናገር አማራጭ እየገባ መሆኑን መረዳቱን አመልክቷል።

" መንግስት ችግሩን በሰከነ መንገድ ፣ በውይይት ፣ በጋራ መግባባት እና በመተማመን የመፍታት ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም በስህተት ላይ ሌላ ስህተት እየደረበ እና ችግሩን በአፈና እና በጉልበት ለመፍታት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዛሬ ጀምሮ ለችግሩ ዘላቂ እልባት እስከሚሰጥ ድረስ መንግስት እና ግብረ-አበሮቹ በአማራ ልዩ ኃይል ፣ በፋኖ እና በአጠቃላይ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚነዟቸውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳዎች በይፋና በተከታታይ አጋልጣለሁ " ብሏል።

አብን በመግለጫው የአማራ ልዩ ኃይልን ለማፍረስ እና ትጥቅ ለማስፈታት መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ እና የሚያደርገው እንቅስቃሴ ኃላፊነት የጎደለውና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ድጋሜ አሳውቋል።

የብልፅግና ፖርቲ ሥራ አስፈፃሚ ያሰፈው ውቃኔ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ ያላገናዘበ ፣ መርኅ አልባ ፣ አድሏዊ እና አምባገነናዊ ነው ሲል ገልጾታል።

ውሳኔውና የአፈፃፀም ሂደቱ በሕግ አግባብ የተመራ ፣ መርኅ ተኮር እንደሆነ ፣ ውይይት እንደተደረገበት እና መግባባት የተደረሰበት እንደሆነ ለማስመሰል የሚቀርቡ አስተያየቶችም በአጠቃላይ ሃሰት ናቸው ብሏል።

(የአብን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
" ሳይገባቸው የሚቃወሙትን ለማስረዳትና ለማሳመን ጥረት እናደርጋለን። ሆን ብለው የአፍራሽነት ሚና በሚጫወቱት ላይ ደግሞ ተገቢው የሕግ ማስከበር እርምጃ እንወስዳለን " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከዚህ በኋላ ክልሎች የፖሊስ ኃይላቸውን አጠናክረው ወንጀልን በመከላከልና አካባቢያዊ ጸጥታን በማስከበር ላይ ብቻ ያተኩራሉ አሉ።

ይህን ያሉት ዛሬ የልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀትን በተመለከተ ባወጡት መግለጫ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ከአሁን በኃላ ክልሎች የፖሊስ ኃይላቸውን አጠናክረው ወንጀልን በመከላከልና አካባቢያዊ ጸጥታን በማስከበር ላይ ያተኩራሉ ፤ ከየትኛውም ኃይል የሚሰነዘር፣ የሀገርን ድንበር ህልውናና ሉዓላዊነት የሚዳፈር ኃይል ሲነሣ ደግሞ የመከላከያ ሠራዊቱ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

ለዚህ የሚሆን አደረጃጀትም በተግባር ላይ ውሏል ሲሉ አሳውቀዋል።

" የክልሎች ፉክክርና ትብብር በልዩ ኃይል ግንባታ ሳይሆን በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ ልማትና በዴሞክራሲያዊ ባህል ላይ ይሆናል " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " ይህ ውሳኔም ለኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ለሕዝቡ ሰላም ሲባል ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን ተግባራዊ ይደረጋል። " ብለዋል።

" ሳይገባቸው የሚቃወሙትን ለማስረዳትና ለማሳመን ጥረት እናደርጋለን። " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ሆን ብለው የአፍራሽነት ሚና በሚጫወቱት ላይ ደግሞ ተገቢው የሕግ ማስከበር እርምጃ ይወሰዳል። ለዚህም በቂ ዝግጅት ተደርጓል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የሚመለከታቸው ተቋማትና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ ፤ የውሳኔውን ሃገራዊ ፋይዳና የሚያስገኘውን ዘላቂ ጥቅም ከግምት በማስገባት ለተግባራዊነቱ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

(ሙሉ መግለጫቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Update

የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ ፤ የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም አሉ።

ይህን ያሉት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ምን አሉ ?

- በሀገር ደረጃ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ልዩ ኃይሎችን በፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ለማደራጀት ተወስኖ ወደ ትግበራ ተገብቷል።

- ውሳኔው በፌዴራል መንግሥት እና በክልል መንግሥታት ስምምነት የተወሰነ ሲሆን በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ይደረጋል።

- በአማራ ክልል ውሳኔውን ለመተግበር እየተሠራ ነው። ይህንን በተመለከተ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተወይይተናል።

- በአፈጻጸም ላይ በታየ ክፍተት እና በተነዛው ፕሮፖጋንዳ ችግሮች ተከስተዋል። ችግር እንኳን ቢኖር ተወያይቶ መፍታት ይቻላል።

- አብዛኛው የልዩ ኃይል አባል ውይይቱን አጠናቆ ውሳኔውን በካምፕ ሆኖ እየተጠባበቀ ነው።

- ልዩ ኃይሉ ትጥቅ የሚፈታና የሚበተን አይደለም ፤ በላቀ አደረጃጃት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል ነው።

- ልዩ ኃይሉ ዓላማውን ተገንዝቦ ለበለጠ ተልእኮ ሊዘጋጅ ይገባል።

- የአማራ ሕዝብ በሁኔታው #ቅሬታ ውስጥ ገብቷል።ቅሬታው የመነጨው በተሟላ መንገድ ለሕዝቡ መረጃ ባለመድረሱ ነው።

- አደረጃጀቱ የሚደገፍ፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የሀገርን አንድነት የሚያረጋግጥ ነው።

- አደረጃጀቱ የአማራን ክልል በተለየ መንገድ የሚጎዳ አይደለም።

- የአማራ ክልልን ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የታለመ ዓላማ የለም።

- በተፈጠረ የመረጃ ክፍተት በአንዳንድ ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ፣ የአድማ ጥሪ እና የሰዎች እና የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴን የመገደብ አዝማሚያዎች እያታዩ ናቸው። አላስፈላጊ አካሄዶች አውዳሚ እና አክሳሪ እንጂ አትራፊ አይደሉም።

- የአማራ ክልል በጦርነት የከረመ ክልል ነው ፤ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ተጎሳቁሏል፣ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳው ኅብረተሰብ እና መሠረተ ልማት ገና ማገገም አልቻለም ፤ ከአንደኛው ችግር ሳናገግም ወደ ሌላ ችግር መሸጋገር ሕዝቡን መጉዳት ነው።

- በመወያየት አላስፈላጊ ጉዳዮችን ማስቆም ይቻላል ፤ ሁሉም አውዳሚ የሆነውን ጉዳይ መከላከል ይገባዋል።

- ግጭት እንዳይፈጠር ወጣቶች እና የሃይማኖት አባቶች የሚመሰገን ሥራ እየሠሩ ናቸው።

- የአማራ ክልል ሕዝብ ጉዳዩን በውል በማጤን፣ በመመካከር እና ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ በማሰብ ማስከን ይገባል።

- የአማራ ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ የሚጎዳ ውሳኔ አልተወሰነም፣ ወጥና ሀገራዊ ውሳኔ ነው የተደረገው፣ በሁሉም ክልል የሚፈጸም ነው፣ ውሳኔው ለሀገር ግንባታ ታላቅ አስተዋጽዖ አለው።

- ከወቅታዊ ጉዳይ አንጻር የሚነሳው ጥያቄ ትክክል ቢሆንም አፈጻጸሙ ለሀገር የሚጠቅም መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

- ከካምፕ የወጡ የልዩ ኃይል አባላት እንዲመለሱ ማድረግ ይገባል።

- የአማራ ሕዝብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ ማየት አለበት ፤ ችግሩ ዳር ወጥቶ ግጭት እንዳይከሰት እያደረጉ ላሉ አካላት ምስጋና ይገባል።

- የልዩ ኃይል አባላት ትጥቅ አትፈቱም፣ የምትበተኑበት ነገር የለም፣ ወደ ላቀ ተልእኮ ነው የምትሸጋገሩት።

- በመደማመጥ ችግሮቻችን እንፈታለን፣ የአማራን ጥያቄዎች እናስመልሳለን።

#AMC

@tikvahethiopia
#ሲዳማ

የ " በላይነህ ክንዴ ግሩፕ "  በሲዳማ ክልል በሎካ አባያ ወረዳ 550 ሔክታር መሬት ተረክቦ በፍራፍሬ እና በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በመመደብ ልማት መጀመሩን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የእርሻ ዘርፍ አስፈጻሚ ዶ/ር አንተነህ አብዋ ለሪፖርተር ጋዜጣ  በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ዶ/ር አንተነህ አብዋ ምን አሉ ?

- በሲዳማ ክልል ሎካ አባያ ወረዳ 550 ሔክታር መሬት ተረክበረን 380 ሔክታር መሬት ላይ አትክልት ከማልማት አስቀድሞ የበጋ ስንዴ እያለማን እንገኛለን ፤ ምርታችንን ለውጭ ገበያ ለማቅረብም አቅደናል።

- በሔክታር ከ30 እስከ 50 ኩንታል ለምግብ ፍጆታ የሚውል ስንዴ ለማልማትና ከዚህም በጥቂቱ ከ11,400 በላይ ኩንታል ስንዴ ለመሰብስብ ታቅዷል። ለዚህም ከ600 በላይ ኩንታል ስንዴ ለዘር ተጠቅመናል።

- ለስንዴና ማዳበሪያ ግዥ ከ300 እስከ 400 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርገናል። 400 ኩንታል ኤንቲኤስ፣ እንዲሁም 400 ኩንታል ዩሪያ መሬቱን ለማሰናዳት ማዳበሪያ ተጠቅመናል።

- የእርሻ ልማቱን ለማከናወን በአጠቃላይ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል፤ ከ20 ኪሎ ሜትር መንገድ እንዲሁም ወደ እርሻው የሚፈሰውን የወንዝ ውኃ ለመቆጣጠር 4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ግድብ ተገንብቷል።

-  የአባያ ሐይቅና የብላቴ ወንዝን ለእርሻው በዋነኛነት እንጠቀማለን፤ ለዚህም ዘመናዊ ፓምፖችን ለመጠቀም ተሰናድተናል።

- በአካባቢው የዝናብ እጥረት ያለበት አካባቢ በመሆኑ ከአባያ ሐይቅ እስከ እርሻው መዳረሻ ድረስ ሦስት ኪሎ ሜትር ያለውን ርቀት በፓምፕ ስቦ ለማምጣት መሠረተ ልማት ተዘርግቷል።

- የበጋ ስንዴ ማልማቱ ሲጠናቀቅ የአትክልትና የፍራፍሬ ልማቱ ይቀጥላል ፤ አቮካዶ፣ ሙዝና ፓፓዬ ለማልማት የችግኝ ግዥ ተፈጽሞ ለመትከል ዝግጅት ላይ ነን።

- መሬቱን ከተረከብን 4 ወራት ብቻ  ሲሆን አትክልትና ፍራፍሬ ማልማቱንም ለማስቀጠል ከ40 ሔክታር መሬት በላይ አቮካዶ ተተክሏል። በቀሪዎቹ ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ እንዲሁም ፓፓዬ ለማልማት ታቅዷል። በዚህ መሬት ላይ ተጨማሪ ፍራፍሬዎችን ለማሰናዳት የችግኝ ማፍላት ሥራ እየተሰራ ነው። ለጊዜው ለ200 የአካባቢው ሠራተኞች፣ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፤ ይኼም ቁጥር ወደ 500 ለማሳደግ ታቅዷል።

በሌላ በኩል ፤ በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር በአካባቢው ለምትገኘው #መራሬ_ከተማ #የውኃ እና #የኤሌክትሪክ_ኃይል ለመዘርጋት የኮንክሪትና የእንጨት ፖል ዝርጋታ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

መንግስት ከክልል ልዩ ኃይል ጋር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ዛሬም ለተከታታይ ቀን መቀጠሉ ለማውቅ ተችሏል።

ዛሬ በደሴ ከተማ ፣ በእንጅባራ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉ ለማወቅ ተችሏል።

ሰልፉ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መፍረስን የሚቃወሙ የተለያዩ መልዕክቶች የተስተጋቡበት ነበር።

በተለይም ፤ " ልዩ ኃይሉ የአማራ ህዝብ ጠባቂ ነው የአማራ ህዝብ ደህንነቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ይህ ውሳኔ መወሰኑ ተገቢ አይደለም " በሚል የሰልፉ ተካፋዮች የመንግሥትን ውሳኔ በመቃወም ሀባቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪ ሌሎች የታጠቁ አካላት ትጥቅ ሳያወርዱ የክልሉን ህዝብ ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ ይህን አይነት ውሰኔ መወሰኑ ተቀባይነት እንደሌለው ነው ያመለከቱት።

ስለዚህም መንግሥት ውሳኔውን እንዲያጤነውና እንዲቀለብሰውም ተጠይቋል።

የፌዴራል መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት ውሳኔ አሳልፎ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል።

ይህ ውሳኔ ለሀገር ሉዓላዊነት እና አብሮነት ሲባል በሁሉም ክልል በተመሳሳይ ወቅት የሚፈፀም እንደሆነም መንግሥት ገልጿል።

የአማራ ክልል መንግሥት በበኩሉ የአማራ ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ እንደሌለ በመግለፅ ክልሉ የተወሰነውን ውሳኔ ለመተግበር እየሰራ እንደሆነ አመልክቷል።

በአፈፃፀም ላይ ክፍተት እየታየ መሆኑን የሚገልፀው ክልሉ ፤ እየተነዛ ባለው ሀሰተኛ ፕሬፖጋንዳ  ችግሮች መከሰታቸውን ገልጿል።

በአማራ ህዝብ ዘንድ ቅሬታን የፈጠረው ሁኔታ የመነጨው በተሟላ መንገድ ለህዝብ መረጀ ባለመድረሱ ስለመሆኑ የአማራ ክልል መንግሥት አሳውቋል።

ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
#GONDAR

በጎንደር ክልከላዎች ተጣሉ።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ክልከላዎችን አስቀመጠ።

ኮማንድ ፖስቱ ፤ ክልከላው " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል " የተቀመጠ መሆኑን ገልጿል።

የተቀመጡ ክልከላዎች ምንድናቸው ?

1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት ተከልክለዋል።

2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ ተከልክለዋል።

3. ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

4. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

5. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ ተከልክሏል።

6. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ ተከልክሏል።

7. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦
- የልዩ ኃይል ፣
- የፓሊስ ፣
- የመከላከያ ሠራዊት ፣
- የፌዴራል ፓሊስ ልብስ መልበስ በጥብቅ ተከልክሏል።

9. ያልተፈቀዱ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት ተከልክሏል።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስተው ወደ ከተማው የመጡ በከተማው በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንዲሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተለልፏል። ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ ተከልክሏል።

12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ  ይጠየቃል።

መረጃው የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ልክ ጎንደር እንደተደረገው በደብረብርሃን ከተማም ክልከላዎች ተጣሉ።

ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ #ህጋዊ_መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል ተብሏል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ " እንዲቻል በሚል ክልከላዎችን መጣሉን አሳውቋል።

ክልከላዎቹ ምንድናቸው ?

1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት ተከልክለዋል።

2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00  ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

3. በከተማ አስተዳደሩ ለጸጥታ ማስከበር ተልዕኮ ከተሠጠው   የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

4. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

5. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ ተከልክሏል።

6. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ ተከልክሏል።

7. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ ተከልክሏል የልዩ ኋይል ፣ የፓሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት ፣ የፌዴራል ፓሊስ ልብስ መልበስ ተከልክሏል።

9 . ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ያልተፈቀደ ሰልፍ ማድረግ ፣ መንገድ መዝጋት  ተከልክሏል።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስተው ወደ ከተማው የገቡ በከተማው በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንዲሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተላልፏል። ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ ተከልክሏል።

12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ  እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል ተብሏል።

13. በከተማው ውስጥ ህጋዊ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል።

14. በከተማው በተፈናቃይ ካምፕ የምትገኙ ተፈናቃይዎች በማንኛውም ሰአት ወቅታዊ ሁኔታው እስከሚስተካከለ ድረስ ከካምፕ ውጭ መገኘት ፈጽሞ ተከልክለዋል።

መረጃው ደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የጸጥታው ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት ነው።

@tikvahethiopia