TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን " ኢፍጣራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚሁ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተገኝቶ ስነስርዓቱን እየታደመ ነው። @tikvahethiopia
#AddisAbaba

የዘንድሮው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።

የዘንድሮው ኢፍጧር ስነስርዓት " ኢፍጧራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን እጅግ ከፍተኛ የሆነ ምዕመን ስነስርዓቱን ታድሟል።

በሌላ በኩል ፥ የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢፍጧር ፕሮግራሙ #በሰላም_መጠናቀቁን አሳውቋል።

ለፕሮግራሙ በሰላም መጠናቀቅ የከተማው ነዋሪ በተለይም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር ማድረጉን ፖሊስ ገልጿል።

ለኘሮግራሙ ሠላማዊነት የድርሻቸውን ላበረከቱ እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት ምስጋና አቅርቧል።

Photo : Mayor Office & Addis TV

@tikvahethiopia
" ሆሣዕና '' (የዐብይ ፆም 8ኛ ሳምንት)

እንኳን አደረሳችሁ !

ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ፆም እሁዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።

ሆሣዕና ማለት የቃሉ ትርጉም  " እባክህ አሁን አድን " ማለት ነው።

ዕለቱ ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም ሽማግሌዎች እና ሕፃናት '' ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሣዕና በአርያም '' በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት ነው፡፡ 

ይህ ዕለት በቤተክርስቲያን ውስጥ ዘንባባ ተይዞ፣ እየተዘመረ እጅግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ይታሰባል።

በዐብይ ጾም ከሰርክ ሆሣዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡

በዚህ ጊዜ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት ካህናት መስቀል በእጃቸው አይዙም፣ አያሳልሙም ፣ ይፍቱኝ ተብሎ ወደካህን አይቀረብም፤ ይህ ሳምንት የጌታን የመጨረሻው ስቃይ የሚታሰብበት ነው።

ፎቶ ፦ ፋይል እና ከማህበራዊ ሚዲያ የተሰበሰበ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሆሣዕና '' (የዐብይ ፆም 8ኛ ሳምንት) እንኳን አደረሳችሁ ! ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ፆም እሁዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና ማለት የቃሉ ትርጉም  " እባክህ አሁን አድን " ማለት ነው። ዕለቱ ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም ሽማግሌዎች…
#ሆሣዕና

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የ2015 ዓ.ም የሆሣዕና በዓል ምክንያት በመድረግ  በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ተገኝተው ቃለምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።

በዛሬው ዕለት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የ2015 ዓ,ም ሆሣዕና በዓል አስመልክተው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተገኝተው ጸሎተ ቅዳሴውን በመምራት ሰፊ ትምህርት፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።

መረጃው / ፎቶው የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia