ኡጋንዳውያኑ ለምን ኢትዮጵያ መጡ ?
ከኡጋንዳ ምሥራቃዊ ክፍል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት " የምፅዓትን ቀን ሽሽት ነው " መባሉ ሐሰት መሆኑን የኛንጋቶም ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ሎኪኛኒጋ ሙርሌ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ተናግረዋል።
ምክትል አስተዳዳሪው ሎኪኛኒጋ ሙርሌ ምን አሉ ?
" ኡጋንዳውያኑ በወረዳችን ይገኛሉ። አመጣጣቸው አካባቢውን ለማየትና የቤተክርስቲያን መልዕክት ለማድረስ ነው።
ይህንንም ከፌደራል ደኅንነት መ/ቤት ለመጡ አካላት አስተድተናል።
በቁጥር ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ 277 ይደርሳሉ ፤ በቤተክርስቲያን የእንግዳ መቀበያ እና በግለሰቦች መኖሪያ ተጠልለው ነው የሚገኙት።
ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት የምጽዓትን ቀን ሽሽት ነው የተባለው የተሳሳተ መረጃ ነው።
በወረዳችን ከዚህ ቀደም በተዘጋጀ ፌስቲቫል ላይ ከኬንያ ቱርካና፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከኡጋንዳ አንድ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ተሳትፈው ነበር።
እነርሱ የመጡት በታሪክም ኛንጋቶም ማኅበረሰብ ከኡጋንዳ ነው የመጣው ብለው ስለሚያምኑ አካባቢውን ለማየት ነው።
ኡጋንዳውያኑ ታኅሳስ ወር ውስጥ ነው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ፤ እንመለሳለን ከማለት ውጭ መቼ እንደሚመለሱ አልገለፁም።
እነርሱ ሲመጡ ዝናብ አልነበረም። ዝናብ እስከሚዘንብ ድረስ ቆይተን ለእናንተ ዘር ሰጥተን ነው የምንሄደው እግዚአብሔር የነገረን መልዕክት ይህ ነው። ከዚያ በኋላ እንመለሳለን ነው ያሉት።
አሁን ላይ ግን በአካባቢው ከፍተኛ ዝናብ እየዘነበ ቢሆንም ኡጋንዳውያኑ አሁንም በሥፍራው ይገኛሉ። "
NB. በኢትዮጵያ በድርቅ ከተጎዱ አካባቢዎች አንዱ የደቡብ ኦሞ ዞን፣ ሲሆን በድርቁ ሳቢያ በርካታ እንስሳት ሞተዋል ፤ በሰዎችም ላይ ጉዳት ደርሷል።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ምንድነው ያሉት ?
አምባሳደር መለስ ዓለም ኡጋንዳውያኑ የምጽዓት ቀን በአካባቢያችን ይኖራል። ሞት መፈናቀል ይኖራል ብለው በመስጋት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አናዱሉ ምን ብሎ ነበር ?
የቱርክ ዜና ወኪል አናዶሉ ከአንድ ወር በፊት ፣ የኡጋንዳን ፖሊስ ጠቅሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን የአንድ ሃይማኖታዊ ቡድን ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን ዘግቦ ነበር።
በዘገባው የሃይማኖት ቡድኑ ተከታዮች የዓለም ፍፃሜ ኡጋንዳ ውስጥ ከሚኖሩበት አካባቢ ይጀምራል ብለው በማመን ከጥፋቱ ለመሸሽ እንደተሰደዱ ፖሊስ በምርመራዬ አረጋግጫለሁ ማለቱን አስነብቦ ነበር።
Via BBC NEWS AMHARIC
@tikvahethiopia

#ብርሃን_ባንክ
ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

TIKVAH-ETHIOPIA
የትኞቹ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ምቹ ናቸው? ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነትን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 አጽድቃ ተቀብላለች። በስምምነቱ መሰረትም ፈራሚ ሀገራት መስማት የተሳናቸው ሰዎች የሕይወትና የማኅበራዊ እድገት ክህሎት እንዲያገኙ ብሎም በማኅበረሰባቸው ውስጥ ሙሉና ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የምልክት ቋንቋ…
በኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋ ሕገ-መንግስታዊ እውቅና ሊሰጠው ይገባል !
በዓለም ላይ #ሰባ_አምስት ሀገራት የምልክት ቋንቋን እንደ ብሔራዊ ቋንቋ አድርገው ከመቀበል ጨምሮ በሰነድ የተደገፈ ሕጋዊ እውቅና ሰጥተዋል፡፡ በአፍሪካ ደግሞ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኡጋንዳ፣ ዙምባቡዌ ብሔራዊ ቋንቋቸው አድርገው ተቀብለውታል፡፡
በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያለው ይኽ ቋንቋ በፖሊሲም ሆነ በአፈጻጸም ትኩረት ያልተሰጠው ቋንቋ ነው፡፡
በኢትዮጵያም የምልክት ቋንቋ ሕገ-መንግስታዊ እውቅና ሊሰጠው ይገባል።
#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

Photo
የቤት ማፍረስ ዘመቻው ...
በአዲስ አበባ ዙርያ " ሸገር ከተማ " እየተካሄደ ያለውን የቤት ማፍረስ ዘመቻን በተመለከተ ኢሰመኮ የደረሰበትን የክትትል ውጤት በላከልን መግለጫ አሳውቋል።
በመግለጫው፤ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ ማስነሳት እርምጃ የመኖሪያ ቤት አልባነትን አባብሷል ብሏል።
ሕገ ወጥ የሆነ ግንባታን የማፍረስ እርምጃ ሕጋዊ ሂደትን መከተልና እርምጃው ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ ቀውስ ከግንዛቤ በማስገባት አማራጭ መፍትሔዎችን ማመቻቸት ያስፈልጋልም ብሏል።
(ከኢስመኮ የተላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

የቤት ማፍረስ ዘመቻው ... በአዲስ አበባ ዙርያ " ሸገር ከተማ " እየተካሄደ ያለውን የቤት ማፍረስ ዘመቻን በተመለከተ ኢሰመኮ የደረሰበትን የክትትል ውጤት በላከልን መግለጫ አሳውቋል። በመግለጫው፤ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ ማስነሳት እርምጃ የመኖሪያ ቤት አልባነትን አባብሷል ብሏል። ሕገ ወጥ የሆነ ግንባታን የማፍረስ እርምጃ ሕጋዊ ሂደትን መከተልና…
ከኢሰመኮ መግለጫ...
በሸገር ከተማ እየተካሄደ ካለው የቤት ማፍረስ እና በግዳጅ ማስነሳት ዘመቻ ጋር በተያያዘ ኢሰመኮ እርምጃው ተገቢ ልየታ ያልተደረገበት መሆኑን ገልጿል።
የቤት ፈረሳውና በግዳጅ ማንሳቱ የሚመለከተው የከተማውን መሪ ዕቅድ በሚጥሱ እና የመንግሥት ይዞታን በመውረርና ከአርሶ አደሩ ጋር በተደረገ ሕገወጥ የመሬት ግብይት የተገኙ ይዞታዎች ላይ የተደረጉ ግንባታዎችን ነው ቢባልም #ሁሉም ቤቶች ግን በተመሳሳይ ሥሪት ላይ የተመሠረቱ ባለመሆናቸው የሚገዛቸውም ሕጎች እና አሠራሮች በዚያው ልክ የተለያዩ ሊሆኑ ይገባ ነበር ብሏል።
ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትልና ምርመራ እየፈረሱ ያሉ ቤቶች በተለያየ አይነት ክፍል የሚመደቡ መሆኑን ገልጿል
👉 የመጀመሪያው ክፍል ፦
ከ2005 ዓ.ም. በፊት የተገነቡ ቤቶች ሲሆኑ እነዚህን ቤቶች በተመለከተ በሀገሪቱ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 6(4) እና (5) እንደተደነገገው አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በኢመደበኛ መልኩ የተገነቡ ቤቶች የከተሞችን ፕላን እና የሽንሻኖ ስታንዳርድ ሲያሟሉ ወደ መደበኛ ስሪት እንደሚዞሩ ደንግጓል። ነገር ግን ኮሚሽኑ ባደረገው ማጣራት እነዚህን ቤቶች ሕጉ በደነገገው መሠረት በወቅቱ ወደ መደበኛ ሥሪት እንዲዘዋወሩ የሚያስችላቸውን መስፈርቶች ማሟላታቸውን በማረጋገጥ የማዘዋወር ሥራ ሳይሠራ እንዲሁ #እንዲፈርሱ ተደርጓል።
👉 ሁለተኛው ክፍል ፦
በግዢ የተገኙ ቤቶች ሲሆኑ ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ መደበኛ ካርታ፣ የአየር ላይ ካርታ እና አረንጓዴ ደብተር ያላቸው እንዲሁም እንዳይፈርሱ የፍርድ ቤት እግድ ያለባቸው ቤቶች ከከተማ ፕላን ጋር የማይሄዱ ናቸው ከተባለ፤ በሕግ አግባብ በተደነገገው መሠረት ተለዋጭ የቤት መሥሪያ ቦታ እና ተገቢው ካሳ ተከፍሏቸው መነሳት የሚገባቸው ነበሩ። ቤቶቹ በገጠር መሬት ላይ የተሠሩ ናቸው የሚባል ቢሆን እንኳ በኦሮሚያ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 6(8) መሠረት በቂ ጊዜ ተሰጥቶ ንብረቶቻቸውን እንዲያነሱ ይደረጋል እንጂ በድንገት ማፍረስ አይገባም ነበር።
👉 ሦስተኛው እና አራተኛው ክፍል ፦
ከአርሶ አደሮች ጋር በተደረገ ሕገ ወጥ የመሬት ሽያጭ በተገኘ ቦታ ላይ የተሠሩ ቤቶች እና ከ2005 ዓ.ም. በኋላ ያለሕጋዊ ፈቃድ በመንግሥት ይዞታዎች ላይ የተገነቡ ቤቶች ናቸው።
ስለሆነም እንዲፈርሱ የተደረጉት ቤቶች በተለያየ አይነት ሥሪት ላይ የተመሠረቱ ስለሆነ እንደየነገሩ ሁኔታ ተገቢው መለየት እና ማጣራት እየተደረገ ሊፈጸም ይገባው ነበር፡፡
ሕገወጥ ግንባታ ማፍረስና የመንግሥት ይዞታ የሆነን ቦታ መልሶ መውሰድ ሕጋዊ እርምጃ ቢሆንም እንኳን፣ የመኖሪያ ቤት ማፍረስና በግዳጅ ማስነሳት ዜጎችን መኖሪያ ቤት አልባ በሚያደርግ መልኩ መደረግ እንደሌለበት እና በሕግ የተፈቀደ እና ለቅቡል አላማ የተደረገ መሆኑ ብቻ በቂ ምክንያት ሊሆን እንደማይችል ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕግ ይደነግጋል።
ዜጎች የመኖሪያ ቤት መብት እንዳላቸው ኢትዮጵያ ያጻደቀችው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ቃልኪዳን በአንቀጽ 11 የደነገገ ሲሆን ኢመደበኛ በሆነ መንገድ እንኳን የተገኙ የመኖሪያ ቤቶችን በሚመለከት መኖሪያ ቤት አልባነትን ለመከላከል ሲባል ሕጋዊ የይዞታ ዋስትና ሊሰጣቸው ወይም አማራጭ መፍትሔ ሊመቻች እንደሚገባ የኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ኮሚቴ በግዳጅ ማንሳትን በተመለከተ ባወጣው አጠቃላይ አስተያየት ቁጥር 7 ላይ አስቀምጧል፡፡
ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/77467?single
ፎቶ፦ Tikvah Family

ከኢሰመኮ መግለጫ... በሸገር ከተማ እየተካሄደ ካለው የቤት ማፍረስ እና በግዳጅ ማስነሳት ዘመቻ ጋር በተያያዘ ኢሰመኮ እርምጃው ተገቢ ልየታ ያልተደረገበት መሆኑን ገልጿል። የቤት ፈረሳውና በግዳጅ ማንሳቱ የሚመለከተው የከተማውን መሪ ዕቅድ በሚጥሱ እና የመንግሥት ይዞታን በመውረርና ከአርሶ አደሩ ጋር በተደረገ ሕገወጥ የመሬት ግብይት የተገኙ ይዞታዎች ላይ የተደረጉ ግንባታዎችን ነው ቢባልም #ሁሉም ቤቶች…
#EHRC
በሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለው የቤት ማፈረስ እና በግዳጅ ማስነሳት ዘመቻ አድሎአዊ እርምጃ ስለመኖሩ የኢሰመኮ የክትትል ሪፖርት አመልክቷል።
" መንግሥት የሚወስዳቸው ማናችውም እርምጃዎች ከአድሎ የጸዱ መሆን እንደሚገባቸው በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች እና በሀገር አቀፍ ሕጎች እውቅና ከተሰጠው የሰብአዊ መብቶች መርሆች መካከል አንዱ ነው " ያለው ኮሚሽኑ ክትትልና ምርመራ ባደረገባቸው አንዳንድ ቦታዎች ላይ አድሏዊ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንዳሉ ለመመልከት መቻሉን አሳውቋል።
ለአብነት በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ ቄስ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተያይዘው ከተሠሩ ቤቶች ውስጥ ሁለት ቤቶችን በማስቀረት ሌሎች ቤቶች እንዲፈርሱ ተደርገዋል።
ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎች አድሎው ብሔር ተኮር እንደሆነ እምነት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን የመንግሥት ኃላፊዎች ግን ይህ እንዳልሆነ አስረድተዋል ሲል ኮሚሽኑ በላከልን የክትትል ሪፖርት ገልጿል።

" ክስ መቋረጥን ተከትሎ ከእስር የመፍታት ስራ ተጀምሯል " - አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ውስጥ ከፌዴራል መንግስት ጋር እየመከረ ይገኛል። ቡድኑ ከፌዴራል መንግስት ጋር እየተወያየ የሚገኘው በትግራይ መልሶ ማቋቋም እና ሌሎች ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስለመሆኑ ተነግሯል። ከዚህ ባለፈ ልዑኩ በአዲስ አበባ ካሉ የትግራይ…
የአንድ ሳምንቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑክ የአዲስ አበባ ቆይታ ምን ይመስል ነበረ ?
በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራው ልዑካን ቡድን ከፌዴራል እና ከክልል አመራሮች ጋር ያደረገውን ምክክር አጠናቆ ዛሬ መቐለ ገብቷል።
ልዑካን ቡድኑ ለአንድ ሳምንት ያህል የተደረገው ምክክር የተጀመረው የሰላም ሂደት የተሟላ እንዲሆን በማድረግ አንፃር ስኬታማ ነበር ብሏል።
ምክክሩ የነበረው ፦
- የትግራይ ግዛታዊ አንድነትን ወደ ቦታው መመለስ፣
- በጀት እንዲለቀቅ ማድረግ፣
- ትግራይን መልሶ ማቋቋም እና መገንባት
- እስረኞች መፍታት የሚሉት ትኩረት ተሰጥቷቸው ውይይት ከተደረጉባቸው ጉዳዮች መካከል እንደሆኑ ተነግሯል።
ምክክሩን በተመለከተ የልዑካን ቡድኑ አባል ዶ/ር ሃጎስ ጎደፋይ ምን አሉ ?
" በወሳኝ ጉዳዮች ላይ እና በልማት ስራዎች ደጋፊ በሚሆኑበት ላይ በግልፅ እና በቅርበት መወያየት አስፈላጊ ስለነበር በተለይ በበጀት ጥያቄ፣ የግዛት አንድነት፣ እስረኞች መፍታት፣ ሰብዓዊ እርዳታ ሁሉም ጉዳዮች ላይ የፌዴራል መንግስት የድርሻውን እንዲያበረክት በሚያስችል መንገድ ሰፊ ውይይት አድርገናል ፤ በልዩ ሁኔታ በተለይ ከፌዴራል መንግስት ጋር ተነጋግረናል።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችም በአካል መጥተው የሚናጋገሩበትን መንገድ የሚጠርግ ነው ፤ መልካም ጅማሮም ታይቷል።
ካሳ፣ የደረሰ ውድመት እንዲሁም ማግኘት ስላለብን በጀት ወዘተ ተነጋግረናል፣ በፓርላማ የተወሰነው የ2015 በጀት እንዲለቀቅልን አሁን ተወስኗል። ሌላው በአስቸኳይ መፈታት ያሉባቸው ጉዳዮች በአፋጣኝ እንዲፈቱ ተነጋግረናል። "
በሌላ በኩል ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ትግራይን መልሶ በማቋቋም ሂደት በሁሉም መስክ የበኩሉን እንደሚወጣ ዝግጅት ማጠናቀቁን የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑካን ጋር የተወያዩ ሲሆን ውይይቱን ተከትሎ በሰጡት ቃል ተከታዩን ብለዋል ፦
" በትግራይ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ጉዳት በህዝቡ ላይ ደርሷል፣ ብዙ ጥፋት ነው የተፈፀመው ያንን ከመሰረቱ በሚቀይር መንገድ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል።
የኦሮሚያ ክልል እዚህ ውስጥ ኃላፊነቱን በመወጣት ግዴታ አለበት፣ የትግራይ ህዝብ ህዝባችን ነው የራሳችን ነው ፤ ለዚህ ህዝባችን የሚያስፈልገውን ልክ ኦሮሚያ ክልል እንደምናደርገው ትኩረት አድርገን እዛ የሚሰሩትን ስራዎች መስራት መቀየር ያስፍልጋል።
ዘር በማቅረብ፣ ቴክኖሎጂ በማቅረብ፣ ችግኝ በማቅረብ፣ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማገዝ ልክ እንደ አንድ ሀላፊነት ወስደን የክልላችን መንግስት ትኩረት አድርጎ በትግራይ ያሉ ስራዎች ላይ እንሳተፋለን ከኛ የሚጠበቀውን ሁሉ እናደርጋለን። "
Credit : TIGRAI TV

#ETHIOPIA
ኢትዮጵያውያን ደማቅ አሻራቸውን ያሳረፉትበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋዩ ከተጣለ ዛሬ 12 ዓመት ደፍኗል።
ዛሬ ላይ ኃይል ማመንጨት የጀመረው ግድቡ ስራው ሙሉ በሙሉ ወደማለቁ እየተቃረበ ይገኛል።
ይህ ግድብ ኢትዮጵያውያን ብዙ ዋጋ የከፈሉበት፣ አሁንም እየከፈሉበት የሚገኝ የሀገር እና የህዝብ ኩራት ሀብት ነው።