TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አቢሲንያ_ባንክ

ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ፣ የይለፍ ቃል ለማንም አይስጡ !

አንዳንድ አጭበርባሪዎች በሞባይል ቴክስት የአንድ ጊዜ መጠቀሚያ የይለፍ ቃል (OTP) እንዲላክ ካረጉ በኋላ ከአቢሲንያ ባንክ የተደወለ በማስመሰል የተላከውን ቁጥር እንዲነግሯቸው እየጠየቁ ሲሆን አንዳንድ ደንበኞችም በቅንነት የሚስጥር ቁጥራቸውን አሳልፈው በመስጠት ለገንዘብ መጭበርበር እየተጋለጡ መሆኑን ደርሰንበታል፡፡

በመሆኑም በምንም መልኩ የሞባይል ባንኪንግ መጠቀሚያ የሚስጥር ቁጥራችሁን ለሶስተኛ ወገን አሳልፋችሁ እንዳትሰጡ እናሳስባለን፡፡

(አቢሲንያ ባንክ)
" ታዳጊዎቹ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ስር ነው የሚገኙት " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ 7 ታዳጊዎች #እንደጠፉ እና #እንደታገቱ ተደርጎ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃ እውነትነት የጎደለውና የተዛባ ነው አለ።

ፖሊስ መረጃው እውነትነት የጎደለውና የተዛባ ስለመሆኑ #አረጋግጥላችኃለሁ ብሏል።

ታዳጊዎቹ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ስር እንደሚገኙም ገልጿል፡፡

ፖሊስ ምን አለ ?

- #አራት ወንድ እና #ሦስት ታዳጊ ሴቶች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 " መካኒሳ ቆሬ " አካባቢ ከሚገኘው የወላጆቻቸው መኖሪያ ቤት እንደጠፉ እና ታግተዋል በሚል በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም።

- ታዳጊዎቹ ለመጥፋት በማሰብ ከወላጆቻቸው መኖሪያ ቤት ልብሶቻቸውን ይዘው እንደወጡ እና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው መኖር እንደሚፈልጉ በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

- በልመና ተግባር ላይ ተሰማርተውም ባገኙት ገንዘብ የተወሰኑ የቤት ቁሳቁስ በማሟላት ሰባቱም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው " ቡልቡላ " አካባቢ በ1 ሺ 800 ብር መኖሪያ ቤት ተከራይተው #ሦስቱ ወንዶችና #ሦስቱ ሴቶች #የፍቅር_ግንኙነት በመመስረት በጋራ እየኖሩ እንደሚገኙ እራሳቸው በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

- የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባትና ከተለያዩ ቦታዎች መረጃ በማሰባሰብ በተደረገው ክትትል ያሉበትን ቦታ እና ሁኔታ ማወቅ ተችሏል።

- ታዳጊዎቹ የስነ-አእምሮና ተያያዥ የጤና ምርመራ እንዲያገኙ እንዲሁም ማህበራዊ ችግራቸው ሊፈታ በሚችልበት ሁኔታ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው።

- አንዳንድ መገናኛ ብዙኃንና ማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃን ስላገኙ ብቻ  የሚያስከትለውን አሉታዊ ጫና ታሳቢ ሳያደርጉ ዜናውን ማሰራጨታቸው በህብረተሰቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያስከትል መሆኑን ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚጠበቅባቸው ሊገነዘቡ ይገባል።

- ወንጀልን በማጣራት እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ስራ ጊዜን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

@tikvahethiopia
#EOTC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ከሰሞኑም ከትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት የተሰጠ መግለጫ በማስመልከት ዛሬ ምላሽ ሰጥቷል።

ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ ? (ከመግለጫው የተወሰደ)

- በጦርነቱ ምክንያት በቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ መዋቅርና በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት መካከል አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ግንኙነት መቋረጡን ተከትሎ በጦርነቱ ምክንያት ሁሉም የባንክ ተቋማት ሥራቸውን በማቆማቸው በየጊዜው እንደሌሎች አህጉረ ስብከት ለትግራይ አህጉረ ስብከት ይላክ የነበረው በጀት መላክ አልተቻለም፡፡

- ምንም እንኳን በባንክ መዘጋት ለአገልጋይ ሠራተኞች በጀት መላክ ባይቻልም የደመወዝ መክፈያ የባንክ ሂሣባቸው በአዲስ አበባ ከፍተው ሲገለገሉ የቆዩት አባቶች በጦርነቱ ወቅትም ሆነ ከጦርነቱ በኋላ እስከአሁን ድረስ ያለምንም መቆራረጥ ወርኃዊ ደመወዛቸው ወደ ባንክ ሂሣባቸው ሲገባ ቆይቷል አሁንም እየገባ ይገኛል፡፡

- ቋሚ ሲኖዶስ ፤ ቤተክርስቲያኗ በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረውን ችግር በጥናት ላይ በመመስረት ችግሩን ሊፈታ የሚችል የአቀራራቢ ሽማግሌ ልዑካንን ለመመደብ በዝግጅት ላይ እያለች መጋቢት 13 ቀን 2015ዓ.ም. የቤተ ክርስቲያኗን ጸንቶ የቆየ ተቋማዊ አንድነትና ነባር መዋቅራዊ አደረጃጀትን በሚንድ መልኩ “ መንበረ ሰላማ የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት” ጽ/ቤት የሚል አዲስ ሕገወጥ ክልላዊ መዋቅር በመፍጠርና ያለምንም በቂ ማስረጃ ፦
• ዋናው መ/ቤት በጀት እንደከለከለ፣
• የሠራተኞችን ደመወዝ እንዳገደ
• በአጠቃላይ በክልሉ በሚገኙ አህጉረ ስብከት ላይ አቅዶ ችግር እንደፈጠረ የሚያስመስልና ሕገ-ቤተ ክርስቲያኑን የጣሰ መግለጫ ተሠጥቷል ብሏል።

- ከመግለጫው በተጨማሪ በሕገ-ቤተ ክርስቲያኑ ላይ በግልጽ እንደተደነገገው በሁሉም አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ሊመደቡ የሚችሉት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ መሆኑ እየታወቀ ሆን ተብሎ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሥራ ላይ እያሉና ሲኖዶሳዊ አንድነቱ ጸንቶ ባለበት ሁኔታ ላይ ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ውጭና ያለቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ አሠራርን በጣሰ ሁኔታ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሊቃነ ጳጳሳት ተመድበው በሚሠሩባቸው የውጭ ዓለማት አህጉረ ስብከት ላይ ሊቃነ ጳጳሳት ከቀኖና ውጭ ራሳቸውን በራሳቸው በመመደብ መግለጫ መስጠታቸውን ቤተክርስቲያንን በእጅጉ እንዳሳሰዘነ ተገልጿል።

ይቀጥላል 👇
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ከሰሞኑም ከትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት የተሰጠ መግለጫ በማስመልከት ዛሬ ምላሽ ሰጥቷል። ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ ? (ከመግለጫው የተወሰደ) - በጦርነቱ ምክንያት በቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ መዋቅርና በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት መካከል አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ግንኙነት መቋረጡን ተከትሎ በጦርነቱ ምክንያት ሁሉም የባንክ ተቋማት ሥራቸውን በማቆማቸው…
ቤተክርስቲያኗ ፦

1. በትግራይ ክልል ለሚገኙ አህጉረ ስብከት በጀት እንዳይላክ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነ አንድም ውሳኔ የሌለና በተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት የባንክ አገልግሎት በመቆሙ የተከሰተ የግንኙነት መቋረጥ መሆኑን ገልጻ በጀቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቆመበት ጊዜ ጀምሮ ከአህጉረ ስብከት ጋር በመነጋገር ለመላክ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።

2. በክልሉ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የደረሰውን ጉዳትና ችግር ቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ የተሰማትን ሐዘንና በችግሩም ወቅት ለአህጉረ ስብከቱ በበጀት ተደራሽ ባለመሆኗ ያስከተለው ችግር ያሳዘናት መሆኑን በቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ መግለጿን አስታውሳ የተከሰተው ጦርነት እንዲቆም በጸሎትና በምሕላ ስትማፀን መቆየቷ ወደጐን ተትቶና ተዘንግቶ የጦርነቱ ደጋፊ በሚያስመስል መልኩ የተሰጠው መግለጫ ተቀባይነት የሌለውና ፍፁም የማይገልጻት መሆኑን ገልጻለች።

3. በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በዳጩ ሆሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሕገወጥ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ፈተና ለመፍታትና የቤተ ክርስቲያኗን ሲኖዶሳዊ አንድነትን ለማጽናት በከፍተኛ ኃላፊነት እየተሰራ ባለበት ሁኔታ ለዚህ የቤተ ክርስቲያኗ ተልዕኮና ተቅማዊ አንድነት መጽናት በጸሎትም በሐሳብም ልንታገዝ ሲገባ  የእምነትና የታሪክ መሠረት በሆነው የትግራይ ሊቃውንት እንዲህ ዓይነት ድርጊት መከሰቱ ለአገሩም ሆነ ለሕዝቡ የሚመጥን አድራጐት ባለመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስባለች።

4. በክልሉ ያለው አጠቃላይ መዋቅራዊ ችግሮችን በሚመለከትና አጠቃላይ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የተከሰቱትን ችግሮች ተወያይቶ ለመወሰን መጋቢት 21/2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ የተጠራ መሆኑን ያሳወቀችው ቤተክርስቲያን በክልሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመድበው በመሥራት ላይ የሚገኙ ሊቃነጳጳሳት በጥሪው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ላይ እንዲገኙና ክልላዊ ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ውይይት ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፋለች።

5. ቤተክርስቲያኗ በትግራይ የሚገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያን በአባቶቻቸው ሐዋርያዊ ተልዕኮ ጸንታ እስከአሁን መቆየቷን ገልጻ በአገራችን በተከሰተው ፖለቲካዊ ችግር ዘመናትን በጽናት የተሻገረችውን እናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አንድነቷ መፍረስ ሲኖዶሳዊ ልዕልናዋ መጣስ የሌለበት መሆኑን በጽናት እንደሚያምኑ እምነቷን በመግለጽ ለቤተ ክርስቲያኗ ተቋማዊ አንድነት አስፈላጊውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል በጽናት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርባለች።

6. የትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት በክልሉ ተፈጥሮ የቆየው ችግር በሰላማዊ መንገድ በውይይት በመፈታቱ ቤተ ክርስቲያን የተሰማትን ደስታ የገለፀች ሲሆን አስቀድሞ ችግሩ ከመከሰቱ በፊት አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተመራው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለቀረበው የሰላም ጥሪ እናት ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛውን ሚና እንደተጫወተች አስታውሳለች። በተከሰተው ችግር የተፈጠሩ ጉድለቶች ካለ ጉድለቶችን ለማረምና ችግሮቹን ለመፍታት ቤተ ክርስቲያኗ ያላትን የጸና አቋም የገለፀች ሲሆን በክልሉ የተከሰተውን ተቋማዊ አንድነትን የሚጥስና ቀኖና የጣሰ አደረጃጀት እንዲቆም የበኩሉን ሚና በመጫወት ለቤተ ክርስቲያኗ ተቋማዊ አንድነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፋለች።

ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/77262?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በክልሉ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህም መግለጫቸው ፤ " የትግራይ ህዝብ እራሱን ከጥፋትና ውድመት ለማዳን ሁሉንም አይነት መስዋዕትነት ከፍሏል። " ያሉ ሲሆን " ጊዜያዊ አስተዳደሩም የትግራይ ህዝብ የታገለለትንና መስዋእትነት የከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት ይሰራል " ብለዋል። አቶ ጌታቸው አስተዳደራቸው የትግራይን…
"...ብዙ ተዳምተናል ይሄ ነገር ሊቀጥል አይችልም ወደድንም ጠላንም ጎረቤት ሆነን ነው የምንቀጥለው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለትግራይ ቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር።

ቃለ ምልልሳቸው ወቅት ስለ ኤርትራ ሰራዊት እንዲሁም ስለ አማራ ክልል ታጣቂዎች ጉዳይ አንስተው ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምንድነው ያሉት ?

" ጠቅላላ የኤርትራ ሰራዊት ትግራይ ውስጥ ነበር የነበረው። የተደራጁት ' ዩኒት ' የሚባሉት እንዲወጡ ከማድረግ አንፃር የተሰራ ስራ አለ ስኬታማ ሊባል የሚችል። ሆኖም ግን አሁንም በርከታ የትግራይ አካባቢዎች ላይ የኤርትራ ሰራዊት አለ ብቻ ሳይሆን በገባባቸው አካባቢዎች በርካታ ግፎችን ይፈፅማል።

የአማራ ታጣቂዎች የእኛ ነው ብለው ባሉት በጉልበት የተያዘ አካባቢ ላይ ፣ ምዕራብ ትግራይ ብቻ ሳይሆን ፀለምትም ፣ ደቡብ ትግራይ ውስጥ ተመሳሳይ ነገሮች ይከናወናሉ። እነዚህ ነገሮች በኛ እምነት ፌዴራል መንግስቱ ይሄንን ነገር የማስቆም ግዴታ አለበት።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ የመጀመሪያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ብለን ከምናስቀምጣቸው ነገሮች ህዝቡ ከተፈናቀለበት ቀዬ እንዲመለስ ማድረግ፣ የማህበራዊ ግልጋሎት ማስጀመር ባልተናነሰ ይሄ ጉዳይ በቂ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

በአማራ ክልል በኩል ያሉ ታጣቂዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሰላሙን ወደኃላ እንዳይመልሰው ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባ ነው።

ሰላሙ ሁላችንንም ነው የሚጠቅመው ፤ የትግራይ ህዝብ ሰላሙ እንዲጠበቅለት ይፈልጋል ይበልጥ ሰላም እንዲመጣለት ዘላቂ ሰላም እንዲሆንለት ነው የሚፈልገው ፤ ያለው ሰላም ወደኃላ እንዲመለስ አይፈልግም።

ይህን ለማድረግ የሚያስችል ከፌዴራል መንግስት ጋር የጀመርናቸው አውንታዊ ግንኙነቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ፤ ያ ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት ወንድማማች እህትማማች ህዝቦችም ጋር ከስሜት በፀዳ መልኩ ብዙ ተዳምተናል ይሄ ነገር ሊቀጥል አይችልም ወደድንም ጠላንም ጎረቤት ሆነን ነው የምንቀጥለው ፤ ይሄን በሰላማዊ መንገድ ፣ በህጋዊ ህገመንግስታዊ መንገድ መፍታት እየከበደንም ቢሆን ህገመንግስታዊ መንገድን መልመዱ የሚያዋጣ ነው የሚል መልዕክት ነው ማስተላለፍ የሚቻለው።

ከዚህ አንፃር አሁንም የሚታዩ ችግሮች በትግራይ ህዝብ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት እንደተጠበቀ ሆኖ በሀገር ደረጃ የተፈጠረው የሰላም ጭላንጭል አደብዝዞ ወለየለት ቁርንቁስ ለመግባት የሚያስችል ሁኔታ ከመፍጠርም አንፃር ያለው ትርጉም ከፍተኛ ስለሆነ በፌዴራል መንግስትም በሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ፣ ከምንም ነገር በላይ ወንድም በሆነው የአማራ ህዝብ ዘንድ ይሄ ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶ እልባት ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ነው ብለን እናምናለን።

ግጭቱን ያስቆምነው ወደ ግጭት ተመልሰን ለመግባት አይደለም በተቻለ መጠን በሰላማዊ መንገድ ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ነው።

ይሄን ነገር የማድረግ እድሉ ዝግ ነው ብለን አናምንም በጉልበት፣ ህገመንግስታዊ ስርዓትን በመጣስ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ዞሮ ዞሮ መጨረሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ግልፅ ነው።

ከዚህ አንፃር ያልተቋጩ ጉዳዮችን በቀጣይ ግንኙነት የምንቋጫቸው ነው ብለን የምናምነው። "

@tikvahethiopia
ብ/ጄነራሉ በጠና ታመዋል።

የቀድሞ የአማራ ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በጠና መታመማቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ገልጸዋል።

ብ/ጄኔራል ተፈራ በአሁኑ ወቅት መንቀሳቀስ እንደማይችሉ እና ከወራት በፊትም ለህክምና ወደ ውጭ አገር እንዳይወጡ መከለልከላቸውን ወ/ሮ መነን ተናግረዋል።

በኅዳር ወር ላይ ጄኔራሉ ወደ እስራኤል ሄደው ለመታከም ቢሞክሩም አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ መውጣት እንደማይችሉ ተነግሯቸው ተመልሰዋል።

ወ/ሮ መነን ኃይሌ ለቢቢሲ ምን አሉ ?

" ለህመሙ መንስዔ የሆነው ከዚህ ቀደም በጥይት የተመታ እግሩ ነው፤ በአሁኑ ወቅት ጥይቱ አቅጣጫውን ለውጦ ነርቩ ላይ አርፏል።

ህመሙ ያለው በቀኝ እግሩ ላይ ቢሆንም ለመነሳትም ሆነ ለመቆም በጣም ይከብደዋል፤ ጭንቅላቱ ላይም ከፍተኛ ህመም አለበት።

በአገር ውስጥ ባሉ የህክምና ተቋማት ከማስታገሻ መድኃኒቶች ውጭ ሌላ ህክምና አላደረገም፤ የሐኪሞች ቦርድ ወደ ውጭ አገር በመሄድ እንዲታከም ደብዳቤ ፅፏል።

ጥቅምት አካባቢ በጠና ታሞ በነበረበት ወቅት ያለበት የጤና ችግር መገጣጠሚያው ላይ ችግር እያመጣ እንደሆነ ተነግሮት በውጭ አገር እንዲታከም ደብዳቤ ተጽፎ ነበር።

ለህክምና ወደ ውጭ አገር ለመጓዝ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ባቀናበት ወቅት አይቻልም ተብሎ ተመልሷል። በዚህም ለከፍተኛ ወጪ ተዳርገናል።

ወደ ውጭ አገር እንዳይጓዝ ለምን እንደተከለከለ ምክንያቱን የትኛውም አካል አላስረዳንም።

ኢሚግሬሽን እኔ አላገድኩም ይላል። እኛ ጋር እግድ የለባቸውም ስለዚህ ከእኛ ጋር የሚገናኝ ነገር የለም ይላሉ። አየር ማረፊያ ስንጠይቅ ደግሞ ወደዚያኛው ይልኩናል። "

እስካሁን የአገሪቱ የሕግም ሆነ የፀጥታ አካል ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ከአገር እንዳይወጡ ተከልክለዋል ስለመባሉ ያለው ነገር የለም።

Via BBC Amharic Service

@tikvahethiopia
ካህኑን ማን ገደላቸው ?

" ኃይሌ ጋርመንት " የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቀዳሽ ካህን ቀሲስ ዐባይ መለስ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።

ካህኑን የሚያውቋቸው አገልጋዮች /ምዕመናን  ስለነበረው ሁኔታ / ስለጥቃቱ ምን አሉ ?

(ለማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከተናገሩት የተወሰደ)

ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን አንድ ፦

" ትላንት/መጋቢት 14 ቅዳሴ ቀድሰው በአጋጣሚ እኔ በውጪ አስቀድሼ ነበር ፤ ወደ ደጀሰላም ገባን ምግብ ተመግበን ተለያይተን ነው እነሱ ወደ ኃላ ነበሩ ከምግብ በኃላ እኛ እዚህ አካባቢ ነበርን ተሻግረው ቤታቸው ቆይተው የሌላ (ቄስ አሰፋ ይባላሉ) የእሳቸው ቤት ነው የፈረሰው የእሳቸው ቤት ፈርሶ ሊሻገሩ ገና ከቤታቸው ወጥተው ትንሽ እራመድ እንዳሉ ነው ተመቱ የሚባል ወሬ ሰማን።

ተደወለና ባጃጅ አምጡ ተብለን እስከቤታቸው ድረስ እንደምንም ተቋቁመውት ሄደዋል ከቤታቸው በኃላ አንድ ካህን አብረው ይዘዋቸው መጡ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲደርሱ ተሸነፉ ወደቁ ፤ እኔ ለማናገር ሞከርኩኝ ምንድነው ? ምን ሆነው ነው ? ምንድነው የተፈጠረው ? ስላቸው ምንም ሊመልሱልኝ አልቻሉም ወዲያው ተናነቃቸው ባጃጅ ላይ አስገባናቸው ወደ ክሊኒክ ወሰድናቸው እዛሪ ሪፈር ተባለ ወደ ጥሩነሽ (ሆስፒታል) ወስደው ሌሊት አረፉ የሚለውን ሰማሁ በጣም አዝኛለሁ። "

ቃላቸውን የሰጡ አገልጋይ ሁለት ፦

" ዘጠኝ ሰዓት ከለሊቱ አረፉ ይሉኛል የደብሩ ዋና ፀሀፊ ፤ እንዴት ? አልኳቸው ፈረሳ ነበረና እዛ ፈረሳ እኔ መጠምጠሜን አልያዝኩም፣ ጋቢም አልያዝኩም ማንም ያወቀኝ ሰው የለም ካህንም ልሁን ምዕመንም ልሁን አሉ፤ እሳቸው ግን ጋቢያቸውን ቆባቸውን አድርገው መጥተው እዛ ነው የደበደቧቸው አሉኝ።  ቅዳሴ ውለዋል ቀድሰው እዛ ማዶ ፈረሳ አለ  ሲባል ግን የኛ የማርያም አገልጋዮችም የፈረሰባቸው ነበረና እዛ ሄጄ አብሬም ልቀላቀል ፤ ባለኝ አቅም ልርዳቸው ብለው ነው ተነስተው የሄዱት፤ እጂ ቀድሰው ውለው ነው የሄዱት። "

ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን ሶስት ፦

" የአሟሟታቸውን ሁኔታ ሲነግሩኝ በዕለቱ በ14 ማለት ነው ፤ ቅዳሴ ቀድሰው ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለው አቀብለው ወጣ እንዳሉ ነው ያልታወቁ ሰዎች መንገድ ላይ አደጋ ያደረሱባቸው የሚል ነው የተሰጠኝ መረጃ።

ቤት የላቸውም ፤ ስለቤቴ ብለው የተከራከሩትም ነገር የለም መንገድ ላይ እየሄዱ ነው የሌላ ሰው ቤት ፈርሶ ወደዚያ ለማስተዛዘን ሲሄዱ ነው ጥቃት የደረሰባቸው ብለው ነው የነገሩኝ አብረዋቸው የነበሩ ሰዎች። "

ቃላቸው የሰጡ ምዕመን አራት፦

" ባጃጅ ላይ ስናስገባቸው አንድ ነገር ብቻ ነው የተናገሩት ' እባካችሁ እዚሁ ቤተክርስቲያን አድርጉኝ አትውሰዱኝ ' ሲሉ ተነፈሱ ከዚያ መናገርም አልቻሉም ፤ ውሃም ስንሰጣቸው መቀበል አልቻሉም እዛም ስንወስዳቸው መረጃ ሊነግሩን አልቻሉም "

የካህኑ ልጅ ፦

" ቤት ሲመጣ ደም ደምቶ እራሱ ላይ ነጠላ አድርጎ ነው የመጣው ከዚያ በኃላ ምን ሆነህ ነው ስለው መተውኝ ነው ያለው ሌላ ቄስ ነበሩ መጡና ሃኪምቤት ወሰዱት።

ሃዘን ናፍቆት ነው የሚሰማኝ አባ አባቴ ስለው በጣም ነው የምወደው ስለዚህ ካለሱ ማንም የሚያሳድገኝ የለም። "

ቀሲስ ዐባይ መለሰ በምዕመኑ እጅግ የሚወደዱ፣ የሚከበሩ፣ ሰርተው የሚያሰሩ ያላቸውን ሁሉም አቅም ለቤተክርስቲያኗ የሚሰጡ ትልቅ አባት እንደነበሩ ምዕመናኑ ገልጸዋል።

ካህናት በአካባቢው ላይ የተፈፀመው ድርጊት ፍርሃት ላይ እንደጣላቸው የተገለፀ ሲሆን በእሳቸው ህልፈት ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እንዳሉ ተጠቁሟል።

ፖሊስ ስለጉዳዩ ምን አለ ? ያንብቡ : https://telegra.ph/Police-03-24-2

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ካህኑን ማን ገደላቸው ? " ኃይሌ ጋርመንት " የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቀዳሽ ካህን ቀሲስ ዐባይ መለስ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። ካህኑን የሚያውቋቸው አገልጋዮች /ምዕመናን  ስለነበረው ሁኔታ / ስለጥቃቱ ምን አሉ ? (ለማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከተናገሩት የተወሰደ) ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን አንድ ፦ " ትላንት/መጋቢት…
#ተጨማሪ

የቀሲስ ዐባይ መለሰ ግድያ በስፋት ተሰማ እንጂ የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ባለችበት አካባቢ ብዙ ፈተና ይገጥማት እንደነበር አገልጋዮችና ምዕመናን ለ " ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን " ተናግረዋል።

እዛው ቤተክርስቲያን አካባቢ ስልክ የተቀሙ ፣ ጩቤ በያዙ ሰዎች ማስፈራሪያ የደረሰባቸው ፣ ሻሽ ጠምጥመው ሲሄዱ #የተመቱ መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ያለውን ችግር የሚመለከታቸው አካላት እንዲያዩ ጠይቀዋል።

አንድ ምዕመን ፤ " ቤተክርስቲያን አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈፀምባት መሆኗን ገልፀው ተልዕኮዋን ለማስፈፀም ሰላም ያስፈልጋታል " ብለዋል።

" የቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ሆኑ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ይህች ቤተክርስቲያን ከሚገባው በላይ እየተጎዳች ስለሆነ ጉዳቷን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ የግድ ነው ፤ መስዋዕትነት መክፈልም ያስፈልጋል ምክንያቱም ቅዱስ ስጋ ክቡር ደሙን ካልተመገብን እኛ ሀገረ እግዚአብሔርን አናገኝም " ሲሉ ገልጸዋል።

መንግስት የመጀመሪያ ስራው ህግ ማስከበር መሆኑን የገለፁት እኚሁ ምእመን እንዲህ ያለ ጥቃት (በቀሲስ ዐባይ መለሰ ላይ የደረሰ) እንዳይደርስ ዜጎች ወጥተው እንዲገቡ ተገቢ የሆነ ጥበቃ ሊያደርግ ይገባዋል " ብለዋል።

" ትልቁ ችግር መንግስት ስራውን ባለመስራቱ ምክንያት ነው ይሄ ሁሉ ችግር እየተፈጠረ ያለው " የሚሉት ምዕመኑ " መንግሥት ከማንኛውም ነገር በፊት ቅድሚያ መስጠት ያለበት ሰላም ለማስከበር ነው ፤ ዜጎች የፈለጉበት ቦታ ሰርተው ፤ ጥረው ግረው እንዲኖሩ ዕልውናቸውንና ደህንነታቸው / ዕልውናችንን መጠበቅ ነው " ሲሉ  አስገንዝበዋል።

" ይህ ባለመሆኑ ነው ሰው በወጣበት የሚቀረው እዚሁ ሰፈሩ ውስጥ ጥቃት የሚደርሰው ፤ መንግሥት እንዲያህ አይነት ድርጊት እንዳይፈፀም ስራው ባለመስራቱ ነው ችግር እየተፈጠረ ያለው ፤ መንግስት ስራውን ሊሰራ ይገባል " ብለዋል።

@tikvahethiopia