TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እንደ ሀገር ምንም አይነት የምርት እጥረት የለም "

የጤፍና ሌሎች የምርቶች ዋጋ ንረትን በተመለከተ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ፣ ከኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ እና ከፌደራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም መግለጫ ወቅት የምርት እጥረት የለም ተብሏል።

ሚኒስቴሩ " የምርቶች የዋጋ ንረት በምርት እጥረት ሳይሆን በህገ-ወጦች አማካኝነት ምርት ወደ ገበያ እንዳይገባ በመደረጉ ነው " ብሏል።

" እንደ ሀገር ምንም አይነት የምርት እጥረት የለም " ያለው ሚኒስቴሩ " የዋጋ ንረቱ የተከሰተው የንግድ ፈቃድ የሌላቸው አካላት ምርቱን በከፍተኛ ዋጋ ገዝተው በመደበቃቸውና ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ ወደ ገበያ ውስጥ እንዳይገባ በማድረጋቸው ነው " ሲል ገልጿል።

ችግሩን ለመቅረፍ ክልሎች ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመስራት ህገ-ወጦችንና ህገ-ወጥ ተግባራቸውን በመግታት በህጋዊ ነጋዴዎች እና በህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ምርት ወደ ገበያ የሚገባበት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል ብሏል።

በአሁኑ ወቅት ዩኒዮኖች እና የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ጤፍና ስንዴን ጨምሮ ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ ምርቶችን በተመጣጠነ ዋጋ ወደ አዲስ አበባ እያስገቡ በመሆኑ ሸማቹ ህብረተሰብ ተረጋግቶ እንዲሸምት በመግለጫው ጥሪ ቀርቧል፡፡

በኦሮሚያ ክልል እና በአማራ ክልል ከደህንነት ኬላዎች ውጪ ምንም አይነት የምርቶችን ህጋዊ እንቅስቃሴ የሚገድቡ ኬላዎች ባለመኖራቸው ማንኛውም ህጋዊ ነጋዴ የንግድ ፈቃዱን ይዞ ምርቶችን በፍጥነት ወደ ገበያ ማቅረብ የሚችል በመሆኑ በህገ-ወጥ መንገድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ተከታትሎ እርምጃ የመውሰድ ስራ እንደሚሰራም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" መርሀባ "

አማራ ባንክ አ.ማ " መርሀባ " ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን እንዲሁም ለአገልግሎቱ የተዘጋጀውን ኮር ባንኪንግ (Multiple Company Multiple Book) ሲስተም ትግበራ ለባንክ ኢንደስትሪው በማስተዋወቅ ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ ሥራ እንደሚያስጀምር ዛሬ በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

ባንኩ ወደ ሥራ ከገባ ጀምሮ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጾ እስከ አሁን ከ35 ሺህ በላይ የመርሃባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች ማፍራት እንደቻለ አመልክቷል።

በዚህ ዓመት መጨረሻም ሙሉ በሙሉ መርሃባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ 30 ቅርንጫፎችን እንደሚከፍትም ባንኩን በላከልን መግለጫው ገልጿል።

@tikvahethiopia
" ምዕራባውያን እንግዳ የሆነ ባህል (የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) እንድንፈቅድ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " - ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ

የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

ሙሴቬኒ ይህን ያሉት አገራቸው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ አዲስ ሕግ እያረቀቀች ባለችበት ወቅት ነው።

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ወንጀል በሆነባት ኡጋንዳ እየተረቀቀ ያለው ሕግ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ላይ የበለጠ ጠንካራ ቅጣት የሚጥል ነው።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ትናንት ሐሙስ መጋቢት 07/2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ይህን ብለዋል ፦

" ምዕራባውያን እንግዳ የሆነ ባህል (የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) እንድንፈቅድ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ።

ምዕራባውያን የራሳቸውን አሰራር በሌሎች ላይ ለመጫን የሚያባክኑትን ጊዜ ማቆም አለባቸው።

አውሮፓውያኑ የአጎት እና የአክስት ልጅ ጋር ትዳር ይመሰርታሉ እዚህ [ኡጋንዳ] የአንድ ጎሳ አባልን ማግባት ነውር ነው።

እነሱ የቅርብ ዘመድ እንዳያገቡ ማዕቀብ እንጣል ? ይህ የእኛ ሥራ አይደለም። "

ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን አፈንጋጭ ብለው የገለጿቸው ሲሆን በጉዳዩ ላይ ብዙ ምክክር መደረግ አለበት ብለዋል።

ኡጋንዳ አሁን ላይ እያረቀቀች ባለችው ሕግ መሠረት በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ውስጥ ያለ ወይም እራሱን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪ ብሎ የሚገልጽ ሰው እስከ 10 ዓመታት የእስር ጊዜን እንዲያሳልፍ ያዛል።

የኡጋንዳ መንግሥት በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የውጭ አገራት መንግሥታት ተቋማት እና ምዕራባውያን ኤጀንሲዎች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን እያስተዋወቁ ነው በማለት ይከሳል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#አፋልጉን

በአዲስ አበባ ሳሪስ አዲስ ሰፈር በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች " ቤዛዊት በቀለ " የምትባል ሞግዚት / ግለሰብ ከምትሰራበት ቤት የ2 ዓመት ህጻን የሆነችውን ሶልያና ዳንኤልን (ከላይ በፎቶ ተያይዟል) ከቤት ይዛት መሰወሯን ቤተሰቦቿ ገልጸውልናል።

እናት እና አባትን ጨምሮ መላው ቤተሰብ ጭነቅት ላይ የሚገኙ ሲሆን የንፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ ጉዳዩን እንዲያውቀው ተደርጓል።

ህፃን ሶልያና ዳንኤልን ይዛ የተሰወረችው የቤት ሰራተኛ መታወቂያም ሆነ ፎቶ ባይኖራትም መንገድ ላይ እሷ ትሆን ብሎ የሚጠራጠር መልኳ ቀይ፣ መካከለኛ ቁመትና ቀጠን ያለች በተደጋጋሚ ታይትና ሻሽ የምትለብስ ሴት ናት ተብሏል።

ህፃን ሶሊያና በወቅቱ ሶቢጫ ኮፍያ ያለው ሹራብ ከክፍት ጫማ ጋር አድርጋ ነበር።

አጠራጣሪ ነገር በመንገድ ላይ / በየትኛውም ቦታ ስትመለከቱ በ0951090999 (ዳንኤል)  እንዲሁም በ0947365252 (ዮብዳር) ብላችሁ ደውሉ።

https://t.iss.one/tikvahethmagazine/19071

Via : @tikvahethmagazine
#GetachewReda #AntonyBlinken

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከህወሓት አመራሮች አንዱ ከሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ አዲስ አበባ ላይ ከብሊንከን ጋር መገናኘታቸውንና ስለ ሰላም ስምምነቱ አተገባበር እድገት እና ስላሉት እንቅፋቶች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ በውይይቱ ወቅት #ለሰላም ያላቸውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት እንዲሁም ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የሚፈጥሩትን ተግዳሮቶች ለመወጣት በእነሱ በኩል ያላቸው የማያወላዳ ቁርጠኝነት እንዳረጋገጡ ገልጸዋል።

" ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረትን ጨምሮ በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት ሁሉ እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን " ሲሉም ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ከብሊንከን ጋር በነበረው ውይይት በትግራይ ውስጥ እና በትግራይ ላይ በተደረገው ጦርነት ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አስፈላጊት ላይ ሃሳባቸውን እንዳካፈሉ አመልክተዋል።

አቶ ጌታቸው፤ ጠንካራ የሽግግር የፍትህ ማእቀፍ ተቀባይነት ያለውና የሚያስመሰግን ቢሆንም በትግራይ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ከሀገራዊ ማዕቀፍ የዘለለ በመሆኑ ዓለም አቀፍ ጥረቶች አስፈላጊ ናቸው የሚል አቋማቸውን እንደገለፁ አስረድተዋል።

አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው ፤ ሀገራቸው አሜሪካ የሰብአዊ ድጋፍን ለማጠናከር፣ ለመልሶ ማቋቋም ሃብት ለማሰባሰብ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በመላው ቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከስምምነቱ ተዋናይ ወገኖች ጋር በጋራ እንደምትሰራ በድጋሚ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

@tikvahethiopia
" 13 ሰዎች ሞተዋል ፤ በርካታ እንስሳት በጎርፍ ተወስደዋል " - የኮንሶ ዞን

በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ገርጨ እና አይሎታ ደካቱ ቀበሌዎች ነፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት 13 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ እንስሳት በጎርፍ መወሰዳቸውን ዞኑ አሳውቋል።

የጎርፍ አደጋው የተከሰተው በሰገን ዙሪያ ወረዳ ዶዴ እና መገርሳ ወንዞች መሆኑን ተገለፀው ዞኑ በአካባቢው አሁን እየዘነበ ያለው ዝናብ ከ4 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ገልጿል።

ዝናቡን ተከትሎ ህብረተሰቡ ለተጨማሪ የጎርፍ አደጋ እንዳይጋለጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የዞኑ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተጨማ ህፃናትና ታዳጊዎች በወንዞች አቅራቢያ እንዳይንቀሳቀሱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ምንጭ፦ የኮንሶ ዞን ኮሚኒኬሽን/ኤፍ ቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የተቋረጠው #የባጃጅ_ትራንስፖርት አገልግሎትን አስመልከቶ ዛሬ መጋቢት 8/2015 ዓ.ም መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ ከሰዓት 9 ሰዓት የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም የተቋረጠውን የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጥ " አሻም ቴሌቪዥን " ዘግቧል።

የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ተከትሎ አሽከርካሪዎች የዕለቱ ጉርሳቸውን ማጣታቸውን፣ ተጠቃሚዎችም ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸውን እየገለፁ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን /ኢሰመኮ ትላንት ባወጣው መግለጫ የባጃጅ ትራንስፖርት እገዳው እንዲነሳ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

Credit : #AshamTV

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ውድ ደንበኞቻችን ፦

ባንካችን አቢሲንያ ለደንበኞቹ የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ለማሻሻል እንዲረዳው የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ማለትም መጋቢት 9 እና 10 ቀን 2015 ዓ.ም ነባሩን ሲስተም የማሳደግ (System Upgrading) ያከናውናል፡፡

በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናት መላው ቅርንጫፎቻችን፤የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን፤ የኦንላይን ባንኪንግ ሲስተሞቻችንና ከባንክ ወደባንክ የማስተላለፍ አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ይሁን እንጂ በተጠቀሱት ቀናት የኤቲኤም ማሽኖቻችን የተለመደውን አገልግሎት የሚሰጡ በመሆኑ ከ1275 በላይ በሆኑት የኤቲኤም ማሽኖቻችንን መጠቀም የምትችሉ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልፃለን፡፡    

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ባጃጅ

• " ገደቡ ከነገ ጀምሮ ይነሳል "

• " በየትኛውም ርቀት ከ5 ብር በላይ ማስከፈል አይቻልም "


በአዲስ አበባ በባጃጅ አገልግሎት ላይ የተጣለው እግድ ከነገ ጀምሮ እንደሚነሳ የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ዛሬ በሰጠው መግለጫ የባጃጅ አገልግሎት ላይ የተጣለው እግድ ከነገ ቅዳሜ መጋቢት 8/2015 ጀምሮ እንደሚነሳ አስታውቋል።

የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በየትኛውም ርቀት ከ5 ብር በላይ ማስከፈል እንደማይችሉ ቢሮው ገልጿል።

ቢሮው የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚመራበት መመሪያ መዘጋጀቱን ይፋ ማድረጉን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

@tikvagethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ባጃጅ • " ገደቡ ከነገ ጀምሮ ይነሳል " • " በየትኛውም ርቀት ከ5 ብር በላይ ማስከፈል አይቻልም " በአዲስ አበባ በባጃጅ አገልግሎት ላይ የተጣለው እግድ ከነገ ጀምሮ እንደሚነሳ የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው ዛሬ በሰጠው መግለጫ የባጃጅ አገልግሎት ላይ የተጣለው እግድ ከነገ ቅዳሜ መጋቢት 8/2015 ጀምሮ እንደሚነሳ አስታውቋል። የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በየትኛውም ርቀት ከ5 ብር በላይ…
#ተጨማሪ

" የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ብቻ ነው " - የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ

ተቋርጦ የነበረው የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ከነገ ጀምሮ ባጃጆቹ በተመደቡላቸው መስመሮች ብቻ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

በመግለጫው ምን ተባለ ?

- ከአገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ለተፈጠሩ ችግሮች መንስኤ ናቸው የተባሉት ፦
• ህግን አክብሮ አገልግሎት አለመስጠት፣
• በአብዛኛው አሽከርካሪ ዘንድ ደረጃውን የሚመጥን መንጃ ፍቃድ አለመያዝ
• የታሪፍ ስርዓት አለመኖር ዋንኞቹ ናቸው።

- አሁን በተዘጋጀ መመሪያ መሰረት ቢሮው በለያቸው የስምሪት መስመሮች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

- 138 ጊዜአዊ ታፔላዎችን ከዋናው መስመር ውጪ ተዘጋጅተዋል።

- የትራፊክ ምልክቶች ተከላ ማከናወን እና ማህበራትን ማደራጀት ዋንኛ ስራ ነበር። በ8 ክ/ከተሞች 123 ማህበራትን የማደራጀት ስራ የተሰራ ሲሆን አገልግሎቱም በኮድ 1 ታርጋ ብቻ ይሰጣል።

- የተሳፋሪ መጠን አሽከርካሪውን ጨምሮ 4 ሰው ብቻ ሴሆን የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ብቻ ነው። ህጉን ተላልፈው የተገኙ አሽከርካሪዎች በየደረጃው ቅጣት ይጣልባቸዋል።

- በከተማው መደበኛ ትራንስፖርት በማይገኝበት ከ0 ነጥብ 9 እስከ 2 ነጥብ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ብቻ በ5 ብር ታሪፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል።

- የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በየትኛውም ርቀት ከ5 ብር በላይ ማስከፈል አይችሉም።

Credit : ADDIS MEDIA NETWORK / FBC

@tikvahethiopia
የጀግና እናቶች ቀን . . .

የኢንፊኒቲ በጎ አድራጎት ድርጅት "የጀግና እናቶች ቀን በሚል" የተለያዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን ተቋቁመው የሚኖሩ እናቶችን ጀግንነት ለመመስከር ያለመ ዝግጅት ነገ ቅዳሜ በግዮን ሆቴል አዘጋጅቷል።

ዝግጅቱ በተለይ በአእምሮ ልምሻ/ Cerbral Palsy የተጠቁ ልጆችን የሚያሳድጉ እናቶች ጥንካሬያቸውንና ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉበት በመሆኑ ይህንን ቀን አብረናቸው እንድናሳልፍ ነው ጥሪ ያቀረቡት።

"እኚህ ጠንካራ እናቶች ያልተሰበረ ጽናት፤ ያልተበገረ ማንነት ያላቸው በመሆናቸው ከምንረዳቸው በላይ የምንማርባቸው ናቸው" በማለት ዝግጅቱን ማሰናዳቱንና ማንኛው ሰው አንዲገኝ ጥሪ መደረጉን ድርጅቱ በላከልን መልዕክት ገልጿል።

ዝግጅቱ ነገ ቅዳሜ መጋቢት 09 በጊዮን ሆቴል ከቀኑ 7:00 ጀምሮ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ሰው በነጻ መሳተፍ ይችላል ተብሏል።

@tikvahethmagazine