TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሐጅ

" በዘንድሮ አመት ሐጅ ለማድረግ ዕቅድ ያላችሁ ቀድማችሁ የጉዞ ሰነዳችሁን (ፓስፖርታችሁን) ከወዲሁ ዝግጁ አድርጉ " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

የ2015/1444 አሂ የሃጅ መስተንግዶ በተሻለ መልኩ ለመስጠት ከክልልና ከተማ አስተዳደር የመጂሊስ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳውቋል።

የ2015/1444 የተከበሩ የአሏህ እንግዶች (ሁጃጆች) መስተንግዶ ቀልጣፋ ለማድረግ የተለያዪ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት የዘንድሮ የሐጅ መስተንግዶ ዘመኑን በዋጀ በአይ ሲቲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚከናወን መሆኑ ተፈልጿል።

የሁጃጆችን አንግልት ለመቀነስ መስተንግዶው በየክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤቶች አማካኝነት ይከናወናል የተባለ ሲሆን የክልል መጅሊሶች ስራቸውን ለማሳለጥ ተጨማሪ ቅርንጫፎችን እንደሚከፍቱ ተገልጿል።

ሰፊ ቁጥር የአሏህ እንግዶች (ሁጃጆች) ተመዝጋቢ የሌላቸው ክልሎች  ወደ አጎራባች ክልል እስልምና ጉዳዮች በመሄድ መስተንግዶ እንዲያገኙ አሰራሮች መዘርጋታቸውን በውይይቱ ወቅት ተመላክቷታ።

ለዘንድሮ  የሐጅ ተጓዦች ጉዞ ከማድረገቸው በፊት በሐጅ ስርዓት (መናሲከል ሐጅ) ዙሪያ በዑለሞች ስልጠና ይሰጣቸዋልም ተብሏል።

በዘንድሮ አመት ሐጅ ለማድረግ ዕቅድ ያላቸው ቀድመው የጉዞ ሰነዳቸውን (ፓስፖርታቸውን) ከወዲሁ ዝግጁ እንዲያደረጉ ጥሪ ቀርቧል።

የዘንድሮ የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ ክፍያ ከውጪ የገንዘቦች ምንዛሪ አኳያ የተወሰነ #ጭማሪ እንደሚኖረው የታወቀ ሲሆን ከቀናት በኃላ ይፋ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ

" ተማሪዎቻችንን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ ስንሆን ይፋዊ መግለጫ እንሰጣለን " - ዶ/ር ፋና ሀጎስ (የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት)

ከትላንት ምሽት አንስቶ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲን የሚመለከቱ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ።

እነዚህ መረጃዎች ፦
- ዩኒቨርሲቲው ወደ መማር ማስተማር ስራው እዲመለስ መወሰኑ፣
- በጦርነቱ አቋርጦ የነበረውን ስራ ከመጪው ሳምንት አንስቶ እንደሚጀምር፣
- በመንግስት በኩል አስፈላጊው #በጀት እንደተለቀቀለት፣
- 24 ሺህ ነባር ተማሪዎችን በቀጣይ 4 ወር ትምህርት እንዲያጠናቅቁ እንደሚያደርግ
- ከመስከረም 2016 ጀምሮ አዲስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የሚገልፁ ናቸው።

ነገር ግን ይህ የተሳሳተ መረጃ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ገልጸዋል።

መቐለ ዩኒቨርሲቲም ቢሆን በይፋዊ የፌስቡክ እና የትዊተር አካውንቱ ላይ ምንም አይነት መረጃ አልለጠፈም።

የተሰራጨውን መረጃ በተመለከተ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋና ሀጎስ ለ" ኢትዮጵያ ቼክ " መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ ዩኒቨርሲቲው ስራ ለመጀመር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየሰራ ቢሆንም በዩኒቨርሲቲው ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን የራሱን ጊዜና ሂደት እንደሚወስድ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፋና " ዩኒቨርሲቲው ሥራውን ይጀምራል ነገር ግን በሚቀጥለው ሳምንት አይደለም ፤ በእርግጥ ይህን ለማድረግ ወራትን ይወስዳል " ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፋና እስካሁን መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ጥሪ እንዳላደረገ ገልፀው " እኛ (ዩኒቨርሲቲው ወይም የትምህርት ሚኒስቴር) ተማሪዎቻችንን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ ስንሆን ይፋዊ መግለጫ እንሰጣለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

Credit : ethiopiacheck.org

@tikvahethiopia
የማመልከቻ ጥሪ

ትልቅ ህልም ያለው ሥራ ፈጣሪ ነዎት? አሁኑኑ ያመልክቱ እና ክህሎትዎን ስራ ላይ ለማዋል ፕሮግራማችንን ይቀላቀሉ። ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከኬንያ እና ከሩዋንዳ ካሉ ሥራ ፈጣሪዎች ጋር ተወዳድረው ይኽንን ትልቅ እድል ያሸንፉ፤ በሂደቱም ብዙ ይማሩ።

የማመልከቻ ጊዜ ከ ጥር 5, 2015 እስከ መጋቢት 27, 2015 ይሆናል።

ለመሳተፍ ብቁ መሆንዎን ካረጋገጡ https://jasiri.org/application ላይ ያመልክቱ።

ለበለጠ መረጃ www.jasiri.org ይጎብኙ ወይም [email protected] ወይም በስልክ 0910795506 ላይ ይጠይቁ።
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር የማለም ተግዳሮቶች ገጥመዋል " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በማለም ፤ ከተማዋንም ወደ አለመረጋጋት የማስገባት ተግዳሮቶች ገጥመዋል ሲሉ ገለፁ።

ከንቲባዋ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይህንን የገለፁት ዛሬ መካሄድ በተጀመረው የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በጉባኤው ላይ የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር እንዲሁም ከተማዋን ወደ አለመረጋጋት የማስገባት ተግዳሮቶች ገጥመዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ፤ " በተለይም ከአንዳንድ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት የፅንፈኝነት የጥላቻ ፣ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሰላምን ከማወክ ባለፈ በዘላቂነት በአብሮነት የኖረውን ህዝብ እርስ በእርስ እንዲጠራጠር ፣ እንዲለያይ ብሎም ከዚህ ያለፈ ግጭት ውስጥ እንዲገባ ብዙ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ እናስተውላለን " ብለዋል።

የከተማዋ ከንቲባ " ከአንዳንድ ክልሎች " ሲሉ ቢናገሩም የትኞቹ ክልሎች እንደሆኑ በግልፅ ሳይናግሩ አልፈዋል።

ወ/ሮ አዳነች " ከዚህም አልፎ የምንሰጠውን አገልግሎት አሰጣጥ ለከተማው ነዋሪ በተሟላ ሁኔታ ተደራሽ እንዳይሆን ስርዓት አልበኝነት እና የመሬት ወረራ እንዲስፋፋ የማድረግ ተግዳሮት መሆኑና እንዲሁም የሌብነት እና ብልሹ አሰራር ተግባር እና አስተሳሰብም ገና ባለመዳከሙ የሚስተዋሉ ችግሮች በርከት ስለሚሉ እነኚህን ለመቅረፍ ብዙ መስራት እንዳለብን እንረዳለን " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ይለግሱ !

ከየትኛውም የአለም ክፍል ሆነው ለኢትዮዽያ ቀይ መስቀል ማህበር የተቻሎትን መለገስ እንደሚችሉ ያውቃሉ ? እንግዲያውስ እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ።  የቪዛ እና ማስተር ካርድን ተጠቅመው በባንካችን የዶኔሽን ድረ ገፅ  በኩል፤ እንዲሁም አቅራቢያ የሚገኝ ቅርንጫፋችን በመሄድ በቀይ መስቀል ሂሳብ ቁጥር 907 በኩል ልገሳውን ያከናውኑ፡፡

ተከታዩን ማስፈንጠርያ በመጫን ወደ ዶኔሽን ድረ ገፅ ይግቡ https://donate.bankofabyssinia.com https://donate.redcrossredcrescent.org
#redcross #donation #mastercard #visacard #bankofabyssinia #thechoiceforall
#ሶማሊያ #ኢትዮጵያ #ኤርትራ

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ መሐሙድ " የሶማልያ እና የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ስልታዊ አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ ነኝ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ፕሬዝደንቱ ይህን የገለጹት ዛሬ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ የሹመት ደብዳቤ በተቀበሉበት ወቅት እንደሆነ የሶማሊያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ መሐሙድ ዛሬ የአምባሳደሩን የሹመት ደብዳቤ የተቀበሉት ለሥራ ጉብኝት ከተጓዙበት አስመራ ወደ ሞቃዲሾ ከተመለሱ በኃላ ነው።

ፕሬዝደንቱ በአስመራ ከኤርትራው አቻቸው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተገናኝተው መወያየታቸው ታውቋል።

ውይይቱ " የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው የቀጠናዊ ጉዳዮች " ላይ እንደነበረ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ለስራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ በተደጋጋሚ ጊዜ መጓዛቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
ብሊንከን ወደ #ኢትዮጵያ እየመጡ ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ ነገ በአዲስ አበባ ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን በዚህ ጉብኝታቸው ወቅት ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን ለማስቆም የተደረሰው ስምምነት አተገባበር እና የሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ሞሊ ፊ ብሊንከን አዲስ አበባ ላይ የትግራይ ክልል ባለሥልጣናትን አግኝተው እንደሚነጋገሩ ተናግረዋል።

ብሊንከን የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን እንደጨረሱ ወደ ኒጀር ያቀናሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር የማለም ተግዳሮቶች ገጥመዋል " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በማለም ፤ ከተማዋንም ወደ አለመረጋጋት የማስገባት ተግዳሮቶች ገጥመዋል ሲሉ ገለፁ። ከንቲባዋ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይህንን…
#Update

ዛሬ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ተከትሎ፤ ከም/ቤት አባላት ጥያቄዎች ቀርበው ነበር።

የም/ቤት አባል ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ " ከአንዳንድ ክልሎች በከፍተኛ መጠን ወደ ከተማዋ ይገባሉ " የተባሉ " ፍልሰተኞችን " በተመለከተ "ከአንዳንድ ክልሎች " የሚለው አገላለጽ ምን ማለት ነው? ክልሎቹ ቢገለጹ " ሲሉ ጠይቀዋል።

" ከአንዳንድ ክልሎች የሚመጡ ሰዎች እንደዚሁ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር አስበው ወይም ህጋዊውን መንግስት ለመገልበጥ አሲረው " በሚል የተቀመጠው ሃሳብ ያልተብራራ መሆኑንም አንስተዋል። 

• የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተከያዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

- የአደባባይ በዓላትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ረብሻ እና ሁከት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች አሉ።

- በአደባባይ በዓላት ላይ ለመፍጠር የሚፈለገው ችግር በተቀናጀ መንገድ የሚመራ ነው፤ ለዚሁ ሲባል ከክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ኃይሎች አሉ።

- ፍልሰቱ የተለመደ ነው ከሁሉም አካባቢ ሰው ይመጣል። ነገር ግን  በዓላት ሲቃረቡ የተለያየ ተልዕኮም ተሰጥቷቸው የሚመጡ አሉ። ባሳለፍነው 2 እና 3 ዓመታት የምናውቃቸው ተጨባጭ የሆኑ መረጃዎች አሉ፤ ይህ ጉዳይ በዚህ ዓመት ብቻ የታየ አይደለም።

- ሰዎች በብዛት ወደ አዲስ አበባ የሚገቡት 64 ፐርሰንት የሚሆኑ ከአማራ ክልል አካባቢ ነው፤ 21 ፐርሰንት የሚሆኑት ከደቡብ አካባቢ ነው። 14 ፐርሰንት ከኦሮሚያ ነው።

• የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ተከታዮቹ ነጥቦች አንስተዋል ፦

- በርከት ያሉ ኃይሎች ሰላም እና ጸጥታ ለማደፍረስ ወደ ከተማ ይገባሉ የመጀመሪያውን ስፍራውን የሚይዙት ከአማራ ክልል የሚገቡ ኃይሎች ናቸው፤ ከደቡብ እና ከኦሮሚያ አጎራባች ክልሎች አካባቢ ወደ ከተማዋ የሚገቡ ሰዎች በተከታታይ ደረጃ ይቀመጣሉ።

- ችግሩን በተደራጀ መልኩ ይዞ መጥቶ፤ ከተማዋን ለመበጥበጥ የሚፈልግ ኃይል አለ።

- አዲስ አበባ ውስጥ ሃይማኖት፣ ብሔር፣ ፖለቲካ እና መደበኛ ወንጀል መከላከልን ማዕከል ያደረጉ ፤ የጸጥታ መደፍረሶች አሉ። ከእነዚህ የፀጥታ ችግር መነሻዎች ውስጥ ከተማዋን በተደጋጋሚ እየፈተናት ያለው በዓላትን መነሻ ባደረጉ እና የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው ኃይሎች የሚፈጸመው ነው።

• ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ ፦

- በዓላትን ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በተመለከተ ዳታው ቅድም የተገለፀው (በፖሊስ ኮሚሽን) ነው።

- ወደ ከተማዋ የሚፈልሱት ሰዎች የሚመጡባቸውን አካባቢዎች ላይ በጣም ከፍተኛ፣ አንጻራዊ ያልሆነ መበላለጥ አለ።

- በከተማዋ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች በሙሉ ከከተማዋ ውጪ በሚመጡ ሰዎች የተፈጸሙ አይደሉም። ከተማው ውስጥ ባለው ኔትወርክ ነው። የተለያየ ጥቅም እና የፖለቲካ ትርፍን ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች ለዚሁ ቅስቀሳ አድርገዋል።

- የመንግስት ስልጣንን በህጋዊ መንገድ ያላገኙ አካላት፤ በተለያየ መንገድ እነኚህን በተለየ ሁኔታ በመቀስቀስ እና ተልዕኮ በመስጠት ወጣቶችን ወደ ጥፋት በመማገድ ላይ ተሰማርተው ታይተዋል።

- ችግሮች በሚፈጠሩበት ጊዜ የም/ቤት አባላት በምታስተላልፏቸው መልዕክቶች ላይ ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል። ችግሮች በሚፈጸሙበት ሰዓት በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች በመጻፍ፣ አነቃቂ ንግግር በሚመስል፣ በተለያየ መንገድ፤ እኛ ልንሞገስበት ህዝቡ ግን ዋጋ ሊከፍልበት የሚደረገው ድርጊት መታረም ያለበት። የምታደርጉት የምትናገሩትና የምትፈፅሙት ነገሮች የህዝብን ሰላምና ደህንነትን ያገናዘበ መሆን አለበት።

#EthiopianInsider

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ተከትሎ፤ ከም/ቤት አባላት ጥያቄዎች ቀርበው ነበር። የም/ቤት አባል ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ " ከአንዳንድ ክልሎች በከፍተኛ መጠን ወደ ከተማዋ ይገባሉ " የተባሉ " ፍልሰተኞችን " በተመለከተ "ከአንዳንድ ክልሎች " የሚለው አገላለጽ ምን ማለት ነው? ክልሎቹ ቢገለጹ " ሲሉ ጠይቀዋል። " ከአንዳንድ…
#አብን

አብን የፌዴራል መንግስቱ/ገዢው ብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከንቲባን ከስልጣን እንዲያስነሳ እና ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠየቀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ ( #አብን ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዛሬ ለምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት አጥብቆ አውግዟል።

ፓርቲው ከንቲባ አዳነች አበቤ ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ ም/ ቤት ባቀረቡት ሪፖርት " ከአንዳንድ ክልሎች የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት መንግስትን በመጣል በኃይል ስልጣን ለመቆጣጠር ያለመ ነው " ሲሉ ሪፖርት ማቅረባቸውን ከተለያዩ ሚዲያ ዘገባዎች እና ከውስጥ ምንጮቻችን አረጋግጠናል ብሏል።

ከንቲባዋ በሪፖርታቸው ይህን ማለታቸው አደገኛ ከፋፋይ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ነው ያለ ሲሆን ይህም አገረ መንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥል እና በማናቸውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው የዓለም አቀፍ ወንጀል ጥሪ ነው ሲል ገልጾታል።

አብን ፤ ዜጎች በነፃነት ተዘዋውረው የመስራት እና የመኖር ሰብዓዊ መብት ያላቸው መሆኑ ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሥምምነቶች ድንጋጌዎች እና በሥራ ላይ ባለው ሕገ-መንግስት ጭምር የተረጋገጡ ተፈጥሯዊ መብቶች ናቸው ብሏል።

ፓርቲው በመግለጫው ፤ ከንቲባዋ " የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ " እየተባለ በሚጠራው ጽንፈኛ እና በአንድ ወቅት መንግስት ራሱ " የሽብርተኞች መጠቀሚያ ነው " ብሎ በፈረጀው ሚዲያ በተከታታይ የወጡ ቅስቀሳዎች ቅጥያ የሆነ አደገኛ የወንጀል ቅስቀሳ አድርገዋል ሲል ከሷል።

" ዓለም አቀፍ ከተማን በከንቲባነት እመራለሁ ከሚል የመንግስት ባለስልጣን እንዲህ ዓይነት አደገኛ ቅስቀሳ በሪፖርትነት መሰማቱ እስካሁን ሲፈፀሙ ለነበሩ በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች እና እየታወጀ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከለላ የሚሆን አደገኛ የወንጀል ድርጊት ጥሪ ነው " ሲል ፓርቲው ገልጿል።

አብን በመግለጫው ፤ " ሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ይኼንን አደገኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ትኩረት በመስጠት አስቀድሞ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ታሪካዊ ጥሪ እያደረግን፤ በተለይ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰቡ ይኼንን ባያደርግ በሩዋንዳ የፈፀመውን ታሪካዊ ስህተት የሚደግመው መሆኑን ማስረገጥ እንሻለን " ብሏል።

በሌላ በኩል ፥ የፌደራል መንግስቱ ሆነ ገዥው የብልጽግና ፓርቲ ይኼንን አደገኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቅስቀሳ ያደረጉትን ግለሰብ ከስልጣን እንዲያነሳና ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪ እናቀርባለን ያለ ሲሆን " መሰል ድርጊት በድጋሚ እንዳይፈፀም መንግስታዊ ማረጋገጫ ጭምር እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብሊንከን ወደ #ኢትዮጵያ እየመጡ ነው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ይገኛሉ። ሚኒስትሩ ነገ በአዲስ አበባ ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን በዚህ ጉብኝታቸው ወቅት ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን ለማስቆም የተደረሰው ስምምነት አተገባበር እና የሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ…
#Update

ብሊንከን አዲስ አበባ ደርሰዋል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ብሊንከን ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በይፋዊ ጉብኝታቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia