TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኤርትራ #ሱዳን

የጎረቤት ሀገር ሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት ጄነራል ሞሀመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄመቲ) ዛሬ ሰኞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ #ኤርትራ፣ አስመራ ማቅናታቸው ተሰምቷል።

ሄሜቲ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሁሉም መስክ ግንኙነታቸውን ማሳደግና ማጎልበት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ይፋዊ ውይይት ያደርሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ደቡብ_ሲዳን

የኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ዛሬ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው #ጁባ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደቡብ ሱዳን የገቡት ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ በዝናብ 🌧 ምክንያት እየተቋረጠ የሚገኘው የሀገራችን ከፍተኛው የእግር ኳስ ውድድር !

የ " ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ " በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛው የእግር ኳስ ውድድር ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ ውድድር ማዕከሉን በአንድ ስፍራ በማድርግ ነው እየተካሄደ ያለው።

ከሰሞኑን ውድድሩ በ " ድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም " እየተደረገ ይገኛል፤ ነገር ግን ለሶስት ጊዜ ያህል በዝናብ ምክንያት ሜዳው አላጫውት በማለቱ ስለመቋረጡ ታውቋል።

ይሄ ትልቅ ውድድር በDSTV አማካኝነት መላው ዓለም ላይ የሚታይ ነው።

ህዝቧ እግር ኳስ እጅግ በጣም በሚወድባት ሀገር ኢትዮጵያ ያሉት የመጫወቻ ስፍራዎች አብዛኞቹ ደረጃቸውን ያልጠበቁና ለጨዋታ ምቹ ያልሆኑ፣ በተለይ ዝናብ / ክረምት በመጣ ቁጥር የሜዳዎቹ ገፅታ እንደ አንድ ሀገር ዜጋ አንገትን የሚያስደፉ ናቸው።

ተጨማሪ ስፖርታዊ ጉዳዮች ፦ https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar ቀጣይ የአውሳ ሱልጣኔት አልጋወራሽ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ በዓለሲመታቸዉን ለመከወን ዛሬ  የአፋር መዲና፣ ሰመራ መግባታቸውን የአፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።     ሱልጣን አህመድ አልሚራህ ሰመራ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመሬሮችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች አቀባባል አድርገዉላቸዋል።…
#AFAR

ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ 15ኛው የሀውሳ ሱልጣኔት ሱልጣን ሆነው በዓለ ሲመታቸው ዛሬ ተከናወነ።

በበዐለ ሲመቱ ላይ ፦ በርካታ ነዋሪዎች፣ በጅቡቲ እና ኤርትራ የሚኖሩ የአፋር ህዝብ ተወካዮች፣ የአርጎባ ህዝብ አመራሮች ተገኝተው ነበር።

በተጨማሪ ፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣ የአፋር ክልል ርዕሠ መስተዳደር ሀጂ አወል አርባ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት የስራ ሀላፊዎች ፣ አምባሳደሮች በበዓለ ሲመቱ ተገኝተው ነበር።

Photo Credit : Argoba Community Radio

@tikvahethiopia
#አሚጎስ_ቁጠባ_እና_ብድር

ከፍተኛ የብድር ጣሪያችንን 8.5 ሚሊዮን ብር አድርሰን በቅልጥፍና እናስተናግድዎታለን! ስለ ብድር እና የተለያዩ አገልግሎቶቻችን የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥራችን +251930086830 / +251111267657
ይደውሉ።
Telegram channel: https://t.iss.one/amigossacco
የቴሌግራም መረጃ መስጫ፡ @amigossacco
ቲክቶክ: https://tiktok.com/@amigossavingandcredit
#ሐጅ

" በዘንድሮ አመት ሐጅ ለማድረግ ዕቅድ ያላችሁ ቀድማችሁ የጉዞ ሰነዳችሁን (ፓስፖርታችሁን) ከወዲሁ ዝግጁ አድርጉ " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

የ2015/1444 አሂ የሃጅ መስተንግዶ በተሻለ መልኩ ለመስጠት ከክልልና ከተማ አስተዳደር የመጂሊስ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳውቋል።

የ2015/1444 የተከበሩ የአሏህ እንግዶች (ሁጃጆች) መስተንግዶ ቀልጣፋ ለማድረግ የተለያዪ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት የዘንድሮ የሐጅ መስተንግዶ ዘመኑን በዋጀ በአይ ሲቲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚከናወን መሆኑ ተፈልጿል።

የሁጃጆችን አንግልት ለመቀነስ መስተንግዶው በየክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤቶች አማካኝነት ይከናወናል የተባለ ሲሆን የክልል መጅሊሶች ስራቸውን ለማሳለጥ ተጨማሪ ቅርንጫፎችን እንደሚከፍቱ ተገልጿል።

ሰፊ ቁጥር የአሏህ እንግዶች (ሁጃጆች) ተመዝጋቢ የሌላቸው ክልሎች  ወደ አጎራባች ክልል እስልምና ጉዳዮች በመሄድ መስተንግዶ እንዲያገኙ አሰራሮች መዘርጋታቸውን በውይይቱ ወቅት ተመላክቷታ።

ለዘንድሮ  የሐጅ ተጓዦች ጉዞ ከማድረገቸው በፊት በሐጅ ስርዓት (መናሲከል ሐጅ) ዙሪያ በዑለሞች ስልጠና ይሰጣቸዋልም ተብሏል።

በዘንድሮ አመት ሐጅ ለማድረግ ዕቅድ ያላቸው ቀድመው የጉዞ ሰነዳቸውን (ፓስፖርታቸውን) ከወዲሁ ዝግጁ እንዲያደረጉ ጥሪ ቀርቧል።

የዘንድሮ የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ ክፍያ ከውጪ የገንዘቦች ምንዛሪ አኳያ የተወሰነ #ጭማሪ እንደሚኖረው የታወቀ ሲሆን ከቀናት በኃላ ይፋ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ

" ተማሪዎቻችንን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ ስንሆን ይፋዊ መግለጫ እንሰጣለን " - ዶ/ር ፋና ሀጎስ (የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት)

ከትላንት ምሽት አንስቶ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲን የሚመለከቱ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ።

እነዚህ መረጃዎች ፦
- ዩኒቨርሲቲው ወደ መማር ማስተማር ስራው እዲመለስ መወሰኑ፣
- በጦርነቱ አቋርጦ የነበረውን ስራ ከመጪው ሳምንት አንስቶ እንደሚጀምር፣
- በመንግስት በኩል አስፈላጊው #በጀት እንደተለቀቀለት፣
- 24 ሺህ ነባር ተማሪዎችን በቀጣይ 4 ወር ትምህርት እንዲያጠናቅቁ እንደሚያደርግ
- ከመስከረም 2016 ጀምሮ አዲስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የሚገልፁ ናቸው።

ነገር ግን ይህ የተሳሳተ መረጃ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ገልጸዋል።

መቐለ ዩኒቨርሲቲም ቢሆን በይፋዊ የፌስቡክ እና የትዊተር አካውንቱ ላይ ምንም አይነት መረጃ አልለጠፈም።

የተሰራጨውን መረጃ በተመለከተ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋና ሀጎስ ለ" ኢትዮጵያ ቼክ " መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ ዩኒቨርሲቲው ስራ ለመጀመር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየሰራ ቢሆንም በዩኒቨርሲቲው ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን የራሱን ጊዜና ሂደት እንደሚወስድ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፋና " ዩኒቨርሲቲው ሥራውን ይጀምራል ነገር ግን በሚቀጥለው ሳምንት አይደለም ፤ በእርግጥ ይህን ለማድረግ ወራትን ይወስዳል " ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፋና እስካሁን መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ጥሪ እንዳላደረገ ገልፀው " እኛ (ዩኒቨርሲቲው ወይም የትምህርት ሚኒስቴር) ተማሪዎቻችንን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ ስንሆን ይፋዊ መግለጫ እንሰጣለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

Credit : ethiopiacheck.org

@tikvahethiopia
የማመልከቻ ጥሪ

ትልቅ ህልም ያለው ሥራ ፈጣሪ ነዎት? አሁኑኑ ያመልክቱ እና ክህሎትዎን ስራ ላይ ለማዋል ፕሮግራማችንን ይቀላቀሉ። ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከኬንያ እና ከሩዋንዳ ካሉ ሥራ ፈጣሪዎች ጋር ተወዳድረው ይኽንን ትልቅ እድል ያሸንፉ፤ በሂደቱም ብዙ ይማሩ።

የማመልከቻ ጊዜ ከ ጥር 5, 2015 እስከ መጋቢት 27, 2015 ይሆናል።

ለመሳተፍ ብቁ መሆንዎን ካረጋገጡ https://jasiri.org/application ላይ ያመልክቱ።

ለበለጠ መረጃ www.jasiri.org ይጎብኙ ወይም [email protected] ወይም በስልክ 0910795506 ላይ ይጠይቁ።
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር የማለም ተግዳሮቶች ገጥመዋል " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በማለም ፤ ከተማዋንም ወደ አለመረጋጋት የማስገባት ተግዳሮቶች ገጥመዋል ሲሉ ገለፁ።

ከንቲባዋ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይህንን የገለፁት ዛሬ መካሄድ በተጀመረው የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በጉባኤው ላይ የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡ የመረጠውን ህጋዊ መንግስት በመጣል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር እንዲሁም ከተማዋን ወደ አለመረጋጋት የማስገባት ተግዳሮቶች ገጥመዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ፤ " በተለይም ከአንዳንድ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት የፅንፈኝነት የጥላቻ ፣ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሰላምን ከማወክ ባለፈ በዘላቂነት በአብሮነት የኖረውን ህዝብ እርስ በእርስ እንዲጠራጠር ፣ እንዲለያይ ብሎም ከዚህ ያለፈ ግጭት ውስጥ እንዲገባ ብዙ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ እናስተውላለን " ብለዋል።

የከተማዋ ከንቲባ " ከአንዳንድ ክልሎች " ሲሉ ቢናገሩም የትኞቹ ክልሎች እንደሆኑ በግልፅ ሳይናግሩ አልፈዋል።

ወ/ሮ አዳነች " ከዚህም አልፎ የምንሰጠውን አገልግሎት አሰጣጥ ለከተማው ነዋሪ በተሟላ ሁኔታ ተደራሽ እንዳይሆን ስርዓት አልበኝነት እና የመሬት ወረራ እንዲስፋፋ የማድረግ ተግዳሮት መሆኑና እንዲሁም የሌብነት እና ብልሹ አሰራር ተግባር እና አስተሳሰብም ገና ባለመዳከሙ የሚስተዋሉ ችግሮች በርከት ስለሚሉ እነኚህን ለመቅረፍ ብዙ መስራት እንዳለብን እንረዳለን " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia