TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አስተያየቶች
ከትላንት በስቲያ የሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በአዲስ አበባ ከተማ መከልከሉን ተከትሎ የተለየዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሀሳባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል። የቀረቡ ሀሳቦችን አንደሚከተለው አቅርበናል።
🧑💻 የባጃጅ ትራንስፖርት በመታገዱ ስለደረሱ መጉላላቶች የተሰጡ አስተያየቶች፦
- " ከለቡ ጀሞ በጣም ተቸግረናል አካባቢያችን በብዛት የነበረው ትራንስፓርት ባጃጅ ነበር ለተማሪ ሰርቪስ ብዙዎቹ ይሰሩ ነበር፤ ልጆቻችንን ት/ት ቤት የሚያደርስልን አጥተናል፣ ዕቃ ገዝተን ኮንትራት የምንይዘው(ከአትክልት ተራም ይሁን ሌላ) በባጃጅ ነበር እና አሁን ሚኒ ባስ ኮንትራት ልንይዝ ነው ? "
😓 ውሳኔው የባጃጅ አሽከርካሪዎችን ሰርቶ የመኖር መብት ስለመጋፉቱ የተሰጡ አስተያየቶች፦
" በባጃጅ ሥራ የሚተዳደር ስንት ሰው አለ! ቢያንስ እንኳ ማስጠንቀቂያ መሰጠት ነበረበት በጣም ነው የሚያሳፍረው እንደዚህ አይደረግም። "
" ብዙ ሰው በዚህ ሥራ ቤተሰብ እንደሚያስተዳድርና ኑሮውን እንደሚገፋ መንግስት ጠፍቶት ነው?! ሥራቸውንስ እየሰሩ ህግ ማስተካከል አይቻልም ነበር? ምን አይነት አሰራር ነው? "
👨💻 የውሳኔ አሰጣጡ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች፦
" ችግር ካለ ሳያግዱ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል። ማገዱ ከባጃጅ ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች በተጨማሪ ተጠቃሚውንም ለእንግልት ይዳርጋል። በዚህ ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገራችን ላይ ታግደው የተረሱ ብዙ ነገሮች አሉ ! "
- " የጅምላ ውሳኔ ይቁም። የመንግስት ኀላፊዎች እና የህግ አስከባሪዎች ደሞዝ የሚከፈላቹ ከሕብረተሰቡ በሚሰበሰብ ግብር መሆኑን አትርሱ ስራችሁን ስሩ ያጠፋውን ለዩ የሚቀጣዉንም ቅጡ። ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ማኅበራት እና አሽከርካሪዎችን በተመደበላቸዉ ቦታ ላይ እና ታሪፍ ብቻ እንዲሰሩ የሚያደርግ አስገዳጅ እና ጠንካራ ህግ አውጡ እንጂ ስራችሁን መስራት ሲያቅታቹ የፈሪ፣ የትዕቢት እና የማንአለብኝነት የጅምላ ውሳኔ አትወስኑ። "
👨💻 ውሳኔውን ተከትሎ ከዚህ ቀደም በአገልግሎቱ ላይ ስለነበሩ ክፍተቶች የተሰጡ አስተያየቶች፦
- " ቤተል-ዓለም ባንክ 0.6Km ለማትሆን መንገድ 10 ብር ያስከፍላሉ ሲመሽ ደግሞ እጥፍ ያደርጉታል፡፡ ግን ደግሞ ባጃጅ ሲታገድ ቦታውን ታክሲዎች ተረክበው በባጃጆች ዋጋ ነው እሚሰሩት፡፡ "
- " በባጃጅ ማኅበሮች ውስጥ አዲስ ባጃጅ መስመር ውስጥ ለመግባት የሚጠየቀው ገንዘብ እጅግ በጣም የተጋነነ ለዚያውም ግለሰቦች ኪስ የሚገባ ገንዘብ ነው "
- " አንዳንድ ባጃጆች ከሚሰጡት አገልግሎት ይልቅ ሌብነትና ዝርፊያ ላይ ተሰማርተዋል። በትንሽ ነዳጅ ብዙ ርቀት የሚሄዱ ሲሆን ለትንሽ ርቀት ከሚኒባስ በላይ ሁለትና ሶስት እጥፍ እያስከፈሉ ያሰቃዩናል። "
@tikvahethiopia
ከትላንት በስቲያ የሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በአዲስ አበባ ከተማ መከልከሉን ተከትሎ የተለየዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሀሳባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል። የቀረቡ ሀሳቦችን አንደሚከተለው አቅርበናል።
- " ከለቡ ጀሞ በጣም ተቸግረናል አካባቢያችን በብዛት የነበረው ትራንስፓርት ባጃጅ ነበር ለተማሪ ሰርቪስ ብዙዎቹ ይሰሩ ነበር፤ ልጆቻችንን ት/ት ቤት የሚያደርስልን አጥተናል፣ ዕቃ ገዝተን ኮንትራት የምንይዘው(ከአትክልት ተራም ይሁን ሌላ) በባጃጅ ነበር እና አሁን ሚኒ ባስ ኮንትራት ልንይዝ ነው ? "
" በባጃጅ ሥራ የሚተዳደር ስንት ሰው አለ! ቢያንስ እንኳ ማስጠንቀቂያ መሰጠት ነበረበት በጣም ነው የሚያሳፍረው እንደዚህ አይደረግም። "
" ብዙ ሰው በዚህ ሥራ ቤተሰብ እንደሚያስተዳድርና ኑሮውን እንደሚገፋ መንግስት ጠፍቶት ነው?! ሥራቸውንስ እየሰሩ ህግ ማስተካከል አይቻልም ነበር? ምን አይነት አሰራር ነው? "
" ችግር ካለ ሳያግዱ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል። ማገዱ ከባጃጅ ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች በተጨማሪ ተጠቃሚውንም ለእንግልት ይዳርጋል። በዚህ ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገራችን ላይ ታግደው የተረሱ ብዙ ነገሮች አሉ ! "
- " የጅምላ ውሳኔ ይቁም። የመንግስት ኀላፊዎች እና የህግ አስከባሪዎች ደሞዝ የሚከፈላቹ ከሕብረተሰቡ በሚሰበሰብ ግብር መሆኑን አትርሱ ስራችሁን ስሩ ያጠፋውን ለዩ የሚቀጣዉንም ቅጡ። ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ማኅበራት እና አሽከርካሪዎችን በተመደበላቸዉ ቦታ ላይ እና ታሪፍ ብቻ እንዲሰሩ የሚያደርግ አስገዳጅ እና ጠንካራ ህግ አውጡ እንጂ ስራችሁን መስራት ሲያቅታቹ የፈሪ፣ የትዕቢት እና የማንአለብኝነት የጅምላ ውሳኔ አትወስኑ። "
- " ቤተል-ዓለም ባንክ 0.6Km ለማትሆን መንገድ 10 ብር ያስከፍላሉ ሲመሽ ደግሞ እጥፍ ያደርጉታል፡፡ ግን ደግሞ ባጃጅ ሲታገድ ቦታውን ታክሲዎች ተረክበው በባጃጆች ዋጋ ነው እሚሰሩት፡፡ "
- " በባጃጅ ማኅበሮች ውስጥ አዲስ ባጃጅ መስመር ውስጥ ለመግባት የሚጠየቀው ገንዘብ እጅግ በጣም የተጋነነ ለዚያውም ግለሰቦች ኪስ የሚገባ ገንዘብ ነው "
- " አንዳንድ ባጃጆች ከሚሰጡት አገልግሎት ይልቅ ሌብነትና ዝርፊያ ላይ ተሰማርተዋል። በትንሽ ነዳጅ ብዙ ርቀት የሚሄዱ ሲሆን ለትንሽ ርቀት ከሚኒባስ በላይ ሁለትና ሶስት እጥፍ እያስከፈሉ ያሰቃዩናል። "
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
" ባጃጅ ታግዷል " በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነገ የካቲት 30 ጀምሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ታገደ። ከነገ ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ አገልግሎት መታገዱን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ " የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት እንዲያስችል አሰራር ማሻሻያ ስራዎችን…
#ባጃጅ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች / ባጃጅ መታገዱን በተመለከተ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አጭር ማብራሪያ ሰጥቷል።
በማብራሪያው ፤ " መንግስት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን #የነዳጅ_ድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረጉ እየታወቀ የባለሶስት ጎማ ወይም በተለምዶ አጠራራቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ እንዲሁም የተወሰኑት በወንጀል ድርጊቶች ላይ በመሰማራት የከተማችን ነዋሪ የቅሬታ ምንጭ ሆነዋል " ብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ የባጃጅ አገልግሎትን ስርዓት ለማስያዝ የአሰራር ማስተካከያ እያደረገ መሆኑን ገልጾ ይህ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ በከተማድ ሁሉም አካባቢዎች የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት #እንዲቆም መወሰኑን ገልጿል።
የተሸርካሪዎቹ ከስራ መውጣት በነዋሪው ላይ የትራንስፖርት ጫና እንዳያሳድር አስተዳደሩ ሌሎቹ የትራንስፖርት አገልግሎቶች በሙሉ አቅማቸውና በቅንጅት አገልግሎት የሚሰጡበትን ሁኔታ መመቻቸቱን አመላክቷል።
(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሌሎች ጉዳዮችንም ያነሳበት የዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#Update #UAE በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት…
" ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ ይቆያሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር
የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ/ም ፤ በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የላቀ ውጤት ላመጡ 273 ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የእዉቅናና ሽልማት ማበርከታቸውና በዕለቱ ለተማሪዎቹ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የውጭ የትምህርት ዕድል መገኘቱን መግለፃቸው ይታወሳል።
ከዚህ የትምህርት እድል ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የትምህርት እድሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ጥረት የተገኘ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ተማሪዎቹ ከመስከረም/2016 ዓ/ም ጀምሮ እንዲማሩ መመቻቸቱን ገልጿል።
ተማሪዎቹ ወደዉጪ እስኪሄዱ ድረስ ያሉትን ግዜያት #የእንግሊዝኛ_ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት በመማርና ሌሎች ለወደፊታቸዉ የሚያግዙ ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረጉ እንዲቆዩ የሚሰራ መሆኑን ገልጿል።
የተፈጠረዉ የትምህርት ዕድል ለተማሪዎቹም እንዲሁም እንደ አጠቃላይ ለሀገር በጣም ጥሩ እድል መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ነገር ግን ዕድሉ ለተፈጠረላቸዉ ተማሪዎች #እንደግዴታ የሚወሰድ አይደለም ሲል አሳውቋል።
ተማሪዎቹ መማር የምፈልገዉ በሀገር ዉስጥ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ነዉ ብለዉ ካሰቡ የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሌለ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በተባበሩት ኤሜሬትስ በየትኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ሊማሩ ይችላሉ ?
- የተባበሩት አርብ ኤምሬትስ ዩኒቨርስቲ ፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ 284ኛ ላይ ሲገኝ በአረብ ወሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ዉሰጥ ደግሞ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። መቀመጫውንም አል አይን በተባለችው የአቡ ዳቢ ከተማ ሲሆን ካሉት ዩኒቨርስቲዎችም በእድሜ ትንሹ ነው።
- አሜሪካን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ ፦ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዉስጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች በሰባተኛነት የተቀመጠ ሲሆን የሚሰጣቸው የትምህርት አይነቶችም በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል መሰረት ነው። በዓለም አቀፍ ተማሪዎችም ተመራጭ የሆነ ዩኒቨርስቲ ነው።
- ካሊፋ ዩኒቨርስቲ ፦ በአለም አቀፍ ደረጃ 211ኛ ላይ ሲገኝ በ2021 በተሰጠው የዩኒቨርስቲዎች ደረጃ ደግሞ በአረብ ዉሰጥ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ውሰጥ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ለትርፍ ያልተቋቋመ ትኩረቱን ሳይንስ ላይ አደረጎ በ2007 የተመሰረተ ዩኒቨርሰቲ ነው። ዩኒቨርሰቲው በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ሞዴል የተቃኘም ጭምር ነው። በውሰጡ ሶሰት ኮሌጆች፣ ሶሰት የምርምር ኢኒስቲቲዩቶች፣ 18 የምርምር ማእከላት እና 36 ዲፓርትመንቶችን በተለያዩ የትምህርት መሰኮች ይዟል።
- ዪኒቨርስቲ ኦፍ ሻርጃ ፦ በ1997 የተቋቋመ ሲሆን በመካከለኛው እሩቅ ምሰራቅ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የትምህርት ተቋም ለመሆን አልሞ እየሰራ ያለ ዩኒቨርሰቲ ነው።
- ዛይድ ዩኒቨርስቲ ፦ በ1998 የተመሰረተና በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ስመ ጥር የሆነ ዩኒቨርሲቲ ነው።
https://www.topuniversities.com
#ትምህርት_ሚኒስቴር

#አሁን
የኢፌዴሪ ብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር የቀድሞ ተዋጊዎችን የመልሶ ማቋቋም ሂደት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በመቐለ እያካሄደ ይገኛል።
ፎቶ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን / ድምፂ ወያነ

" አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን " - ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ
ጎረቤት ሀገር ኬንያ በትምህር ቤቶች ውስጥ ተንሰራፍቷል ያለችውን " የተመሳሳይ ጾታ " አጀንዳ ላይ ዘመቻ መጀመሯ ታውቋል።
የኬንያ የትምህርት ሚንስትር ኢዚኬል ማቾጉ ፥ " በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች አጀንዳ ሰርጎ ገብቷል " ሲሉ ለአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተናግረዋል።
ሚንስትሩ በት/ ቤቶች ውስጥ " የተመሳሳይ ጾታ አጀንዳን " ለማስቀረት በኬንያ አንጀሊካን ቤተ-ክርስቲያን የሚመሩ ጉዳዩን የሚከታተሉ ሰዎች ይሾማሉ ብለዋል።
በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚከታተል ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው #መማሪያ እና #አጋዥ_መጽሐፍትን መከለሰን ሊያካትት እንደሚችል ትምህር ሚንስትሩ ገልጸዋል።
ይህ የኬንያ ትምህርት ሚንስቴር እቅድ የተሰማው ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ " የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አደጋ ፈጥሯል " በማለት በመላው ኬንያ #ጸሎት_እንዲደረግ ካወጁ በኋላ ነው።
የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባለቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ቤተሰብ በሚባለው ተቋም ላይ አደጋ ደቅኗል " ብለዋል።
ቀዳማዊት እመቤቷ ፤ " አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በአፍሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት የለውም። የቤተሰብ እሴቶችን እንጠብቅ " ብለዋል።
የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ኬንያ ውስጥ #ሕጋዊ_አይደለም።
የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚቃወሙ አመለካከቶች ባለፉት ቀናት ጠንከር ብለው መታየታቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።
ፎቶ ፦ ፋይል (ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ)

#TeklehaimanotGeneralHospital
ማርች 8 የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ከ የካቲት 29 እስከ መጋቢት 6 የእርግዝና ክትትል ለሚጀምሩና ለሚወልዱ ነፍሰጡር እናቶች ልዩ ልዩ ስጦታዎችና እስከ ወሊድ ጊዜያቸዉ የሚቆይ የ 25% ቅናሽ በሁሉም አገልግሎታችን ላይ ማድረጋችንን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነዉ።
ተክለሀይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል
Facebook: https://www.facebook.com/teklehaimanothospital
Instagram: https://www.instagram.com/teklehaimanotgeneral
Telegram: https://t.iss.one/teklehaimanothospital
LinkedIn: https://www.linkedin.com/.../teklehaimanot-general-hospital/
Twitter: https://twitter.com/TeklehaimanotG4
Website: www.teklehaimanothospital.com
E-mail: [email protected]

ይኽን አስተውለው ያውቃሉ?
- በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መስማት የተሳናቸው ወገኖቻችን ይገኛሉ።
- ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የምልክት ቋንቋ ባለቤት ናት፤ ይህ ማለት ይህንን ቋንቋ ሚሊዮኖች ይናገሩታል ማለት ነው።
- ቋንቋ መግባቢያ ሲሆን የምልክት ቋንቋም እንደማንኛውም ቋንቋ ከሰዎች ጋር የምንነጋገርበት፤ የምንግባባበት ነው።
እጆች ይናገራሉ .... አይኖች ያዳምጣሉ ስንል፦
- በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያለው ይኽ ቋንቋ በፖሊሲም ሆነ በአፈጻጸም ትኩረት እንዲሰጠው፤
- መስማት የተሳናቸው ዜጎች ከሌሎች ዜጎች እኩል የመስራትና የመማር እድል እንዲፈጠርላቸው፥ እንዲሁም በወረቀት የተከበረላቸው ህጎች በተግባር እንዲተገበሩ፤
- መንግስትም ሆነ ህብረተሰቡ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች በተለይም ለሴቶች በቂ ትኩረት እንዲሰጥ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ነው።
#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ
@tikvahethiopia @RWethiopia