TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray
በሽረ ከተማ የሚገኘው መናኸሪያ መቐለ ጨምሮ ወደ ተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጋዮችን እና የመናኸሪያውን የስራ ኃላፊዎች ዋቢ በማድረግ ኢዜአ ዘግቧል።
ተጓዦች በጦርነቱ ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ በመቆየቱ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው እንደነበር ገልጸዋል።
የፌደራል መንግስት ከህወሓት ጋር የሰላም ስምምነት መድረሱን ተከትሎ ግን መቐለን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስረድተዋል።
የተፈጠረው ሰላም ከፍተኛ እፎይታና ደስታ እንደፈጠረላቸው ጠቁመዋል።
የሽረ ከተማ መናኸሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ተክላይ ገብረየሱስ በበኩለቸው ፤ የሽረ መናኸሪያ መቐለን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ለሚንቀሳቀሱ የህዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች ስምሪት እየሰጠ ነው ብለዋል።
የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መጀመሩ አሽከርካሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ፣ ተሳፋሪዎች ደግሞ ወደ ሚፈልጉት ከተማ እንዲንቀሳቀሱ ማስቻሉን አንስተዋል።
የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማሳለጥ መንግስት ነዳጅ እያቀረበ መሆኑን ጠቁመው፥ በቀጣይ ለህብረተሰቡ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የጀመሩትን ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ይደረጋል ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።
#ኢዜአ
@tikvahethiopia

👍622🕊77👎31🙏16❤7😢6🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌግራም፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ መሰል የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ ገደብ ከተደረገባቸው ዛሬ 19ኛ ቀን ተቆጥሯል። የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ " ለምን ገደብ እንደተጣለ " እንዲሁም " ገደቡ መቼ እንደሚነሳ " በየትኛውም አካል በኩል ለህዝብ ማብራሪያም ሆነ ገለፃ ያደረገ የለም። ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛዎች…
" መንግስት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለውን ገደብ ያንሳ " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙት ላይ የጣለው ገደብ ሚዲያዎች ስራቸውን በአግባቡ ለህዝቡ ተደራሽ እንዳያደርጉ እንቅፋት እየፈጠረ በመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ መጠየቁን ለቲክቫህ በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡
ከሰሞኑን መንግስት በአንዳንድ የኢንተርኔት የግንኙነት መተግበሪያዎች ላይ የጣለው ገደብ መገናኛ ብዙሃን መረጃ የማሰባሰብ፤ የማደራጀትና ተደራሽ የማድረግ ላይ ተግዳሮት ከመፍጠሩ ባሻገር የሰበሰቡትን መረጃ በሀገርና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ተደራሲያን ኢንተርኔትን እንደ ዋነኛ የመረጃ ማሰራጫ የሚጠቀሙ መገናኛ ብዙሃን ስራቸውን በአግባቡ ለመከወን መቸገራቸውን በመግለጫው ተመላክቷል።
በመሆኑም ሰሞኑን በሀገሪቱ ከተፈጠረው ኃይማኖታዊ አለመግባባቶች ጋር በተያያዘ የችግሩን ስፋትና ክብደት ከግምት በማስገባት ሊቀለበስ የማይችል አደጋን ምክንያት በማድረግ ካልሆነ በስተቀር ሕግን መሰረት በማድረግ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ መንግስት ገደብ ሊያደርግ እንደማይገባ ምክር ቤቱ እንደሚያምን አሳውቋል።
ከዚህ አንፃር በአንዳንድ የኢንትርኔት መረጃ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች ላይ የተጣለው ገደብ ሶስት ሳምንታትን ያስቆጠረ ከመሆኑም በላይ ገደቡ የተደረገበትን ምክንያት የሚመለከተው መንግስታዊ አካል የሰጠው ግልጽ ማብራሪያ ባለመኖሩ የጠቅላላ ህዝቡን መረጃ የማግኘትና የማሰራጨት መብት ላይ ገደብ ለመጣል የሚያበቃ አማራጭ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት ገልጿል።
ም/ቤቱ ገደቡ እንዲነሳ በይፋ ጥሪ አቅርቧል።
#NB. በማህበራዊ መገናኛዎች (ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ዩትዩብ...) ላይ ገደብ ከተጣለ ዛሬ 24ኛ ቀን ሆኗል።
More : @tikvahethmagazine

👍3.06K👎201❤49🕊45🙏32🤔25😢23🥰11😱7
#ብርሃን_ባንክ
የገንዘብ እንቅስቃሴዎን ቀላል እና ምቹ ለማድረግ የቪዛ እና ማስተር ካርድዎን እንዲሁም የብርሃን ባንክ ካርድዎን ይጠቀሙ!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!

👍124👎101🤔5❤2🥰1
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል
ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው መማር ለሚቸገሩና የመግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የኢመርጀርሲ ሜዲካል ቴክኒሽያን ባለሙያ ደረጃ 4 ውስን ሰልጣኞችን ተቀብሎ የነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማመቻቸቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በላከው መልዕክት አሳውቋል።
የመግቢያ መስፈርቶች ፦
1. ከ2011 - 2013 ባለው የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁና ውጤታቸው ለወንዶች ከ293 በላይ ለሴቶች ከ278 በላይ ያመጡ፡፡
2. የ2014 ዓ.ም (በ2015 ዓ.ም ) ፈተና ለወሰዱ
ሀ.ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ለወንዶች ከ158 በላይ ለሴቶች ከ157 በላይ፤
ለ. ለሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ለወንዶች 149 በላይ ለሴቶች ከ145 በላይ ውጤት ያለቸው
3. ዕድሜ ከ30 ዓመት ያልበለጠ/ያልበለጠች፡፡
4. የኮሌጁን መግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል፡፡
5. ከፍለው ለመማር የማይችሉ መሆኑን የሚገልጽ ከሚኖሩበት ቀበሌ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. ለሴት ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ ይሰጣል
7. ስልጠናውን ለ20 ወራት በመደበኛ ፕሮግራም የሚሰጥ በመሆኑ ሙሉ ጊዜውን ለስልጠናው ለመጠቀም ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች፡፡
የምዝገባ ጊዜ ከየካቲት 27 - መጋቢት 2/2015 ዓ.ም ድረስ ከላይ መስፈርቱን በሟሟላት በጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ በመገኘት መመዝገብ ትችላላችሁ። ( 👉 አድራሻውን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ)
ለምዝገባ ሲመጡ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ትራንስክሪፕት፤ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በ8035 ወይም 0943302400 /0923514151 በስራ ሰዓት መደወል ይቻላሉ።

👍667👎19❤18😢12🕊8🤔3🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የንግድ ሱቆች ጨረታ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል "
በአዲስ አበባ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ ለጨረታ ከቀረቡ 5,397 የንግድ ቤቶች ውስጥ ከሰነድ ሽያጭ ብቻ 21.5 ሚሊየን ብር መሰብሰቡ አሳወቀ።
በ11 ሳይቶች በሚገኙ 5397 የንግድ ሱቆች ሽያጭ 52,614 የጨረታ ሰነድ የተሸጠ ሲሆን ከሰነድ ሽያጭ ብቻ 21.5 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል ተብሏል።
ከሱቆቹ ሽያጭ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ይገኛል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ገንዘቡ ከተማ አስተዳደሩ ለግንባታ ወጪ ያለበትን የቦንድ ብድር የሚቀንስበት እንደሚሆን ተገልጿል።
በአዲስ አበባ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለ9 የስራ ቀናት ተጫራችች በተገኙበት ሲከፍት የቆየውን የንግድ ሱቆች ጨረታ ትላንት በ24/06/2015 ዓ.ም አጠናቋል።
የንግድ ሱቆች ጨረታ ውጤቱን በቅርቡ በጋዜጣ እና በተቋሙ ማህበራዊ ሚዲያ ይፋ የሚያደርግ ተገልጿል።

👍637👎242❤27😱19😢14🤔13🥰7
አቢሲንያ ባንክ ፦
ውድ ደንበኞቻችን !
በአቢሲንያ ባንክ ስም በተከፈተ ሀሰተኛ ድረ ገፅ አማካኝነት፣ ባንካችን ያለ መያዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝና፣ ብድር ፈላጊዎች አስቀድመው ገንዘብ በማስገባት የብድር ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች መረጃ እየተላለፈ ይገኛል፡፡
ነገር ግን ይህ ሀሰተኛ መረጃ በመሆኑ ከዚህ እና ከመሰል የተሳሳቱ መረጃዎች እንዲሁም ማጭበርበሮች እንድትጠነቀቁ እያሳሰብን፣ የባንካችንን ትክክለኛ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን የሚከተሉት እንደሆኑ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
የአቢሲንያ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች
Website: https://www.bankofabyssinia.com/
Telegram: https://t.iss.one/BoAEth
Facebook: https://www.facebook.com/BoAeth/
Instagram: https://www.instagram.com/abyssinia_bank/
Twitter: https://twitter.com/abyssiniabank
TikTok: https://www.tiktok.com/@abyssinia_bank
YouTube: https://www.youtube.com/@abyssinia_bank
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/

👍307👎15🤔6😱6😢5🕊5❤4🙏4🥰3
#Repost
የካራማራ ድል !
የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበትና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት ቀን ነው።
ዘንድሮ ይህ ድል 45ኛ አመት ሞልቶታል ቀኑም እየታሰበ ነው።
ከጦርነቱ በፊት ለረጅም ጊዜ የሶማሊያ ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅነት ነበረው። በወቅቱ አሜሪካ እና የሶቪየት ህብረት በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ ነበሩ።
በቅድሚያ በሶቪየት ህብረት ከፍተኛ ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ ካራማራ ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሶል፡፡
በጦርነቱ መጀመሪያ ሶማሊያን ስትደግፍ የነበረችው ሶቪየት ህብረት ወደ ኢትዮጵያ አዘንብላ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ አድርጋለች ፤ አሜሪካ ደግሞ ወደ ሶማሊያ ፊቷን አዙራለች።
በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመንና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል።
ከ16 ሺ በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። ደቡብ የመንም ጦሯን ለኢትዮጵያ አሰልፋ ነበር።
በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው የዚያድባሬን ጦር የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያ አንድነት ዳግም በጉልህ የታየበት ስለመሆኑ ይነገርለታል፡፡
በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የ " ካራማራ ድል " ዘንድሮም ለ45ኛ ጊዜ እየታሰበ ይገኛል፡፡
https://telegra.ph/Ethiopia-03-05

👍1.93K❤163👎39🕊30🙏27🥰12🤔11😱8😢8
' ሰላተል ኢስትስቃ '
ነገ በመላ ሀገሪቱ "ሰላተል ኢስ ትስቃ" እንዲሰገድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጥሪ አቅርቧል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቦረና ዞን በዝናብ እጥረት ምክንያት የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ " ሰላተል ኢስ ትስቃ " እንዲሰገድ ለመላው ምዕመን ጥሪ አድርጓል።
ነገ ሰኞ በመላው ሀገሪቱ እንዲሰገድ ጥሪ የቀረበው " ሰላተል ኢስትስቃ " ዝናብ በሚርቅበት ጊዜ የሚሰገድ ሰላት መሆኑን ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በሌላ በኩል ፤ ጠቅላይ ም/ቤቱ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን ዕርዳታ የሚውል ድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጎ ድጋፍ እያሰባሰበ እንደሆነ ተሰምቷል።
ጠቅላይ ም/ቤቱ ይፋ ያደረጋቸው የባንክ ቁጥሮች ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 5582 ፣ ዳሸን ባንክ ሂሣብ ቁጥር 795571270973፣ ዘምዘም ባንክ ሂሣብ ቁጥር 222255፣ ሂጅራ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 308010 ፣ ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ቁጥር 1000093406226 ናቸው።

👍3.31K👎309❤279🙏141🕊45🥰42🤔39😢25😱22
" ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን " - የዳዋ ዞን አስተዳደር
በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን አስተዳደር ባጋጠመ ድርቅ በርካታ እንስሳት የሞቱ ሲሆን የሰዎች ሕይወትም አደጋ ላይ መውደቁ ተገልጿል።
የዞኑ አስተዳደር ያለው ሁኔታ ከአቅም በላይ መሆኑን አስታውቋል።
ከኦሮሚያ የቦረና ዞን ጋር የሚዋሰነው ዞኑ፣ በድርቅ የተነሳ ከሚሞቱ እንስሳት አልፎ ሰዎች #ለሆስፒታል እየተዳረጉ መሆኑን ገልጿል፡፡
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሀቢቻ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦
" የድርቁ ጉዳት ከዞኑ አቅም በላይ ነው።
ዞናችን ከቦረና ጋር በሁለት ወረዳዎች በኩል ይዋሰናል፡፡ ወደ 700 ሺሕ የሚጠጋ አርብቶ አደር ነዋሪ ያለው ሲሆን፣ ለ3 ተከታታይ ዓመታት የደረሰው ድርቅ ከብቱን በሙሉ ጨርሶበታል።
በክልሉ አደጋ ሥጋት ቢሮና በተለያዩ የዕርዳታ ድርጅቶች ርብርብ ዘንድሮ ለድርቁ ተጎጂዎች ዕርዳታ እየቀረበ ነው ይሁን እንጂ ዕርዳታው በቂ አይደለም። ችግሩም ከአቅም በላይ ነው።
በኦሮሚያ ክልል ለሚገኘው ለአጎራባቻችን ቦረና ዞን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንዳለው ሁሉ፣ ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን። "
ዳዋ ዞን በሥሩ ሞያሌ፣ ሙባረክ፣ ካደዱማና ሁደት የተባሉ አራት ወረዳዎች ያሉት ሲሆን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ዝናብ ባለማግኘቱ ትልቁ የዳዋ ወንዝ ጭምር ደርቋል።
ድርቅ የሚቋቋሙ ግመሎችን ጨምሮ ከብቶችና ፍየሎች በከፍተኛ ቁጥር ማለቃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

😢2.41K👍767🙏117❤60🕊35😱21🤔15🥰14
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ATTENTION
" ለሕዝቡ አስቸኳይ ዕርዳታ ካልደረሰለት አደጋው ከአሁኑ ሊብስ ይችላል "
በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሀቢቻ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦
" ሕዝቡ የሚኖረው በከብቶቹ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ ድርቁ እስከ መቼ እንደሚቀጥል አይታወቅም፡፡
ለሕዝቡ አስቸኳይ ዕርዳታ ካልደረሰለት አደጋው ከአሁኑ ሊብስ ይችላል።
የሞተውን የእንስሳት ሀብት ቁጥር ገና እየተጠና ነው፤ በሰዎች ላይ የደረሰውንም ጉዳት እየተገመገመ ነው።
ስለጉዳቱ የተጣራ አኃዝ ባይኖረንም በምግብ እጥረት ችግር ወደ ሆስፒታል የገቡ ሰዎች መረጃ አለን። "
NB. አምና በሶማሌ ክልል ካሉ 11 ዞኖች በአሥሩ ከባድ የድርቅ አደጋ ደርሶ #ከአንድ_ሚሊዮን ያላነሱ እንስሳትን ገድሏል። የዳዋ ዞን ገና ከዚህ አደጋ ያላገገመ ሲሆን ዘንድሮም ከባድ አደጋ ገጥሞታል።
Credit : #Reporter

😢577👍292🙏17🤔4😱4❤3🕊3🥰1