TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዓድዋ

እንኳን ለ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ቀን በሰላም፣ በፍቅር እና በጤና አደረሳችሁ !!

" ዓድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእነርሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች " - ጂጂ

መልካም የድል በዓል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ !!

@tikvahethiopia
የዓድዋ በዓል በአዲስ አበባ ?

ዛሬ የዓድዋ ድል በዓል በመላው ሀገሪቱ እየተከበረ ነው።

በመዲናዋ በሚገኘው የአፄ ሚኒሊክ ሀውልት ግን እንደ ከዚህ ቀደሙ እንዳልነበር ወደ ስፍራው የሄዱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ አንድ የቤተሰባችን አባል እንዲህ ሲል ዛሬ ጥዋት የተመለከተው አስረድቷል፦

" በመጀመሪያ ከጥቁር አንበሳ ጀምሮ ቀይ ለባሾች፣ አድማ በታኞች እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከታች ወደ ላይ እየተመላለሱ ህዝቡን ሲቃኙ ነበር።

ህዝቡ በብዛት ወደ ምኒሊክ ሃውልት እንደወትሮ እየሄደ ነበር፤ እኔም እንደ ድሮው መስሎኝ እስከ ሃውልቱ ድረስ ሄጃለሁ።

እዛ ስንደርስ ግን ድሮ ሚደረጉ የነበሩ ፕሮግራሞች ምንም አልነበሩም። ፌዴራሎች ሀውልቱን ከበው መንገዱን ዘግተው ነበር።

ህዝቡ መበሳጨት ጀምሮ 'ይሄ ነው ንጉሱ' እያለ መጨፈር ጀመረ አልፎ አልፎም ' ሿ ሿ እያለ ድምፁን ያሰማል። ጥቂት ቆይቶ ቀይ ለባሾች እና ፌደራሎች አዲስ ከሚሰራው ዓድዋ ህንፃ እና ማዘጋጃ መሃል ይመጡ የነበሩ ሰዎችን አስቆሙ።

እኔ ቀድሜ ደርሼ ስለነበር ወደ ምኒልክ አደባባይ ተጠግቶ የተቆረጠው ህዝብ ውስጥ ነበርኩኝ፤ የአድማ በተና መኪና ሲጠጋ ሳይ ጥግ ይዤ ወደ ሀውልቱ እንዳይደርስ የተቆረጠው ህዝብ ጋር ተቀላቀልኩ፤ ወዲያድ መተኮስ ተጀመረ ህዝቡም መሮጥ ጀመረ።

ከላይ የላኩት ቪድዮ እና ፎቶ ቸርቸል ከወርድኩ በኃላ የቀረፅኩት ነው። "

በሌላ በኩል፤ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በዓሉ በምኒልክ አደባባይ መከበሩንና ባለስልጣናት የአበባ ጉንጉን ማኖራቸውን ዘግበዋል።

ከዚህ ባለፈው በዓሉ በዓድዋ ድልድይ ስለመከበሩ አመልክተወዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዓድዋ በዓል በአዲስ አበባ ? ዛሬ የዓድዋ ድል በዓል በመላው ሀገሪቱ እየተከበረ ነው። በመዲናዋ በሚገኘው የአፄ ሚኒሊክ ሀውልት ግን እንደ ከዚህ ቀደሙ እንዳልነበር ወደ ስፍራው የሄዱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። ጉዳዩን በተመለከተ አንድ የቤተሰባችን አባል እንዲህ ሲል ዛሬ ጥዋት የተመለከተው አስረድቷል፦ " በመጀመሪያ ከጥቁር አንበሳ ጀምሮ ቀይ ለባሾች፣ አድማ በታኞች እና የፌዴራል…
#ዓድዋ

ዛሬ በምኒሊክ አደባባይ አካባቢ ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያያዘ ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ሰሜን ሆቴል አካባቢ ወደ ምኒሊክ አደባባይ እና ወደ ቅዱስጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ማለፍ ተከልክሎ እንደነበር ገልጿል።

" አስለቃሽ ጭስ እና ድንጋይ ውርወራ ነበር " ያለው ይኸው ቤተሰባችን አባል አንዳንድ ወጣቶች ላይም ድብደባ ተፈፅሟል " ሲል አስረድቷል።

በተመሳሳይ ፤ ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ዛሬ የፌደራል ፖሊሶችና አድማ በታኞች ወደ ጊዮርጊስ መስመር የሚሄደውን ሰዉ ከሰሜን ሆቴል እና ከዮሀንስ ቤ/ክ አካባቢ ማለፍ አይቻልም በሚል እየመለሱ እንደነበር ገልጿል።

እስካሁን #በመንግስት_አካላት በኩል በምኒልክ አደባባይ ስለነበረው እና ስለተፈፀመው ሁኔታ ማብራሪያ አልተሰጠም።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የድል በዓሉ በአደባባዩ መከበሩን በስፋት ዘግበዋል።

#ዓድዋ127

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ 127ኛው #የዓድዋ_ድል_በዓል በመስቀል አደባባይ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የፀጥታ ኃይል አባላት፣ ከፍተኛ የመንግስት  ባለስልጣናት በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

ለየት ባለ ሁኔታም በበዓሉ ላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ ትርኢት አሳይተዋል።

Photo Credit : Ethiopian Press Agency

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ ዛሬ እየተከበረ በሚገኘው 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ላይ #የኢትዮጵያ 🇪🇹 የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጥቅም ላይ ያዋላቸውን ቀላል እና ከባድ የጦር መሳሪያዎች በመስቀል አደባባይ በነበረው ትርኢት ላይ አሳይቷል።

Photo Credit : EBC

@tikvahethiopia