ፎቶ ፦ በትግራይ በነበረው ጦርነት ምክንያት የማምረት ስራውን አቁሞ የነበረው " ሞሃ የለስላስ መጠጥ ምርቶች ፋብሪካ " #የመቐለ ቅርንጫፍ ዳግም ስራ መጀመሩን ድምፂ ወያነ ዘግቧል።
በጦርነቱ ምክንያት ፋብሪካው ላለፉት ሁለት አመታት ስራ በማቆሙ ከ400 ሚልዮን ብር በላይ ለሆነ ኪሰራ መዳረጉ ተነግሯል።
ከዚህ ባለፈ የፋብሪካው ሰራተኞቹ ለከፋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጋልጠው መቆየታቸው ተገልጿል።
የፋብሪካው ዳግም ስራ በመጀመር በጦርነቱ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው ለቆዩት የተቋሙ ሰራተኞች ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን የፋብሪካው አመራሮች እና ሰራተኞች መናገራቸውን ድምፂ ወያነ ዘግቧል።
Photo Credit : Demtsi Weyane
@tikvahethiopia

" 1 ዓመት ከ8 ወር ተፈርዶበታል "
የ12 አመት ህፃን ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ዲያቆን ጌታቸው ላይ የ1 ዓመት ከ8 ወር የእስራት ቅጣት ተወሰነበት።
በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ወጣት ላይ የ1 ዓመት ከ8 ወር የእስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አሳውቋል።
ተከሳሽ ዲያቆን ጌታቸው አለልኝ የተባለው ግለሰብ አግባብ ባለው የቤተሰብ ህግ ከተፈቀደው ውጭ ለአካለ መጠን ያልደረሰች ልጅ ለማግባት በማሰብ ጥር 6/2015 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 11፡0ዐ ሲሆን በግ/ወይን ከተማ ዐ1 ቀበሌ ልዩ ቦታው አርሴማ ቤተክርስቲያን ውስጥ የግል ተበዳይ የ12 ዓመት ህፃንን በተክሊል ጋብቻ ወይም በሀማኖት ስርዓት ያገባት መሆኑ ታውቋል።
ተከሳሽ በፈፀመው ለአካለ መጠን ያልደረሰችን ልጅ ማግባት ወንጀል ዓ/ህግ የሰውና ጋብቻው ሲፈፀም የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃ በማያያዝ ክስ መስርቶ ተከሳሽም የዓ/ህግ ክስ በችሎት ተሰጥቶት የዓ /ህግ ክስ በችሎት ተነቦለት ክሱን እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ወንጀሉን መፈፀሙን አምኖ ነገር ግን " ህፃናትን ማግባት በቤተክርስቲያን ህግ የተፈቀደ ነው ወንጀል አይደለም " በማለት ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱ የህግ ምስክሮችን ሰምቶ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ ቁ113/2/ መሠረት ፍ/ቤቱ ወደ ወንጀል ህግ አንቀጽ 648 /ሀ/ በመቀየር እንዲከላከል ቢጠይቀውም ተከሳሽ ግን የመከላከያ ምስክር የለኝም ብሏል።
በዚህም ፍርድ ቤቱ በቀን 13 / 06/ 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ያስተምራል ተብሎ የታሰበውን የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ቅጣት ውሳኔ ተላልፎበታል።
ምንጭ፦ ጎንቻ ኮሚኒኬሽን

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦረና
በኦሮሚያ ክልል፤ ቦረና ዞን በተራዘመ ድርቅ በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
ቦረና ዞን የተራዘመው ድርቅ የአርሶ አደሮችን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶቻቸውን በመግደል አስከፊነቱን የቀጠለ ሲሆን የሰዎችም ህይወት በድርቁ ሳቢያ እያለፈ ነው ተብሏል።
በቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ነዋሪው አርብቶ አደር ማሊቻ ሞሌ ከድርቁ ጋር በተያያዘ ሰዎች እየሞቱ ስለመሆኑ ለሬድዮ ጣቢያው እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ፦
" ... በድርቁ ሰው የከፋ ችግር ውስጥ ነው ያለው ። ያላቸው ከብቶች በግ እና ፍየል እንኳ ሳይቀር አልቀዋል። ጠብ ያለ ዝናብ ባለመኖሩ የሚወጣ እህል የለም።
የሚሸጥ ከብት በሙሉ በድርቁ አልቀዋል። አሁን ሰው በችግሩ በሕይወት እስከማለፍ ደርሷል። የሚቀመስ በመጥፋቱ በዚሁ ዓመት ብቻ በዚህች ቀበሌያችን አራት ሰው የሚደርስ ተጎሳቅለው አልፈዋል ። "
በደቡብ ኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና ሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍሎች ድርቁ የከፋ መሆኑን ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።
ፎቶ ፦ ፋይል

#MoE
የአቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ ዛሬ ያበቃል።
በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫቸውን በየት/ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እንዲያስተካክሉ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዛሬ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ያበቃል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ ናቸው።
ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከዚህ ቀደም 50 % እና ከዛ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ምደባ ያካሄደ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት የሚከታተሉ ተማሪዎችን ምደባ ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል።
More : @tikvahuniversity

#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

#ሶማሌላንድ
በሶማሌላንድ ግዛት በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርከታ ሰዎች ሰላም ፍለጋ ወደ #ኢትዮጵያ እየገቡ ናቸው።
እስካሁን ግጭት የሸሹ ከ83 ሺ በላይ የሶማሌላንድ ነዋሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በመዝለቅ በሶማሌ ክልል መስፈራቸው ተነግሯል።
የተመድ የስደተኞች ኮሚሽንን ዋቢ በማድረግ #ሪፖርተር ጋዜጣ እንዳስነበበው "ላስካኑድ" በምትባለው ከተማ በተከሰተው ግጭት፣ የበርካታ የሶማሌላንድ ነዋሪዎችን ሕይወት የተቀጠፈ ሲሆን በርካታ ሴቶችና ሕፃናት ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል፤ ዶሎ ዞን እየገቡ ናቸው።
እንደ ኮሚሽኑ መረጃ ፦
- እስከ ቅዳሜ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ 14 ሺሕ የሚሆኑ አዳዲስ አባወራዎች (ወይም 83 ሺሕ ግለሰብ ስደተኞች) ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።
- ስደተኞቹ በዶሎ ዞን፤ ቦህ፣ ገልሃሙርና ዳኖድ በተባሉ 3 ወረዳዎች ተጠልለው ይገኛሉ።
- አብዛኞቹ ስደተኞች ባለፈው ሳምንት ነው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት።
- ስደተኞች በ3 ወረዳዎች በ13 ቦታዎች ሠፍረው የሚገኙ ሲሆን የተወሰኑት በትምህርት ቤትና መሰል የሕዝብ መገልገያ ሥፍራዎች ላይ ተጠልለዋል፤ ሌሎች ደግሞ ያለ መጠለያ ሜዳ ላይ ይገኛሉ።
- ከሶማሌ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ቢሮ ጋር በመሆን ከ1,500 በላይ ለሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ ለተጎዱ አባዎራዎች የተለያዩ ቁሳቁሶችና መሰል ድጋፎችን እየተሰጠ ነው። ለተጨማሪ 9 ሺህ አባዎራዎች በቀጣይ ቀናት ድጋፍ ይደረጋል።
የሶማሌ ክልል፤ የስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ መግባት ያረጋገጠ ሲሆን ከተመድ የስደተኞች ኮሚሽን፣ ከዓለም አቀፍ ፍልሰት ድርጅት፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋር በመሆን የዳሰሳ ጥናት አካሂዷል።
ያንብቡ : telegra.ph/ER-02-22

#Turkey ትላንት ምሽት ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች። እጅግ አስከፊው የመሬት መንቀጥቀጥ (7.8) ከተከሰተ ከሁለት ሳምንት በኃላ ቱርክ ትላንት ምሽት በሬክተር ስኬል መለኪያ 6.3 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቷ ተሰምቷል። የመሬት መንቀጥቀጡ የመታው አካባቢ ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከባድ ጉዳት ባጋጠመው በሃታይ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ደቡባዊዋ ሳማንዳግ ከተማ አቅራቢያ…
#ቱርክ
አንድ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ባለስልጣን በቱርክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተከሰተው የመሬት መቀጥቀጥ 1.5 ሚሊዮን ሰዎች #ቤት_አልባ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪ እኚሁ ባለስልጣን ፤ ሀገሪቱ ውስጥ ወደ 500,000 የሚጠጉ ቤቶች እንደገና መገንባት አለባቸው ብለዋል።
በሌላ በኩል ፤ ከትላንት ወዲያ በድጋሚ ቱርክን በመታት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 8 ስለመድረሱ የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

500 ሺህ ቁርኣን ሊሰበሰብ ነው።
" ኑር የቁርኣን ባንክ " ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመሆን ግማሽ ሚሊዮን (500,000) ቁርኣን ለመሰብሰብ ዝግጅት ማድረጉ ተሰምቷል።
500 ሺህ ቁርኣን ለመሰብሰብ ዝግጅት የተደረገው በመጪው ታላቁ የረመዷን ጾም ወቅት ሲሆን ቁርኣኑ የሚሰበሰበው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ከሚገኙ ወገኖች እንደሆነ ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ሼህ ሱልጣን አማን ጉዳዩን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ፤ " ቁርኣን በሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ በህዝበ ሙስሊሙ ፍላጎት አለ ፤ ይህን ለማሟላት የቁርኣን እጥረት አለ " ያሉ ሲሆን " ኑር የቁርኣን ባንክ ሙስሊሙ ያጋጠመውን የቁርኣን እጥረት ከየመስጊዶቹ፣ ከየአካባቢዎቹ በመሰብሰብ ለህዝቡ በተለይ #በገጠር ፤ ከከተማ ውጭ ላለው ወንድም ፤ እህቶቻችን ለማድረስ የተቋቋመ ድርጅት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
ሼህ ሱልጣን ፤ ቁርኣን የማሰባሰቡ ተግባር ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥቅም ስላለው ምክር ቤቱ ከድርጅቱ " የአብረን በትብብር እንስራ " ጥያቄ ሲቀርብለት በደስታ መቀበሉንና በጋራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የታቀደው 500 ሺህ ቁርኣን የማሰባሰብ ስራ ከግብ እንዲደርስ ሁሉም ህብረተሰብ እንዲተባበር ሼህ ሱልጣን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ረመዷን የቁርኣን ወር በመሆኑ በዚህ ወቅት ቁርኣን ለሌላቸው አካባቢዎች ቁርዓን ማዘጋጀት እና ማድረስ ከህዝበ ሙስሊሙ ትልቅ ጥቅም እንዳለው አሳውቀዋል።

የማመልከቻ ጥሪ
ትልቅ ህልም ያለው ሥራ ፈጣሪ ነዎት? አሁኑኑ ያመልክቱ እና ክህሎትዎን ስራ ላይ ለማዋል ፕሮግራማችንን ይቀላቀሉ። ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከኬንያ እና ከሩዋንዳ ካሉ ሥራ ፈጣሪዎች ጋር ተወዳድረው ይኽንን ትልቅ እድል ያሸንፉ፤ በሂደቱም ብዙ ይማሩ።
የማመልከቻ ጊዜ ከ ጥር 5, 2015 እስከ መጋቢት 27, 2015 ይሆናል።
ለመሳተፍ ብቁ መሆንዎን ለማረጋገጥ በዚህ አድራሻ [email protected] ወይም በስልክ 0910795506 ያግኙን።
ለማመልከት jasiri.org/application ላይ ያመልክቱ
ለበለጠ መረጃ www.jasiri.org ይጎብኙ

#MoE #EIASC
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤት ዋና ፀሐፊ በሆኑት በሼይኽ ሐሚድ ሙሳ የተመራ ልዑክ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከተመራ የሚኒስቴር መስራቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዉይይት ማድረጉን ምክር ቤቱ ዛሬ አሳውቋል።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተደረገው ውይይት ፦
- በሙስሊም ተማሪዎች የሰላት ጉዳይ ከመደበኛ ትምህርት ቤቶች እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) ፤
- የሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብና ያጋጠሙ ችግሮች፤
- በትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የካሪኩለም ዝግጅት እና በተማሪዎች የመማሪያ መፅሀፍት ሚዛናዊነት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።
ም/ቤቱ የነበረው ውይይት #ዉጤታማ እንደነበር ገልጾ " በቀጣይም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ተቋማቱ ተቀራርበው ለመስራት የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል " ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በሚቋቋመው እና በዘርፉ ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በቀጣይ ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የባለሙያዎች ቡድን ጋር ዉይይት ለማድረግ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

#ቦረና በኦሮሚያ ክልል፤ ቦረና ዞን በተራዘመ ድርቅ በርካታ የቤት እንስሳት አልቀው የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ነዋሪዎችም ከድርቁ ጋር በተያያዘ መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። ቦረና ዞን የተራዘመው ድርቅ የአርሶ አደሮችን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶቻቸውን በመግደል አስከፊነቱን የቀጠለ ሲሆን የሰዎችም ህይወት በድርቁ ሳቢያ እያለፈ ነው ተብሏል። በቦረና…
#ቦረና
- በቦረና ዞን ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል።
- በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ 85 በመቶዎቹ የቀንድ ከብቶች ናቸው።
- በዞኑ የቀሩት 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ሲሆኑ፤ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ ያስፈልጋል። በተጨማሪ 135 ሺህ ኩንታል መኖ የሚያስፈልግ ሲሆን በዞኑ ማቅረብ የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ ነው።
- እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ የታሰበውን ያህል ችግር ውስጥ የሚገኙ ከብቶችን መታደግ ከባድ ሊሆን ይችላል።
- እስካሁን በቀንድ ከብቶች ሞት ምክንያት 33 ቢሊየን የሚገመት ብር ታጥቷል።
(የቦረና ዞን አስተዳደሪ ጃርሶ ቦሩ ለኤፍ ቢ ሲ ከሰጡት ቃል)
#ኤፍቢሲ