#AU
ኮሞሮስ የ2023 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን #ከሴኔጋል በይፋ ተረክባለች።
36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል።
በጉባዔው መክፈቻ መርሐግብር የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀ መንበር ሴኔጋል ለኮሞሮስ ሊቀ መንበርነቷን በይፋ አስረክባለች።
የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ከፕሬዜዳንት ማኪ ሳል የሊቀመንበርነቱን ቦታ የተረከቡ ሲሆን 2023ን የህብረቱ ሊቀመንበር ሆነው ያገለግላሉ።
#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከቀናት በፊት ስምምነት ላይ የደረሱት አባቶች ስምምነቱን እንዲሁም ቀኖናውን ደግመው መጣሳቸውን አሳወቀች። ይህንን በተመለከተ ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ ፅህፈት ቤት መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በመግለጫው ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተከታዩን ብለዋል ፦ " ከሁለት ቀናት በፊት ሰላም መፈጠሩን ማወጃችን ይታወሳል። በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች…
#Update
ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ ስምምነቱን ሳይሸራረፍ እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅዱስ ሲኖዶስ በመገኘት ቃላቸውን ሰጥተው አረጋግጠዋል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።
እነ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ/ም በተደረገው ውይይት የተስማሙባቸውን (10) ዐሥር ነጥቦች ያለመሸራረፍ ለመፈጸም እንዲሁም ቀጣዩን ተግባር በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ለማከናወን ተስማምተናል ሲሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት በመገኘት ቃላቸውን መስጠታቸው ተገልጿል።
#EOTCTV

#AU ኮሞሮስ የ2023 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን #ከሴኔጋል በይፋ ተረክባለች። 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል። በጉባዔው መክፈቻ መርሐግብር የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀ መንበር ሴኔጋል ለኮሞሮስ ሊቀ መንበርነቷን በይፋ አስረክባለች። የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ከፕሬዜዳንት ማኪ ሳል የሊቀመንበርነቱን ቦታ የተረከቡ ሲሆን 2023ን የህብረቱ…
#AU #ETHIOPIA
የ36ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ትላንት ቅዳሜ እንዲሁም ዛሬ እሁድ ተደርጎ ተጠናቋል።
ይህን ተከትሎ የጉባኤው ተሳታፊ ሀገራት መሪዎች ወደ አገራቸው መመለስ ጀምረዋል።
እስካሁን የበርካታ ሀገራት መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
እስካሁን ድረስ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት መካከል ፦
- የጋና፣
- የሞዛምቢክ፣
- የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣
- የኬኒያ፣
- የሩዋንዳ፣
- የሞሮኮ፣
- የማዳጋስካር ፣
- የኡጋንዳ፣
- የዚምባብዌ ፣
- አንጎላ ፣
- ደቡብ አፍሪካ ፣
- ኮንጎ ብራዛቢል፣
- ቻድ እንዲሁም የሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ መሪዎች ይጠቀሳሉ።
የተመድ ዋና ፀሀፊት አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ ሌሎችም የጉባኤው ተካፋዮች ተሸኝተዋል።
መሪዎቹ ትላንትናና ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከመሳተፍ ባለፈ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል።
በሌላ በኩል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ #በሰላም መጠናቀቁን ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

#Oromia
ከቀናት በፊት ከኦሮሚያ ክልል መንግስትና መንግስት " ሸኔ " እያለ የሚጠራው እራሱን የ " ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት " ከሚለው ቡድን የሰላም ድምጾች ተሰምተዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ በተካሄደው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ስብሰባ ላይ ፦
" በዚህ በተከበረው ጨፌው ፊት በክልላችን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ማለትም ኦነግ ሸኔ በእርቅ ወደ ሰላማዊ መንገድ ተመልሶ እንዲገባ በክብር ጥሪ አቀርባለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።
ይህ ጥሪ ከቀረበ በኋላ መግለጫ ያወጣው መንግስት " ሸኔ " እያለ የሚጠራው የ " ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት " በበኩሉ በኦሮሚያ ያለውን ችግር በሰላም ለመፍታት የቀረበውን ጥሪ እንደሚቀበለው ገልጿል።
ድርጅቱ የሚያደረገው ንግግር የተሳካ እንዲሆን ገለልተኛ የሦስተኛ ወገን የውጭ አሸማጋዮች እንዲኖሩ እንደሚፈለግ ገልጾ፣ ይህ የማይሆን ከሆነ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር መካከል የተደረሰው ‘ የአሥመራው ስምምነት ’ አይነት እንቅፋት ያጋጥመዋል ሲል አሳስቧል።
የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጀዋር መሐመድ በበኩላቸው " የኦሮሚያ የሰላም ጉዳይ መስመር እየያዘ ይመስላል " ሲሉ የገለጹ ሲሆን መንግስት በውጪ አደራዳሪዎች ላይ ያለውን ጥርጣሬ ማንሳት እንዳለበት ጠቁመዋል።
" የፖለቲካ አመራሩ፣ ምሁራኑና አጠቃላይ ህብረተሰቡ ለሁለቱም ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ለዚህ ተስፋ በፍጥነት ተግባራዊ መሆን የበኩሉን መወጣት አለበት።" ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያሰፈሩት።
ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/Oromiya-02-20

Telegraph
Oromiya
ከቀናት በፊት ከኦሮሚያ ክልል መንግስትና መንግስት " ሸኔ " እያለ የሚጠራው እራሱን የ " ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት " ከሚለው ቡድን የሰላም ድምጾች ተሰምተዋል። ከሰሞኑ በተካሄደው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ስብሰባ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በክልሉ ታጥቆ ለሚንቀሳቀሰው "የኦነግ ሸኔ" ቡድን የሰላም እና የእርቅ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ታጣቂ ቡድኑ ጥሪውን እንደሚቀበል አሳውቋል። ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ…
📢📢📢 Jasiri Talent Investor Cohort 4 Application is now OPEN!
Jasiri is offering individuals who show potential in entrepreneurial talent an opportunity to develop as responsible entrepreneurs by applying for the Talent Investor Program.
To apply, visit https://lnkd.in/dE4XgkN5
#Jasiri4Africa

#ETHIOPIA በኢትዮጵያ የማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ገደብ ከተገደረገባቸው ስድስተኛ ቀኑን ይዟል። " #ቴሌግራም " ን ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ መገናኛዎች ምክንያቱ በግልፅ ወይም በይፋ ባልተነገረበት ሁኔታ ገደብ ከተደረገባቸው ስድስተኛ ቀን ሆኗል። ይህ መልዕክት ተፅፎ እስከተላከበት ሰዓት ድረስ አገልግሎቶቹ ያልተመለሱ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች " ኢትዮ ቴሌኮም…
#ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ የማህበራዊ ሚዲያዎች ገደብ ከተደረገባቸው ከአንድ ሳምንት በላይ ተቆጥሯል።
#ቴሌግራም እና ፌስቡክ መሰል የማህበራዊ መገናኛዎች ከተቋረጡ ዛሬ አስራ ሁለተኛ (12) ቀን ተቆጥሯል።
የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለምን ገደብ እንደተጣለ እንዲሁም ገደቡ መቼ እንደሚነሳ በየትኛውም አካል በኩል ለህዝብ ማብራሪያም ሆነ ገለፃ ያደረገ የለም።
ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛዎች በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች በኩል ተገድበው የሚገኙ ሲሆን በርካቶች ገደቡን በVPN በማለፍ አገልግሎት እያገኙ ናቸው።

#Oromia ከቀናት በፊት ከኦሮሚያ ክልል መንግስትና መንግስት " ሸኔ " እያለ የሚጠራው እራሱን የ " ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት " ከሚለው ቡድን የሰላም ድምጾች ተሰምተዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ በተካሄደው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ስብሰባ ላይ ፦ " በዚህ በተከበረው ጨፌው ፊት በክልላችን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ማለትም ኦነግ ሸኔ በእርቅ ወደ ሰላማዊ መንገድ ተመልሶ…
#JawarMohammed
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (OFC) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ የኦሮሚያን የሰላም ጉዳይ በተመለከተ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያሰፈሩት ሃሳብ ፦
" የኦሮሚያ የሰላም ጉዳይ መስመር እየያዘ ይመስላል።
የሰላም ሂደቱ ከሽማግሌዎች አልፏል ፤ ይህ ዕድል በ2011 ዓ.ም ላይ ያመለጠ ነው።
መንግስት በውጪ አደራዳሪዎች ላይ ያለውን ጥርጣሬ ማንሳት አለበት ፤ ለቴክኒክ፣ ለሎጅስቲክስ እንዲሁም ለህጋዊና ለጋራ ትምምን ሲባል የውጭ አካላት ድርድሩን እንዲመሩት ያስፈልጋል።
የፖለቲካ አመራሩ፣ ምሁራኑ እና አጠቃላይ ህብረተሰቡ ለሁለቱም ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ለዚህ ተስፋ በፍጥነት ተግባራዊ መሆን የበኩሉን መወጣት አለበት።
በአሁን ሰዓት ሰላምን ከማስፈን እና ህዝባችንን ከከባድ ጥፋት ከማዳን የተሻለ ነገር የለም። "

Photo
#Turkey
ትላንት ምሽት ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች።
እጅግ አስከፊው የመሬት መንቀጥቀጥ (7.8) ከተከሰተ ከሁለት ሳምንት በኃላ ቱርክ ትላንት ምሽት በሬክተር ስኬል መለኪያ 6.3 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቷ ተሰምቷል።
የመሬት መንቀጥቀጡ የመታው አካባቢ ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከባድ ጉዳት ባጋጠመው በሃታይ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ደቡባዊዋ ሳማንዳግ ከተማ አቅራቢያ ነው ተብሏል።
አሁን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክ ውስጥ እስካሁን የሀገሪቱ መንግስት ባስታወቀው 3 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከ200 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በሰሜን ምዕራብ #ሶሪያ ውስጥ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን እስካሁን በታወቀው 130 ሰዎች ተጎድተዋል።
ምናልባት በአዲሱ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጨማሪ ተጎጂዎች ይኖሩ ይሆን እንደሆነ ተብሎ ፍለጋዎች መቀጠላቸው ታውቋል።
ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው በሬክተር መለኪያ 7.8 በተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርክ እና በሶሪያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ47,000 አልፏል።